THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
በፓኪስታን አጥፍቶ ጠፊ ባቡር ጣቢያ ላይ በፈጸመው ጥቃት 20 ሲሞቱ 53 ሰዎች መቆሰላቸው ተነገረ።

ጥቃቱ ስልጠና አጠናቀው ወደ ስምሪት ሲሄዱ በነበሩ ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የኩዌታ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለጥቃቱ የባሎችስታን ነጻነት ግንባር (BLF) ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሸባዝ ሸሪፍ ጥቃቱን አውግዘው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ፈጣን ህክምና እንድያገኙ ለህክምና ባለሙያዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡ #shine #novinite

@thiqahEth
😭16👍71🔥1🤔1
ደቡብ ሱዳን ውስጥ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ 20 ሰዎች ህይታቸው አለፈ፡፡

በአደጋው 17 ደቡብ ሱዳናዊ፣ ሱዳናዊ እና አንድ ቻይናዊ ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን የደቡብ ሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ጋትዎች ቢፓል ተናግረዋል፡፡

ከተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ሁለቱ የበረራ አባላትና አንድ ህንዳዊ እንዲሁም አንድ የሀገሪቱ ዜጋ ከአደጋው ተርፈው ወደ ሆፒታል መላካቸውን የጁባ ዓለማቀፍ አየር መንገድ ዳይሬክተር ኢንጅነር ሳልህ አኮት ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ተጓዦች ግሬተር ፒዎነር ኦፕሬቲንግ ካምፓኒ (GPOC) የተባለ የነዳጅ ዘይት ካምፓኒ ሠራተኞች እንደነበሩ ተነግሯል።

ሠራተኞቹ ለ28 ቀናት በሥራ ቆይተው ከዩኒቲ ግዛት እየተመለሱ በነበረበት ወቅት አደጋው እንደተፈጠረ ሚኒስትሩ ለራዲዮ ታማዙጂ አረጋግጠዋል፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የአቪየሽን ባለስልጣን ስለሁኔታው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቁ ተዘግቧል፡፡ #Anadolu #Shine #Reuters

@ThiqahEth
😭12👍83🤔2
THIQAH
"በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ የተጣለው ቀረጥ ከቅዳሜ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል"  - ካሮሊን ሌቪት "አስገዳጅ ሊሆን ይችላል ግን ምክንያታዊ መሆን አለበት"  - ጀስቲን ትሩዶ በካናዳ እና ሜክሲኮ ላይ የ25% እንዲሁም በቻይና ላይ ደግሞ የ10% የቀረጥ ጭማሪ መደረጉን የነጩ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ሌቪት ገልጸዋል። "በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ የተጣለው ቀረጥ ተግባራዊ ይሆናል" ነው ያሉት።…
"ካናዳ አሜሪካ ንግድ ላይ ለወሰደችው እርምጃ 155 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጀመሯን አሳውቃለሁ"  - ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ

ካናዳ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ውሳኔ ላይ የአፀፋ እርምጃ ወስዳለች።

ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ የተጣለባት ካናዳ፣ በአሜሪካ ምርቶች ላይም ተመሳሳይ ታሪፍ ጥላለች።

የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ፣ "ዛሬ ካናዳ አሜሪካ ንግድ ላይ ለወሰደችው እርምጃ 155 ቢሊየን ዶላር በሚያወጡ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ መጀመሯን አሳውቃለሁ" ብለዋል።

ከአሜሪካ በሚገቡ የቢራ እና የወይን ምርቶች ላይ ቀረጥ መጣላቸውን አስታውቀዋል።

የነጩ ቤተ መንግሥት እርምጃ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ ውሳኔው የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች እንደሚጎዳ ግልጽ ነው ብለዋል። #bbc #shine

@ThiqahEth
👍45🔥84😁2