TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update ሐያት ሆስፒታልና ሐያት ሜዲሲን ኮሌጅ ተሸጠ። ቦሌ የሚገኘውን ሐያት ሆስፒታል በከፍተኛ የሼር ድርሻ የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት የሆኑት አቶ #ድንቁ_ደያስ እንደገዙት ምንጮቼ ገልፀዋል ሲል ጉለሌ ፖስት ዘግቧል። በከፍተኛ የሼር ድርሻ የተገዛው ሐያት ሆስፒታልና ሐያት ሜዲሲን ኮሌጅ ሲሆን የሸጡት የሆስፒታሉ ባለቤት አቶ #ኢብራይም_ናኦድ በትውልድ ኤርትራዊ ናቸው ብሏል ዘገባው።

ምንጭ፦ ጉለሌ ፖስት(ውብሸት ታዬ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Sheger___የቅማንት_ማንነት_አስመላሽ_ኮሚቴ_በሚ.3gp
801.2 KB
የቅማንት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በሚል የሚንቀሳቀስ ቡድን በአማራ ክልል አለመረጋጋትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እያደረገ ነው ሲል የክልሉ መንግስት ተናገረ፡፡ ቡድኑ ከተግባሩ የማይቆጠበ ከሆነም ያለ አንዳች ማመንታት #እርምጃ ወስዳለሁም ብሏል፡፡


ከላይ ዝርዝር ያዳምጡ...

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 7 ቀን 2011 ዓ.ም ይመረቃል። ኢንዱስትሪ ፓርኩ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና ክልል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት እንደሚመረቅም ተገልጿል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከAAU🔝

"በአለም ለ27 ኛ ጊዜ #በኢትዮጽያ ለ26 ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሳቲ በአሁኑ ሰዓት " የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎ መብት እንጂ ችሮታ አደለም" በሚል መርህ ቃል በዕውቀቱ ሰው መሆን ፍልፍሉ እንደሁም እንደ ኛ እንስት ድምፃዉያን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል (ዮሴፍ ከበደ )AAU Broadcast Journalism"

@tsegabwold @tikvahethiopia
#UpdateSport በስድስተኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ ቅዳሜ በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን ለመግጠም መርሐ ግብር የወጣለት ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ እሁድ እንዲሸጋገርለት ጠየቀ።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ከመከላከያ ጋር የነበረው ጨዋታ በብሔር ብሔረሰቦች በዓል ምክንያት ወደ ሰኞ በመሸጋገሩ ቡድኑ ቀጣይ ሳምንት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ላለበት ጨዋታ በቂ የዝግጅት ግዜ እንደሌለው የገለጸው ክለቡ እሁድ ታኅሳስ 7 የትግራይ ስታድየም ከማንኛውም ፕሮግራም ነፃ በመሆኑ በዚህ ቀን እንዲደረግ አያይዞ ገልፅዋል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የወሰነውን ውሳኔ ተማሪዎች ተቃወሙ። ተቋሙ እስከ ዛሬ 11:00 ድረስ በየትምህርት ክፍላቸው ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በገዛ ፍቃዳቸው ትምህርታቸውን #እንዳቋረጡ የሚገልፅ ማስታወቂያ አውጥቷል። ከተማሪዎች ለመስማት እንደቻልነው ዩኒቨርሲቲው ድምፃችንን አፍኖ ሊያስተዳድረን እየሞከረ ይገኛል ይህን ደግሞ በፍፁም አንቀበልም፤ ለጥያቄዎቻችን ተገቢ ምላሽ ይሰጠን ብለዋል። በአሁን ሰዓት በግቢው ውስጥ የፀጥታ ሀይሎች የሚገኙ ሲሆን ተማሪው በያለበት ሆኖ በጩኸት እየተቃወመ ይገኛል።

እንደአዲስ ያልተመዘገቡ፦

•የላይብረሪ አገልግሎት አያገኙም

•ከግቢ ውጭ ከወጡ ተመልሰው መግባት አይችሉም

•ዩኒቨርሲቲው በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ገደብ ተጥሎባቸዋል።

በሌላ በኩል...

እንደ አዲስ ፈርመው የተመዘገቡ የተቋሙ ተማሪዎች ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው ብለዋል።

🔹ተማሪዎቹ እያነሷቸው ባሉት ጉዳዮች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲው ምልሽ ለማድረግ ጥረት እያደረኩ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️

የአልኮል መጠጦች ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በፊት በመገናኛ ብዙሃን #እንዳይተዋወቅ የሚያዝ ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ የአልኮል ይዘቱ ከ10 በመቶ በላይ የሆነ መጠጥን የሚያመርቱ፣ ወደ ሀገር የሚያስገቡና የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች የሕዝብና የመንግሥት በዓላትን፣ ስብሰባዎችን፣ የንግድ ትርኢቶችን፣ ስፖርታዊ ውድድሮችን፣ የትምህርት ቤት ዝግጅቶችንና ወጣቶች የሚሳተፉባቸውን መድረኮች ስፖንሰር እንዳይደርጉ ይከለክላል፡፡

አልኮል መጠናቸው ከ10 በመቶ በታች የሆኑትም በሜዲያ ማስተዋወቅ የሚፈቀደው ከምሽቱ 3:00 እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡ ከ18
ዓመት በታች ላሉ ታዳጊዎቸ አልኮል መሸጥ ክልክል እንደሆነም ማስታወቂያዎች ለመግለጽ ይገደዳሉ፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ🔝

#ሰላም ወረደ! በአሁን ሰዓት #የአማራ እና #የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ተቃቅፈው ይቅር እየተባባሉ ነው። ያለፈውን አስጨናቂ እና መጥፎ ቀናት በይቅርታ አልፈው ይኸው በፍቅር ተደምረዋል። ደስታቸውንም በጋራ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ እየገለፁ ይገኛሉ።

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ🔝የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የመግቢያ ሰዓት ላይ ገደብ የጣለ ሲሆን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ተማሪዎቹ ከነገ ጀምሮ ወደትምህርት ገባታቸው እንዲመለሱ ጥብቅ ማስታወቂያ አውጥቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ #ናፍታ_በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ተገዢነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ #አህመድ_መሀመድ እንዳስታወቁት፥ በህገ ወጥ መንገድ ናፍታ ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ተሽከርካሪዎች በሱማሌ ክልል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ነዳጅ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ መኪናዎች አሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ አህመድ አስታውቀዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነዳጅ ፍላጎትና አቅርቦት ካለመመጣጠን ጋር በተያያዘ በየነዳጅ ማደያዎች ረጃጅም ሰልፎችን መመልከት እየተለመደ መጥቷል። ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ አንዱ ሲሆን፥ ተገቢ ያልሆነ ውድድር እና የሎጅስቲክስ አቅርቦቱ ምቹ አለመሆን የዘርፉ ችግሮች በመሆን ይጠቀሳሉ።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዋልታ ቴሌቪዥን!!

"ለክቡራን ተመልካቾቻችን የፍትህ ሰቆቃ በሚል ርእስ በሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ የሚያተኩር ዶክመንተሪ ዛሬ ምሽት ከ2:30 ላይ በዋልታ ቴሌቪዥንና በዚህ የፌስቡክ ገፃችን በቀጥታ እንደምንቀርብ እየገለፅን እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጋብዛለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛው ጀማል ካሾጊ በታይም መፅሄት የ2018 ምርጥ ሰው ሆነ ተመረጠ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #በታጣቂዎች በፈጠሩት የጸጥታ ስጋት ቀደም ሲል ለተረጅዎች ዕርዳታ ለማድረስ የሄዱ 5 ከባድ መኪናዎች ለ28 ቀናት መመለስ አለመቻላቸውን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሸገር ተናግሯል፡፡

በኮሚሽኑ የአቅርቦትና ሎጅስቲክ
ዳይሬክተር #ሐይድሮስ_ሀሰን እንዳሉት ኮሚሽኑ ባሁኑ ሰዓት በ10 ካሚዮኖች አስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ ቢያስጭንም በጸጥታ ስጋት ሳቢያ ወደ ካማሺ ዞን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡ ለአማራጭ በአማራ ክልል ኢንጅባራ በኩል ለመላክ የታሰበ ሲሆን የቤንሻንጉል ክልል መንግሥትም በፖሊስ አሳጅባለሁ ብሏል፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopa
#update የገቢዎች ሚኒስቴር በጠረፍ ላይ ለሚገኙ ዜጎች በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጥ የሚያገኙበትን አገልግሎትን ማቆሙን አስታወቀ። የገቢዎች ሚኒስቴር የፍራንኮ ቫሉታ ለታለመለት አላማ ባለመዋሉ ምክንያት አገልግሎቱን መስጠት ማቆሙን አስታውቋል። የፍራንኮ ቫሉታ አገልግሎት መቆምን ተከትሎም ጠረፍ ላይ ለሚገኙ ዜጎች ሸቀጦችን እንዲያገኙ ሌላ መፍትሄ እያመቻቸ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia