TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ🔝

#ሰላም ወረደ! በአሁን ሰዓት #የአማራ እና #የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ተቃቅፈው ይቅር እየተባባሉ ነው። ያለፈውን አስጨናቂ እና መጥፎ ቀናት በይቅርታ አልፈው ይኸው በፍቅር ተደምረዋል። ደስታቸውንም በጋራ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ እየገለፁ ይገኛሉ።

#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያና 1 ሺህ 300 ጥይቶች በቁጥ ጥር ስር ማዋሉን #የአማራ_ክልል_ፖሊስ አስታወቀ።

#የጦር_መሳሪያዎቹን ከጋምቤላ ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ በኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ በማስገባት ላይ እያለ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፥ የመኪናው አሽከርካሪም በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ገልጿል።

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥረት 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ!!

"#የአማራ_ክልል_ህዝቦች አንጡራ ሐብት የሆነ #ጥረት_ኮርሬፖት በተለያዩ ምክኒያቶች #ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።" ADP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኧረ ንቃ‼️

አንድ #የሰይጣን መንፈስ ያለበት ሰው በፌስቡክ በለጠፈው #የአማራ ህዝብ ብለህ ያን ሁሉ የተከበረ ህዝብ ስትሳደብ ትውላለህ...ደሞ #ትግሬ...ብለህ ያንን ሁሉ ኩሩ ህዝብ ስትዘረጥጥ ታመሻለህ...

#ኦሮሞ እንደዚህ ነው...እያልክ ያንን ሁሉ ቆፍጣና ህዝብ በአንድ ባለጌ ያሳደገው የተነሳ ስትሳደብ ታነጋለህ ... ከዚያ ከስር መፋጀት ትጀምራለህ...

ወዳጄ ኧረ ንቃ... ከሶሻል ሚዲያው በላይ ማሰብ ጀምር!

እውነት ከአማራ አካባቢ ወደ ገጠሪቱ ትግራይ ሂደህ አሳድሩኝ ብትል አልጋውን ለቆ የሚያሳድርህ #ኩሩ እንግዳ ተቀባይ ህዝብ እንዳለ ማን በነገረህ...

ከትግራይ ወደ ገጠራማው አማራ አካባቢ ሂደህ ቢመሽብህና " የመሸበት እንግዳ ነኝ " ብትል... ሞሰቡን ሙሉ እንጀራ አቅርቦ ሙክት አርዶ የሚያስተናግድህ ኩሩ ህዝብ እንዳለ ማን በነገረህ...

ከትግራይ ገጠሪቱ ኦሮሚያ ብትሄድ እርጎና ወተቱን በአኮሌ አቅርቦ እግርህን አጥቦ የሚያሳድርህ ኩሩ ህዝብ እንዳለ ማን በነገረህ...

እንግዲህ ይሄን ህዝብ ነው አንዳንድ የሰይጣን መልክተኞች በሚለጥፉት ስትሳደብ የምትኖረው።

ኧረ ንቃ...ንቃ! ስልህ በደንብ መንቃትን ንቃ... ራሱን ሰውየውን ንገረው... ዘወር በል አንተ ሰይጣን በለው!

Via ሚኪ
#ሼር #Share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" #የአማራ እና #የትግራይ ህዝቦች ዝም ብሎ ጆግራፊ አይደለም ያስተሳሰራቸው ፤ የጋራ ታሪክ አላቸው ፈለግንም አልፈለግንም አብሮ መኖራቸው አይቀርም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ከብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህ ቃለ ምልልሳቸው ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲሱ አመት 2016 ዓ/ም አስተዳደራቸው ፦

- የሰላም ጅምሩ እንዲጠናከር እንደሚሰራ ፤
- ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንደሚሰራ፤
- ከምንም በላይ በዜጎች አእምሮ ላይ የተፈጠረውን ስብራት ለመጠገን እንደሚሰራ፣
- የተቋረጡ የማህበራዊ አገልግሎቶች ለአብነት ትምህርት ፣ጤና አገልግሎቶች ከጦርነት በፊት ወደነበሩበት ለመመለስ ተስፋ ሠጪ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንደሚሰራ፤
- ምርጫ ተድርጎ የሚመረጠው አስተዳደር በተሟላ መልኩ ትግራይን የሚያስተዳድረበት በፌዴሬሽኑ ውስጥ ትግራይ ያላትን ተሳትፎ የሚያረጋግጥ መንግሥት እንዲሆን የፖለቲካ ስራዎችን ለመስራት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ምርጫ መቼ ነው ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ጌታቸው " ዋናው መሬት ላይ ያለው እውነታ ነው። ምርጫ ብቻችንን አይደለም የምናደርገው ፤ የፌዴራል መንግሥቱ ፣ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉዳይ ውስጥ መካከት አለባቸው ፤ የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች ሙሉ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ምርጫ መሆን አለበት " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ምርጫ ስለሚደረግበት ቀን ቁርጥ ያለ ጊዜ አልተናግሩም።

የአማራና የትግራይ ህዝቦችን ግንኙነት በተመለከተ በአዲሱ አመት ስለታቀዱ እቅዶች ተጠየቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " ጥያቄ ካለ በሰላማዊ መንገድ የሚጠየቅበትን ሁኔታ መመቻቸት አለበት ፤ ለዚህ ችግር የለብንም ብለን ብዙ ሰው በእኛ አካባቢ የችኮላ ነው የሚለውን እርምጃ ባህር ዳር ሄደን ያለንን የሰላም ፍላጎት ገልጸናል። ከዛ አንስተን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ ተፈናቃዮችን መመለስ ጀምረን ልዩነቶቻችንን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚያስችል ነገር ውስጥ እንገባለን ብለን መንቀሳቀስ ጀምረን ነበር " ብለዋል።

ይህ እንቅስቃሴ በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም ያለቱ ፕሬዜዳንቱ " በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም ማለት አይሄድም ማለት አይደለም። እንዲሄድ መስራት አለብን ምክንያቱም የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች ዝም ብሎ ጆግራፊ አይደለም ያስተሳሰራቸው ፤ የጋራ ታሪክ አላቸው ፈለግንም አልፈለግንም አብሮ መኖራቸው አይቀርም ፤ ቢረፍድ ይሻላል ፈፅሞ ከሚቀር እንደዚህ አይነት ነገር ስለዚህ እሱን (የተጀመረውን ግንኙነት) በአዲሱ አመት አጠናክረን እንቀጥላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

አዲሱን ዓመት በማስመልከተም አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና በውጭ ላለው ዳያስፖራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቀው የሚገባው ፤ ግጭት አንድ አካባቢ ስላለ cheer ማድረግ ይቁም። አንድ አካባቢ ያለ ግጭት የሁላችንም ግጭት መሆኑን እንረዳ፤ አንድ አካባቢ ያለ ጥፋት የሁሉም ጥፋት ነው ብለን እንቀበል ፤ መንግሥት ወደልማት ጎኑ ለመሄድ የሚያደርገውን ጥረት የሚያደናቅፍ ነገር ካለ ልማት ነው የሚያዋጣን የሚለው ድምፅ ጎልቶ እንዲወጣ ለማድረግ የሚያስችል እገዛ ይደረግ " ብለዋል።

" ዳያስፖራ ማጋጋል ፣ ማጋጋል ፣ ማጋጋል መሆን የለበትም ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግጭትን ከማጋጋል ስለሰላም መስበክ የሁሉም ድምፅ መሆን መቻል አለበት፤ እነ እገሌን ካላንበረከክን እነ እገሌን ካላሸነፍን ሞተን እንገኛለን የሚል አስተሳሰብ ሁላችንንም ወደ ጥፋት የሚወስድ እንጂ አንዱን የሚጠቅም አይደለም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ኢሰመኮ፦ - ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል። - የካቲት 20/2016…
#Oromia

ኢሰመኮ ፦

- ታኀሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ በተፈጸመ #የድሮን_ጥቃት
° በየነ ጢቂ፣
° ጉደታ ፊጤ፣
° ሀብታሙ ንጋቱ፣
° ታዴ መንገሻ፣
° ዳመና ሊካሳ፣
° ዱጋሳ ዋኬኔ፣
° ሕፃን አብዲ ጥላሁን
° ሕፃን ኦብሳ ተሬሳ የተባሉ 8 ሰዎች ተገድለዋል።

በተጨማሪም፦
• ስንታየሁ ታከለ፣
• ሽቶ እምሩ፣
• ተሜ ኑጉሴ
• አለሚ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) በሰፊው ይንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚደረጉ ውጊያዎች አልፎ አልፎ #በድሮን_ይጠቀም የነበረ መሆኑን ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

- ጥር 9/2016 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ለሌላ_ግዳጅ አካባቢውን ለቅቆ ይወጣል። ይህን ተከትሎም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች በማግስቱ አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ “ ለመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ምግብ ስታቀርቡ ነበር ” በማለት 01 ቀበሌ የሚገኘው ሳላይሽ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥበቃ የነበሩት አቶ ስዩም ካሴን #በጥይት_በመምታት ገድሏል። አቶ ከበደ ዓለማየሁ የተባሉ ነዋሪን ከመኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው ከወሰዷቸው በኋላ በአካባቢው ጫካ አስክሬናቸው ወድቆ ተገኝቷል።

- ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና አባያ ወረዳ ኤርገንሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት በመጓዝ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የገላና አባያ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። እንዲሁም 3 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ከየካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ #የአማራ_ታጣቂ_ቡድኖች የኦሮሚያ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ #በተከታታይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 25 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል ፤ 
➡️ 4 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትን አድርሰዋል
➡️ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎችን #አግተው ወስደዋል። በታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።

- በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶው “ ኦነግ ሸኔ ”) ታጣቂዎች ከኅዳር ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 15 ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎች #ተገድለዋል
➡️ ቁጥራቸው ለጊዜው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ነዋሪዎችን #አግተው_ወስደዋል
➡️ በርካታ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈዋል
➡️ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።

- መጋቢት 1/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልካምባ ከተማ ላይ የኦሮሞ ነጸነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የወረዳው አበዪ ሄቤን ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ ሹመቴ ፋርስ እና ወ/ሮ ተቀባ አበጋዝ የተባሉ አረጋዊያን በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ተገድለዋል።

- መጋቢት 16/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባሉት ሰዓታት ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ 7 ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዕለቱ በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌው ነዋሪ የሆነ እና የምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነ ግለሰብ ፣ ከባለቤቱ እና #ከ2_ልጆቹ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንዲሁም ሌላ አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። 

- መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በዶዶላ ወረዳ በደነባ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ 4 የቀበሌው ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች/ቡድኖች በጥይት ተመተው ሲገደሉ 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ” ) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ውስጥ “ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት ቤተሰቦች ናችሁ ” በሚል ወይም “ለመንግሥት አካላት ትብብር አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በየካቲት እና ሚያዝያ ወራት በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ ንብረት ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል።

ለምሳሌ ፦

👉 በወረዳው አቡዬ ጀብላል ቀበሌ የካቲት 7/ 2016 ዓ.ም. በፈጸመው ጥቃት 11 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፤ መኖሪያ ቤቶችንና ሞተር ብስክሌቶችን አቃጥሏል፤ የቀንድ ከብቶችን ዘርፏል።

👉 መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. በወረዳው ቆታ ከተማ ላይ በፈጸመው ጥቃት 31 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ 3 ሲቪል ሰዎችን አቁስሏል፣ የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም ንብረቶችን አቃጥሏል።

👉 ሚያዝያ 8/2016 ዓ/ም በደራ ቲርቲሪ ቀበሌ ላይ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት 2 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል ፣ ከ100 በላይ የተለያዩ የቀንድ ከብቶች ዘርፏል።

👉 በሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም በጎምንቦሬ አሊይ ቀበሌ 36 የቀንድ ከብቶችንና 3 የሞቶር ብስክሌት ዘርፏል።

#Oromia #Ethiopia #EHRC

@tikvahethiopia