THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
የጃፓን ግዙፍ የተሸከርካሪ አምራች ካምፓኒዎች ሆንዳ እና ኒሳን ለመዋሃድ ማቀዳቸውን አስታወቁ፡፡

ሁለቱ ግዙፍ ተሽርካሪ አምራች ድርጅቶች ጃፓን በዓለም ላይ በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ምርት በገበያ ላይ ተወዳዳሪ እድትሆን በማለም ነው ለመዋሃድ ያሰቡት ተብሏል፡፡

ውህደቱን እውን ለማድረግ የሁንዳ ሥራ አስፈጻሚ ቶሺሂሮ ሚቤ እና የኒሳን ስራ አስፈጻሚ ማኮቶ ኡቺዳ ዛሬ የመግባቢያ ስምነት ተፈራርመዋል፡፡

ሆንዳ እና ኒሳን ከተዋሃዱ በዓለም ላይ ከቶዮታ እና ቮልስዋገን በመቀጠል ሶ
ሦስተኛውን ግዙፍ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ እንደሚመሰርቱ ተዘግቧል፡፡

ሁለቱ ግዙፍ ተቋማት 2026 ላይ አዲሱን ካምፓኒ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ #aljazeera

@ThiqahEth
👍325
''የሆነ ቀን ዩክሬን የሩሲያ ሆና ልናያት እንችላለን'' - ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የዩክሬንን ባለስልጣናት፣ ''ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ ላያደርጉም ይችላሉ፤ አንድ ቀን የሩሲያ ሊሆኑ ይችላሉ ላይሆኑም ይችላሉ'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ ዩክሬን በጦርነቱ ከአሜሪካ የተደረገላትን ወደ 500 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ድጋፍ፤ ያሏትን ማዕድናት በካሳ መልክ እንድታቀርብ አዘዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንድሪ የርማክ በበኩላቸው፣ ከሩሲያ ጋር ለሚደረገው ስምምነት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፤ የደህንነት ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
#aljazeera    #associatedpress

@ThiqahEth
😁46👍6😱2
"ለገጠመን የኑሮ ውድነት ችግር ጥብቅ የሞነታሪ ፖሊሲ መከተል ግድ ይለናል'' - የህንድ ባንክ

ህንድ ሁሉም ባንኮች ወለድ እንዲያቆሙ አዘዘች፡፡

የህንድ ማዕከላዊ ባንክ የኢኮኖሚ ቀውስን ለመግታት በሚል ለመጀመሪያ ጊዜ የባንክ ወለድ እንዲቀር ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ 

የባንኩ ገዥ ሳንጃይ ማልሆትራ፣ ''ለገጠመን የኑሮ ውድነት ችግር ጥብቅ የሞነታሪ ፖሊሲ መከተል ግድ ይለናል'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ማልሆትራ፣ ''የዋጋ መረጋጋትን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እና የፋይናንስ መረጋጋትን ለመፍጠር የማክሮ ኢኮኖሚክ መሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል'' ብለዋል፡፡

በህዝብ ቁጥር ከዓለም አንደኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው እስያዊቷ ሀገረ ህንድ የምጣኔ ሃብት እድገቷ ላለፉት አምስት ተከታታይ አመታት እየቀነሰ መምጣቱን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡
#aljazeera

@ThiqahEth
👍10🔥41
ሀማስ እስራኤልን ታጋቾችን በማዘግየቷ ወቀሰ።

620 ታጋቾች አለመለቀቃቸውን የገለፀው ሀማስ "እስራዔል ግልፅ ጥሰት" ፈፅማለች ሲል  አውግዟል። 

እስራኤል ፍልስጤማውያን ታጋቾችን የመልቀቋን ውሳኔ ይፋ ባላደረገችው ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ አራዝማለች።

ይሁን እንጂ ሀማስ በስምምነቱ መሰረት መልቀቅ ያለበትን ስድስት እስራኤላውያን ታጋቾችን ለቋል።
#aljazeera

@ThiqahEth
👍18
THIQAH
Photo
#Update

"እያንዳንዱ ሰው መትረፉንም ሆነ መሞቱን እስከምናረጋግጥ እዚህ እንቆያለን" - ጁዋን ሜንዴዝ

በዶሚኒካን ሪፐብሊክ የሟቾች ቁጥር 218 ደረሰ።

የአደጋ ምርመራ ዳይሬክተር ጁዋን ሜንዴዝ፣ "189 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ችለናል ግን አስቸጋሪ ሁኔታ ገጥሞናል" ብለዋል።

"በህይወት የተረፉትን ማዳን ተስፋ አስቆራጭ ሆኗል" ያሉት ዳይሬክተሩ፣ "እያንዳንዱ ሰው መትረፉንም ሆነ መሞቱን እስከምናረጋግጥ እዚህ እንቆያለን" ሲሉ ተናግረዋል። #aljazeera

@ThiqahEth
😢11👍6😱1
በኮንጎ በተከሰተ ጎርፍ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች ሞቱ።

በአደጋው አብዛኛዎቹ ሟቾች ህፃናት እና አረጋውያንን ናቸው የተባለ ሲሆን፣ 28 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

የዘነበው ከባድ ዝናብ በተለይ በምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል ከተሞች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
#aljazeera

@ThiqahEth
😭24🔥1😱1😡1
የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ላይ "ወረራ" ሲፈጽሙ በንጹሐን ላይ ሞትና መቁሰል አጋጠመ።

በወረራ በያዙት ዌስት ባንክ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም በወሰዱት የኃይል እርምጃ አንድ ፍልስጤማዊ ህይወቱ ሲያልፍ 30 የሚደርሱት ቆስለዋል።

የራማላህ፣ ናቡልስ፣ ቤተልሔም እና ጄኒን ከተሞች ውድመት ደርሶባቸዋል ተብሏል።
#aljazeera

@ThiqahEth
😡26👍6🔥3🤔21🥰1😢1
"አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" - ናይጄሪያ

ናጄሪያ በጎርፍ አደጋ የሞቱ፣"እስካሁን 115 አስክሬኖች አንስተናል" አለች።

በማክዋ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።

የናይጄሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ አስተዳደር (SEMA) ቃል አቀባይ ኢብራሂም ሁሴን "አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" ሲሉ ተናግረዋል።

በባለፈው አመት በተከሰተ ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ ከ1200 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
#aljazeera

@ThiqahEth
😢155😭5🕊2
"ከ30 በላይ እርዳታ ፈላጊዎች በእስራኤል ተገድለዋል" - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር

"የደረሰ ጉዳት የለም፣የእርዳታ ስርጭቱ በሰላም ተጠናቋል" - የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን

የእስራኤል ጦር በራፋህ የእርዳታ ጣቢያ ምግብ በመጠባበቅ ላይ በነበሩ ንፁሃን ላይ ጥቃት ማድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 170 የሚደርሱት መጎዳታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን (GHF) በበኩሉ ደረሰ የተባለውን ጉዳት "በእርዳታ ወቅት ሰዎች በስነስርዓቱ ተከፋፍለው ሂደዋል" በማለት በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ማስተባበያ ሰጥቷል።

የእስራኤል ጦርም በተመሳሳይ "በንፁሃን ላይ የተቃጣ እርምጃ የለም" ሲል የቀረበበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።

አንድ የአይን እማኝ ግን "የእስራኤል ወታደሮች በሺዎች የሚቆጠሩ እርዳታ ጠባቂዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር" በማለት ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ሆስፒታል ላይ በፈፀመችው ጥቃት 54 ሰዎች መገደላቸውንና የኩላሊት መታጠቢያ ማሽንን ሙሉ በሙሉ ማውደሟን ተመድ አስታውቋል።
#cnn #aljazeera

@ThiqahEth
😢21😡43🙏3🕊2😱1
"ሂዝቦላ ከመሰረተ ልማቶች ቀጥሎ የመሸገው እናንተ ውስጥ ነው"  - እስራኤል

እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ድብደባ መፈጸሟ ተነግሯል።

የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ አቪቻይ አድራየ በሀዳት፣ ሀረት ኸሪክ እና ቡርጂ አልባራን የሚገኙ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።

"ሂዝቦላ ከመሰረተ ልማቶች ቀጥሎ የመሸገው እናንተ ውስጥ ነው" ብለዋል ቃል አቀባዩ።

በእስራኤልና ሊባኖስ መካከል ባሳለፍነው ህዳር ወር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ላለፉት ሰባት ወራት አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ የእስራኤል ጦር ከሂዝቦላህ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረገ በኋላ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ጥቃት አድርሷል። 
#aljazeera

@ThiqahEth
12😡6
በደቡብ አፍሪካ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ49 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ጠፉ።

ከሞቱት ሰዎች መካከል ከትምህርት ቤት ወደ ቤታቸው በመመለስ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት የኢስተርን ኬፕ ግዛት ባለስልጣን ኦስካር ማቡያኔ ተናግረዋል።

በጎርፍ አደጋው የተጎዱ ከ500 በላይ የሚደርሱ ሰዎች ወደ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።

ማቡያኔ በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መጣሉ ለአደጋው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
#aljazeera

@ThiqahEth
😢92💔2
"ጊዜው አልረፈደም" - ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን በእስራኤል ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እንድታቆም አሁንም ጠየቁ።

ትራምፕ ፣"ቴህራን የቦምብ ጥቃቱን ለማቆም ጊዜው አልረፈደባትም" ብለዋል።

"ይህ የሚሆነው ግን የኑክሌር ፕሮግራም ላይ ስምምነት ላይ ከደረሰች ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል በበኩሏ የኢራንን ሚሳዔል ኢላማ ማድረጓን እንደምትቀጥል ገልፃለች።
#aljazeera

@ThiqahEth
😡1812👏2
እስራኤል ዛሬ ሰነዘረችው በተባለ ጥቃት 59 ፍልስጤማውያንን መገደላቸው ተነገረ።

ሟቾቹ በጋዛ የሰብዓዊ እርዳታ ለመቀበል በመጠበቅ ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

እስራኤል በኔትዛሪም ኮሪደርና በራፋህ አልማስራዊ የሚገኙ የስደተኞች ጣቢያ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ነው የፍልስጤማውያኑ ህይወት ያለፈው። #aljazeera

@ThiqahEth
😭67😢83💔3🕊1
ኢራን በአሁኑ ሰዓት በእስራኤል ላይ የድሮንና ሚሳዔል ጥቃት እየፈጸመች ስለመሆኗ መረጃዎች እየወጡ ነው።

ኢራን እስራኤል ከሰዓታት በፊት በብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ እየወሰደች እንደምትገኝ አስታውቃለች።

እስራኤል የኢራን ዜጎች ከቴህራን ለቀው እንዲወጡ ስታሳስብ፣ ኢራንም በቴላቪቭ ለሚኖሩ እስራኤላውያን ተመሳሳይ ጥሪ አቅርባለች። 
#aljazeera

@ThiqahEth
15😢3🕊1
ፓኪስታን ምን እያለች ነው?

ፓኪስታን ዶናልድ ትራምፕ በ2026 የኖቤል ተሸላሚ እንዲሆኑ ጠየቀች።

ኢስላማባድ ፕሬዝዳንት ትራምፕ "በፓኪስታንና በህንድ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በመፍታት የሚሊየኖችን ህይወት ከሞት ታድገዋል" ስትል ገልፃለች።

በደቡብ እስያ ቀጠና ሊፈጠር የነበረውን አውዳሚ ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ወሳኝ መፍትሄ ማምጣት ችለዋል ብላለች።

ፓኪስታን ትራምፕን፣ "ግጭትን በድርድር እንዲፈታ የማድረግ አቅም ያለው ትልቅ ሰላም ፈጣሪ ሰው ነው" ብላለች።

ይሁን እንጂ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቅርቡ በህንድና ፓኪስታን የተኩስ አቁም ስምምነት "አሜሪካ አላሸማገለችንም፣ የዋሽንግተን ሚና አልነበረም" ብለው ነበር።

ትራምፕ የፓኪስታንና የህንድን ጨምሮ፣ የኢትዮጵያ እና የግብጽን ውዝግብ እንደፈቱ በመግለጽ በተደጋጋሚ ነገር ግን ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ የሰላም ኖቤል ሽልማት እንዳላገኙ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
#aljazeera

@ThiqahEth
😡3921🤔5🕊3😱1🙏1💔1😭1
ኢራን በኳታር እና ኢራቅ የሚገኘውን የአሜሪካ ጦር ሰፈር ደበደበች።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሁለቱም ሀገራት የሚገኙት የጦር ሰፈሮች ላይ ከባድ የሚሳዔል አደጋ ማድረሱን ገልጿል።

ቴህራን አሜሪካ በጦርነቱ የምትሳተፍ ከሆነ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የጦር ሰፈሮችን እንደምታጠቃ በተደጋጋሚ አስጠንቅቃለች።
#aljazeera

@ThiqahEth
👏4411🕊4😱3😡3
ኳታር ሙሉ በሙሉ የአየር ክልሏን ዘጋች።

ከኳታር በተጨማሪ ሌሎች አራት ሀገራት ማለትም ኦማን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬት፣ ኢራቅ እና ኩዌት የአየር ክልላቸውን በከፊል ዘግተዋል ተብሏል።

አሜሪካና እንግሊዝ ዜጎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ እንዲጠለሉ አስጠንቅቀዋል።

ማስጠንቀቂያው የመጣው ኢራን በኳታር የሚገኘውን አል ኡዳይድ ወታደራዊ ስፍራ መደብደቧን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።
#aljazeera

@ThiqahEth
21😢1🕊1😭1
"እስራኤል ትራምፕ ባቀረቡት እቅድ ትስማማለች" - ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ባወጡት መግለጫ ሀገራቸው በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማካኝነት ለቀረበው የተኩስ አቁም ስምምነት መተግበር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

"እስራኤል ትራምፕ ባቀረቡት እቅድ ትስማማለች" ያሉት ኔታንያሁ "ለጥረታቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕን አመሰግናለሁ" ብለዋል።
#aljazeera

@ThiqahEth
20🤔6😱1
"ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንልካለን" - ትራምፕ ለዩክሬን

ትራምፕ አሜሪካ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ልታደርግ እንደምትችል ጠቆሙ።

"ዩክሬን አሁን በጣም እየተጎዳች ነው" ያሉት ትራምፕ "የመጀመሪያ ዙር ድጋፋችን ሊሆን የሚችለው የመከላከያ መሳሪያዎችን ማጓጓዝ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ትራምፕ "ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንልካለን፣ እሱን ማድረግ አለብን፣ ራሳቸውን (ዩክሬናውያን) መከላከል አለባቸው" ብለዋል።

የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሴን ፓርኔል በበኩላቸው፣ ትራምፕ ለዩክሬን የጦር  መሳሪያ የመላክ እቅድ እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
#aljazeera #Independent

@ThiqahEth
15😡3🙏2🕊1