THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
''በደቡብ አፍሪካ ጸረ-አሜሪካዊነት ተስፋፍቷል''  - ማርክ ሩቢዮ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ፣ ደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የቡድን 20 ስብሰባ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባሳለፍነው ረቡዕ በደቡብ አፍሪካ ''አዲስ የመሬት አጠቃቀም ህግ'' ያስፈልጋል ማለታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ውጥረት እንድሰፍን ምክንያት ሆኗል፡፡

ትራምፕ የራማፎዛ አስተዳደር በደቡብ አፍሪካ መሬት ያለ አግባብ እየወረሰ ነው ሲሉ ወንግለዋል። ፡፡

በጆ ባይደን አስተዳደር በነጩ ቤተመንግስት ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አንድሪው ባቲ፣ ትራምፕ በደቡብ አፍሪካ ላይ ማራመድ የጀመሩት ፖሊሲ የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነነት የሚጎዳ ነው በማለት ተችተውታል፡፡ #newsbytes

@ThiqahEth
👍254😡1
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አዲስ ለሚወለዱ ህጻናት 5,000 ዶላር እንደሚሰጡ ቃል ገቡ፡፡

ትራምፕ የእናቶችን የወሊድ መጠን ለማበረታታት አዋጭ ያሏቸውን እርምጃዎች እየወሰዱ ነው ተብሏል፡፡

ውሳኔው፣ "አሜሪካን እንደገና ጤናማ ማድረግ" ከሚለው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔድ እቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

የወቅቱ የአሜሪካ መንግስት አሜሪካውያን እንዲያገቡና ብዙ ልጆች እንዲወልዱ እያበረታታ እንደሚገኝ ተዘግቧል፡፡  
#newsbytes

@ThiqahEth
🥰2110👍4🤔4😁3🔥2
THIQAH
ዩክሬን እና አሜሪካ የማዕድን ውል ሊፈራረሙ መሆኑ ተሰምቷል። የውሳኔ ዝርዝር ሲሰጥ ይዘን የምንመለስ ይሆናል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማርክ ሩቢዮ ከዚህ ቀደም፣ "የዩክሬን ጦርነት የአሜሪካ ጦርነት አይደለም፣ አሁን ባለንበት ሁኔታ አንቀጥልም" ሲሉ ተደምጠው ነበር። @ThiqahEth
#Update

ዩክሬን እና አሜሪካ አከራካሪ የነበረውን የማዕድን ስምምነት ፈረሙ።

ኪቭ ቀደም ሲል ስትቃወመው የነበረ ቢሆንም "አሜሪካ እስካሁን ላደረገችው ድጋፍ በማዕድን ሀብት ታካክሳለች" በሚለው ሀሳብ መስማማቷን የስምምነት ሰነዱ አመላክቷል ተብሏል።

የዩክሬን ባለስልጣናት ስምምነቱ አሜሪካ የምትሰጠውን፣ "ወታደራዊ ድጋፍ" ያስቀጥላል የሚል እምነት አላቸው ቢባልም፣ በስምምነት ሰነዱ ስለ "ደህንነት ድጋፍ" የሚገልፅ ሀሳብ እንዳልተካተተ ተገልጿል።   

ስምምነቱ የተፈጸመው በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት በሰንትና በዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሊያ ሲርደንኮ አማካኝነት ነው።
#newsbytes   #malaylamanorama

@ThiqahEth
😁8👍5😢5🔥1🥰1
በአርጀንቲና በሬክተር ስኬል 7.5 የተለካ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ።

በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ኡሹዓያ ከተማ የተከሰተው ይህ አደጋ 220 ኪሎ ሜትር ማካለሉን ባለስልጣናት ተናግረዋል። 

እስካሁን በአደጋው የደረሰው ጉዳት አለመመዝገቡም ተገልጿል።
#newsbytes #miamiherald

@ThiqahEth
🤔9👍5😭3😁21
"በመሰረቱ የኛ ጉዳይ አይደለም" - አሜሪካ

አሜሪካ በህንድና ፓኪስታን ግጭት ጣልቃ እንደማትገባ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄይዲ ቫንስ ገለጹ፡፡

ቫንስ፣ "ልናደርግ የምንችለው ግጭቱ እንደሐበርድ መሞከር ነው፤ ከዚያ ውጭ የኛ ጉዳይ ባልሆነ ነገር ጣልቃ አንገባም " ብለዋል፡፡

ግጭቱን "አስፈሪ" ሲሉ የገለጹት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው፣ "ሁለቱንም ሀገራት አውቃቸዋለሁ የምረዳቸው ነገር ካለ እገኛለሁ" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ህንድ "የአሸባሪዎች ካምፕ" ባለቻቸው በፓኪስታን የሚገኙ ዘጠኝ ወታደራዊ ስፍራዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ፤ ፓኪስታን የአጸፋ እርምጃ ከወሰደች በኋላ ሀገራቱ ግጭት ውስጥ ገብተዋል፡፡
#newsbytes

@ThiqahEth
👍12😁8🔥21🤔1