THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
THIQAH
Photo
#Update

"እያንዳንዱ ሰው መትረፉንም ሆነ መሞቱን እስከምናረጋግጥ እዚህ እንቆያለን" - ጁዋን ሜንዴዝ

በዶሚኒካን ሪፐብሊክ የሟቾች ቁጥር 218 ደረሰ።

የአደጋ ምርመራ ዳይሬክተር ጁዋን ሜንዴዝ፣ "189 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ችለናል ግን አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞናል" ብለዋል።

"በህይወት የተረፉትን ማዳን ተስፋ አስቆራጭ ሆኗል" ያሉት ዳይሬክተሩ፣ "እያንዳንዱ ሰው መትረፉንም ሆነ መሞቱን እስከምናረጋግጥ እዚህ እንቆያለን" ሲሉ ተናግረዋል። #aljazeera

@ThiqahEth
😢11👍6😱1
THIQAH
"በቻይና እና በአሜሪካ መካከል በተፈጠረው የንግድ ጦርነት ሳቢያ የደህንነት ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ" - ቻይና ቻይና ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ዜጎቿ ጥንቃቄ እንድያደርጉ አሳስባለች፡፡ በዚህም የቻይና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ "ዜጎች ከጉዟቸው በፊት አደጋዎችን ማጤን አለባቸው" በማለት አስጠንቅቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ባወጣው ይፋዊ ማሳሰቢያ፣ "በቻይና እና በአሜሪካ መካከል በተፈጠረው የንግድ ጦርነት ሳቢያ…
#Update

"125% ታሪፍ የጣልነው ተናጠላዊ የጉልበት እርምጃ ስለተወሰደብን ነው" - የቻይና ገንዘብ ሚኒስቴር

የቻይና ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ "በጉልበትና አስገዳጅነት የተጣለብን ታሪፍ የአጸፋ እርምጃ እንድንወስድ አስገድዶናል" ብሏል፡፡

የአጸፋ እርምጃውን በተመለከተም፣ "125% ታሪፍ የጣልነው ተናጠላዊ የጉልበት እርምጃ ስለተወሰደብን ነው" ነው ያለው።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው፣ ትራምፕ ታሪፍ መጣላቸውን ከቀጠሉ የአሜሪካ ምርቶች ከቻይና ገበያ ሊወጡ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል፡፡

አሁን ባለው የታሪፍ ሁኔታ ምክንያት የአሜሪካ ምርቶች በቻይና ያላቸው ተቀባይነት ቀንሷል
መባሉን #Upi ተዘግቧል።

ቻይና ከቀናት በፊት፣ "በቻይና እና በአሜሪካ መካከል በተፈጠረው የንግድ ጦርነት ሳቢያ የደህንነት ችግሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ" ማለቷን #thestreetstimes መዘገቡ ይታወሳል።

በዘገባው መሠረት፣ አሜሪካ ለጣለችባት የ67% ታሪፍ በአጸፋው በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ84% ታሪፍ እንደምትጥል ነበር ቻይና ያስታወቀችው።

@ThiqahEth
👍13🤔1
THIQAH
Photo
#Update

በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ከ150 በላይ ሰዎች መጎታቸው ተገለጸ፡፡

በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለማምለጥ የሞከሩ ሰዎች ተጎድተው ለህክምና ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል፡፡

በሬክተር ስኬል 6.2 በተመዘገበው በዚሁ አደጋ በድምሩ 16 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባቸውን ሦስት ከተሞች ማካለሉ ተዘግቧል፡፡
#timescolonist

@ThiqahEth
😢14👍21🔥1🥰1
THIQAH
ዩክሬን እና አሜሪካ የማዕድን ውል ሊፈራረሙ መሆኑ ተሰምቷል። የውሳኔ ዝርዝር ሲሰጥ ይዘን የምንመለስ ይሆናል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማርክ ሩቢዮ ከዚህ ቀደም፣ "የዩክሬን ጦርነት የአሜሪካ ጦርነት አይደለም፣ አሁን ባለንበት ሁኔታ አንቀጥልም" ሲሉ ተደምጠው ነበር። @ThiqahEth
#Update

ዩክሬን እና አሜሪካ አከራካሪ የነበረውን የማዕድን ስምምነት ፈረሙ።

ኪቭ ቀደም ሲል ስትቃወመው የነበረ ቢሆንም "አሜሪካ እስካሁን ላደረገችው ድጋፍ በማዕድን ሀብት ታካክሳለች" በሚለው ሀሳብ መስማማቷን የስምምነት ሰነዱ አመላክቷል ተብሏል።

የዩክሬን ባለስልጣናት ስምምነቱ አሜሪካ የምትሰጠውን፣ "ወታደራዊ ድጋፍ" ያስቀጥላል የሚል እምነት አላቸው ቢባልም፣ በስምምነት ሰነዱ ስለ "ደህንነት ድጋፍ" የሚገልፅ ሀሳብ እንዳልተካተተ ተገልጿል።   

ስምምነቱ የተፈጸመው በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት በሰንትና በዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሊያ ሲርደንኮ አማካኝነት ነው።
#newsbytes   #malaylamanorama

@ThiqahEth
😁8👍5😢5🔥1🥰1
THIQAH
"ስምምነቱ 24 ሰዓት ሳይሞላው ተጥሷል" - ህንድ ህንድ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መጣሱን ገለጸች። የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፀሐፊ ቪክራም ሚስሪ፣ "ፓኪስታን በዛሬው እለት ድንበር ላይ ስምምነቱን የጣሰ አሳፋሪ ጥቃት ፈጽማለች" ብለዋል። "ፓኪስታን ስምምነቱ እንድተገበር አስፈላጊ እርምጃዎችን እንድትወስድ ጥሪ እናቀርባለን" ሲሉም ተናግረዋል። ትራምፕ ትናንት ሁለቱ የደቡብ እስያ ሀገራት በአሜሪካ…
#Update

"የቀረበብን ውንጀላ መሰረተቢስ ነው" - ፓኪስታን

የፓኪስታን ባለስልጣናት ህንድ ያቀረበችውን ወቀሳ "ውንጀላ" በሚል የመልስ ምት ሰጥተዋል።

የፓኪስታን ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አታዑላህ ታራር ህንድ፣ "ፓኪስታን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች" በማለት ላቀረበችው ወቀሳ፣ "የቀረበብን ውንጀላ መሰረተቢስ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም፣ "ኢስላማባድ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለመተግበር ቁርጠኛ ናት" ሲል አስታውቋል።

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሸባዝ ሻሪፍ ከስምምነቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት "በህንድ ላይ ላገኘነው ድል የፓኪስታን ወታደሮች ብቻ ሳትሆኑ መላው ህዝባችን እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።

"የፓኪስታን ጦር እና ጄት የህንድን ጦር በሰዓታት ውስጥ እንዴት ፀጥ እንዳደረገው ታሪክ ሁሌም ሲያስታውሰው ይኖራል" ሲሉም ተናግረዋል
ሲል #geonews ዘግቧል።

ህንድ፣ "ፓኪስታን በዛሬው እለት ድንበር ላይ ስምምነቱን የጣሰ አሳፋሪ ጥቃት ፈጽማለች" ስትል ወቅሳ ነበር።

@ThiqahEth
👍24🔥2🥰2🤔2😁1😱1
THIQAH
Photo
#Update

የሰብዓዊ እርዳታ የጫነው የመጀመሪያው ተሽከርካሪ ዛሬ ወደ ጋዛ ገባ።

ይህም እስራኤል እርዳታ እንዳይገባ ከከለከለች ከ11 ሳምንታት የገባ በኋላ የመጀመሪያው እርዳታ ሆኗል።

የእስራኤል ጦር ሌሎች አምስት እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ መፍቀዱን አስታውቋል።
#africannews

@ThiqahEth
👍19🥰4🙏2🤔1😡1
THIQAH
Photo
#Update

የሟቾች ቁጥር 151 ደርሷል።

በናይጄሪያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን የሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር (SEMA) አስታውቋል።

ጎርፉ 380 ኪሎሜትር መሸፋኑን የገለፀው አስተዳደሩ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማፈላለግ ስራው ቀጥሏል ብሏል።

በዚህ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ከ3000 የሚበልጡ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ መልኩ 500 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል።
#associatedpress #pbsnews #telegraphindia

@ThiqahEth
😢177😭4🤔1😱1
#Update

በናይጄሪያው ጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ200 እንዳሻበቀ፣ 500 ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ፣ የሟቾች ብዛት 700 እንደሚደርስ ተነገረ።

በናይጄሪያዋ ሞካዋ ከተማ በጎርፍ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ እንደሆነ፣ ቁጥሩ እስከ 700 እንደሚደርስ ቢቢሲ ዘግቧል።

ዘገባው፣ “እስካሁን 500 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ተከትሎ የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በሕይወት የሚገኝ ሰው ከዚህ በኋላ አይኖርም በሚል እምነት የነፍስ አድን ጥረቱ ተቋርጧል” ብሏል።

በአካባቢው ተላላፊ በሽታ እንዳይዛመት በጎርፉ የተቀበሩ ግለሰቦችን ቆፍሮ በማውጣት ተገቢው የቀብር ሥነ ሥርዓት ማከናወን በቅርቡ እንደሚጀመር የሞካዋ አካባቢ አስተዳዳሪ ሙሐመዱ አሊዩ ተናግረዋል።

ባለቤቱ እና ጨቅላ ልጁ በጎርፍ የተወሰዱበት አዳሙ ዩሱፍ የተባለው ግለሰብ "ቤተሰቤን ጎርፍ ሲወስድ ምንም ማድረግ ሳልችል ቆሜ ተመልክቻለሁ። እኔም መዋኘት በመቻሌ ነው የተረፍኩት" ሲል ገልጿል።

እ.አ.አ በ2022 በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ600 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
#BBC

@ThiqahEth
😭162🤔1😱1😢1
THIQAH
Photo
#Update

ሊ ጃይ ምዩንግ አዲሱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

በትናንትናው እለት ምርጫ ባካሄደችው ሴዑል የሊበራል ፓርቲው ሊቀመንበር ምዩንግ ማሸነፍ ችለዋል።

አዲሱ ፕሬዝዳንት በወታደራዊ አስተዳደር (martial law) ምክንያት የመልካም አስተዳደር ስርዓት መሸርሸር ታይቶባታል ለተባለችው ደቡብ ኮሪያ ድሞክራሲን ያሰፍናሉ የሚል ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
#asiaone

@ThiqahEth
11👏4🕊3
THIQAH
የእስራኤል ጦር ግሬቴ ተንበርግን የያዘችውን መርከብ አገደ። መርከቧ ወደ ጋዛ ለመግባት 200 ኪሎሜትር ሲቀራት እንድትቆም መደረጓ ተገልጿል። መርከቧ ከተንበርግ በተጨማሪ ሌሎች 12 የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ይዛለች ተብሏል። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ግሬታ ተንበርግን እና የሰብዓዊ እርዳታ የጫነችው መርከብ ወደ ጋዛ እንዳትገባ ለእስራኤል ጦር ትዕዛዝ አስተላልፊያለሁ ማለታቸው…
#Update

የመብት ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግ ከእስራኤል መውጣቷ ተገለጸ።

የአካባቢ ጥበቃ አክቲቪስት ተንበርግ ወደ ስዊድን እንድትመለስ ማድረጉን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ግሬታ ተንበርግ ከሌሎች 3 ሰዎች ጋር በመሆን ወደቤንጉሪን አየርመንገድ መሸኘታቸውን አስታውቋል።

አንድ የአውሮፓ ፓርላማ አባልና ሌሎች 8 የሚደርሱት ደግሞ የመመለሻ ፎርሙን (Deportation paperwork) ለመሙላት ፍላጎት አላሳዩም ብሏል።

አክቲቪስት ተንበርግ ከሌሎች 11 የመብት ተሟጋቾች ጋር በመሆን የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ጋዛ በሚገቡበት ወቅት በእስራኤል ጦር ተይዘው ነበር። 
#foxnews

@ThiqahEth
11👏1🙏1
THIQAH
በአውሮፕላን አደጋ ቢያንስ የ30 ሰዎች ህይወት አለፈ። 242 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ኤይር ኢንዲያ AI171 አውሮፕላን በጉጅራት ከተማ ተከስክሷል። በአደጋው ህይወታቸው ያለፉ 30 አስክሬን ማንሳቱን ያስታወቀው የህንድ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ሌሎች ተጎጅዎችን የማፈላለግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል። #thestraitstimes @ThiqahEth
#Update

"ከ100 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል" - የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች

ከህንድ ወደ እንግሊዝ እየተጓዘ የነበረው አዎሮፕላን ባጋጠመው መከስከስ የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ማሻቀቡ ተገልጿል።

አውሮፕላኑ 242 ተጓዦችን አሳፍሮ እንደነበር የተመለከተ ሲሆን፤ በሕይወት የተረፉ እንዳሉና እንደሌሉ በግልጽ አልተነገረም።

ሆኖም ጉዳት የደረሰባቸውን ተጓዦች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋልም ተብሏል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በጋራ መኖሪያ ህንፃ ላይ ነው ሲሆን፣ 80% የሚሆነው ሙሉ በሙሉ ወድሟል።  

ከተጓዦቹ መካከል 11ዱ ህፃናት እንደሆኑ ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። 
#thenorthweststar

@ThiqahEth
😢135😭2
THIQAH
Photo
#Update

"በህይወት የተረፈ ተሳፋሪ የለም" - የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች

በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሁሉም 242 ተጓዦች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

ከተጓዦቹ ውስጥ 53 የእንግሊዝ ዜጎች፣ ሰባት የፖርቹጋል ዜጎች ሲሆኑ፣ 12 የበረራ አባላትም ነበሩ ተብሏል።

ከህንድ ወደ እንግሊዝ እየበረረ የነበረው አውሮፕላን ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ የ100 ሰዎችን አስክሬን ብቻ ማንሳት መቻሉን በስፍራው የተሰማሩት የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች አስታውቀዋል።

ምርቱ የቦይንግ በሆነው አውሮፕላን ለመከስከስ አደጋ የተጋለጠበት ምክንያት እስካሁን ድረስ አልተገለጸም። 
#lbc

@ThiqahEth
😭465😢1
THIQAH
#Update "በህይወት የተረፈ ተሳፋሪ የለም" - የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሁሉም 242 ተጓዦች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ። ከተጓዦቹ ውስጥ 53 የእንግሊዝ ዜጎች፣ ሰባት የፖርቹጋል ዜጎች ሲሆኑ፣ 12 የበረራ አባላትም ነበሩ ተብሏል። ከህንድ ወደ እንግሊዝ እየበረረ የነበረው አውሮፕላን ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ የ100 ሰዎችን አስክሬን ብቻ ማንሳት መቻሉን በስፍራው የተሰማሩት…
#Update

"በበረራ ከጀመርን ከ30 ሰከንድ በኋላ የሚረብሽ ድምፅ ተሰማ፣ ወዲያውኑ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፣ ነገሮች በፍጥነት ነው የተፈጠሩት" - ታዕምረኛው ራመሽ

242 ሰዎችን ጭኖ ነበር የተባለው አውሮፕላን በመከስከሱ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው በስፋት ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል ተብሏል።

ቪሽዋሽ ኩማር ራመሽ የተባለው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ግለሰብ በህይወት በመገኘቱ ለህክምና ሆስፒታል ገብቷል።

ራመሽ፣"በበረራ ከጀመርን ከ30 ሰከንድ በኋላ የሚረብሽ ድምፅ ተሰማ፣ ወዲያውኑ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፣ ነገሮች በፍጥነት ነው የተፈጠሩት" ብሏል።

የጉጃሪት ከተማ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዳናንጃይ ድቪድ "አንድ ሰው በህይወት መገኘቱን ማረጋገጥ ችለናል" ሲሉ ተናግረዋል።  

ራመሽ በሰውነቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ኃላፊው ገልጸዋል። 
#cbsnews

@ThiqahEth
18
THIQAH
Photo
#Update

ሦስት ጊዜ በዋስ እንዲፈታ በፍርድ ቤቶች ቢወሰንለትም ፓሊስ ሳይፈታው የቆየው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ዛሬ ከእስር ተፈትቷል።

@ThiqahEth
👏16🙏5😡1
THIQAH
ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሳካት የተፈጸመ ግድያ ነው" - ሚኒሶታ በአሜሪካ ሁለት የዲሞክራት ፓለቲከኞች በተኩስ መገደላቸው ተነግሯል። በሚኒሶታ ግዛት ዲሞክራቶችን በመወከል የምክር ቤት አባል የሆኑት መሊሳ ሆርትማን እና ባለቤታቸው ማርክ በመኖሪያ ቤታቸው ተገድለው ተገኝተዋል። የሚኒሶታ አስተዳዳሪ ቲም ዋትዝ፣ "ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሳካት የተፈጸመ ግድያ ነው" ብለዋል። ፖሊስ፣ ግድያው በማን እንደተፈጸመ…
#Update

በሚኒሶታ የዲሞክራቶችን ባለስልጣናት የገደለውን ተጠርጣሪ መያዙን ፓሊስ አስታወቀ።

የሚኒሶታ ምክር ቤት አባልና ባለቤታቸውን "በመግደል" የተጠረጠረው የ57 አመቱ ቫንስ ሉተር ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ከመኖሪያ ቤቱ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ተደብቆ እንደነበር ፓሊስ ገልጿል። 

የአሜሪካ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ተጠርጣሪው ያለበትን ለጠቆመ 50,000 ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቶ ነበር።

ግድያው ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ፍትህ እንዲሰጥ አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል።
#gulftoday

ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ የተያዘ ተጠርጣሪ እንዳልነበር ፓሊስ ከወቅቱ ተገልጾ ነበር።

@ThiqahEth
6🙏1
THIQAH
ኢራን የሞሳድን ዋና መስሪያ ቤት ደበደበች። የኢራን ሚሳዔሎች የእስራኤል ኢንተሊጀንስ አገልግሎት (MOSSAD) ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተገልጿል። እስራኤል ሞሳድ ላይ ተፈጽሟል ስለተባለው ጉዳት የሰጠችው ማብራሪያ የለም።  #trendnewsagency @ThiqahEth
#Update

"ሁሉም እዛው ኢራን ውስጥ ናቸው" - ሞሳድ

ሞሳድ ዛሬ በሞሳድ ዋና መስሪያ ቤት ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ላለችው ኢራን ምላሽ ሰጥቷል።

"ኢራን የሞሳድ ህንፃ ላይ በሚሳዔል ጥቃት አድርሰናል ብላለች" ያለው የእስራኤል ኢንተሊጀንስ ቢሮ፣ "እንደ እድል ሆኖ ማንም በዚያ የለም" ሲል አስታውቋል።

ሞሳድ አክሎ፣ "ሁሉም እዛው ኢራን ውስጥ ናቸው" በማለት ገልጿል።
#mossacomentary

@ThiqahEth
🤔4515👏5😱4🕊1😭1
THIQAH
"ሀገር ሊኖረን ይገባል" - ፕሬዝዳንት ሩቶ በኬንያ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 8 ሰዎች ተገደሉ። ኬንያውያን ፖሊስን በህብረተሰቡ ላይ የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል። በናይሮቢ እየተካሄደ ባለው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ፖሊስ አሁንም ጥይት በመተኮስና አስለቃሽ ጭስ በመልቀቅ ተቃውሞውን ለመግታት ጥረት እያደረገ ይገኛል። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ የተቃውሞ ሰልፉ ሰላማዊ…
#Update

በኬንያው ተቃውሞ ከ300 የሚበልጡ ዜጎች መጎዳታቸው ተገለጸ።

ከተጎጂዎች መካከል 67 የሚሆኑት በተኩስ ተመትተው በጀሞ ኬንያታ ሆስፒታል ጥብቅ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

እስካሁን ድረስ የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የኬንያ ቢሮ አስታውቋል።

ተቃውሞው 20 በሚደርሱ ከተሞች ተስፋፍቷል ተብሏል።

ፖሊስና ልዩ ኃይሎች ተቃውሞውን ለማብረድ አስለቃሽ ጭስና ውሃን እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

የተቃውሞ ሰልፉ ባለፈው አመት በግብር ጭማሪ ቅሬታ የተጀመረውና ፕሬዝዳንት ሩቶ ከስልጣን እንዲነሱ የሚጠይቀው ዘመቻ አካል ነው ተብሏል።
#akipress

@ThiqahEth
20😱3🕊2😢1😡1
#Update

በቴክሳስ የሟቾች ቁጥር 27 መድረሱ፣ 800 ሰዎች ከአካባቢው መልቀቃቸው ተነገረ።

በማዕከላዊ ቴክሳስ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ካለፉት 27 ሰዎች መካከል ዘጠኙ ህፃናት ናቸው ተብሏል።

800 ሰዎች ከአካባቢው እንዲለቁ መደረጉን የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
#rfi

@ThiqahEth
😢14👏8🕊64
THIQAH
#Update በቴክሳስ የሟቾች ቁጥር 27 መድረሱ፣ 800 ሰዎች ከአካባቢው መልቀቃቸው ተነገረ። በማዕከላዊ ቴክሳስ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ህይወታቸው ካለፉት 27 ሰዎች መካከል ዘጠኙ ህፃናት ናቸው ተብሏል። 800 ሰዎች ከአካባቢው እንዲለቁ መደረጉን የከተማዋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።#rfi @ThiqahEth
#Update

በጎርፍ አደጋው የሟቾች ቁጥር 50 ደረሰ።

በአሜሪካ የቴክሳስ ግዛት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 50 መድረሱንና የጠፉት እየተፈለጉ መሆናቸውን የከተማዋ የአደጋ ዲፓርትመንት አስታውቋል።

ከጠፉት ውስጥ 27ቱ ሴቶች መሆናቸውን ዲፓርትመንቱ ገልጿል።
#malayalamanorama

@ThiqahEth
😢178🙏5😭3👏2🕊2