THIQAH
13.2K subscribers
2.61K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
"ከአሜሪካ መከላከያና ገንዘብ ቢሮ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን በግድ እንዲለቁ ተደርገዋል" - የአሜሪካው ዳኛ

በትራምፕ የተባረሩ ሰራተኞችን ወደ ስራቸው
እንዲመልሱ ሁለት የሀገሪቱ ዳኞች መጠየቃቸው ተሰምቷል።

ዳኞቹ፣ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ከስራቸው የተባረሩ የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ አሳስበዋል።

በካሊፎርኒያ ግዛት የሚኖሩት ዳኛ ዊሊያም አልሰፕ፣ ሰራተኞችን ከስራቸው ማፈናቀልን "አሳፋሪ ስትራቴጂ" ሲሉ ተቃውመዋል።

ሌላኛው የሜሪላንድ ነዋሪ ዳኛ በበኩሉ፣ ከአሜሪካ መከላከያና ገንዘብ ቢሮ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን በግድ እንዲለቁ ተደርገዋል ብለዋል። #thewashingtonpost #reuters

@ThiqhEth
👍19🤔1