TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል #በታጣቂዎች በፈጠሩት የጸጥታ ስጋት ቀደም ሲል ለተረጅዎች ዕርዳታ ለማድረስ የሄዱ 5 ከባድ መኪናዎች ለ28 ቀናት መመለስ አለመቻላቸውን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሸገር ተናግሯል፡፡

በኮሚሽኑ የአቅርቦትና ሎጅስቲክ
ዳይሬክተር #ሐይድሮስ_ሀሰን እንዳሉት ኮሚሽኑ ባሁኑ ሰዓት በ10 ካሚዮኖች አስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ ቢያስጭንም በጸጥታ ስጋት ሳቢያ ወደ ካማሺ ዞን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡ ለአማራጭ በአማራ ክልል ኢንጅባራ በኩል ለመላክ የታሰበ ሲሆን የቤንሻንጉል ክልል መንግሥትም በፖሊስ አሳጅባለሁ ብሏል፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopa