THIQAH
"ስምምነቱ 24 ሰዓት ሳይሞላው ተጥሷል" - ህንድ ህንድ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መጣሱን ገለጸች። የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፀሐፊ ቪክራም ሚስሪ፣ "ፓኪስታን በዛሬው እለት ድንበር ላይ ስምምነቱን የጣሰ አሳፋሪ ጥቃት ፈጽማለች" ብለዋል። "ፓኪስታን ስምምነቱ እንድተገበር አስፈላጊ እርምጃዎችን እንድትወስድ ጥሪ እናቀርባለን" ሲሉም ተናግረዋል። ትራምፕ ትናንት ሁለቱ የደቡብ እስያ ሀገራት በአሜሪካ…
#Update
"የቀረበብን ውንጀላ መሰረተቢስ ነው" - ፓኪስታን
የፓኪስታን ባለስልጣናት ህንድ ያቀረበችውን ወቀሳ "ውንጀላ" በሚል የመልስ ምት ሰጥተዋል።
የፓኪስታን ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አታዑላህ ታራር ህንድ፣ "ፓኪስታን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች" በማለት ላቀረበችው ወቀሳ፣ "የቀረበብን ውንጀላ መሰረተቢስ ነው" ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም፣ "ኢስላማባድ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለመተግበር ቁርጠኛ ናት" ሲል አስታውቋል።
የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሸባዝ ሻሪፍ ከስምምነቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት "በህንድ ላይ ላገኘነው ድል የፓኪስታን ወታደሮች ብቻ ሳትሆኑ መላው ህዝባችን እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።
"የፓኪስታን ጦር እና ጄት የህንድን ጦር በሰዓታት ውስጥ እንዴት ፀጥ እንዳደረገው ታሪክ ሁሌም ሲያስታውሰው ይኖራል" ሲሉም ተናግረዋል ሲል #geonews ዘግቧል።
ህንድ፣ "ፓኪስታን በዛሬው እለት ድንበር ላይ ስምምነቱን የጣሰ አሳፋሪ ጥቃት ፈጽማለች" ስትል ወቅሳ ነበር።
@ThiqahEth

👍24🔥2🥰2🤔2😁1😱1