THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
እስራኤል በቤሩት ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተሰማ።

እስራኤል ከሂዝቦላ ጋር የደረሰችው የተኩስ አቁም ስምምነት ቀነ ገደብ ካለቀ በኋላ በሊባኖስ የመጀመሪያ ጥቃት ማድረሷ ተገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ሂዝቦላ በሰሜን እስራኤል በኩል ጦርነት በመክፈቱ መሆኑን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።

ጦሩ አክሎም ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው የሂዝቦላ የድሮን ክምችት ላይ ነው ብሏል። 
#cbsnews

@ThiahEth
😡22👍18🔥72
"የዩክሬን ጦርነት የአሜሪካ ጦርነት አይደለም፣ አሁን ባለንበት ሁኔታ አንቀጥልም" - ማርክ ሩቢዮ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ፣ "በሰላም ድርድሩ መፍትሄ የማይመጣ ከሆነ አሜሪካ ራሷን ልታገል ትችላለች" ብለዋል።

ሩቢዮ ዋሽንግተን ከሩሲያ እና ዩክሬን አደራዳሪነት ሚናዋ ለቃ ልትወጣ እንደምትችል ጠቁመዋል።

"የኛ ጦርነት አይደለም፣ እኛን አያገባንም" ያሉት ሩቢዮ፣ እስካሁን በተደረገው የሰላም ጥረት ለውጥ አለመምጣቱን ገልጸዋል።

የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ ሚና አስፈላጊ መሆንና አለመሆኑን በቀጣይ ሳምንት ለንደን በሚደረገው ስብሰባ የመጨረሻ አቋሙን ያሳውቃል ብለዋል።   #cbsnews #onmanorama

@ThiqahEth
👍182😁2😡1
ሩዋንዳ አፍሪካዊ ስደተኞችን ለመቀበል ከአሜሪካ ጋር መስማማቷ ተገለጸ።

የትራምፕ አስተዳደርና የሩዋንዳ መንግስት አፍሪካዊና ሩዋንዳዊ ያልሆኑ ስደተኞችን ወደ ኪጋሊ ለመመለስ "በመርህ ደረጃ" መስማማታቸው ታውቋል።

ሩዋንዳ ስደተኞችን በመቀበሏ የገንዘብ ድጋፍ የምታገኝ ሲሆን፣ ስለገንዘቡ በቀጣይ ሳምንት ውይይት እንደሚደረግ ተመልክቷል።

ሩዋንዳ በ2024 ከጠቅላይ ሚኒስትር ረሺ ሱናክ መንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞችን ለመቀበል ያደረገችው ስምምነት ቁጣን ተቀስቅሶ እንደነበር አይዘነጋም።
#cbsnews

@ThiqahEth
😁14👍8😡41🤔1👌1
THIQAH
#Update "በህይወት የተረፈ ተሳፋሪ የለም" - የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሁሉም 242 ተጓዦች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ። ከተጓዦቹ ውስጥ 53 የእንግሊዝ ዜጎች፣ ሰባት የፖርቹጋል ዜጎች ሲሆኑ፣ 12 የበረራ አባላትም ነበሩ ተብሏል። ከህንድ ወደ እንግሊዝ እየበረረ የነበረው አውሮፕላን ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ የ100 ሰዎችን አስክሬን ብቻ ማንሳት መቻሉን በስፍራው የተሰማሩት…
#Update

"በበረራ ከጀመርን ከ30 ሰከንድ በኋላ የሚረብሽ ድምፅ ተሰማ፣ ወዲያውኑ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፣ ነገሮች በፍጥነት ነው የተፈጠሩት" - ታዕምረኛው ራመሽ

242 ሰዎችን ጭኖ ነበር የተባለው አውሮፕላን በመከስከሱ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው በስፋት ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል ተብሏል።

ቪሽዋሽ ኩማር ራመሽ የተባለው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ግለሰብ በህይወት በመገኘቱ ለህክምና ሆስፒታል ገብቷል።

ራመሽ፣"በበረራ ከጀመርን ከ30 ሰከንድ በኋላ የሚረብሽ ድምፅ ተሰማ፣ ወዲያውኑ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፣ ነገሮች በፍጥነት ነው የተፈጠሩት" ብሏል።

የጉጃሪት ከተማ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዳናንጃይ ድቪድ "አንድ ሰው በህይወት መገኘቱን ማረጋገጥ ችለናል" ሲሉ ተናግረዋል።  

ራመሽ በሰውነቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ኃላፊው ገልጸዋል። 
#cbsnews

@ThiqahEth
18
"በጣም ከባድ የአየር ጥቃት ተፈፅሞብናል"  - ዩክሬን

ሩሲያ ከጦርነቱ መጀመር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የተባለውን የአየር ጥቃት ፈፀመች።

ሞስኮ፣ "በጣም ከባድ የአየር ጥቃት" በተባለው በዚህ ጥቃቷ በድምሩ "537 የአየር ላይ ጥቃቶችን ፈፅማለች" ተብሏል።

ከእነዚህ ጥቃቶች ውስጥ 477 የሚሆኑት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መሆናቸው ተገልጿል። 

የዩክሬን ጦር ከተቃጡት ጥቃቶች "249 የሚሆኑትን አክሽፊያለሁ" ብሏል።

ሩሲያ ፈፀመች ስለተባለው ጥቃት የሰጠችው ማብራሪያ የለም።
#cbsnews

@ThiqahEth
👏96😢5🕊5💔2😭1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"በደማስቆ የተፈፀመው ጥቃት አሳስቦናል" - አሜሪካ

እስራኤል በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ከፍተኛ የአየር ድብደባ ፈጸመች።

የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር አሜሪካ እስራኤል የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታስቆም ጥሪ አቅርቧል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ "በደማስቆ የተፈጸመው ጥቃት አሳስቦናል" ብለዋል።

ሩቢዮ፣ "የተረጋጋች እና ሰላማዊ ሶሪያን ለመፍጠር ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል" ሲሉም ተናግረዋል።
#cbsnews

@ThiqahEth
😢2011🕊8😡4👏1
በህንድ ትምህርት ቤት ተደርምሶ የ7 ህፃናት ህይወት ሲያልፍ 20 የሚሆኑ ተጎዱ።

በራጃስታን ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ  ትምህርት ቤት ተደርምሶ ከሞቱት በተጨማሪ 20 ተማሪዎች ተጎድተዋል ተብሏል።

በትምህርት ቤቱ ውስጥ 60 ተማሪዎች እና መምህራን እንደነበሩ ተገልጿል።   #cbsnews

@ThiqahEth
😭314😢3👏1😱1🕊1💔1