THIQAH
13K subscribers
2.63K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
በችካጎ በደረሰ ጥቃት 100 ሰዎች ሲገደሉ 19 ሰዎች በገዳይነት ተጠርጥረው ተያዙ፡፡

የከተማዋ ከንቲባ ብራንደን ጆንሰን "የችካጎን ነፍሶች አጥተናል" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን መሰል የግድያ ተግባር "በቃ ልንለው ይገባል" ነው ያሉት።

ከንቲባው በከተማዋ በጥይት ተኩስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደጨመረ ገልጸው፣ በአሜሪካ እንደ ወረርሽኝ ያስቸገረ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የፌደራሉ መንግስት የጥይት ግድያዎችን እንዲያቆምና የጉዳቱ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች ድጎማ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ #CNN #AFP

@ThiqahEth
😭25👍12🤔21
በቡርኪናፋሶ በደረሰ የሽብር ጥቃት የሟቾች ቁጥር 500 ደረሰ፡፡

ምንም እንኳን የሀገሪቱ መንግስት እስካሁን ድረስ የሟቾችን ቁጥር በይፋ ባይገልጽም፤ በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 500 መድረሱን የዓይን እማኞች መግለጻቸው እየተዘገበ ነው።

ከሟቾች በተጨማሪ 140 ሰዎች መጎዳታቸውን የዓይን እማኞችን ዋቢ አድርገው ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት እሁድ እለት ለደረሰው ጥቃት በአካባቢው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱትን የአልቃይዳና የአይ ኤስ ቡድኖች ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

የተ.መ.ድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቡርኪናፋሶ የደረሰውን የሽብር ጥቃት አውግዘዋል፡፡ #aljazeera #dailypost #cnn

@thiqaheth
👍7😱4😢3
የዩክሬኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ፡፡

ላለፉት አራት አመታት የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ድሜትሪ ኩሌባ፣ የመልቀቂያ ደብዳቢያቸውን ለፓርላማ አፈጉባዔ ማስገባታቸው ተሰምቷል፡፡

ኩሌባ ስልጣን እንዲለቁ የገፋፋቸውን ምክንያት ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ሌሎች ስማቸው ያልተገለጸ ሚኒስትሮችም የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የፓርላማው አፈጉባዔ ሩስላን ስቴፋንቹክ ገልጸዋል፡፡ #trtworld #washingtonpost #cnn

@thiqaheth
👍21😁3
"እስራኤል በ 7 ግንባሮች ጦርነት ገጥሟታል"  - ኒታንያሁ።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኒታንያሁ፣ "ከእነዚህ ሰባት ቡድኖች ጀርባ ኢራን ቁማለች" ሲሉ ወንጅለዋል።

ቢኒያም ኒታንያሁ፣ በሊባኖስ ላይ 9 ሺህ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ገልፀዋል።

ሂዝቦላ በአንፃሩ 1, 500 ጥቃቶችን ፈጽሟል። #cnn #theindependent

@thiqahEth
😢26👍14😁5😭43😱2👌2
"ዶክሜንቱ በምን መልኩ እንደወጣና ማን እንዳወጣው ለህዝብ ግልጽ ይደረጋል" - አሜሪካ

አሜሪካ ሾልኮ በወጣው የእስራኤልን የጥቃት እቅድ በዝርዝር የያዘው ዶክመንት ላይ ምርመራ መጀመሯን አስታወቀች።

እስራኤል የምትፈፅማቸውን ጥቃቶች ዝርዝር የያዘው ሚስጥራዊ መረጃ በትናንትናው ዕለት ከፔንታጎን ሾልኮ ወጥቷል።

ጥብቅ መረጃው እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው እርምጃ የአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ ድጋፍ እንዳለበት ያሳያል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን "ዶክሜንቱ በምን መልኩ እንደወጣና ማን እንዳወጣው ለህዝብ ግልጽ ይደረጋል" ብለዋል። #scrippnews #axios #cnn

@thiqaheth
👍38😁28
ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ሀገር ጥለው ኮበለሉ።

የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ ስሟ ወዳልተጠቀሰ ሀገር ወጥተዋል ተብሏል።

በትናንትናው እለት የፕሬዝዳንቱ ፅ/ቤት በሽር አላሳድ ሀገር ጥለው አልሸሹም ሲል መግለጫ አውጥቶ ነበር።

አማፂያኑ በአሁኑ ወቅት ዋና ከተማዋን ደማስቆን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። #cnn #aninews

@thiqaheth
👍26
የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሶማሊያ ገቡ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሰላም አስከባሪ ኃይሎች ስምሪት ዙሪያ ለመምከር ወደ ሞቃድሾ አቅንተዋል።

ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም ድጋፍ ሰጭ ኃይል (AUSSOM) ውስጥ የሚኖራትን ሚና በተመለከተ ከሶማሊያ አቻቸው ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ለአንድ አመት በዘለቀ ውዝግብ ውስጥ ቢቆዩም አንካራ ላይ ባደረጉት ስምምነት ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማምተዋል። #borkena #cnn #bloomberg

@ThiqahEth
👍132😁2🤔2🔥1
''ቲክቶክን የመግዛት እቅድ የለኝም'' -ኤለን መስክ

የቴስላ እና ስፔስ ኤክስ ባለቤት መስክ በቻይናው የባይት ዳንስ ኩባንያ የሚተዳደረውን የቪዲዮ ማጋሪያ ቲክቶክ ለመግዛት እንደማያስብ አስታውቋል፡፡

መስክ፣ ''ቲክቶክ ቢኖረኝ ምን እንደምሰራበት እቅድ ስሌለለኝ ለጨረታ አልተዘጋጀሁም'' ብለዋል።

አሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት አለው ባለችው የቻይና ኩባንያ ላይ በመላ ሀገሪቱ እንዲዘጋ አልያ ከፊል ድርሻው ለአሜሪካውያን ባለሃብቶች እንዲሸጥ ጠይቃለች፡፡

ከሚሸጥ መዘጋቱን የሚመርጠው የባይትዳንስ ኩባንያ በባይደን ዘመን ተዘግቶ የነበረ ቢምንም፤ ትራምፕ እገዳው ለ75 ቀናት እንዲቆይ ወስነዋል፡፡ #cnn

@thiqahEth
👍9😁2👌1
"ከ30 በላይ እርዳታ ፈላጊዎች በእስራኤል ተገድለዋል" - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር

"የደረሰ ጉዳት የለም፣የእርዳታ ስርጭቱ በሰላም ተጠናቋል" - የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን

የእስራኤል ጦር በራፋህ የእርዳታ ጣቢያ ምግብ በመጠባበቅ ላይ በነበሩ ንፁሃን ላይ ጥቃት ማድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 170 የሚደርሱት መጎዳታቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጋዛ ሰብዓዊ ፋውንዴሽን (GHF) በበኩሉ ደረሰ የተባለውን ጉዳት "በእርዳታ ወቅት ሰዎች በስነስርዓቱ ተከፋፍለው ሂደዋል" በማለት በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ማስተባበያ ሰጥቷል።

የእስራኤል ጦርም በተመሳሳይ "በንፁሃን ላይ የተቃጣ እርምጃ የለም" ሲል የቀረበበትን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል።

አንድ የአይን እማኝ ግን "የእስራኤል ወታደሮች በሺዎች የሚቆጠሩ እርዳታ ጠባቂዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር" በማለት ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ሆስፒታል ላይ በፈፀመችው ጥቃት 54 ሰዎች መገደላቸውንና የኩላሊት መታጠቢያ ማሽንን ሙሉ በሙሉ ማውደሟን ተመድ አስታውቋል።
#cnn #aljazeera

@ThiqahEth
😢21😡43🙏3🕊2😱1
ደቡብ ኮሪያ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እያካሄደች ትገኛለች።

ላለፉት ስድስት ወራት በፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የቆየችው ደቡብ ኮሪያ በዛሬው እለት ሀገራዊ ምርጫ በማካሄድ ላይ ናት።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮዔል በህዳር ወር ባወጁት የወታደራዊ አስተዳደር (martial law) ምክንያት ከስልጣናቸው መነሳታቸው ይታወቃል። 
#cnn

@ThiqahEth
🤔2🕊2
በሎስ አንጀለስ ከ150 በላይ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የስደተኞችን ፍሰት ለመቆጣጠር 2000 ብሄራዊ ዘብ ወደ ሎስ አንጀለስ ልከዋል።

ድርጊቱን የተቃወሙ ስደተኞች ወደ ስፍራው ከተላኩት ፖሊሶች ጋር ግጭት ውስጥ በመግባት መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ተቃዋሚዎቹ የፌዴራል ኢሚግሬሽን ባለስልጣናትን ስም እየጠሩ ትችት ያዘለ መልዕክት ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል።

ፖሊስ በተቃዋሚዎች ላይ ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተገልጿል።
#cnn

@ThiqahEth
👏1912😱4😢2
"በናንታዝ እና ኢስፋሃን የሚገኙ የኑክሌር ጣቢዎች ወድመዋል" - የእስራኤል ጦር

እስራኤል ሦስት ቁልፍ የተባሉ የኢራን የኑክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ማድረሷ ተነግሯል።

የእስራኤል ጦር ማምሻውን በፈጸመው ሦስተኛ ዙር ጥቃት (IDF)፣ "በናንታዝ እና ኢስፋሃን የሚገኙ የኑክሌር ጣቢዎች ወድመዋል" ብሏል።

ኢራን እነዚህ ጣቢያዎች ካሁን በፊት በተፈጸሙ ጥቃቶች ከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጻ ነበር።
#cnn

@ThiqahEth
👏195🤔4🕊2
ትራምፕ የቡድን 7 አባል ሀገራት ስለኢራን ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ አልፈርምም አሉ።

አባል ሀገራቱ በመግለጫቸው እስራኤል እና ኢራን የገቡበትን ጦርነት እንዲያረግቡ ጠይቀዋል።

በተዘጋጀው ዶክመንት ላይ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ስም አለመስፈሩን በስብሰባው የታደሙ የዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል።  

ፕሬዝዳንቱ በካናዳ እየተካሄደ የሚገኘው የቡድን 7 ስብሰባ ሳይጠናቀቅ ወጥተው ሂደዋል ተብሏል።
#cnn

@ThiqahEth
14🤔7😡4👏2🕊1😭1