TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ #ናፍታ_በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የህግ ተገዢነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ #አህመድ_መሀመድ እንዳስታወቁት፥ በህገ ወጥ መንገድ ናፍታ ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ተሽከርካሪዎች በሱማሌ ክልል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ነዳጅ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ መኪናዎች አሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ አህመድ አስታውቀዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የነዳጅ ፍላጎትና አቅርቦት ካለመመጣጠን ጋር በተያያዘ በየነዳጅ ማደያዎች ረጃጅም ሰልፎችን መመልከት እየተለመደ መጥቷል። ለዚህም በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ አንዱ ሲሆን፥ ተገቢ ያልሆነ ውድድር እና የሎጅስቲክስ አቅርቦቱ ምቹ አለመሆን የዘርፉ ችግሮች በመሆን ይጠቀሳሉ።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia