THIQAH
13.3K subscribers
2.61K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
በሜክሲኮ የድልድይ መደርመስ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ 50ዎቹ ላይ ጉዳት ደረሰ።

በሰሜናዊ ሜክሲኮ በምትገኘው የኖቮ ሊዮን ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ነው ድልድዩ የተደረመሰው፡፡

ከሞቱት ባለፈ 50 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን የግዛቷ አስተዳዳሪ ሳሙዔል ጋርሺያ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።#timeslive

@thiqaheth
😢13👍2🤔21
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በአህጉር ደረጃ የጤና ስጋት ሆኗል?

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (Africa CDC) የሜፖክስ (Mpox) ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታን አህጉራዊ የጤና ስጋት አደጋ መሆኑን አውጇል።

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው ሜፖክስ (Mpox) ዌም በተለምዶ የዝንጀሮ በሽታ ወረርሽኝ በማዕከሉ በይፋ አህጉራዊ የጤና አደጋ ስጋት (PHECS) ተደርጎ ታውጇል።

የኤጀንሲው ጄነራል ዳይሬክተር ጂያን ካሰያ፣ በሽታው በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸው ሀገራት ጥንቃቄ እንድያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በአህጉሪቱ በሽታውን ለመከላከል ከ10 ሚሊዮን በላይ ክትባት የሚያስፈልግ ቢሆንም የተገኘው ግን 200 ሺህ ብቻ መሆኑን ጀነራል ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡ #timeslive

@thiqaheth
👍12🤔3🙏3
የሞዛምቢክ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአወዛጋቢው ምርጫ ገዥው ፖርቲ ማሸነፉን አወጀ።

ፍርድ ቤቱ ጥቅምት ላይ የተካሄደውን ምርጫ አሁን ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው የፍሬሊሞ ፖርቲ አሸንፏል ብሏል።

ምርጫው በተካሄደበት ወቅት በማጭበርበር የተሞላ ነበር ያሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች አድማ ጠርተው ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደው ነበር።

የፍሬሊሞ ፓርቲ እ.ኤ.አ ከ1975 ጀምሮ 35 ሚሊዮን ህዝብ ያላትን ሞዛምቢክን እያስተዳደረ ቆይቷል። #timeslive

@ThiahEth
😁12👍2🔥1
በሱዳን በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 200 ንጹሐን ተገደሉ፡፡

የሱዳን ጦር ጥቃቱን የፈጸመው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሆኑን የሀገሪቱ ጦር ቢያስታውቅም ከወደ "አማጺ ቡድኑ" በኩል ግን እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የለም፡፡

በዋይት ናይል ግዛት የተፈጸመው ጥቃት ለተከታታይ ሦስት ቀናት የቆየ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ከሀገሪቱ ጦር ጋር የጦርነት ፍልሚያ ውስጥ የሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አብዛኛውን የምዕራብ ሱዳን ክፍል ተቆጣጥሮ ይገኛል
#timeslive

@ThiqahEth
👍9😢5😡2
የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል በመኖሪያ ቤት ላይ በጣለው ቦምብ ቢያነስ ስምንት ሰዎች ቆሰሉ፡፡

የአሜሪካና ደቡብ ኮሪያ ወታደሮች የጋራ ወታደራዊ ልምምድ አገልግሎት ላይ የነበረው የአየር ኃይሉ ጄት በድንገት በጣለው ቦምብ በመኖሪያ ቤትና በቤተክርስስቲያን ላይ ጉዳት አድርሷል ተብሏል፡፡

አየር ኃይሉ በክስተቱ ይቅርታ መጠየቁም ተዘግቧል።

ጉዳት ያደረሰው 225 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ኤም ኬ 82  ቦምብ ከኬይ ኤፍ 16 ጄት ወድቆ መሆኑን የደቡብ ኮሪያ አየር ኃይል አስታውቋል፡፡

ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ በአካባቢው ወታደራዊ ልምምድ መደረግ የለበትም በሚል ለአመታት ያቀረቡትን ጥያቄ ከዘጋው በኋላ በሰላማዊ እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡
#timeslive

@ThiqahEth
😢7👍5🔥1🥰1
"ለጋሽ አካላት ፈጣን የምግብ እርዳታ ካላደረጉ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተደቅኗል" - WFP

እርዳታ በመቋረጡ በመላው ዓለም የሚገኙ 58 ሚሊዮን ሰዎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም "ለጋሽ አካላት ፈጣን የምግብ እርዳታ ካላደረጉ ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተደቅኗል" ሲል  አስጠንቅቋል።

ድርጅቱ ከባለፈው አመት አንፃር በ2025 የእርዳታ መጠኑ 40% መቀነሱን ገልጿል።

በዓለም ላይ 123 ሚሊየን ሰዎች የምግብ እርዳታ ፈላጊ መሆናቸውን የአለም ምግብ ፕሮግራም መረጃዎች አመላክተዋል። 
#timeslive

@ThiqahEth
👍15🤔62
ከ50 በላይ ሀገራት በቀረጥ ዙሪያ ከትራምፕ መንግስት ጋር ንግግር  እንዲጀመር ጠየቁ።

የፕሬዝዳንቱ የምጣኔ ሀብት አማካሪ፣ "የተጣለው ታሪፍ አሜሪካ ከገጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ የምታግምበት ስትራቴጂ አካል ነው" ብለዋል።

የአሜሪካ ብሄራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ዳይሬክተር ኬቪን ሀሴት የትራምፕ ውሳኔ የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮችን ለማበረታታት የወሰዱት እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ትራምፕ እየጣሉት ያለው ታሪፍ ተፅዕኖ አሳድሮብናል ያሉ ሀገራት ውይይት እንድደረግ ማመልከታቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል የታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ የንግድ መዛባት እንዳይፈጠር በማሰብ ከአሜሪካ የሚገቡ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ እንድገቡ መወሰናቸውን ተናግረዋል።
#reuters #timeslive

@ThiqahEth
😁104👍4🔥1
አልቡርሃን ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾሙ።

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ድፕሎማቱን ዳፋላህ አሌሀጅ አሊን ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።

እንዲሁም ኦማር ሳድቅን ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል።

ሹመቱ የሱዳን ጦር የሀገሪቱን ዋና ከተማ፣ የፕሬዚዳንቱን ቤተመንግስት እና ዋና ዋና ተቋማት መቆጣጠሩን ተከትሎ የተሰጠ ነው ተብሏል።
#timeslive

@ThiqahEth
👍10😁41
ፕሬዜዳንት ራማፎዛ አሜሪካ ገቡ።

ፕሬዜዳንቱ እየተካረረ በመጣሙ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙርያ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የፕሬዜዳንቱ ጽሕፈት ቤት "የጉብኝቱ ትኩረት የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ማስተካከልና የንግድ ግንኙነቶችን ማጠናከር ላይ ነው" ሲል አስታውቋል።

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ "አናሳ በመሆናቸው ጥቃት እየደረሰባቸው ነው" ላላቸው 49 ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ባለፈው ሳምንት የጥገኝነት ፍቃድ በመስጠት ወደ አሜሪካ እንዲገቡ አድርጓል።

ራማፎዛ ወደ ዋሽንግተን ባደረጉት ጉዞ የውጭ ጉዳይ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ እንዲሁም የግብርና ሚኒስትራቸውን የልዑካን ቡድናቸው አካል አድርገዋል።  
#timeslive

@ThiqhEth
👍148🤔2
የትራምፕ አስተዳደር በ12 ሀገራት ላይ ሙሉ በሙሉ በ7 ሀገራት ላይ ደግሞ ከፊል እገዳ ጣለ።

ትራምፕ "የውጭ ሽብርተኞችን" ለመከላከል የውጭ ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በሚል የወጣው አዋጅ ላይ ፈርመዋል።

በዚሁ መሠረት ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኢራን፣ አፍጋኒስታን፣ ማይናማር እና ሄይቲ ሙሉ ለሙሉ እገዳ የተጣለባቸው ናቸው። 

ከፊል እገዳ የተጣለባቸው ደግሞ ቡርንዲ፣ ሴራሊዮን፣ ቶጎ፣ ኩባ፣ ሌኦስ፣ ቱርኪሚስታን  እና ቬንዙዌላ ናቸው።
#timeslive

@ThiqahEth
👏103🕊2😢1
"ከኤለን መስክ ጋር የተፈፀሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን እንሰርዛለን" - ዶናልድ ትራምፕ

"ትራምፕ ያለ እኔ እገዛ ምርጫ አያሸንፍም ነበር" - ኤለን መስክ

የቴስላ የአክሲዮን ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ በ150 ቢሊዮን ዶላር ቀንሷል።

ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ፕሬዝዳንቱና ባለሀብቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የገቡበት ውዝግብ የቴስላን ኩባንያ ለኪሳራ ዳርጓል።

የዓለም ቁጥር አንድ ባለሀብቱ መስክ ፕሬዝዳንት ትራምፕን "ያለ እኔ ድጋፍ ምርጫ ማሸነፍ አይችሉም ነበር" ብሏቸዋል።

"የትራምፕ አስተዳደር በታሪፍ ጭማሪ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የአሜሪካን ኢኮኖሚ እየጎዳ መጥቷል" በማለትም ተችቷል።

ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ ለኤለን መስክ ድጎማ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

"በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወጭዎችን ለመቆጠብ ከኤለን መስክ ጋር የተፈጸሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን መሰረዝ ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።

በትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ትልቅ ድጋፍ ያደረገው መስክ በፕሬዚዳንቱ አስተዳደር ሹመት እስከማገኘት ደርሷል።  
#timeslive #theirishtimes

@ThiqahEth
22👏10🕊2😭2🤔1
THIQAH
"ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" - ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኤለን መስክ ለዲሞክራቶች የገንዘብ ድጋፍ እንዳያደርግ አስጠነቀቁ። "ለድሞክራትች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" ሲሉ ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንቱ ይገጥመዋል ስላሉት አደጋ በዝርዝር አልተናገሩም። #nbcnews #aa @ThiqahEth
"በትራምፕ ጉዳይ የፃፍኳቸው አንዳንድ አስተያየቶች ይጸጽቱኛል" - ኤለን መስክ

ቢሊየነሩ መስክ ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ትራምፕን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ያሰፈርኳቸው ፅሑፎች "በጣም የተጋነኑ ነበሩ" አሉ።

"በትራምፕ ጉዳይ የፃፍኳቸው አንዳንድ አስተያየቶች ይጸጽቱኛል" ያሉት መስክ፣ ለጸጸት የዳረጋቸው የትኛው አስተያየት እንደሆነ በግልጽ ባይናገሩም የተወሰኑትን አጥፍቷቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው፣ ከኤለን መስክ ጋር ያላቸውን ግንኙነት "ያበቃ ጉዳይ ነው" ቢሉም "የተለየ ችግር የለብኝም" ብለዋል።

ትራምፕና መስክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እርስበርስ አወዛጋቢ አስተያየቶችን ተለዋውጠው ነበር።
#timeslive

ከመንግስታዊ ኃላፊነት የተነሱት መስክ ትራምፕ በተለያዩ ሀገራት ላይ የሚያሳልፉትን የታሪፍ ውሳኔ "አስቀያሚ ነው። የአሜሪካን ኢኮኖሚ ይበልጥ ያዳክመዋል" በሚል፤ የዋይትሐውስ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት፣ "አስተያየቱ የፕሬዝዳንት ትራምፕን ውሳኔ አይቀይረውም"በሚል የመጀመሪያ ትችት ተወራውረው ነበር።

እንዲሁም ትራምፕ፣ "ከኤለን መስክ ጋር የተፈጸሙ መንግስታዊ ኮንትራቶችን እንሰርዛለን" ሲሉ፣ መስክ ደግሞ "ትራምፕ ያለ እኔ እገዛ ምርጫ አያሸንፍም ነበር" በመባባል ተቃቅረው ነበር።

ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ሁለቱ አካላት ውዝግብ ውስጥ በመግባታቸው፣ የቴስላ የአክሲዮን ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ በ150 ቢሊዮን ዶላር መቀነሱም ከሳምንት በፊት ተዘግቦ ነበር።

በኋላም ትራምፕ መስክን፣ "ለዲሞክራትች ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ያልጠበቀው አደጋ ይገጥመዋል" ብለው ነበር።

@ThiqahEth
16🕊3😭3🤔2😱1
እስራኤል በሁቲ ላይ ሦስት ጥቃቾችን ሰነዘረች።

እስራኤል በዚሁ ጥቃቷ በየመን የሚገኙ ወደቦችን እና የሀይል ማመንጫዎችን ኢላማ ማድረጓ ተገልጿል።

ይህ ጥቃት በቡድኑ ላይ ከአንድ ወር በኋላ የፈፀመችው ነው ተብሏል።  

የእስራኤል ጦር ጥቃቱን የፈፀመው ከሁቲ ሁለት የሚሳዔል ጥቃት ስለተሰነዘረበት እንደሆነ አስታውቋል።
#timeslive

@ThiqahEth
👏127😡4🕊2🤔1🙏1