THIQAH
13K subscribers
2.61K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
በእንግሊዝ የሂትሮው አየርመንገድ በመዘጋቱ 1300 በረራዎች መቋረጣቸው ተገለጸ፡፡

የእንግሊዙ ሄትሮው አየር መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይል ፈንድቶ የእሳት አደጋ ተከስቷል ተብሏል፡፡

በዚህ አደጋ ምክንት በሺዎች የሚቆጠሩ የአየር መንገዱ ደንበኞች ጉዟቸው መስተጓጎሉን የገለጸው አየር መንገዱ፤ በቀጣይ ስለክስተቱ ተጨማሪ ማብራሪያ እስኪሰጥ ድረስ ወደ ውስጥ መግባት እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

የአየር መንገዱ የኢነርጅ ድፓርትመንት ፅሐፊ ኤድ ሚልባንድ፣ የተቋጠውን ኃይል በፍጥነት በመመለስ አገልግሎት ለመስጠት እንሞክራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
#bbc     #aa

@ThiqahEth
👍91🔥1🤔1
የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን አወገዙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኦልመርት የወቅቱን የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁን "በፍልስጥኤማውያን ላይ ወንጀል ፈጽመዋል" በማለት ከሰዋል።

ዌስት ባንክን ጨምሮ በፍልስጥኤም ግዛቶች ላይ ግፍ ተፈጽሟል ብለዋል ኦልመርት።

የእስራኤል መንግስት መጠለያ ካምፕ ላይ በሚገኙ ንጹሐን ዜጎች አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙ ሊወገዝ የሚገባ እርምጃ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
#aa

@ThiqahEth
👍56🤔3😢2😱1😭1
"በታሪክ ትልቁ የመከላከያ ስምምነት ተፈጽሟል" - ዋይትሃውስ

አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ከእስከዛሬው ትልቅ የተባለና
#የ142_ቢሊዮን_ዶላር የመሳሪያ ሽያጭ ስምምነት ፈጸሙ።

ስምምነቱ የአየር ኃይል ማሻሻልን፣ የሚሳዔል መከላከያ፣ የምድር ኃይል ማዘመንንና የግንኙነት ስርዓት መገንባትን ያጠቃልላል ተብሏል።

ነጩ ቤተ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፣ ስምምነቱ የሰው ኃይል ማሰልጠንንና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚያካትት ገልጿል።
#aa

@ThiqahEth
👍212🔥2😁2🥰1😱1
"የነፃነት ዞን ለመፍጠር አሜሪካ ጋዛን ማስተዳደር ይኖርባታል" - ዶናልድ ትራምፕ

"የጋዛ ችግር በዚህ ከቀጠለ መቼም አይፈታም" ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ "አሜሪካ ሀላፊነት ወስዳ ጋዛን ሙሉ በሙሉ ማስተዳደር ይኖርባታል" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው፣ "ጥሩ ነገሮች መፈጠር ይኖርባቸዋል፣ ህዝቦች ደህንነት በሚሰማቸው ቦታ መኖር አለባቸው" ብለዋል።  

ትራምፕ አሜሪካ ጋዛን በባለቤትነት የማስተዳደር ፍላጎት እንዳላት የጠቆሙት ባሳለፍነው የካቲት ወር ሲሆን፣ ከፍተኛ ተቃውሞም ገጥሟቸው ነበር።
#aa

@ThiqahEth
😡44👍11😱7😢2🤔1
"እስራኤል ኢራንን የማጥቃት ፍላጎቷ ከቅርብ ወራት ወዲህ በእጅጉ ጨምሯል" - የአሜሪካ ደኀንነት ቢሮ

እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል የአሜሪካ ደህንነት ቢሮ ጠቆመ።

የቴላቪቭ ጥቃት በቴህራን የኑክሌር ማብላያ ጣቢያዎች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነም ቢሮው ገልጿል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የደህንነት ቢሮው ባልደረባ፣ "እስራኤል ኢራንን የማጥቃት ፍላጎቷ ከቅርብ ወራት ወዲህ በእጅጉ ጨምሯል" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ የእስራኤል እቅድ የተሰማው አሜሪካና ኢራን የኑክሌር ምርትን በተመለከተ 5ኛውን ዙር ውይይት ለማድረግ በተዘጋጁበት ወቅት ነው።
#aa

@ThiqahEth
😁17👍12😱2🔥1🤔1
"እሺ ተኩስ እናቁም እንበል፣ ከዚያ ጥቃት ሲፈጸምብን ዝም ብለን አይተን በኋላ ምላሽ ልንሰጥ? እንደዚያ አናደርግም" - ሰርጌ ላቭሮቭ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዩክሬን ያቀረበችውን "አስቸኳይ የተኩስ አቁም" እቅድ ውድቅ አደረገ።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፣ "ኪቭ የተኩስ አቁም ስምምነትን ጦሯን እንደ አዲስ አደራጅታ በሩሲያ ላይ ጥቃት ለማድረስ ነው የምትጠቀምበት" ሲሉ ወንጅለዋል።

"እሽ ተኩስ እናቁም እንበል፣ ከዚያ ጥቃት ሲፈጸምብን ዝም ብለን አይተን፣ በኋላ ምላሽ ልንሰጥ? እንደዚያ አናደርግም" ነው ያሉት

በዩክሬን ለቀጠለው ጦርነት የአውሮፓ ህብረትን ተጠያቂ አድርገዋል።
#aa

@ThiqahEth
👍20😁53🤔2🥰1😱1
"ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" - ትራምፕ

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤለን መስክ ለዲሞክራቶች የገንዘብ ድጋፍ እንዳያደርግ አስጠነቀቁ።

"ለድሞክራትች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንቱ ይገጥመዋል ስላሉት አደጋ በዝርዝር አልተናገሩም። 
#nbcnews #aa

@ThiqahEth
😱105🤔2😡1
አሜሪካ ብዛት ያላቸውን የጦር አውሮፕላኖች ለእስራኤል ላከች።

የአሜሪካ የጦር አውሮፕላኖች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየተጓዙ መሆናቸው ተመልክቷል።

ቬትናም የነበሩት "ዩኤስኤስ ኒሚትዝ" የተሰኙት አውሮፕላኖች፣ "ለአስቸኳይ ዘመቻ ተፈላጊነት" ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየገቡ ይገኛሉ።

አውሮፕላኖቹ በደቡብ ቻይና ባህር ለግዳጅ ተሰማርተው ነበር ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስፈላጊ ከሆነ አሜሪካ ወደ ጦርነቱ ትቀላቀላለች ብለው ነበር።
#aa

@ThiqahEth
24😱6🕊3💔2😭1
"አያቶላሕ አሁን መግደል አንፈልግም" - ትራምፕ

"የአያቶላሕ መገደል ጦርነቱን አያባብሰውም" - ኔታንያሁ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ "አሜሪካ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ የት እንደተደበቀ ታውቃለች፣ ግን አሁን መግደል አንፈልግም" አሉ።

"በቀላል ኢላማ ውስጥ ነው ያለው፣ ደህና ነው ፣ ግን ይዘን ማምጣት አንፈልግም" ነው ያሉት።

ፕሬዚዳንቱ "ነገር ግን ህፃናት በሚሳዔል እንዲያልቁ፣ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲሞቱ አንፈልግም" ሲሉም አክለዋል።  

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ሀገራቸው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ አሊ ኮሚኒ ላይ ግድያ የመፈጸም ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል።

"አያቶላሕ ቢገደሉ በቴላቪቭ እና በቴህራን መካከል ያለውን ጦርነት እያባባሰውምሟ እንዲያው ጦርነቱ ቶሎ ይቋጫል" በማለትም ተናግረዋል።

"ወደ ዝርዝር ጉዳዮች መግባት አልፈልግም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ከፍተኛ የኑክሌር ሳይንቲስቶችን እንደገደልን ግን ላረጋግጥላችሁ እችላለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። 
#aa #gulftoday

@ThiqahEth
29😡14😱2
"ማንም በዚህ ጉዳይ ሊደናገጥ አይገባም፣ ትራምፕ ኢራን ኑክሌር እንደማይኖራት ባለፉት አስርት አመታት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል" - ዋይትሃውስ

"የኢራን ኑክሌር ምርት ስጋት ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካም ጭምር ነው" ሲል  ዋይትሃውስ አስታውቋል።

ትራምፕ፣ "ባለው ሁኔታ ውስጥ ከኢራን ጋር ተካሄደም አልተካሄደም በቅርቡ የድርድር እድል ይኖራል" ማለታቸውን የዋይትሃውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ተናግረዋል።

ሌቪት፣ "ማንም በዚህ ጉዳይ ሊደናገጥ አይገባም፣ ትራምፕ ኢራን ኑክሌር እንደማይኖራት ባለፉት አስርት አመታት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል" ሲሉ አብራርተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በጦርነቱ ውስጥ ስለሚኖራቸው ሚና ሌቪት "በሁለት ሳምንት ውስጥ የሚወስኑ ይሆናል" ሲሉም አብራርተዋል።
#aa

@ThiqahEth
17😡17👏4🕊2
"እኛ ገለልተኛ አይደለንም ከኢራን  ጎን እንቆማለን" - ሂዝቦላ

"የሂዝቦላ ኃላፊ ከቀደሙት አመራሮች እየተማረ አይደለምን" - እስራኤል

የሂዝቦላ ዋና ፀሐፊ ናዒም ቃሲም፣ "በአሁኑ ወቅት የአሜሪካና እስራኤልን ጭቆና ድርጊት በግልጽ እየተመለከትን እንገኛለን" ብለዋል።

ቃሲም ትናንት ምሽት በሰጡት መግለጫ፣ "እኛ ገለልተኛ አይደለንም ከኢራን  ጎን እንቆማለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ሂዝቦላን አስጠንቅቋል።

ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ ሂዝቦላ በኢራን እና እስራኤል ጦርነት ጣልቃ እንዳይገባ አሳስበዋል። እስራኤል፣ "የሂዝቦላ ኃላፊ ከቀደሙ አመራሮች እየተማረ አይደለምን" ብላለች።

ካትዝ፣ "የሂዝቦላ ሀላፊ ከቀደሙት አመራሮች እየተማረ አይደለምን፣ ከኢራን ጎን እንደሚቆም እያስፈራራ ነው" ብለዋል። 
#aa

@ThiqahEth
17🤔4🕊3😡1
25 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት ተገደሉ።

የእስራኤል ጦር በከፈተው ተኩስ ከ100 የሚበልጡት  ቆስለው ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በጋዛና ክሃን የኑስ ከተማ መሆኑን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
#aa

@ThiqahEth
😭288🕊2👏1
በኮሎምቢያ 22 ሰዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በቤሎ እና አልቶስ ግዛቶች በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ 8 ሰዎች እስካሁን አለመገኘታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የመሬት መንሸራተት አደጋው በከባድ ዝናብ ምክንያት መከሰቱ ተገልጿል።
#aa

@ThiqahEth
😢165😭5
የ80 ዓመቱ ሙሴቪኒ ለ6ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ።

የኡጋንዳው የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ በቀጣይ አመት በሚካሄደው የሀገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።

የ80 አመቱ ሙሴቪኒ በዓለማችን ረጅም አመት በስልጣን የቆዩ መሪ ሲሆኑ፣ ፓርቲያቸው ናሽናል ረዚስታንስ ሞመንት (NRM) ከ1986 ጀምሮ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ይገኛል።
#aa

@ThiqahEth
😱15🕊4😭4😡4👏21
"ወታደራዊ ዘመቻዎችን እናስቀጥላለን፣ ነገር ግን ይህን በፖለቲካና ዲፕሎማሲም መድገም እንፈልጋለን" - ፑቲን

ፑቲን ከትራምፕ ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት የሰላም ጥረቶች ለውጥ ባለማምጣታቸው ሩሲያ ጦርነቱን እንደምትቀጥል ገልፀውላቸዋል ተብሏል።

የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ድሜትሪ ፔስኮቭ ፕሬዝዳንት ፑቲን "ስኬታማ ወታደራዊ ዘመቻዎችን እናስቀጥላለን፣ ነገር ግን ይህን በፖለቲካና ዲፕሎማሲም መድገም እንፈልጋለን" ማለታቸውን ተናግረዋል።

ፔስኮቭ አክለው፣ "ትራምፕ ከፑቲን ጋር ካደረጉት የስልክ ቆይታ በኋላ የሰጡትን ሀሳብ በተመለከተ "የትራምፕን ንግግር በጥንቃቄ እያጤነው ነው" ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው አቻቸው ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩ ሲሆን የዩክሬኑን ጦርነት ማስቆም ስለሚቻልበት ሁኔታ ተነጋግረዋል።

ይሁን እንጂ ትራምፕ በውይይቱ "ምንም የአቋም ለውጥ የለም" ሲሉ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል።
#aa

@ThiqahEth
11😡8👏6🕊1
"ቀረጥ ለመጨመር የሚደረግ የተናጠል እርምጃ በብራዚል የአፀፋ እርምጃ ህግ መሰረት ምላሽ ይሰጣል" - ብራዚል

ብራዚል በአሜሪካ ላይ የ50% ታሪፍ ልትጥል እንደምትችል አስጠነቀቀች።

ትራምፕ የሚወስዷቸውን ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች የተቹት ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ፣ "ቀረጥ ለመጨመር የሚደረግ የተናጠል እርምጃ በብራዚል የአፀፋ እርምጃ ህግ መሰረት ምላሽ ይሰጣል" ብለዋል።

አሜሪካና ብራዚል ባለፉት 15 አመታት የ410 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ትራምፕ ከብሪክስ ጋር አጋርነት በፈጠሩ ሀገራት ላይ የ10% ታሪፍ እጥላለሁ ማለታቸውን ተችተዋል።

ሲልቫ "ብራዚል ሉዓላዊ ሀገር በመሆኗ የትኛውንም አይነት ጣልቃ ገብነት አትቀበልም" ሲሉ ተናግረዋል።
#aa

@ThiqahEth
23🤔1🙏1
"አብሮ ለመቀጠል መፍትሄ ያስፈልጋል" - ቻይና

ቤጂንግ እና ዋሽንግተን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ግንኙታቸውን ማስቀጠል እንደማይችሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ ተናግረዋል።

ዋንግ የአሜሪካ መንግስት ቻይና "አላማ ያላት ውስን ፣ ተራማጅ እሳቤ" ያላት ሀገር መሆኗን ይረዳል ብየ አስባለሁ ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም በሁለትዮሽ ግንኙነት "አብሮ ለመቀጠል መፍትሄ ያስፈልጋል" ሲሉ ተናግረዋል።
#aa

@ThiqahEth
11🕊8
እስራኤል ፍልስጤማውያንን ለማዘዋወር አዲስ እቅድ አቀረበች።

በኳታር እየተካሄደ በሚገኘው ድርድር እስራኤል በካርታ የተደገፈ እቅድ ማቅረቧ ተገልጿል።

ሀማስ ግን የእስራኤል ተደራዳሪዎች ያቀረቡትን እቅድ ተቃውሟል።

አደራዳሪዎች በበኩላቸው ሁለቱም ወገኖች ሚዛናዊ የሰላም ሀሳብ እንድያቀርቡ ጠይቀዋል ተብሏል።
#aa

@ThiqahEth
😡13🤔52🙏2
ኢራን እና ሶስቱ የአውሮፓ ሀገራት ከኢራን ጋር የኑክሌር ድርድር ለማድረግ ተስማሙ።

"E3" በመባል የሚታወቁት ሀገራት ማለትም ጀርመን፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ በመጪው አርብ ለውይይት እንደሚቀመጡ ተገልጿል።

እነዚህ ሀገራት የኢራን የኑክሌር ምርት እቅድን በተመለከተ የሚያደርጉት ውይይት በቱርክ አንካራ ይካሄዳል ተብሏል።
#aa

@ThiqahEth
9😱2👏1
"ዋነኛ አላማው ለዘላቂ ሰላም የሚያግዝ የተኩስ አቁም ስምምነት መፈጸም ነው" - ቱርክ

የሩሲያ እና ዩክሬን ሦስተኛው ዙር ድርድር በአንካራ ተጀምሯል።

ከውይይቱ መጀመር በፊት መግለጫ የሰጡት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ካሁን በፊት በተደረጉት ሁለት የሰላም ድርድሮች የተገኙ ውጤቶች ይገመገማሉ ብለዋል።

ሦስተኛው ዙር ንግግር ከሰባት ሳምንት በኋላ መካሄድ መጀመሩን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ "ዋነኛ አላማው ለዘላቂ ሰላም የሚያግዝ የተኩስ አቁም ስምምነት መፈጸም ነው" በማለት አብራርተዋል።

ሁለቱ ሀገራት የድርድር ልዑካን ቡድናቸውን ወደ አንካራ ልከዋል።
#aa

@ThiqahEth
11😱1😢1🙏1