TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️Miss Grand Ethiopia 2018 #ሳምራዊት_አዝመራው ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ማይናማር ከተማ ዛሬ ለሊቱን ትበራለች። በቻናላችን ስም መልካም ዕድል እንመኝላታለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በማይናማር እየተካሄደ ባለው በሚስ ግራንድ ኢንተርናሽናል አለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ላይ ሀገራችንን #ኢትዮጵያን ወክላ እየተወዳደረች ላለችው #ሳምራዊት_አዝመራው ከታች ባለው ዌብሳይት ላይ በሶስት ዘርፍ ኢትዬጵያን በመምረጥ ድምፅ ይስጡ።

Www.missgrandinternationalvote.com

ምንጭ፦ ኢዮሲያስ ምትኩ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰኔ16

ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ሰኔ 16 2010 ዓ.ም በተደረገ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦምብ አፈንድተዋል ተብለው ክስ የተመሰረተባቸው 5 ግለሰቦች ክሳቸውን እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቷል።

Via #ሳምራዊት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ መልካም ስራችን እንመለስ!

በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት ለእህት እና ወንድሞቻችን እንዲሁም ለልጆቻችን ተገቢውን ነገር ሳናደርግ ቆይተናል፦

#1

√ስም፦ #ሳምራዊት_አረጋ
√እድሜ 22
√የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
√በደረሰባት ድንገተኛ የኩላሊት ህመም በአልጋ ላይ የወደቀች እህታችን...ልጃችን

#2

√ስም፦ #ምህረቱ_መንግስቴ
√ከ8ተኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጦ ለ11አመታት በየሆስፒታሉ ሲንከራተት የቆየ በሰው እቅፍ ካልሆነ መንቀሳቀስ የማይችል ሲመገብም ሆነ ለተፈጥሮ ግዳጅ መቀመጥ የማይችል
√በከፋተኛ የአጥንት ቁስለት እየተሰቃየ ከግራታፋው 5 የተለያዩ ቁስለቶች ፈሳሽ የሚፈሰው
√ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውጭ ሀገር እንዲታከም ሪፈር የፃፈለት 1.2ሚሊየን ብር የተጠየቀ ነገር ግን ወላጁን በሞት ያጣና ምንም ገቢ የሌለው አሳዛኝ የ21 አመት ታዳጊ

#3

√ስም፦ #ካሊድ_ኡመር
√የ16 አመት ታዳጊ
√በኩላሊት ህመም የሚሰቃይ ልጃችን..ወንድማችን

በTIKVAH-ETH አተባባሪነት 1የጋራ የባንክ አካውንት እንዲከፍቱ ተደርጓል።

1000278664612 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

💰400,000 ብር (ለማሰባሰብ የታቀደው ገንዘብ)

በትንሹ 40 ሺ አባላት ተሳታፊ እንድትሆኑ እንማፀናለን ፦ 10 ብር * 40,000 የtikvahethiopia አባላት=400,000 ብር

🏷እስካሁን የተገኘው 48,000 ብር

የሞባይል ባንኪንግ ተጠቅችሁ አሁኑኑ ድጋፋችሁን ታደርጉ ዘንድ እንማፀናለን! #TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የችሎትወሬ

/#ሳምራዊት/

አቶ ኢሳያስ ዳኘው በቀረበባቸው ሁለተኛ የክስ መዝገብ ላይ አቃቤ ህግ ሀምሌ 26 ለክስ መቃወምያ ምላሽ አስገብቶ ዛሬ ማለትም ነሀሴ 6 ለብይን ተቀጥሮ የነበረ ቢሆንም አቃቤ ህግ ምላሹን ያስገባው ነሀሴ 3 በመሆኑ ዳኞች በአቃቤ ህግ ችግር ምክንያት መርምረን በቀጠርነው ቀን ብይን መስጠት አልቻልንም ብለዋል፡፡በዚህ መዝገብ የኢትዮ ቴሌኮም የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ አማረ አምሳሉን ጨምሮ 10 ተከሳሾች የተካተቱ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም ላይ 295 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል በሚል ነው አቃቤ ህግ ሀምሌ 2 ክሱን የመሰረተው በመቃወምያው ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia