TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray “ የክልሉም የፌደራሉም መንግስታት ሕግ ማስከበር አለባቸው ካልሆነ በስተቀር የከበደ የጦርነት አደጋ እየመጣብን ነው ” - ስምረት ፓርቲ ➡️ “ የኤርትራ ታጣቂዎች ከዚህ በፊት ይዘዋቸው የነበሩ ቦታዎችን እንደያዟቸው ናቸው፡፡ አዳዲስ የያዟቸው ቦታዎችም አሉ ! ” “ አዲስ ጦርነት እንዳይከፈት ” በሚል የተፈጠረውን ስጋት ጨምሮ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በእነ አቶ…
#Tigray
" የስምረት ፓርቲ ታጣቂ ሀይል በሰነዘረው ጥቃት አንድ ሰው ተገድሏል " - የትግራይ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
➡️ " እኛ ታጣቂ ሰራዊት የለንም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
ከሰሞኑን በአላማጣ ከተማ በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የቦንብ ተፈጽሞ የሰው ህይወት አልፏል።
የትግራይ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ባወጣው መግለቻ " ጥቃቱን የፌደራል መንግስት አጣርቶ እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አለበት " ብሏል።
ሀምሌ 21/2017 ዓ.ም ሌሊት በአላማጣ ከተማ ነዋሪ በሆኑት ባለሀብት ሰለሙን አያሌው መኖሪያ ቤት በታጣቂዎች በደረሰ የቦንብ ጦቃት ሁለት ልጆቻቸው ሞተው እሳቸውና ባለቤታቸው የሚገኙባቸው 3 ሰዎች በከባድ ቆስለው በህክምና ክትትል ስር ይገኛሉ።
ቢሮው፤ " ለጥቃቱ ከተማዋን በኮማንድ ፓስት ስር እያስተዳደረ ያለው የፌደራል መንግስት ኃላፊነት ይወስዳል " ብሏል።
" ስለሆነም የፌደራል መንግስት የጥቃቱ ፈፃሚዎች አጣርቶ ህግ ፊት ያቅርብ " ሲል ገልጿል።
በሌላ በኩል ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም በደቡባዊ ምስራቅ ዞን የዓዲ ጉዶም ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ የወጀራት ነዋሪዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው መገደሉንና ተኳሹ ማን እንደሆነ እስከ አሁን እንደማይታወቅ ያመለከተው ቢሮው " እስከመጨረሻው አጣራለሁ " ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ቢሮው ሀምሌ 23/2017 ዓ.ም በዓፋር ክልል ይንቀሳቀሳል ያለው " የስምረት ፓርቲ ታጣቂ ሀይል " በእንደርታ ወረዳ ምላዛት ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በሚገኝ የትግራይ ኃይል ላይ በሰነዘረው ጥቃት አንድ አባል ተሰውቷል ሲል ከሰዋል።
" ስምረት ፓርቲ በሽብር ተግባር እየተሳተፈ ነው " ሲል የገልጾ " በላያችን ላይ እየተወሰደ ባለው ትንኮሳ ትዕግስታችን ተሟጠዋል " ሲል አስጠንቅቋል።
የስምረት ዴምክራሲያዊ ፓርቲ መስራችና መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ለዚሁ ክስ በሰጡት ምላሽ " በምስረታ ሂደት የሚገኘው ስምረት የፓለቲካ ፓርቲ ታጣቂ ሰራዊት የለውም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia

❤267🕊53😢20😡17💔8🤔7😭6👏5🙏1
#MoE
ከ84 ሺህ በላይ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ላይ መሰረት ያደረገ ስልጠና ከመጪው ሰኞ ጀምሮ እንደሚወስዱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡት መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች በ30 ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚወስዱ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ ሰልጣኝ የሁለተኛ ደረጃ መምህራኑን በመቀበልና በአግባቡ በማሰልጠን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳስበዋል፡፡
" መምህራኑ እና አመራሮቹ የተዘጋጀላቸውን የስልጠና ሞጁል መጨረሳቸውን፣ ስልጠናውን በአግባቡ መከታተላቸውን እና መመዘናቸውን ዩኒቨርሲቲዎቹ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል " ብለዋል።
ሰልጣኞቹ ስልጠናውን ካጠናቀቁ እና ከተመዘኑ በኋላ የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
Via @tikvahuniversity

❤223😡30🤔23👏18🙏9🕊6😱4💔3😭3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የተገደለው አሽከርካሪ ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል " - ጣና አሽከርካሪዎች ማህበር
ከትላንት ወዲያ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ሁለት ሰአት አካባቢ ጉዞውን ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ ያደረገ " ግዮን ባስ " የተሰኘ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ፍቼ ሰላሌ ኢስት ሲሜንት አካባቢ ሲደርስ በታጣቂዎች በተፈጸመበት ጥቃት ሹፌሩን ጨምሮ ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናገራቸው ይታወሳል።
በታጣቂዎች በደረሰበት ጉዳት ህይወቱ ያለፈው አሽከርካሪ አቶ ጌታቸው ደጉ የሚባል የ45 አመት ጎልማሳ እና የሦስት ልጆች አባት ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አስክሬኑ በትላንትናው ዕለት ባህርዳር ከተማ እንደገባና ቀብሩ በዛሬው ዕለት በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ በምትገኘው ሽሜ ማርያምን ቤተክርስቲያን መፈጸሙን ከጣና አሽከርካሪዎች ማህበር ጸሐፊ አቶ ሰጡ ብርሃን አረጋግጧል።
አቶ ሰጡ " በጥቃቱ የተገደለው አሽከርካሪው ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል የሟቹን ፎቶ ይዘው የሚታዩት እናቱ ናቸው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

😭1.48K❤325💔117😢57😡36🕊15🙏12🥰5😱4🤔2
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተገደለው አሽከርካሪ ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል " - ጣና አሽከርካሪዎች ማህበር ከትላንት ወዲያ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ሁለት ሰአት አካባቢ ጉዞውን ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ማርቆስ ያደረገ " ግዮን ባስ " የተሰኘ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ፍቼ ሰላሌ ኢስት ሲሜንት አካባቢ ሲደርስ በታጣቂዎች በተፈጸመበት ጥቃት ሹፌሩን ጨምሮ ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ…
" በየቦታው ሹፌሮች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት የግፍ ውድድር ይመስላል " - ማህበሩ
ባለፉት 45 ቀናት ብቻ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች 77 ሹፌሮች እና ረዳቶቻቸው ሲታገቱ 34 ሹፌር፣ ረዳት እና ተሳፋሪዎች ደግሞ መገደላቸውን ስሜ አይጠቀስ ያሉ የጣና አሽከርካሪዎች ማህበር አባል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ስሜ አይጠቀስ ያሉ የማህበሩ አባል መረጃውን ያጋሩት ባለፉት 45 ቀናት ወደ "የሾፌሮች አንደበት" ገጽ የመጡ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሾፌር፣ ረዳት እና ተሳፋሪዎች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን ብቻ ነው።
" በየቦታው ሹፌሮች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት የግፍ ውድድር ይመስላል ይህ ሁሉ ጥቃት የሚፈጸመው ሁሉም ሰው በአካባቢው የሚፈጸመውን ጥቃት ማውገዝ ባለመቻሉ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አክለውም " ይፋ ያደረግነው መረጃ ወደ ገጹ የመጣውን ብቻ እንጂ ሙሉ የጥፋቱን መጠን አያሳይም ነው " ያሉት።
" የተጠቀሰው ቁጥርም ባለፉት 45 ቀናት ወደ ገጹ የመጣውን ብቻ ነው ወደ ኋላ ብንሄድ ከእዚህም ከፍ ያለ የሟች እና የተጎጂዎች ቁጥር ይፋ ማድረግ ይቻላል " ሲሉ አክለዋል።
ማህበሩ ባጋራው መረጃ ፦
➡️ በ03/10/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከጎንደር ደባርቅ መሀከል 44 የሚባል ቦታ ላይ 2 ሹፌሮችን ከእነ ረዳቶች ታፍነው ተወስደዋል።
➡️ በ04/10/2017 ዓ/ም በአፋር ክልል ገዳማዊቱ አካባቢ አንድ ህዝብ ጫኝ አውቶብስ በጥይት ተመቶ የ1 ተሳፋሪ ህይወት አልፏል።
➡️ በ03/10/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከጃዊ ወደ ፓዊ ሲጓዝ ከጃዊ ትንሽ ወጣ ብሎ የነበረ ሲኖ ተሳቢ ሹፌሩን እና ረዳቱን አግተው ወስደዋል።
➡️ በ04/10/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ፈለገ ብርሀን ወጣ ብሎ ጭየ የሚባል አካባቢ 1 የ fsr አሽከርካሪ በታጠቁ አካላቶች በጥይት ተመቶ ተገድሏል።
➡️ በአፋር ክልል በአዳይቱ እና ገዋኔ መሀል ባለችው ያንጉዲ የሚባል ኬላ ያለበት ቦታ ላይ አንድ አባዱላ ሚኒባስ ሹፌር በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል።
➡️ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን በቡለን ወረዳ ሰኔ 9/10/2017 ዓ/ም 9 ሹፌር ረዳቶች ታግተው ተወስደዋል።
➡️ በ14/10/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን ከደብረ ማርቆስ እና አማኑኤል መካከል 1 ሹፌር ከነረዳቱ ታግተው ተወስደዋል።
➡️ በ16/10/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከመተማ ጎንደር መንገድ መቃ ላይ 6 ሹፌር እና ረዳቶች ተገድለዋል።
➡️ በ18/10/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከሶሮቃ አብረሀጂራ መንገድ እርጎየ አካባቢ 3 የኦባማ 2 የ FSR ሹፌሮች ከእነ ረዳቶቻቸው በድምሩ 10 ሹፌር እና ረዳቶች በአጋች ዘራፊዎች ታግተው ተወስደዋል።
➡️ በ18/10 /2017 ዓ/ም በአብርሀጅራ መተማ በኮሩመር አድርገው እየሄዱ የነበሩ አሽከርካሪዎች ልዩ ስሙ ደለሎ አብደረግ ከሚባል ቦታ 1 ሹፌር ሲገደል 7 ተሳፍሪና ሾፌር ታፍነው ተወስደዋል።
➡️ በ18/10/2017 ዓ/ም ከጎንደር መተማ መንገድ 4 ሹፌር እና ረዳቶች ታፍነው ተወስደዋል።
➡️ ደብረ ብርሀን መስመር ከሰንቦ ወደ ምንጃር የሚያስወጣው መንገድ ሀገረ ማርያም ላይ 1 ሾፌሮች በ19/10/2017 ዓ/ም ተገድሏል።
➡️ በ23 /10/2017 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ ኤክስካቬተር ጭኖ እየሄደ የነበረ ሎቤድ በኦሮሚያ ክልል ከነቀምቴ 5 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ በዘራፊ ወንበዴዎች ሹፌሩ ተገድሏል።
➡️ በኦሮሚያ ክልል ከያዩ ፊንጫ መንገድ በታጠቁ ወንበዴወች 1 አሽከርካሪ ተገድሏል።
➡️ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አንቦ ኣለፍ ብሎ ጌዶ ሚባል አከባቢ 1 አሽከርካሪ በሽፍቶች ተገድሏል።
➡️ በ02/11/2017 ዓ/ም አዲስ አበባ ጅማ መንገድ ጊቤ ላይ 1 ሹፌር ታፍኖ ተወስዷል።
➡️ በ11/11/2017 ዓ/ም ማክሰኝት እና እንፍራዝ መሀል አንድ ሹፌር በዘራፊ ወንበዴዎች ተገድሏል።
➡️ በ12/11/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከጎንደር መተማ መንገድ ሰራባ ዝቅ ብሎ ባለው የመንገድ ክፍል 6 የተሳቢ 1 የአይሱዙ ሹፌር እና ረዳቶች በዘራፊ ወንበዴዎች በድምሩ 14 ታግተው ተወስደዋል።
➡️ በ11 /11/2017 ዓ/ም ከመትሀራ ወለንጭቲ መሀል ወለንጪቲ መግቢያ 1 ሹፌር ታግቶ ተወስዷል።
➡️ በአማራ ክልል በሰሜን ጎጃም ዞን 14/11/2017 ዓ/ም መራይ ቢኮሎ መሀል አቦ መስክ 3 ሹፌር ከእነ ረዳት በድምሩ 6 ታፍነው ተወስደዋል።
➡️ አሰቦት እና አዋሽ መሀል ሚዛን መዳረሻ 2 ሾፌር እና ረዳት በድምሩ 4 ሰዎች ታግተው ተወስደዋል።
➡️ በ17/11/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከደባርቅ ጃናሞራ ጨነቅ ላይ አንድ አሽከርካሪ ላይ ግድያ ተፈፅሟል።
➡️ በ18/11/2017 ዓ/ም በአማራ ክልል ከአብርሀጅራ እርጎየ አሪዳ የሚባል ልዩ ቦታ 1 ሹፌር 1 ተሳፋሪ በድምሩ 2 ሰው ላይ ግድያ ተፈፅሟል።
➡️ 18/112017 ዓ/ም በአማራ ክልል በሰሜን ጎጃም ዞን ከመራዊ ቢኮሎ ሹፌር ከእነ ረዳቱ ታግቷል።
➡️ በ23/11/2017 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ፍቸ ወጣ ብሎ 2 ሹፌር ከእነ ረዳት እገታ ሲፈፀምባቸው አንድ ሹፌር እና ተሳፋሪ ላይ ግድያ ተፈፅሟል።

😭798❤397💔48😡25😢21🕊21🙏15😱4🥰2
#AddisAbaba
በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ4 ኪሎ ፕላዛን ፣ የ4 ኪሎ የገበያ ማዕከልን እና የመኪና ማቆሚያን በማስመረቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
ፕሮጀክቱ ምን ይዟል ?
- ከመሬት በታች የተገነቡ ዘመናዊ የሆኑ 102 የስጦታ እና የአልባሳት መደብሮች፣ ካፌዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ማንበቢያ ስፍራዎች፣ ሱፐር ማርኬቶች፤
- ከ100 በላይ ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ የመኪና ማቆሚያ፤
- በአንድ ጊዜ እስከ 5,000 ሰዎችን መሰብሰብ የሚያስችል የፕላዛ፣ የአንፊ ቴአትርና የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን ማቅረቢያ ስፍራዎችን ይዟል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ " ፕሮጀክቱ የሲቪል ተሳትፎን፣ የባህል ዕድገትን፣ የእግር ጉዞን የሚያበረታታ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ነው " ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች እና ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን አመልክተዋል።
#MayorOfficeofAA

❤967😡263👏75🙏17🥰16🤔16💔14😢12🕊10😱9
#Tigray
ከእገታ ማስለቀቂያ 2 ሚሊዮን ብር የተጠየቀበት ህፃን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተገድሎ ተጥሎ ተገኘ።
ከ5 ቀናት በፊት የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳባጉና ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ የሆነው ህፃን ናኦድ ተኽላይ ብርሃነ በአጋቾች ታፍኖ መወሰዱንና አጋቾቹ ለማስለቀቅያ 2 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸው የሚጠቅስ በህፃኑ ፎቶ የታጀበ ፅሁፍ በበርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ሲዘዋወር ነበር።
ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ወደ ህፃኑ ቤተሰብ ደውለው ነው የማስለቀቅያ ብሩን የጠየቁት ይላል ሲዘዋወር የቆየው ፅሁፍ።
ዛሬ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም የተሰማው ግን እጅግ አስደንጋጭ መርዶና ከሰውነት የወጣ የጭካኔ ተግባር ነው።
ህፃን ናኦድ ተኽላይ በጭካኔ ተገድሎ የፀጥታ አካላት በተገኙበት አስክሬኑ በፍሳሽ መተላለፍያ ቦይ ተጥሎ ተገኝቷል።
የሟች ህፃን ናኦድ ተኽላይ አስክሬን ለምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከእንዳስላሰ-ሽረ የመረጃ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል።

😭1.42K💔321❤161😡55🕊21😢20😱10🙏5🤔4🥰3