THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
#ሩሲያ

"ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ወዳጅ በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ሽብርተኞችን እየደገፈች ነው" - ሩሲያ

ሩሲያ በአፍሪካ "ሁለተኛውን ግንባር" ከፍታለች በሚል ዩክሬንን ከሰሰች።

ሩሲያ፣ "ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ወዳጅ በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ሽብርተኞችን እየደገፈች ነው" ነው ያለችው።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ የቀረበበትን ክስ አጣጥሏል።

ማሊና ኒጀር ከዩክሬን ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸው ይታወሳል። #reuters#trtworld

@thiqaheth
👍26🤔3😡2
የቴሌግራም መስራች ፓቫል ዱሮቭ ፈረንሳይ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ።
 
ሩሲያዊው ዱሮቭ በቁጥጥር ስር የዋለው በመሰረተውና በሚያስተዳድረው የቴሌግራም መተግበሪያ ይዘቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ባለመቻሉ መሆኑ ተገልጿል።  
 
በፈረንሰይ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ጉዳዩን ለማጣራት ፈጣን እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።
 
የቴሌግራም መተግበሪያ በዓለም ላይ አንድ ቢሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ይነገራል። #timesnow #reuters #thehindu

@thiqaheth
 
😡25👍6😢31
የሂዝቦላ መሪ ሰዒድ ሀሰን ናስራላህ ተገደሉ፡፡

የሂዝቦላ መሪ የሆኑት ናስራላህ ቤሩት ውስጥ መገደላቸውን የእስራኤል ጦር አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ የሂዝቦላህ ቡድን በመሪው ግድያ ዙሪያ እስካሁን ድረስ የሰጠው ማስተባበያም ይሁን ማረጋገጫ የለም፡፡

ሰዒድ ሀሰን ናስራላህ በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰውን የሂዝቦላ ቡድን ለ32 አመታት በኃላፊነት መርተዋል፡፡
#onmanorama #reuters

@thiqaheth
👍37😱12😢3😭2👌1
"ዛሬ ጠዋት አካባቢ የጁባላንድ ኃይሎች በሶማሊያ ፌደራል ወታደሮች ላይ ጥቃት አድርሰዋል" - ሶማሊያ

"ዛሬ ጠዋት የፌዴራል ኃይሎች ከሞቃዲሾ ራስካምቦኒ ሆነው በጁባላንድ ኃይሎች ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽመዋል" - ጁባላንድ

በጁባ ላንድና በሶማሊያ መካከል ይፋዊ ጦርነት ተጀመረ።

ለጥቂት ወራት ውዝግብ ውስጥ የቆዩት ሶማሊያ እና ጁባላንድ ዛሬ በይፋ ወደ ጦርነት መግባታቸውን ከሁለቱም በኩል የተሰጡት መግለጫዎች ያመላክታሉ።

የጁባላንድ ግዛት ምክትል ደህንነት ሚኒስትር አዳን አህመድ ሀጂ በዋና ከተማዋ ኪስማዩ በሰጡት መግለጫ፣ "ዛሬ ጠዋት የፌዴራል ኃይሎች ከሞቃዲሾ ራስካምቦኒ ሆነው በጁባላንድ ኃይሎች ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽመዋል" ሲሉ ወቅሰዋል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር መሀመድ ኑር በበኩላቸው፣ "በዛሬው ዕለት ጠዋት አካባቢ የጁባላንድ ኃይሎች በሶማሊያ ፌደራል ወታደሮች ላይ ጥቃት አድርሰዋል" ሲሉ ጦርነቱ በግዛቷ ኃይሎች እንደተጀመረ አብራርተዋል።

ጁባላንድ ያካሄደችው ምርጫ ለውዝግቡ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል። #reuters

@thiqaheth
👍13🔥3😢3😱1
የሳህል ጥምረት ከ5000 በላይ ጦር ለማዋጣት ተስማሙ፡፡

"በወታደራዊ ጁንታ" እየተዳደሩ የሚገኙት ማሊ፣ ቡርኪናፋሶና ኒጀር የጅሃድስት መስፋፋትን ለመግታት ከ5000 በላይ ጠንካራ የጋራ ጦር ለመመስረት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሦስቱ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በቅርቡ ''የተባበሩት ኃይል" የተሰኘ የሦስትዮሽ ጥምረት እንደሚመሰርቱ የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴትር ሳሊጉ ሞዲ ገልጸዋል፡፡

''የሳምንታት ጉዳይ ነው እንጅ ይህን ኃይል በቅርቡ እናየዋለን'' ብለዋል ሞዲ።

ሦስቱ የቀድሞ የፈረንሳይ ቅኝ ተገዥ ሀገራት ከ2020 – 2023 መፈንቀለ መንግስት አስተናግደዋል፡፡ #reuters #associatedpress

@ThiqahEth
👍12
ደቡብ ሱዳን ውስጥ በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ 20 ሰዎች ህይታቸው አለፈ፡፡

በአደጋው 17 ደቡብ ሱዳናዊ፣ ሱዳናዊ እና አንድ ቻይናዊ ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን የደቡብ ሱዳን የመረጃ ሚኒስትር ጋትዎች ቢፓል ተናግረዋል፡፡

ከተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ሁለቱ የበረራ አባላትና አንድ ህንዳዊ እንዲሁም አንድ የሀገሪቱ ዜጋ ከአደጋው ተርፈው ወደ ሆፒታል መላካቸውን የጁባ ዓለማቀፍ አየር መንገድ ዳይሬክተር ኢንጅነር ሳልህ አኮት ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ተጓዦች ግሬተር ፒዎነር ኦፕሬቲንግ ካምፓኒ (GPOC) የተባለ የነዳጅ ዘይት ካምፓኒ ሠራተኞች እንደነበሩ ተነግሯል።

ሠራተኞቹ ለ28 ቀናት በሥራ ቆይተው ከዩኒቲ ግዛት እየተመለሱ በነበረበት ወቅት አደጋው እንደተፈጠረ ሚኒስትሩ ለራዲዮ ታማዙጂ አረጋግጠዋል፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና የአቪየሽን ባለስልጣን ስለሁኔታው ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቁ ተዘግቧል፡፡ #Anadolu #Shine #Reuters

@ThiqahEth
😭12👍83🤔2
"ከአሜሪካ መከላከያና ገንዘብ ቢሮ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን በግድ እንዲለቁ ተደርገዋል" - የአሜሪካው ዳኛ

በትራምፕ የተባረሩ ሰራተኞችን ወደ ስራቸው
እንዲመልሱ ሁለት የሀገሪቱ ዳኞች መጠየቃቸው ተሰምቷል።

ዳኞቹ፣ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ከስራቸው የተባረሩ የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ አሳስበዋል።

በካሊፎርኒያ ግዛት የሚኖሩት ዳኛ ዊሊያም አልሰፕ፣ ሰራተኞችን ከስራቸው ማፈናቀልን "አሳፋሪ ስትራቴጂ" ሲሉ ተቃውመዋል።

ሌላኛው የሜሪላንድ ነዋሪ ዳኛ በበኩሉ፣ ከአሜሪካ መከላከያና ገንዘብ ቢሮ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን በግድ እንዲለቁ ተደርገዋል ብለዋል። #thewashingtonpost #reuters

@ThiqhEth
👍19🤔1
"አሜሪካ የበርበራ፣ ቦሳሶ እና ባሊዶግሌ ወደብን ሙሉ በሙሉ እንድታስተዳድር ፍቃደኛ ነን"  - ሶማሊያ

"አሜሪካ ከእኛ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን እናውቃለን" - ሶማሌላንድ

ሶማሊያ አሜሪካ በብቸኝነት የምትቆጣጠረው የአየር ኃይል እና ወደብ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ለትራምፕ በፃፉት ደብዳቤ መግለፃቸው ተዘግቧል።

ሀሰን ሼክ ይህን ፍላጎታቸውን የገለጹት አሜሪካ ለተገንጣይዋ የሶማሌላንድ ግዛት እውቅና እንዳትሰጥ በሚል ስጋት ነው ተብሏል።

የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱረህማን ዳሂር በበኩላቸው፣ "የምን ትብብር፣ አሜሪካ ይህን የከሸፈ የሶማሊያ መንግስት ረስታዋለች" ብለዋል።

"አሜሪካ ሞኝ አይደለችም" ያሉት አብዱረህማን፣ "ከማን ጋር መደራደር እንዳለባት በደምብ ታውቃለች" ሲሉ አክለዋል።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሞቃዲሾ የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ሀርጌሳን እውቅና ሊሰጥ ይችላል የሚሉ መረጃዎች በተደጋጋሚ ሲወጡ ቆይተዋል።
#reuters #newarab #bbc

@ThiqahEth
😁23👍9😢32🤔2
ከ50 በላይ ሀገራት በቀረጥ ዙሪያ ከትራምፕ መንግስት ጋር ንግግር  እንዲጀመር ጠየቁ።

የፕሬዝዳንቱ የምጣኔ ሀብት አማካሪ፣ "የተጣለው ታሪፍ አሜሪካ ከገጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ የምታግምበት ስትራቴጂ አካል ነው" ብለዋል።

የአሜሪካ ብሄራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ዳይሬክተር ኬቪን ሀሴት የትራምፕ ውሳኔ የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮችን ለማበረታታት የወሰዱት እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ትራምፕ እየጣሉት ያለው ታሪፍ ተፅዕኖ አሳድሮብናል ያሉ ሀገራት ውይይት እንድደረግ ማመልከታቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል የታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ የንግድ መዛባት እንዳይፈጠር በማሰብ ከአሜሪካ የሚገቡ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ እንድገቡ መወሰናቸውን ተናግረዋል።
#reuters #timeslive

@ThiqahEth
😁104👍4🔥1
"አሜሪካም ፈጣን የታሪፍ መፍትሄን ትፈልጋለች። ማጋነን አይገባም፣ ከአሜሪካ ጋር የጋራ መፍትሔ እንፈልጋለን" - ጀርመን

የጀርመን ምክትል መራሄ መንግስት እና የገንዘብ ሚኒስትር ላርስ ክሊንግቤል አሜሪካ እና አውሮፓ በታሪፍ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ተናግረዋል።

"ማጋነን አይገባም፣ ከአሜሪካ ጋር የጋራ መፍትሄ እንፈልጋለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ "አሜሪካም ፈጣን የታሪፍ መፍትሄን ትፈልጋለች" ሲሉ ገልጸዋል።

ጀርመን 183 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ አሜሪካ በመላክ ከአውሮፓ ተቀዳሚ ሀገር ናት።

የትራምፕ መንግስት በአውሮፓ ምርቶች ላይ 50% ታሪፍ መጣላቸውን አስታውቀዋል።
#reuters

@ThiqahEth
😁9👍5🤔2😱2🥰1
"አሜሪካ ኢራን የኑክሌር ባለቤት እንድትሆን አትፈቅድም፤ ስምምነቱን የማትቀበለው ከሆነ የኃይል እርምጃ እንወዳለን" - ፕሬዚዳንት ትራምፕ

ትራምፕ አሜሪካ ከመካከለኛው ምሥራቅ ልትወጣ እንደምትችል ጠቆሙ።

ውሳኔው የመጣው በዋሽንግተንና በቴህራን መካከል፣ "በኑክሌር ፕሮግራም" ላይ የተደረጉ ውይይቶች ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ነው ተብሏል።

"ወታደሮቻችን አካባቢውን ለቀው መውጣት አለባቸው" ያሉት ትራምፕ፣  "ምክንያቱም አደገኛ ቦታ ይሆናል" ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ባደረጉት ንግግር፣ "አሜሪካ ኢራን የኑክሌር ባለቤት እንድትሆን አትፈቅድም፤ ስምምነቱን የማትቀበለው ከሆነ የኃይል እርምጃ እንወዳለን" ሲሉ ተደምጠዋል።

በተያያዘ መረጃ አሜሪካ በኢራቅ የሚገኘው ኤምባሲዋ የሚገኙ ሰራተኞችን በግማሽ መቀነሷ ተሰምቷል። 
#reuters

#ThiqahEth
11🤔4🕊2
THIQAH
"ሦስት ከፍተኛ የኢራን ጦር አመራሮች እርምጃ ተወስዶባቸዋል" - የእስራኤል ጦር ሦስት የኢራን ከፍተኛ ጦር አመራሮች እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲሉ የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ብርጋጄር ጀነራል ኢፊ ደርፊን ገልጸዋል። በዚሁ ጥቃቱ የተገደሉትም የኢራን ኢታማዦር ሹም ሙሀመድ ቡጋሪ፣ የአብዮታዊ ዘብ አዛዥ ሁሴን ሳላሚ እና ሲኒየር ኮማንደር ጎላም አሊ ራሻድ መሆናቸው ተመልክቷል። እስራኤል ኢራንን ለማጥቃት…
"ቢያንስ 20 ከፍተኛ ኢራናውያን ኮማንደሮች ተገድለዋል" - ኢራን

ከእስራኤል ሌሊቱን በተሰነዘረባት ጥቃት ቢያንስ 20 ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦቿ መገደላቸውን ኢራን አስታወቀች።

በጥቃቱ ስድስት የኒኩሌር ሳይንቲስቶች፤ ቢያንስ 20 ከፍተኛ ኢራናዊያን ኮማንደሮች መገደላቸው ነው የተገለጸው።

የእስራኤል ጦር ባደረሰው ጥቃት ከፍተኛ የኢራን የጦር አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል ማለቱን ኢራን ስታስተባብል ቆይታ ነበር። 
#reuters

የእስራኤል ጦር፣ "ሦስት ከፍተኛ የኢራን ጦር አመራሮች እርምጃ ተወስዶባቸዋል" ነበር ያለው።

@ThiqahEth
25😢7👏2🕊2😡2
"ኢራን በጭራሽ የኑክሌር ፕሮግራም አይኖራትም፣ አለቀ" -  ዶናልድ ትራምፕ

ፕሬዚደንት ድናልድ ትራምፕ የኢራን ዜጎች ከቴህራን ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ።

"የሰው ህይወት ማጣት ያሳፍራል" ያሉት ትራምፕ፣ "ኢራን በጭራሽ የኑክሌር ፕሮግራም አይኖራትም፣ አለቀ ስምምነቱን በፍጥነት መፈጸም አለባት" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ስብሰባ ጠርተው ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#reuters

@ThiqahEth
🤔1514😡4👏2
"የኢራንን አመራር መውደቅ የኛ ግብ አይደለም፣ ግን ውጤቱ ሊሆን ይችላል" - ኔታንያሁ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ፣ በኢራን ጉዳት የደረሰበትን የሶሮካ ሆስፒታል" ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር እስራኤል የኢራንን ኑክሌር ማበልጸጊያዎች የማስወገድ አቅም አላት ብለዋል።

"የኢራንን መንግስት መቀየር ወይም መጣል የእስራኤል ፍላጎት አይደለም" ሲሉም ተደምጠዋል።

"አገዛዙን የመቀየርና የመጣል ጉዳይ የኢራን ህዝብ ነው" ብለዋል።

"ይህን እንደ ግብ አልቆጥረውም ግን ውጤት ሊሆን ይችላል" ሲሉ ገልፀዋል። 
#reuters

@ThiqahEth
30😡12🕊2
"ኢራን የሚሳዔል ጥቃት በመፈጸም ስምምነቱን ጥሳለች" - እስራኤል

"ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ የተፈጸመ ጥቃት የለም" - ኢራን

"ኢራን የሚሳኤል ጥቃት አድርሳለች" ያለችው እስራኤል በመከላከያ ሚኒስትሯ በኩል በኢራን ላይ ጥቃት እንዲሰነዘር አዛለች።

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ "ኢራን የሚሳዔል ጥቃት በመፈጸም ስምምነቱን ጥሳለች" ሲሉ ወንጅለዋል።

ኢራን በበኩሏ የቀረበባትን ወቀሳ "የተሳሳተ ሪፖርት ነው" በማለት እንደማትቀበለው ገልፃለች።

"ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ የተፈፀመ ጥቃት የለም፣ ጥቃት አልሰነዘርንም" ብላለች።
#reuters

@ThiqahEth
21🤔9🕊2
በሱዳን ከ40 በላይ ሰዎች ተገደሉ።

ሆስፒታል ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የህክምና አገልግሎት በማግኘት የነበሩ ታካሚዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገልጸዋል።

ሟቾቹ ቢያንስ ከ4ዐ በላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ዳይሬክተሩ ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ ባይገልጹም ከሟቾቹ መካከል ህፃናት እንደሚገኙበት ተናግረዋል። 
#reuters

@ThiqahEth
😢177🕊2
THIQAH
ተመድ በኬንያ ያለው ተቃውሞ "ያሳስበኛል" አለ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባሳለፍነው ሳምንት በናይሮቢ በነበረው የተቃውሞ 15 ሰዎች መሞታቸውንና ከ100 የሚበልጡት መቁሰላቸውን አስታውቋል። የተቃውሞ ሰልፉ በሀገሪቱ በሚገኙ 16 ከተሞች መካሄዱንም ገልጿል። #peoplesgazette @ThiqahEth
"ሰልፈኞቹን እግሯቸውን በማለት አስቁሟቸው" - ፕሬዝዳንት ሩቶ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ አሳሰቡ።

ሩቶ በተቃውሞ ሰልፉ መሰረተ ልማቶች እየወደሙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዚደንቱ "ሰልፈኞቹን እግሯቸውን በማለት አስቁሟቸው" ሲሉ ለፖሊስ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

ይህን ተከትሎ ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ሰልፉን ለመበተን ጥረት እያደረገ ይገኛል ተብሏል።

በኬንያ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የተቃውሞ ሰልፍ እስካሁን 31 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።
#reuters

@ThiqahEth
🕊5😢43👏3
THIQAH
#Update "በበረራ ከጀመርን ከ30 ሰከንድ በኋላ የሚረብሽ ድምፅ ተሰማ፣ ወዲያውኑ አውሮፕላኑ ተከሰከሰ፣ ነገሮች በፍጥነት ነው የተፈጠሩት" - ታዕምረኛው ራመሽ 242 ሰዎችን ጭኖ ነበር የተባለው አውሮፕላን በመከስከሱ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸው በስፋት ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ አንድ ሰው በህይወት ተገኝቷል ተብሏል። ቪሽዋሽ ኩማር ራመሽ የተባለው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ግለሰብ በህይወት በመገኘቱ…
"አውሮፕላኑ የተከሰከሰው የነዳጅ መቆጣጠሪያው በመፈንዳቱ መሆኑ ተረጋግጧል" - የህንድ አቪየሽን ባለስልጣን

ባለፈው ወር ከህንድ ወደ እንግሊዝ ሲበር የተከሰከሰውና የ241 ተጓዦችን ህይወት የነጠቀው የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ውጤት ይፋ ሆኗል።

የኤይር ኢንድያ ንብረት የሆነው Boing 787 ድሪምላይነር የመንገደኞች አውሮፕላን የነዳጅ መቆጣጠሪያው ከፈነዳ በኋላ አደጋው መከሰቱን የህንድ አቪየሽን ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ የምርመራውን ውጤት በተመለከተ "አውሮፕላኑ የተከሰከሰው የነዳጅ መቆጣጠሪያው በመፈንዳቱ መሆኑ ተረጋግጧል" ሲል አስታውቋል።

አብራሪው ሞተር ላይ በተፈጠረው ክስተት ተደናግጦ እንደነበር የምርመራ ውጤቱ አመላክቷል።

ይህም ለአደጋው መፈጠር ምክንያት መሆኑን ገልጿል።
#reuters

@ThiqahEth
11😭8🕊2🤔1
"ለዲፕሎማሲያችን ቅድሚ ለመስጠት የውስጥ አሰራሮችን ላይ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ነው" - የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

"አሜሪካ ከውጭ የሚቃጣባትን ስጋት መቋቋም እንዳትችል፣ በሌሎች ሀገራት ላይ ብሄራዊ ጥቅሟን እንዳታስከብር ያደርጋታል" - የተባረሩ ሠራተኞች


ሠራተኞችን ማባረር የጀመረው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከ1,350 በላይ ሠራተኞችን ከስራቸው እንዲሰናበቱ ማድረጉ ተገልጿል።

ሠራተኞቹ መቀመጫቸው እዛው ኒውዮርክ ሲሆን፣ 1107 በሀገር ውስጥ ጉዳዮች ክፍል ሠራተኞች፣ 246 የውጭ ጉዳዮች ክፍል ላይ በሚሰሩ ባለሙያዎች ናቸው ተብሏል።

ሚኒስቴሩ፣ "ለዲፕሎማሲያችን ቅድሚ ለመስጠት የውስጥ አሰራሮችን ላይ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ነው" በማለት አስታውቋል።

"የሠራተኛ ቅነሳ ማድረጋችን የዕለት ተዕለት ስራችንን አይጎዳውም" ሲልም አክሏል።

ነገር ግን ከስራቸው የተባረሩ ሠራተኞች "አግባብነት የጎደለው እርምጃ ነው" በማለት ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ።

የተቀነሱት ሠራተኞች ይህ እርምጃ "አሜሪካ ከውጭ የሚቃጣባትን ስጋት መቋቋም እንዳትችል፣ በሌሎች ሀገራት ላይ ብሄራዊ ጥቅሟን እንዳታስከብር ያደርጋታል" ሲሉ እርምጃውን ተቃውመውታል።

በቀጣይ "3,000 የሚደርሱ ሠራተኞች ይቀነሳሉ" ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመልክቷል።

አሜሪካ በሀገር ውስጥ ብቻ የሚገኙ 10,000 የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሠራተኞች እንዳሉ ይነገራል።
#reuters

@ThiqahEth
13😢3👏2🙏2🕊2
"አብረን እንሰራለን፣ ምርመራ ማድረግ ግን አደጋ ነው" - ኢራን

ኢራን ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር ያላትን ትብብር ማስቀጠል እንደምትችል አስታወቀች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ "አብረን እንሰራለን፣ ምርመራ ማድረግ ግን አደጋ ነው" ሲሉ የኤጀንሲው ስልጣን ውስን እንደሚሆን ተናግረዋል።

የኢራን ፓርላማ ሀገሪቱ ከኑክሌር ተቆጣጣሪ ተቋሙ ጋር የነበራትን ግንኙነት እንድታቋርጥ የሚያዘውን ረቂቅ አዋጅ ባለፈው ወር አፅድቋል።  

የፓርላማውን ውሳኔ ተከትሎ እስራኤል በኢራን ላይ ማዕቀብ እንድጣልባት ስትጠይቅ፣ ጀርመን ውሳኔው እንዲሻር አሳስባለች።
#reuters

@ThiqahEth
19🕊6😡2😭1