TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሜቴክ ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (#ሜቴክ) የተሰየመው አዲሱ የሥራ አመራር ቦርድ፣ በኮርፖሬሽኑ ያለ ገበያ #ጥናት ተመርተው ገዥ ማግኘት ባለመቻላቸው በአዳማ የእርሻ መሣሪያዎች ኢንዱስትሪ ከስድስት ዓመታት በላይ ተከማችተው የሚገኙ ከአሥር ሺሕ በላይ የሚሆኑ ትራክተሮችና መለዋወጫዎች፤ከተቻለ በርካሽ ዋጋ እንዲሸጡ ካልሆነም ለክልሎች በስጦታ እንዲበረከቱ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጉምቢ ቦርደዴ ግጭት የአመራሮች እጅ ነበረበት ተባለ!

ለ10 ሰዎች ሞትና ለበርካታ ዜጎች ጉዳት መንስኤ በሆነው በምእራብ ሀረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ላይ የአመራሮች እጅ ነበረበት ተባለ፡፡

በቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር እና የሰዎች ህይወት ህልፈት ላይ የአመራሮች እጅ እንደነበረበት ተሰምቷል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከወረዳው ሊቀመንበር ጀምሮ የተለያዩ አመራሮች፣ የቦርደዴ ወራዳ ወንጀል መከላከል ፖሊሶች ጭምር በድርጊቱ ተሳትፈው ነበር ብለዋል፡፡

በወረዳው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ያደረሱ እንዚህ አካላትን ጨምሮ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተሰምቷል፡፡

የሀገር መከላከያ፣ፌደራል ፖሊስ እና የሀገር ሽማግሌዎች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመወያየት ወንጀለኞችን አሳልፈው እንዲሰጡ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ጥቃት አድራሾቹን ህብረተሰቡ አሳልፎ መስጠቱንም አቶ ጀይላን ተናግረዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ችግሩ የተከሰተበትን አካባቢ የማረጋጋት እና ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረቡን ስራ እያከናወነ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ሀረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ የታጠቁ ሀይሎች በወረዳዋ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ፈፀመው 10 ሰዎችን መግደላቸው የሚታወስ ነው፡፡

Via #EthioFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ የርብ ወንዝ ሞልቶ ጉዳት እያደረሰ ነው። በወረዳው 8 ቀበሌዎች የሚገኙ 2 ሺህ 203 ቤቶች እንዲሁም በፎገራ ወረዳ በ10 ቀበሌዎች ውስጥ 2 ሺህ 400 ቤቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል በውሃ ተውጠዋል።

በሊቦ ከምከም እና ፎገራ ወረዳዎች በሚገኝ የሩዝ ሰብል ላይ ደግሞ እስከ 80 ከመቶ ጉዳት መድረሱን የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሶ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ_ዩንቨርስቲ

‹‹2012 የሰላምን ምንነት የምናሳይበት እንዲሆን እየሰራን ነው›› - ዶክተር #አብዲ_አህመድ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት
.
.
የ2012 የትምህርት ዘመን በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ብቻ ሳይሆን የሰላምን ምንነት ለማሳየት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። በትምህርት ዘመኑ 3ሺ612 አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱም ተጠቁሟል። የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር አብዲ አህመድ ሀሰን እንደተናገሩት፤ የ2011 የትምህርት ዘመን የጎላ ችግር አይታይበት እንጂ ለዩኒቨርሲቲው አመራር፣ መምህራንና አጠቃላይ ሰራተኛው ፈተና ሆኖ አልፏል። ከዚህ ሂደት በመማርም የ2012 የትምህርት ዘመን ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን፤ ተግባሩም ዩኒቨርሲቲው የሰላምን ምንነት የሚያሳይበት፤ ህብረተሰቡም ሰላምን የሚያስተምርበት እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ ነው ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሰጠ ማሳሰቢያ!

የፊታችን ረቡዕ ነሃሴ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቸራልያ ፋብሪካ፣ በገነተ መናፈሻ ኮንደሚኒየም፣ በማሩ ብረታ ብረት፣ በወህኒ ቤት ጀርባ፣ በቂሊንጦ ማረሚያ፣ በሳሪስ አቦ ቤተ ክርስቲያን፣ በቦሌ ቡልቡል ኮንዶሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞሪያ፣ በክሬሸር፣ በባሌስትራ ፋብሪካ፣ በGW2 ውሃ፣ በጎፋ ካምፕ ኮንደሚኒየም፣ በመካኒሳ፣ በከፍያለው መድሀኒት ማከፋፈያ፣ በቫቲካን ኤምባሲ፣ በመካኒሳ አቦ ቤተ ክርስቲያን፣ በቄራ ይመስገን ጋራዥ እና በአካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ይቋረጣል፤

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ በቡና ቦርድ፣ በምርጫ ቦርድ፣ በዳችያ፣ በጎፋ መብራት ኃይል፣ በአየር መንገድ፣ በቦሌ ሚካኤል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማሕበር እና በአካባቢዎቻቸው፤

በማግስቱ ሐሙስ ነሃሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም በእሕል በረንዳ፣ በአውቶብስ ተራ፣ በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ በገነሜ ትምህርት ቤት፣ በአማኑኤል ቤተ ክርስቲያን፣ በሻወል ደማ ትምህርት ቤት፣ በሰባተኛ ትራፊክ መብራት፣ በዶሮ ተራ፣ በጦር ሀይሎች፣ በመኮንኖች ክበብ፣ በቶሎሳ ሰፈር፣ በገዳመ እየሱስ፣ በወንድማማቾች፣ በሜክሲኮ፣ በፍሬህይወት ትምህርት ቤት እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ፤

እንዲሁም አርብ ነሃሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም በለቡ፣ በጆሞ 1 በከፊል እና አካባቢዎቻቸው ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ፤ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
65 በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ህጋዊ መለያ የለውም!

በኢትዮጵያ 65 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በመንግስት የተመዘገበ ህጋዊ መለያ እንዳሌለው የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ገለጸ። የወሳኝ ኩነት ምዝገባ በዘመናዊነት የአኗኗር ዘይቤ ህይወቱን የሚመራ ህብረተሰብ ሁነኛ መገለጫ እንደሆነም ተገልጿል። ይህ የተገለጸው ሁለተኛው አህጉር አቀፍ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ስታትስቲክስ ቀን ዛሬ በአዲስ አበባ ሲከበር ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ የወደመው ንብረት ከእጥፍ በላይ ጭማሪ አሳየ!

በ2011 የበጀት አመት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች አማካኝነት የወደመው ንብረት ካለፈው አመት የ815 ሚሊዮን ብር ጭማሪ በማሳየት አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን የ113 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ታወቀ። በ2010 የ720 ሚሊዮን ብር ጉዳት የደረሰ ሲሆን በተገባደደው የበጀት አመት በተለይም የቀላል እና ከባድ አካል ጉዳት የቀነሰ ሲሆን የሞት ቁጥር በ 372 ጨምሮ በ በአንድ አመት ውስጥ የ4010 ሰዎች ህይወት በትራፊክ አደጋ አልፏል። ከባድ የአካል ጉዳትም 5871 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ካለፈው አመት በ0.4 በመቶ ወይም በ 42 አደጋ የቀነሰ ሲሆን አራት ነጥብ ስድስት በመቶ መቀነስ ያሳው የቀላል የአካል ጉዳት አደጋም 5375 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ካለፈው አመትም በ515 አደጋ መቀነስ አሳይቷል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም አገግመው ወደ ቤታቸው ተመለሱ ተባለ!

#በአስመራ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለዋል ተብለው የነበሩት የኤርትራ የማዕድን ምኒስትር ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም አገግመው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን በጃፓን የኤርራ አምባሳደር #እስጢፋኖስ_አፈወርቂ አስታወቁ። ጄኔራል ስብሃት በአስመራ ከተማ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል የተባለው ባለፈው ታኅሳስ 2011 ዓ.ም. ነበር። በኤርትራ ላይ የሚያተኩሩ እና በተቃዋሚዎች የሚተዳደሩ ማኅበራዊ ድረ-ገፆች ጄኔራሉ በሽጉጥ ጭንቅላታቸው ላይ ተመተው መቁሰላቸውን ፅፈው ነበር።

የኤርትራ መንግሥት በአገሪቱ የትጥቅ ትግል ከፍ ያለ ሚና እንደነበራቸው በሚነገርላቸው ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም ላይ ተሞከረ ስለተባለው ግድያ በይፋ የሰጠው ማብራሪያ አልነበረም። አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ «ጄኔራል ስብሃት ኤፍሬም በውጭ ሀገር ከተደረገላቸው ስኬታማ ሕክምና በኋላ አገግመው ከውድ ቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ አስመራ መመለሳቸውን በመስማቴ ደስ ብሎኛል» ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል። አምባሳደሩ የማዕድን ምኒስትሩ ሕክምና የተደረገላቸው የት እንደሆነ በይፋ ያሉት ነገር የለም። በአስመራ ከተማ በጄኔራል ስብሃት ላይ ጥቃቱ መፈጸሙ ከተሰማ በኋላ የተሰራጩ መረጃዎች ለሕክምና ያመሩት ወደ ዱባይ እንደነበር ይጠቁማሉ።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የችሎትወሬ

/#ሳምራዊት/

አቶ ኢሳያስ ዳኘው በቀረበባቸው ሁለተኛ የክስ መዝገብ ላይ አቃቤ ህግ ሀምሌ 26 ለክስ መቃወምያ ምላሽ አስገብቶ ዛሬ ማለትም ነሀሴ 6 ለብይን ተቀጥሮ የነበረ ቢሆንም አቃቤ ህግ ምላሹን ያስገባው ነሀሴ 3 በመሆኑ ዳኞች በአቃቤ ህግ ችግር ምክንያት መርምረን በቀጠርነው ቀን ብይን መስጠት አልቻልንም ብለዋል፡፡በዚህ መዝገብ የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ አማረ አምሳሉን ጨምሮ 10 ተከሳሾች የተካተቱ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም ላይ 295 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል በሚል ነው አቃቤ ህግ ሀምሌ 2 ክሱን የመሰረተው በመቃወምያው ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
342,200 የቤተሰብ አባላት #HOPE #ተስፋ #TIKVAH #ETHIOPIA

Voice of Hope🇪🇹TIKVAH-ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የማህድንና ነዳጅ ሚኒስቴር

በ2011 በጀት ዓመት በማዕድን ዘርፍ 4 ነጥብ 95 ቢሊየን ብር ኢንቨስትመንት መመዝገቡን የማእድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢፌዴሪ ማዕድንና የነዳጅ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫው ነው ይህንን ያስታወቀው።

በበጀት ዓመቱ 5 የምርት እና 19 የምርመራ ፈቃዶች የተመዘገቡን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፥ የኢንቨስትመንት መጠኑም 4 ነጥብ 95 ቢሊየን ብር መድረሱን ነው የሚያመላክተው።

የወርቅ፣ የዕብነ በረድ፣ ብረት፣ የከበሩ የጌጣጌጥና ሌሎች ማዕድናት ፍለጋና ልማት ሥራ ላይ የዋለው ኢንቨስትመንት ካፒታል ብር 1 ነጥብ 124 ቢሊየን ሲሆን፥ በነባር 11 የነዳጅ ፍለጋና ልማት ሥራ ስምምነቶች፣ የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ለማካሄድ ከ1 ነጥብ 96 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት ተደርጓል፡፡ በኦጋዴን የተገኘውን 6 ነጥብ 3 ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ለማልማት ማስተላለፊያ ቧንቧ ዝርጋታ ስምምነት መፈረምና ወደ ስራ መግባት የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ያሳድገዋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ሚኒስቴሩ የተገለጸው።

በበጀት ዓመቱ በኩባንያዎችና #በባህላዊ አምራቾች ለብሔራዊ ባንክና ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የተለያዩ ማዕድናት 48 ነጥብ 938 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መመገኘቱም ተገልጿል። የአካባቢና ማህበረሰብ አልሚዎች 34 ሚሊየን ብር ገቢ ማድረግ መቻላቸውም በመግለጫው ተካቷል።

በዘርፉ በኩባንያዎችና በባህላዊ ማዕድን አምራቾች ከ179 ሺህ በላይ ዜጎቻችን የስራ ዕድል መፈጠሩንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የነበሩ የፀጥታ ችግሮች ከዘርፉ መገኝት ያለበትን ውጤት እንዳይገኝ ተግዳሮት መሆናቸው ጠቁሟል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሐይማኖት መሪዎች ተከታዮቻቸውን ስለስነምግባር ለማስተማር ጥረት ቢያደርጉም የተፈለገው ለውጥ እንዳልመጣ ተገለጸ!

የሃይማኖት መሪዎች ተከታዮቻቸውን ስለስነምግባር ለማስተማር ጥረት ቢያደርጉም የተፈለገውን ያህል ለውጥ በህብረተሰቡ ውስጥ ማስረጽ እንዳልተቻለ የፌዴራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዛሬ ገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የፌዴራል የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ በስነምግባር ግንባታ ዙርያ በጋራ ለመስራት የተዘጋጀ የጋራ መግባቢያ ሰነድ በተፈረመበት ወቅት ነው፡፡ ሰነዱን የፈረሙት የፌዴራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉዓለም እንዳሉት በስነምግባር የታነጸ ማህበረሰብ ለመገንባት የሐይማኖት ተቋማት የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቅሰው፤ ከዚህ በፊት ተቋማቱ ስለስነምግባር ለማስተማር ጥረት ከማድረግ በዘለለ የተቀናጀና ቀጣይነት ባለው መልኩ ባለመሰራቱ የተፈለገው ውጤት ሊመጣ አልቻለም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሀፊ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው በስነምግባር እሴት ግንባታ ላይ በቀጣይ ከፀረሙስና ኮሚሽን ጋር በጋራ ለመስራት ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ስነምግባር ማለት የአንድን ማህበረሰብ እምነት፣ ወግ፣ ባህልና ታሪክ በሀሳብና በድርጊት ተቀባይነት ባለው መንገድ መፈፀም ማለት ነው ያሉት ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ የሰዎችን የብስለት ደረጃም ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል። ግብረገብነትን የማስተማር ጉዳይ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ነው ያሉት ጠቅላይ ፀሀፊው 97.3 በመቶ በላይ ህዝቧ ሐይማኖተኛ ነው በምትባለው በኢትዮጵያ ውስጥ የስነምግባር ግድፈት መባበሱም አሳሳቢ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PHEIs_እስከ_ሰኔ_2011ዓም_ባለው_መረጃ_መሰረት.pdf
2.9 MB
PHEIs እስከ ሰኔ 2011ዓም ባለው መረጃ መሰረት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዕውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ዝርዝር...
#ሰኔ15 #ባህርዳር

በእነየማነ ታደሠ መዝገብ በተጠርጣሪዎች ላይ ቀዳሚ ምርመራ ለመስማት ለነሐሴ 9/2011 ተቀጠረ። በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው ‘መፈንቅለ መንግሥት’ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የ47ቱ ጉዳይ ዛሬ በባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታይቷል። ችሎቱ ቀዳሚ ምርመራን ለመስማት ቢሰየምም ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ለማቆም በቂ ጊዜ አልነበረንም፤ የክስ ወረቀትም አልደረሰንም በሚል ጉዳያቸው ሌላ ቀን እንዲታይ ጠይቀዋል።

ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ለማዘጋጀት ከአርብ ጀምሮ ጊዜ ነበራቸው፤ የክስ ወረቀትም ያልደረሳቸው ምስክሮች ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ ይችላል በሚል መሆኑን ጠቅሶ ለቀዳሚ ምርመራው የመንግሥት ጠበቃም ቢሆን ቆሞላቸው ችሎቱ ይቀጥል ብሏል።

ግራ ቀኙን ያደመጠው ፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎች የክስ ወረቀት ሊደርሳቸው ይገባል፤ ጠበቃ ማቆም የሚችሉ ከሆነ የመንግሥት ጠበቃ የሚያስቀርብ አይደለም በሚል ቀዳሚ ምርመራውን ለመስማት ለሐሙስ ቀጥሯል።

Via #BBCAMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሐዋሳ

የሲዳማ ሚዲያ ኔትወርክ ኃላፊዎችን ጨምሮ በሲዳማ ዞን ተቀስቅሶ በነበረ ኹከት እጃቸው አለበት የተባሉ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተከስተው የነበሩ ሁከቶችን በማስተባበር የተጠረጠሩ የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋናና ምክትል ስራ አስኪያጆችን ጨምሮ የዘጠኝ ተጠርጣሪዎችን ጉዳት ተመለከተ።

በዛሬው ችሎት ከቀረቡት ተጠርጣሪዎች መካከል የሲዳማ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ጌታሁን ደጉዬ ፣ ምክትላቸው ታሪኩ ለማና የዚሁ ጣቢያ የቦርድ አባል የሆኑት በላይ ባልጉዳ ይገኙባቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/HAWASSA-08-12
የጎዳና ተዳዳሪዎች በዝቅተኛ ደሞዝ ሥራ አንይዝም አሉ!

የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በመልሶ ማቋቋም ካሰለጠናቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች ውስጥ ከ500 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ሥራ ለመግባት የቀረበልን ደመወዝ ዝቅተኛ ነው በማለት ያለሥራ በካምፕ ውስጥ መቀመጣቸውን አስታወቀ።

ተማሪዎቹ ሰልጥነው ወደ ሥራ ሲገቡ በዝቅተኛው ደሞዝ ማለትም በ1 ሺሕ 700 ብር የሚቀጠሩ ከሆነ በኮካ ኮላ የመጠጥ ፋብሪካ የሚከፈል ሰባት መቶ ብር የቤት ኪራይ ለሰባት ወር ቢዘጋጅም ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማኅበራዊ ደኅንነት ልማት ማስፋፍያ ዳይሬይክተር እንደሻው አበራ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት በመልሶ ማቋቋም ከሰለጠኑ 966 ተማሪዎች ውስጥ 225ቱ በሥራ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ሠልጥነው የተለያዩ ሥራዎች ከተቀጠሩት ሠልጣኞች ውስጥም ከ1 ሺሕ 700 ብር እስከ 11 ሺሕ ብር ደሞዝ በተለያዩ ድርጅቶች ያስቀጠረ ሲሆን ሥራ ካላገኙ ተማሪዎች በተጨማሪ በዝቅተኛ ደሞዝ ሥራ መጀመር አንችልም ብለው ያለ ሥራ የተቀመጡ ተማሪዎችም እንዳሉ አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇#ማለዳአዲስ
https://telegra.ph/E-08-12-2
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች ለመጪው የትምህርት ዘመን እያዘጋጀ ያለውን አዲስ የደንብ ልብሶችን በጋርመንቶች በመገኘት ተመልክተዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በመጪው ዓመት የደንብ ልብስን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን በነፃ ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች ለማቅረብ እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የደንብ ልብሱ በአዲስ መልክ ዲዛይኑ ተሰርቶ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የደንብ ልብሶቹ ስፌት እስከ ነሐሴ 25 ድረስ ተጠናቅቆ ለተማሪዎች የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

Via @mayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይነበብ

በህገ ወጥ መንገድ ኢትዮጵያውያንን ለስራ ወደ ውጭ አገር የመላክ ወንጀል የሚያስከትለዉ ተጠያቂነት!

ከህገ ወጥ ስደት ጋር ተያይዞ በየጊዜው የሚደመጡት መረጃዎች በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው አደጋ እየጨመረ መምጣቱን የሚያመላክት ነዉ፡፡

ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደትን እንደ አማራጭ በመውሰድ የሚያደርጉት ስደት የተወሰነ ጊዜ የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት በባህር ላይ ህይወታቸውን የሚያጡ እንዲሁም እንደ እነሊቢያ እና የመንን በመሳሰሉ አገራት ውስጥ በህገ ወጥ ግለሰቦች ቁጥጥር ስር ሆነው በባርነት እስከ ማገልገል ደርሰው በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙበት ሁኔታ በመታየት ላይ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/FD-08-12-2
አማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን!

ትናንት ነሐሴ 5/2011 ዓ.ም የተከበረው 1440ኛ የአረፋ በዓልና በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም የተካሄደው የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን የእግር ኳስ ጨዋታ ‹‹ያለምንም የፀጥታ ችግር›› መጠናቀቃቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽ አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽንና ሚድያ ልማት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ትናንት የተከበረው 1440ኛው የኢድ አል አድሐ (አረፋ) በዓል በሠላማዊ ሁኔታ ተጠናቅቋል፡፡ የሃይማኖቱ ተከታዮች በተረጋጋ ሁኔታ ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን መከወናቸውንም አስረድተዋል፡፡

https://telegra.ph/AA-08-12-3

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማሮ ልዩ ወረዳ 1 ሰው ሞተ!

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ትናንት ምሽት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል ሌሎች አምስት ሰዎች ላይ መቁሰላቸውን የወረዳው ባለስልጣን አሰታወቁ። በተለምዶ ባጃጅ ተብሎ በሚጠራ ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው የአማሮ ወረዳን ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ከሚያዋስነው ኮምቦልቻ በተባለ የገጠር መንደር ውስጥ ነው።

ጥቃቱ በተሽከርካሪው ላይ በነበሩ ስድስት ሰዎች ላይ መፈጸሙን የተናገሩት የአማሮ ወረዳ የባህል፣ ቱሪዝምና መንግስት ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ተወካይ አቶ አማረ አክሊሉ «የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል፣ ሁለቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል» ሲሉ ተናግረዋል። ስለ ጥቃቱ ፈፃሚዎችም ሆነ ስለ ጥቃቱ መንስኤ የታወቀ ነገር የለም። በአካባቢው ባለፈው አንድ አመት በተፈጸሙ ጥቃቶች እና በተቀሰቀሱ ግጭቶች የበርካታ ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia