TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሆንግ_ኮንግ

የሆንግ ኮንግ አውሮፕላን ማረፊያ በከተማዋ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የዛሬ በረራዎችን ሰረዘ። የአውሮፕላን ማረፊያው ባለስልጣናት እንዳሉት በዛሬው ዕለት ፕሮግራም ተይዞላቸው ሰዓታቸውን በመጠባበቅ ላይ ያሉ የመነሻና መዳረሻ በረራዎች በሙሉ እንዲሰረዙ ተወስኗል።

ለበረራዎቹ መሰረዝ ምክንያቱ የዴሞክራሲ አቀንቃኞቹ ተቃዋሚዎች በአውሮፕላን ማረፊያው የመንገደኞች ማስተናገጃ ገብተው ለተቃውሞ በመቀመጣቸው ነው። ከውሳኔው በፊት ለመብረር ዝግጅታቸውን የጨረሱ እና ወደ ሆንግ ኮንግ ጉዞ የጀመሩ አውሮፕላኖች ክልከላው እንደማይመለከታቸውም ተጠቁሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጳጉሜን 2 እና 3 ቀን 2011 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የይቅርታ፣ አንድነትና ሰላም ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው፡፡ አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ ከሰዓት በሰጠው መግጫ ሀገር አቀፍ የይቅርታ፣ አንድነትና ሰላም ፌስቲቫል የፊታችን ጳጉሜን 2 እና 3 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይፋ አድርጓል፡፡ አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ሂልተን አዲስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የአሚር ኑር ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት በአረፋ በአል ዋዜማ በተደረጉ #ድንገተኛ ፍተሻዎች ልዩ ስሙ #ዱክበር በተባለ አካባቢ አንድ የቱርክ ስሪት EKOL.P29 #ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ከወረዳው ፖሊስ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል።

Via AD/#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ🔝

#HawassaUniversity #ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ
ተፎካካሪ ፓርቲዎች!

ግንቦት 2011 ዓ/ም-107 ፓርቲዎች
ነሀሴ 2011 ዓ/ም-137 ፖርቲዎች


በ2011 ዓ.ም በግንቦት ወር 107 የነበሩ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ቁጥር አሁን ላይ 137 እንደደረሰ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አድርጓል። ይህ ለምን ሆነ?

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፦

• ገዥው ፓርቲ ህገ ወጥ በሆነ መልኩ ፓርቲዎችን የመቀለቡን ሲያቆም እነዚህ ፓርቲዎች ወደፊት ወደ ገዥው ፓርቲ ይጠቃለላሉ ወይም ከጨዋታ ውጭ ይሆናሉ፤

• ገዥው ፓርቲ ብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ለማዳከም ብሎ የሚፈጥራቸው ፓርቲዎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን ቁጥር እንዲበራከት ማድረጉን፣ እነዚህ ፓርቲዎች የኢህአዴግን ቀለብ ካላገኙ መኖር የማይችሉ ፓርቲዎች አሉ፣ ይህም የፓርቲዎችን ቁጥር ይቀንሳል፣

• የብሄር ፖለቲካ ለፓርቲዎች ቁጥር መበራከት አስተዋፅኦ የለውም ባይባልም ችግሩ የመጣው ከታሪካችን ነው። በኢትዮጵያ የብሄር ጥያቄ ካልተመለሰ በስተቀር በአዋጅ አይፈታም፣

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፎካካሪ ፓርቲዎች!

ግንቦት 2011 ዓ/ም-107 ፓርቲዎች
ነሀሴ 2011 ዓ/ም-137 ፖርቲዎች


አቶ ኤፍሬም ማዲቦ፦

• በኢትዮጵያ ሰዎች በፓርቲ ውስጥ መደራጀትን የሚያገናኙት ከኢኮኖሚ ጥቅም መኖሩ ነው ቁጥሩን ያበዛው፣

• በቅርቡ እንኳ ከምርጫ ቦርድ ጋር የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ድርድር ላይ የውሎ አበል ስጡን ብለው መንግስትን የጠየቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው ምን ያህል ለጥቅም የቆሙ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ነው፣

• የፖለቲካ ፓርቲ በየትኛውም አገር ውስጥ ሲመሰረት በህዝብ ድጋፍና በአባላት መዋጮ ድጋፍ እንጂ በመንግስት አይደለም። በተቃራኒው በኢትዮጵያ ውስጥ ግን መንግስት ሲሸፍንላቸው መቆየቱ፣

• እያንዳንዱ ብሄር የእኔን ጥቅም የሚያስጠብቀው በብሄር የተደራጀው ነው በሚል ሁሉም በየዘውጉ እንዲደራጅ ምክንያት መሆኑ

• 100 ፓርቲ በመጪው ምርጫ ቢወዳደሩ ፓርቲዎች በመከፋፈላቸውና ድምጻቸው በመበታተኑ ምክንያት ብቻ ኢህአዴግ ተመልሶ ስልጣን ላይ እንዲመጣ ሊያደርግ ይችላል፣

• ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ባላት አገር ከ10 ሺ በላይ ፊርማ ማሰባሰብ በጣም አነስተኛ ቁጥር ነው። ይህን የተቃወመ ሁሉ አለ።

• እኛም አገር ፓርቲ የቤተሰብ ፓርቲ ማለትም አባት ፕሬዚዳንት እናት ገንዘብ ያዥ፣ ወንድም የህዝብ ግኙነት ሀላፊ የሆነበት ፓርቲ ይዘን የትም አንደርስም።

#አዲስ_ዘመን

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/EPA-08-12

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ140 በላይ ኢትዮጵያውያ ከእስር ተለቀቁ!

ባለፈው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ጂፒ በተሰኘው የንግድ አካባቢ ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ታስረው ከነበሩ 150 ኢትዮጵያውያን ከ140 በላይ የሚሆኑት እስከ ትናንት ምሽት ድረስ መለቀቃቸው ተነገረ።

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም ለቢቢሲ ሲናገሩ ታስረው የነበሩት ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፍቃድ እንዳላቸው ከተረጋገጠ በኋላ እንደተፈቱ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹ 450 የሚሆኑት እስረኞች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን ባላቸው መረጃ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል ኢትዮጵያዊያን እንዳልነበሩ አምባሳደሩ ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ጨምረው እንደተናገሩት አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን በተመለከተ ኤምባሲው አስፈላጊውን ማጣራት እና ከሚመለከታቸው የሃገሪቱ ሃላፊዎች ጋር ንግግር እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ፖሊስ ኢትዮጵያዊያኑን ያሰራቸው ተመሳሳይ ተደርገው የተሰሩ ሃሰተኛ ምርቶችን ይሸጣሉ በሚል ጥርጣሬ ነበር።

ተመሳሳይ ያልሆኑና በፖሊስ የተወሰዱ የኢትዮጵያዊያኑን እቃዎች ለማስመለስ ኢትዮጵያዊያኑ ጠበቃ ቀጥረው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱትና ኤምባሲውም ለዚህ ድጋፍ እንደሚያደርግ አምባሳደሩ አመልክተዋል።

Via #BBCአማርኛ
@tsegabwde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት መንሸራተት ሊያጋጥም ይችላል ተባለ!

በዘንድሮው የክረምት ወራት ከሚያጋጥመው መጠኑ ከፍ ያለ ዝናብ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 30 ድረስ ድንገተኛ መሬት መንሸራተት ያጋጥማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ጨምሮ እንደገለጸው በክረምቱ ወራት ከፍ ያለ የዝናብ መጠን የሚያገኙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ድንገተኛ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት እንደሚያጋጥማቸው ገልፆ ከእነዚህም ውስጥ መዲናችን አዲስ አበባ በመሬት መንሸራተት ልትመታ እንደምትችል እና ነዋሪው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ አሳስቧል።

መግለጫው ጨምሮ እንደገለፀው፤ ከመዲናዋ አዲስ አበባ በተጨማሪ የዝናብ ስርጭቱ በበርካታ አካባቢዎች ላይ ጎልቶ የሚታይ ሲሆን በውሃው ዘርፍ እንቅስቃሰው ላይ ሊያሳድር የሚችለው አዎንታዊ አስተዋፅዖ ሲሆን፤ በአብዛኛው የክረምት ተጠቃሚ ተፋሰሶች ላይ በመጠንም ሆነ በስርጭት የተሻለ እርጥበት ይኖራቸዋል ተብሎ ይገመታል።

#ኢጀንሲው አያይዞም ከአዲስ አበባ #በተጨማሪ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ያገኛሉ የተባሉትን አካባቢዎችንም ይፋ አድርጓል። ከዚህም ጋር ተያይዞ #በአብዛኛው_የአባይ፣ ተከዜ፣ ባሮ አኮቦ፣ የኦሞ ጊቤ የላይኛውና የመካከለኛው አዋሽ፣ ስምጥ ሸለቆ፣ ዋቢ ሸበሌ እና የላይኛው ገና ሌዳዋ ተፋሰሶች ላይ ከከፍተኛ እርጥበት እስከ እርጥበታማ የዝናብ መጠን ይኖራቸዋል ሲል አስታውቋል።

#አዲስ_ማለዳ_ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-08-12-4
ነዋሪዎች እንዲጠነቀቁ መልዕክት ተላለፈ!

የርብ ግድብ በመሙላቱ በታችኛው ተፋሰስ ያሉ ነዋሪዎች እንዲጠነቀቁ መልዕክት ተላለፈ፡፡ በደቡብ ጎንደር መስተዳድር ዞን የሚገኘው የርብ ግድብ የሚጠበቀውን ያህል ውኃ በመያዙ ማስተንፈስ እንዳስፈለገ የርብ ፕሮጀክት ተጠባባቂ ተጠሪ መሐንዲስ አስታወቁ፡፡ ተጠባባቂ ተጠሪ መሐንዲሱ ኢንጂነር አሸብር ቶንጃ ለአብመድ እንዳስታወቁት የርብ ግድብ ውኃ መድረስ ከሚጠበቅበት 1 ሺህ 940 ሜትር ከፍታ ላይ እየደረሰ ነው፡፡

የውኃ መጠኑ ከፍ በማለቱ በማስንፈሻው ለመውጣት የ50 ሴንቲ ሜትር ከፍታ ብቻ እንደቀረው የተናገሩት ተጠባባቂ መሐንዲሱ በጉና ተራራና አካባቢው ዛሬ ምሽት ከፍተኛ ዝናብ ከጣለ ውኃው በማስተንፈሻው በኩል ሊወጣ ይችላል፡፡ ስለሆነም በተፋሰሱ ዳርና ዳር የሚገኙ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ከግድቡ አካባቢ መደብ ጉግዳ ቀበሌ አንስቶ እስከ አዲስ ዘመንና ፎገራ ሜዳ ድረስ ያሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳሰቡት ተጠባባቂ መሐንዲሱ እስከ 10 ኪሎ ሜትር #ስኩዬር ድረስ ጎርፉ #ሊሸፍን እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

የርብ ግድብ 234 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የመያዝ አቅም አለው፡፡ ተጠባባቂ ተጠሪ መሐንዲሱ እንደገለጹት አሁን ላይ ግድቡ መያዝ የሚችለውን የውኃ መጠን ለመያዝ ተቃርቧል፤ የግድ ማስተንፈስንም የሚጠይቅበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዳማ ሁለተኛው ኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው!

ኢትዮጵያ እና ቻይና በ300 ሚሊየን ዶላር የጋራ ወጭ በአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው። በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ተጠሪ ሊው ዩ፣ በአዳማ የሚገነባው አዲሱ የኢንዱስትሪ ፓርክ በያዝነው የፈረንጆች 2019 ዓመት ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ሊጀመር ይችላል ሲሉ ለዥንዋ ተናግረዋል።

85 በመቶ የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ ወጭ ከቻይና መንግሥት በሚገኝ ዝቅተኛና በተራዘመ ጊዜ በሚከፈል የብድር ወለድ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል። ቀሪው 15 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል። “የሚገነባው ፓርክ በዋናነት መሣሪያዎችን የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ነው” ያሉት ሊው፣ በአሁኑ ወቅት መሬት እና ገንዘብ ማግኘት ጋር የተያያዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በቻይና ድጋፍ እና ሞያዊ እገዛ የሚገነባው አዲሱ ፓርክ ለአዳማ ከተማ ሁለተኛው ይሆናል። “የቻይና እና የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ውጤታማ የሆነ ጠንካራ ግንኙነት አላቸው” ሲሉም ሊው ተናግረዋል።

ምንጭ:-ዥንዋ/ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አደጋው የሁለት ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል!

በፎገራና ሊቦከምከም ወረዳዎች የተከሰተ የጎርፍ አደጋ በሰው ህይዎት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ፡፡ መንግስት በአስቸኳይ ሊደርስላቸው እንደሚገባ በጎርፍ አደጋው የተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጠይቀዋል። በወንዞቹ ምክንያት ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደረስ እየሰራ እንደሆነም ተገልጿል። ርብ እና ጉማራ የተባሉ ወንዞች በየዓመቱ መሙላት በአካባቢው ኅብረተሰብ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ዘንድሮ ግን ችግሩ የከፋ ሆኗል፤ በተለይ የርብ ወንዝ የአደጋ መጠኑ ከፍተኛ ሆኖ የሁለት ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፤ የእርሻ ሰብል አውድሟል፤ በርካታ ዜጎችም ከመኖሪያ ስፍራቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰላም ፣ፍቅር ፣ አንድነትና ብሄራዊ ኩራት ከአዲስ አበባ እንዲጀምር እንፈልጋለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ ይህንን ያሉት በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የስፖርቱን ዘርፍ ለማሳደግ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በተዘጋጀው የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡

እንደ ምክትል ከንቲባው ገለፃ አዲስ አበባ የሀገራችን ዋና ከተማ እንደመሆኗ መጠን ብዙ መልካም ነገሮችን በመጀመር ለክልል ከተሞችም አርአያ መሆን አለባት፤ ለአብነትም የዛሬ አመት የተሰራውን የችግረኞች ቤት እድሳትና በጠቅላይሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የችግኝ ተከላ ጅማሮውን በአዲስ አበባ አድርጎ ወደ ክልልም መውረዱን በማውሳት አሁንም በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የተጀመሩት ስራዎች ወደክልልም ይወርዳሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

‘’የከተማውን ወጣት ማገልገል ግዴታችን ነው’’ ያሉት ምክትል ከንቲባው የወጣቱን ፍላጎት ለሟሟላት እንደሚሰሩ በመግለፅ ፤ ስፖርትም የልማቱ አንድ አካል ስለሆነ ወጣቶችን በስፖርት ለማሳደግና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ...

#ሰላም_ለኢትዮጵያ አስጎብኚና የጉዞ ወኪል!
አሶሳን በተኩስ ሲያውካት ያመሸው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዋለ!

ባልተገባ ስነ-ምግባር በስካር መንፈስ በከፈተው ተኩስ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎችን ጸጥታ ሲያውክ ያመሸውን የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማው ፖሊሰ አዛዥ ኮማንደር አኑር ሙስጠፋ እንዳስታወቁት ትናንት ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ አንድ የጸረ-ሽምቅ ፖሊስ አባል በስካር መንፈስ በመነሳሳት በከፈተው ተኩስ የአካባቢውን ሰላም አውኳል።

ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ሊያውሉት የሞከሩ ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ላይም መተኮሱን የገለጹት አዛዡ በዚህም የአካባቢውን ጸጥታ ለደቂቃዎች አውኮት እንደነበር አመልክተዋል።

የጸጥታ ሃይሎች የግለሰቡን ትጥቅ ያስፈቱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በከተማው ወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ግለሰቡ ባካሄደው ተኩስም ሆነ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል ባደረጉት ጥረት በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ኮማንደር አኑር ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስረድተዋል።

በአሁኑ ሰዓት ነዋሪው ዕለታዊ ተግባሩን በተረጋጋ ሁኔታ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን እና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የተቀናጀ የፀጥታ ማስከበር ሥራ መቀጠሉን አዛዡ ጨምረው ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካሜሩኑ አምባሳደር አ/አ ውስጥ ሞተው ተገኙ!

በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደር ጃኩዌዝ አልፍሬድ ሞተው ተገኙ። አምባሳደር ጃኩዌ ትናንት በአዲስ አበባ መኖሪያ ቤታቸው ሞተው እንደተገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። ለአምባሳደሩ ሞት ምክንያቱ በመጣራት ላይ እንደሆነ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጥንቃቄ!

"ይህ የሚታየው አደጋ የተከሰተው ከቂሊንጦ ወደ ኮዬ ፈጬ ሰፈር መኪና ለመዝረፍ ታቅዶ የነበር ሲሆን፤ መጀመሪያ ሊፍት እንደመጠየቅ ብለው ነበር እና ለመዝረፍ ተብሎ በተወረወረ ድንጋይ የደረሰ አደጋ ነው። ጋቢና ከሹፌሩ አጠገብ በነበረው ሰው ላይ ቀለል ያለ ጉዳት ደርሶ ህክምና ላይ ይገኛል። ይሄ የሆነው ሀሙስ ከምሽቱ 2:30 ነው፤ ከዚህ አደጋ በመማር ሰዎች እንዲጠነቀቁ ነው። የታቀደው ዝርፊያ ሹፌሩን መትተው አቅጣጫ ስቶ ሲጋጭ እነሱ መኪናውን ለመውሰድ ነው።" #Lid

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር

#በመፈናቀል ምክንያት ትምህርት #ያቋረጡ_ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ከቁሳቁስ እስከ ምገባ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia