THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
#USA

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተፈጸመባቸው የግድያ ሙከራ ሕዳር 2017 ላይ የሚደረገውን የምርጫ ሂደትን ከመቀየሩም በላይ የአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ክስተት ነው ተብሏል።

ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ በ20 ዓመት ወጣት የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል።

ህክምና ተደርጎላቸውም ቤታቸው ገብተዋል።

ሙከራውን የፈጸመው ወጣትም በሴክሬት ሰርቪስ በስናይፐር ተመቶ ተገድሏል።

የግድያ ሙከራው የመጪውን ምርጫ ሂደት ይቀይራል ፤  የአገሪቱ ፖለቲካ ላይም ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ክስተት ነው ተብሏል። #BBC

@thiqaheth
👍21😱31🥰1👌1😭1
በትግራይ ክልል የረሃብ ቀውስ መኖሩን የሚያጋልጥ የሳተላይት ምስል ይፋ ሆነ፡፡

ከሳተላይት ምስሉ በተጨማሪ የህክምና ዶክተሮች ስለተከሰተው የረሃብ አደጋ ምስክርነት ሰጥተዋል ተብሏል፡፡

ድርቅ፣ የሰብል ምርት እጥረትና ከጦርነቱ በኋላ የተስፋፋው የደህንነት ችግር በትግራይ ክልል ለተከሰተው ረሃብ ዋነኛ ምክንያቶች ተደርገው ተወስደዋል፡፡

በክልሉ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ በረሃብ አደጋ ውስጥ እንደሚገኝ የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ #BBC

@thiqaheth
😭16🙏71👍1😁1😱1😢1
በዩናይትድ ኪንግደም ጸረ-ስደተኛ ተቃውሞ ተባብሷል።

ተቃውሞ ሊረግብ ባለመቻሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪየር ስታርመር ካቢኔያቸው አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።

ይህ ሙስሊም ጠል እና ጸረ- ስደተኛ መልክ እየያዘ የመጣው አመጽ ዜጎች እና ንብረተ ላይ ጉዳት አድርሷል።

ፖሊስ 150 ቀኝ አክራሪ ነውጠኞችን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ ብሏል።

ሮተራም በምትባለው የዩኬ ከተማ ነውጠኞች፣ ስደተኞች አርፈውበታል በሚባል ሆቴል ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

ይህን ተከትሎ ሰር ኪየር ስታርመር ድርጊቱን ኮንነዋል።

ከሮተራም ሌላ በታምዎርዝ፣ ሚድልቦሮ እና ሮተርሃም ትናንት እሑድ ነውጡ አይሎ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ቦዘኔ " ያሏቸውን ነውጠኞች ለሕግ እንደሚያቀርቡ ዝተዋል።

ዛሬ ሰኞ ሰር ኪየር ስታርመር የጠሩት ድንገተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ካቢኔያቸውን ጨምሮ ደኅንነትና ፖሊስን የሚያካትት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስተር ሰር ስታርመር ትናንት እሑድ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር " በጸረ-ስደተኞች አመጽ ውስጥ የተሳተፉ ሁሉ ከመጸጸታቸው በፊት እጃቸውን እንዲሰበስቡ እመክራለሁ " ብለዋል።

" በአገራችን ዩኬ ሁሉም ሕዝብ ደኅንነቱ ተጠብቆ ይኖራል። ይሁንና ሙስሊሞች የጥቃት ሰለባ ሆነዋል። መስጊዶች አደጋ እየደረሰባቸው ነው፤ ሌሎች አናሳ ማኅበረሰቦችም ስጋት ላይ ናቸው፣ የናዚ ሰላምታ በየጎዳናው እየታየ ነው። ፖሊስ ተደብድቧል። ይህ የአደገኛ ቦዘኔነት ድርጊት ነው። ይህ ነውረኛ ድርጊት በስሙ ለመጥራት አላፍርም፤ ይህ የቀኝ አክራሪዎች የአደገኛ ቦዘኔነት ተግባር ነው " ብለዋል።

የአገር ውስጥ ሚኒስትር ለመስጊዶች ልዩ ጥበቃ እንዲያደርግ አዟል። ምዕመናን ወደ መስጊዶቻቸው በፍጥነት እንዲመለሱም እየተሠራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል ገብተዋል። #BBC

@thiqaheth
👍492😁1😡1
''45 ሰዎች ሙተዋል 61 ሰዎች ደግሞ ጠፍተዋል'' - IOM

በጅቡቲ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ 45 ሰዎች መሞታቸውን አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል፡፡

ጀልባዋ ከየመን 310 ሰዎችን አሳፍራ መነሳቷን ነው ድርጅቱ የገለጸው፡፡

ከተጓዦቹ ውስጥ 115 ሰዎችን ከአደጋው ማትረፍ ተችሏል፡፡ #bbc #iom @thiqaheth
😭11👍42
ዩክሬን ከእንግሊዝ በተረከበችው ሚሳኤል ሩሲያ ላይ ጥቃት አደረሰች።

ኪቭ ከእንግሊዝ በተበረከተላት የስቶርም ሻዶው መሳሪያ ሞሶኮን ስታጠቃ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ዩክሬን ረጅም ርቀት ሚሳዔሎችን ተጠቅማ ጥቃት እንዳትሰነዝር የጦር መሳሪያ ድጋፍ የሚያደርጉላት ሀገራት ክልከላ ጥለውባት ነበር።

ከቀናት በፊት ከአሜሪካ የተረከበችውን ባለስቲክ ሚሳኤል በመጠቀም በሩሲያ ላይ ጥቃት ሰንዝራ ነበር። #bbc

@thiqaheth
👍11🔥3
በፓኪስታን በተፈጠረ ድንገተኛ አመጽ ከ80 በላይ ሲገደሉ፣ 156 የሚደርሱት ሰዎች ደግሞ ቆሰሉ።

አመጹ የተፈጠረው አንድ ታጣቂ የሺያ ሙስሊም ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ነው።

በኩራም ግዛት የሺያና ሱኒ ሙስሊሞች በመሬት ይገባኛል ጥያቄ በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ እንደገቡ ተዘግቧል።

አመጹ የተቀሰቀሰባት የኩራም ግዛት ፓኪስታን ከአፍጋኒስታን ጋር የምትዋሰንባት ድንበር ናት። #bbc

@thiqaheth
👍14😁4🔥3😱32🙏1
THIQAH
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወታደሮች "ለኤም 23 እጅ እየሰጡ ነው"? የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንኮ ወታደሮች "ለኤም 23 እጅ እየሰጡ ነው" ተባለ። ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችና የፖሊስ ኦፊሰሮች በታጣቂዎች ታጅበው በተሸከርካሪ ተጭነው ሲሄዱ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ሆኗል፡፡ በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው ታጣቂ ቡድኑ ዛሬ Su-25 ታንክ መማረኩን አስታውቋል፡፡ በሀገሪቱ ወታደሮች እና…
#Update

"በአምስት ቀናት  ውስጥ ብቻ 700 ሰዎች ተድለዋል፤ 2,800 ሰዎች ቆስለዋል" - ተ.መ.ድ

የመንግስታቱ ድርጅት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንደ አዲስ በተለይ ጎማ ከተማ ያገረሸውን ጦርነ፣ "አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሷል" ሲል ገልጾታል።

"በአምስት ቀናት ውስጥ ብቻ 700 ሰዎች ሞተዋል፤ 2,800 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል" ብሏል።

የታጣቂ ቡድኑ ኤም 23 ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠራት የጎማ ከተማ ሰብዓዊ ቀውስ መጎባቱንም ገልጿል።

በሩዋንዳ እንደሚደገፍ የሚነገርለት ቡድኑ ሰፋፊ ስትራቴጂካዊ ስፍራዎችን መቆጣጠር ጀምሯል።

የምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦርነት በአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ ቢጀመርም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ተባብሷል።

የቱትሲ ብሔርን ያቀፈው የኤም23 አማጺያን ለአናሳዎች መብት እንደሚታገሉ ይናገራሉ።

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት በበኩሉ በሩዋንዳ የሚደገፉት "አማጺያኑ" በማዕድን ሃብታም የሆነውን የምስራቃዊውን ሰፊ ሥፍራ ለመቆጣጠር ይፈልጋሉ ሲል ይወቅሳል።

#Anadoluagency #Bbc

@ThiqahEth
😭14👍10
THIQAH
"በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ የተጣለው ቀረጥ ከቅዳሜ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል"  - ካሮሊን ሌቪት "አስገዳጅ ሊሆን ይችላል ግን ምክንያታዊ መሆን አለበት"  - ጀስቲን ትሩዶ በካናዳ እና ሜክሲኮ ላይ የ25% እንዲሁም በቻይና ላይ ደግሞ የ10% የቀረጥ ጭማሪ መደረጉን የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ሌቪት ገልጸዋል። "በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ የተጣለው ቀረጥ ተግባራዊ ይሆናል" ነው ያሉት።…
"ካናዳ አሜሪካ ንግድ ላይ ለወሰደችው እርምጃ 155 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጀመሯን አሳውቃለሁ"  - ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ

ካናዳ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔ ላይ የአፀፋ እርምጃ ወስዳለች።

ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ የተጣለባት ካናዳ፣ በአሜሪካ ምርቶች ላይም ተመሳሳይ ታሪፍ ጥላለች።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፣ "ዛሬ ካናዳ አሜሪካ ንግድ ላይ ለወሰደችው እርምጃ 155 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጀመሯን አሳውቃለሁ" ብለዋል።

ከአሜሪካ በሚገቡ የቢራ እና የወይን ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣላቸውን አስታውቀዋል።

የነጩ ቤተ መንግሥት እርምጃ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ ውሳኔው የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች እንደሚጎዳ ግልጽ ነው ብለዋል። #bbc #shine

@ThiqahEth
👍45🔥84😁2
የአረብ ሀገራት መሪዎች የትራምፕ "ጋዛን መልሶ ማልማት" እቅድ ፈጽሞ ተገቢ እንዳልሆነ ገለጹ፡፡

መሪዎቹ ከ2 ሚሊዮን በላይ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሙሉ በሙሉ ያፈናቅላል በተባለው የትራምፕ እቅድ ዙሪያ በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ አስቸኳይ ስብሰባ አድርገዋል፡፡

ግብጽ ያቀረበችው ባለ 91 ገጽ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ ከትራምፕ እቅድ ጋር የተቃረነ ነው ተብሏል፡፡

እቅዱ የልማትና የብልጽግና ሳይሆን የፖለቲካና ለፍልስጤማውያን ደግሞ የመብት ጉዳይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
#bbc

@ThiqahEth
👍40🔥2
በእንግሊዝ የሂትሮው አየርመንገድ በመዘጋቱ 1300 በረራዎች መቋረጣቸው ተገለጸ፡፡

የእንግሊዙ ሄትሮው አየር መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይል ፈንድቶ የእሳት አደጋ ተከስቷል ተብሏል፡፡

በዚህ አደጋ ምክንት በሺዎች የሚቆጠሩ የአየር መንገዱ ደንበኞች ጉዟቸው መስተጓጎሉን የገለጸው አየር መንገዱ፤ በቀጣይ ስለክስተቱ ተጨማሪ ማብራሪያ እስኪሰጥ ድረስ ወደ ውስጥ መግባት እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

የአየር መንገዱ የኢነርጅ ድፓርትመንት ፅሐፊ ኤድ ሚልባንድ፣ የተቋጠውን ኃይል በፍጥነት በመመለስ አገልግሎት ለመስጠት እንሞክራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
#bbc     #aa

@ThiqahEth
👍91🔥1🤔1
"አሜሪካ የበርበራ፣ ቦሳሶ እና ባሊዶግሌ ወደብን ሙሉ በሙሉ እንድታስተዳድር ፍቃደኛ ነን"  - ሶማሊያ

"አሜሪካ ከእኛ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን እናውቃለን" - ሶማሌላንድ

ሶማሊያ አሜሪካ በብቸኝነት የምትቆጣጠረው የአየር ኃይል እና ወደብ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ለትራምፕ በፃፉት ደብዳቤ መግለፃቸው ተዘግቧል።

ሀሰን ሼክ ይህን ፍላጎታቸውን የገለጹት አሜሪካ ለተገንጣይዋ የሶማሌላንድ ግዛት እውቅና እንዳትሰጥ በሚል ስጋት ነው ተብሏል።

የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱረህማን ዳሂር በበኩላቸው፣ "የምን ትብብር፣ አሜሪካ ይህን የከሸፈ የሶማሊያ መንግስት ረስታዋለች" ብለዋል።

"አሜሪካ ሞኝ አይደለችም" ያሉት አብዱረህማን፣ "ከማን ጋር መደራደር እንዳለባት በደምብ ታውቃለች" ሲሉ አክለዋል።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሞቃዲሾ የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ሀርጌሳን እውቅና ሊሰጥ ይችላል የሚሉ መረጃዎች በተደጋጋሚ ሲወጡ ቆይተዋል።
#reuters #newarab #bbc

@ThiqahEth
😁23👍9😢32🤔2
ሦስት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 67 አፍሪካዊያን ስደተኞች በአሜሪካ ጥቃት ሲገደሉ፣ 47 የሚሆኑት ቆሰሉ።

አሜሪካ በሳዳህ ከተማ ባደረሰችው የአየር ላይ ጥቃት 67 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ሌሎች 47 የሚሆኑት ቆስለዋል ተብሏል።

ከሟቾቹ ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ አፍሪካዊ ስደተኞች ናቸው ተብሏል።

ኢትዮጵያውያኑ ከትግራይ ክልል የተሰደዱ መሆናቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። 
#borkena #almasirahtv #bbc

@ThiqahEth
😢22👍2🙏21🤔1😱1😭1😡1
245 ሚሊዮን ዶላር ያጭበረበሩት የቀድሞው ጠቅላይ የሚኒስትር በጉልበት ሥራ ተቀጡ።

የቀድሞው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦውገስቲን ማታታ ፖንዮ በሙስና ወንጀል ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀድሞው የማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ ጋር በመመሳጠር ወንጀሉን መፈጸማቸውን የኮንጎ ህገ መንግስታዊ ፍር ድቤት አስታውቋል።

የማታታ ጠበቃ፣ "ከህግ አግባብ ውጭ የተፈጸመ የፖለቲካ ውሳኔ ነው" ሲል ፍርዱን አጣጥሎታል።
#bbc

@ThiqahEth
😁25👍3🤔3🔥1
#Update

በናይጄሪያው ጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ200 እንዳሻበቀ፣ 500 ሰዎች ያሉበት እንደማይታወቅ፣ የሟቾች ብዛት 700 እንደሚደርስ ተነገረ።

በናይጄሪያዋ ሞካዋ ከተማ በጎርፍ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ200 በላይ እንደሆነ፣ ቁጥሩ እስከ 700 እንደሚደርስ ቢቢሲ ዘግቧል።

ዘገባው፣ “እስካሁን 500 ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ተከትሎ የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በሕይወት የሚገኝ ሰው ከዚህ በኋላ አይኖርም በሚል እምነት የነፍስ አድን ጥረቱ ተቋርጧል” ብሏል።

በአካባቢው ተላላፊ በሽታ እንዳይዛመት በጎርፉ የተቀበሩ ግለሰቦችን ቆፍሮ በማውጣት ተገቢው የቀብር ሥነ ሥርዓት ማከናወን በቅርቡ እንደሚጀመር የሞካዋ አካባቢ አስተዳዳሪ ሙሐመዱ አሊዩ ተናግረዋል።

ባለቤቱ እና ጨቅላ ልጁ በጎርፍ የተወሰዱበት አዳሙ ዩሱፍ የተባለው ግለሰብ "ቤተሰቤን ጎርፍ ሲወስድ ምንም ማድረግ ሳልችል ቆሜ ተመልክቻለሁ። እኔም መዋኘት በመቻሌ ነው የተረፍኩት" ሲል ገልጿል።

እ.አ.አ በ2022 በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ600 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
#BBC

@ThiqahEth
😭162🤔1😱1😢1
"ዋነኛው የመርከቦች መጓጓዣ መዘጋት የለበትም" - አሜሪካ

አሜሪካ በኢራን ውሳኔ ቻይናን ተማፀነች። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ቻይናና ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ከመዝጋት እንዲታስቆማት ጠይቀዋል።

ሩቢዮ "ዋነኛው የመርከቦች መጓጓዣ መዘጋት የለበትም" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፣ "የትኛውም መስተጓጎል በአለም ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል" ብለዋል። 
#bbc

@ThiqahEth
🤔1712😭3😡2😢1
"ኔታንያሁን የምትጠብቁበት ጊዜ ላይ ናችሁ" - ትራምፕ።

ትራምፕ የኔታንያሁ የሙስና ክስ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ፣ "አሜሪካ በኢራን ጦርነት ከእስራኤል በኩል ጣልቃ የገባችው በእሱ ምክንያት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

"ኔታንያሁ በእስራዔልና ኢራን ጦርነት ትልቅ ለውጥ አምጥተዋል" ያሉት ዶናልድ ትራምፕ "ኔታንያሁን የምትጠብቁበት ጊዜ ላይ ናችሁ" ብለዋል።

የትራምፕ ንግግር በእስራኤል የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በገንዘብ ማጭበርበርና እምነት ማጉደል ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2020 የጀመረው የፍርድ ሂደታቸውን እንደማይቀበሉት ቢገልጹም እስካሁን ድረስ መቋጫ አላገኘም።
#bbc

@ThiqahEth
18😡11👏4🤔1😢1
"170 በረራዎችን ለመሰረዝ ተገደናል" - የራይነር አየር መንገድ

የፈረንሳይ አየር መንገድ የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ጥቃት እንደደረሰበት ተገለፀ።

ጥቃቱን ተከትሎ የ30,000 ተጓዦች በረራ መቋረጡን የራይነር አየር መንገድ ገልጿል።

አየር መንገዱ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መግለጫ፣ "170 በረራዎችን ለመሰረዝ ተገደናል" ሲል አስታውቋል።

በአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያው ላይ የደረሰውን አደጋ በተመለከተ አየር መንገዱ የሰጠው ማብራሪያ የለም።
#bbc

@ThiqahEth
7👏1🙏1
የሩሲያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ከስልጣን ከተነሱ ከሰዓታት በኋላ ሙተው ተገኙ።

ፕሬዝዳንት ፑቲን የትራንስፖርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ሮማን ስትራቮይትንን ዛሬ ከኃላፊነት አንስተዋል።

በምትካቸውም ምክትላቸውም የነበሩትን አንድሬይ ኒኪቲን ሹመዋል።

ስትራቮይት በሰዓታት ልዩነት ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የምርመራ ኮሜቴው አስታውቋል። ፑቲን ከኃላፊነት ያነሱበት ምክንያት በግልጽ አልተነገረም ተብሏል።
#bbc #newsmax

@ThiqahEth
🤔127😢5💔4
ዶናልድ ትራምፕ የአምስት አፍሪካ ሀገራት መሪዎችን በዋይትሐውስ ሊጋብዙ ነው ተባለ።

ዶናልድ ትራምፕ የጋቦን፣ ጊኒ ቢሳው፣ ላይቤሪያ፣ ሞሪታንያ እና ሴኔጋል መሪዎችን መርጠው በቤተመንግሥታቸው ለመወያየት ማቀዳቸው ተገልጿል።

ፕሬዝዳንቱ "እርዳታ ሳይሆን ንግድ" በሚለው ፖሊሲያቸው ከመሪወቹ ጋር የንግድ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ውይይት ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#bbc

@ThiqahEth
👏185😱4🕊2
ቡርኪናፋሶ "ገንዘብ አባካኝ" ያለችውን  የምርጫ ኮሚሽን እንቅስቃሴን አገደች።

የቡርኪናፋሶ ባለስልጣናት ኮሚሽኑ በውጭ አካላት ተፅዕኖ ስር ወድቋል በሚል እገዳ እንደጣሉበት ተገልጿል።

የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር የኮሚሽኑን ስራ ደርቦ እንድሰራ መወሰኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 
#bbc #rtbtv

@ThiqahEth
15🕊4🤔3😱1😡1