ኢራን በፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ አሟሟት ላይ ሁለት የምርመራ ውጤቶችን ይፋ አደረገች፡፡
ሄሊኮፕተሯ በወቅቱ በነበረው መጥፎ የአየር ንብረት ሳቢያ በገጠማት አደጋ የዘጠኙ ባለስልጣናት ሕይወታቸው እንዳለፈ የመጀመሪያው የምርመራ ውጤት አመላክቷል፡፡
በተመሳይ መልኩ ባለስልጣናቱ ህይወታቸው ያለፈው ሄሊኮፕተሯ መያዝ ከምትችለው አቅም በላይ በመያዟ መሆኑን ሁለተኛው የምርመራ ውጤት አሳይቷል፡፡
በኢራን ፕሬዝዳንት ራይሲና የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩን ሆሴንን ጨምሮ ዘጠኙ ባለስልጣናት ባለፈው ግንቦት ወር ተሳፍረውባት የነበረችው አሜሪካ ሰራሽ ሄሊኮፕተር በመከስከሷ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡#independent
@thiqahEth

😁30👍12😭11🤔4❤1
"ኢራን አለማቀፋዊ ደህንነት እንዳይኖር የምታደርገው ሙከራ አደገኛና ተቀባይነት የሌለው ነው" - እንግሊዝ
እንግሊዝ በኢራን ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች።
ማዕቀቡ የተጣለው ኢራን ሩሲያ ለዩክሬኑ ጦርነት የምትጠቀምባቸው የባለስቲክ ሚሳኤልና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ በማድረጓ ነው ተብሏል።
የኢራን ብሔራዊ አየር መንገድ እና የጦር መሳሪያውን አጓጉዟል የተባለ በመንግሥት የሚተዳደር የመርከብ ካምፓኒ ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ አግዳለች።
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዴቪድ ላሚ፣ "ኢራን አለማቀፋዊ ደህንነት እንዳይኖር የምታደርገው ሙከራ አደገኛና ተቀባይነት የሌለው ነው" ብለዋል። #independent
@thiqaheth

😡34👍23❤4😁4🔥1🥰1
የዓለም ሀገራት ትናንት ትራምፕና ዘለንስኪ ያደረጉትን ሀይለ ቃል የተሞላበት ውይይት ተከትሎ አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
ፈረንሳይ፦ ፕሬዝዳንት ማክሮን "ወራሪ አለች ሩሲያ፣ ተጎጂ አለች ዩክሬን" በማለት ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል።
"ከሶስት አመት በፊት ዩክሬንን መርዳታችንና ሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላችን ልክ ነበር" ያሉት ፕሬዚዳንቱ ይህ እርምጃ ወደ ፊትም ይቀጥላል ብለዋል።
ዩናይትድ ኪንግደም፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር "መከባበር የተሞላበት ዲፕሎማሲ ለሰላም ወሳኝ ነው። የአውሮፓ መከፋፈል የሚጠቅሙ ሩሲያን ነው" ያሉት ስታርመር የትኛውም የሰላም ስምምነት ዩክሬንን ያሳተፈ ሊሆን እንደሚገባ አብራርተዋል።
ኖርዌ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ስቶሬ፣ "ከነጩ ቤተመንግሥት የተመለከትነው ነገር ልብ የሚሰብር ነው" ብለዋል። ትራምፕ ዘለንስኪን "በሶስተኛው የአለም ጦርነት እየተጫወትክ ነው ያሉት ንግግር ምክንያታዊ አይደለም" በማለት ተችተዋል።
ፖላንድ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ፣ "የተከበሩ ዘለንስኪ፣ የተከበራችሁ የዩክሬን ወዳጆች ብቻችሁን አይደላችሁም" ሲሉ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
ጀርመን፦ አዲሱ ፕሬዝዳንት ሜርዝ፣ "በጥሩውም ሆነ በመጥፎው ጊዜ ከዘለንስኪና ከዩክሬን ህዝብ ጎን እንቆማለን" ብለዋል።
ሩሲያ፦ ምንም እንኳን በመንግሥት በኩል ይፋዊ አስተያየት ባይሰጥም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግን ብዙዎችን ላስቆጣው ውይይት አድናቆት ሰጥተውታል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የሩሲያ ደህንነት ምክርቤት ምክትል ሀላፊ ድሜትሪ ሜድቬዴቭ፣ "ትራምፕ ትክክል ናቸው፤ የኪቭ አገዛዝ በሶስተኛው የአለም ጦርነት እየቀለደ ነው" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። #foxnews#independent#theglobeandthemail
@ThiqahEth

👍40😱3❤1
በዳርፉር ስደተኞች ካምፕ ላይ በደረሰ ጥቃት የ100 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ከሟቾቹ መካከል 20ዎቹ ህፃናት፣ ዘጠኙ የእርዳታ ሰራተኞች መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
ጥቃቱን ያደረሰው ከሱዳን ጦር ጋር የሚፋለመው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሆኑ ተገልጿል።
ላለፉት ሁለት አመታት በዘለቀው የርስበርስ ጦርነት ከ24,000 በላይ ሱዳናውያን መገደላቸውን ተመድ አመላክቷል።
በጄነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ የሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ስለቀረበበት ውንጀላ የሰጠው ግብረመልስ የለም። #independent

😭9👍2🔥1😱1
"ከአሜሪካ ሁሉን አቀፍ የንግድ ጦርነት ተከፍቶብናል" - የአውሮፓ ህብረት ንግድ ኮሚሽን
የአውሮፓ ህብረት የንግድ ኮሚሽን"አውሮፓን ለማዳን አራት ሳምንታት አሉን" ሲል ገለጸ።
የህብረቱ የንግድ ኮሚሽነር ማሮስ ሰቭኮቪች "ከአሜሪካ ሁሉን አቀፍ የንግድ ጦርነት ተከፍቶብናል" ሲሉ ተናግረዋል።
አሜሪካ በአውሮፓ ገበያ ላይ 50% ቀረጥ መጨመሯን ያስታወቁት ሰቭኮቪች "አውሮፓን የምናድንበት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንገናኛለን"ብለዋል።
የትራምፕ አስተዳደር የጣለው ታሪፍ "ምክንያታዊ እና ግልጽነት የጎደለው ነው" ሲሉ ተችተዋል። #independent

👍12🔥3🥰1🤔1
"ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንልካለን" - ትራምፕ ለዩክሬን
ትራምፕ አሜሪካ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ልታደርግ እንደምትችል ጠቆሙ።
"ዩክሬን አሁን በጣም እየተጎዳች ነው" ያሉት ትራምፕ "የመጀመሪያ ዙር ድጋፋችን ሊሆን የሚችለው የመከላከያ መሳሪያዎችን ማጓጓዝ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ትራምፕ "ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንልካለን፣ እሱን ማድረግ አለብን፣ ራሳቸውን (ዩክሬናውያን) መከላከል አለባቸው" ብለዋል።
የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሴን ፓርኔል በበኩላቸው፣ ትራምፕ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ የመላክ እቅድ እንዳላቸው አረጋግጠዋል። #aljazeera #Independent

❤15😡3🙏2🕊1
ቢያንስ 31 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ባንግላዴሽ የሦስት ቀን ሀዘን አወጀች
በባንግላዴሽ በልምምድ ላይ የነበረው የጦር አውሮፕላን ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 31 ሲደርስ፣ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች መጎዳታቸው ተገልጿል።
አደጋው የጦር ኮሌጅ ተማሪዎች የተግባር ልምምድ እያደረጉ በነበረበት ወቅት የቴክኒክ ችግር የተፈጠረ መሆኑን የሀገሪቱ አየር ሀይል አስታውቋል። #independent

😢14😭4❤2🤔2
"ፕሬዚዳንት ፑቲን ለሰላም ዝግጁ ነው" - ክሬሚሊን
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ድሜትሪ ፔስኮቭ ፑቲን ለተኩስ አቁም ድርድር ዝግጁ ናቸው ብለዋል።
"ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሰላም ዝግጁ ነው" ያሉት ፔስኮቭ "ሩሲያ ጥቅሟንና ፍላጎቷን ባስከበረ መልኩ ለመነጋገር ዝግጁ ናት" ሲሉ ተናግረዋል።
የሩሲያ እና የዩክሬን ድርድር በነገው እለት በቱርክ እንደሚካሄድ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ አስታውቀዋል። #independent

❤8🕊5🤔2👏1