Ethio telecom
319K subscribers
7.23K photos
124 videos
129 files
2.47K links
A Leading Digital Solutions Provider
Provide Reliable Communications & Digital Financial Services to Simplify Life and Accelerate Digital Transformation of Ethiopia.

Pioneer – Serving Since 1894 Beyond Connectivity

https://t.iss.one/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
ኩባንያችን በዛሬው ዕለት የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ለመተግበር የሚያስችል ስምምነት ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ!

ስምምነቱ የክላውድ አገልግሎት፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ ባለ ከፍተኛ አቅም የፋይበር መስመር እና ተያያዥ የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባት እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት፣ ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችን ያዘምናል።

የስማርት ሲቲ ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን በዲጂታል ሶሉሽኖች ቴክኖሎጂ በማስታጠቅ እንዲሁም ክፍያዎችን በቴሌብር ለመፈጸም በማስቻል አሰራርን በእጅጉ ከማዘመን ባሻገር የከተማዋን ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ያስችላል፡፡

ስምምነቱ የተገልጋዮችን ጊዜ፣ ገንዘብ እና እንግልት በመቀነስ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማገዝ ህይወታቸውን ለማቅለል እና የአኗኗር ዘይቤያቸውን ለመቀየር ያስችላል፡፡

ፕሮጀክቱ ከተማዋን ለኢንቨስትመንት መዳረሻነት ምቹና ተመራጭ በማድረግ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፤ የሥራ ፈጠራን በማበረታታት እና የቢዝነስ እንቅስቃሴን በማሳለጥ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትንም በእጅጉ ያሻሽላል፡፡

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#Smartcity #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #GSMA #ITU
👍23345😡16🙏14🥰6😁6🤪1
ኢትዮ ቴሌኮም እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮ ቴሌኮምን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውጥኖች በገንዘብ በመደገፍ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ የበለጠ የሚያሳድግ እና የአፍሪካን ሰፊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያሰፋ ስትራቴጂያዊ ውይይት ጀመሩ።


📡 #DigitalEthiopia #DigitalEconomy #AfDB #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #Innovation #SustainableGrowth @AfDB_Group
👍7824🎉12😢1🤩1
በኦሬንጅ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ቢዝነስ ግሩፕ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ብሬሎት ባ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በቴሌብር የዲጂታል ፋይናንሻል አገልግሎት ዕድገት እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ረገድ ያሉትን ተሞክሮዎች ለመቅሰም የሚያስችል ጉብኝት በኢትዮ ቴሌኮም አደረገ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ ከፍተኛ ልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፣ በተለይም የኩባንያውን ፈጣን የለውጥ ጉዞ፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ዕይታ እንዲሁም ከመደበኛው ኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ ግለሰቦችን፣ የግል ቢዝነስ ድርጅቶችን እና የመንግስት ተቋማትን አቅም በመገንባት የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማፋጠን ላይ ያለውን ከፍተኛ ሚና ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኤክስፒሪያንስ ማዕከላችን ጉብኝት ያደረገ ሲሆን፣ በጉብኝቱም ወቅት ከግብርና፣ ከትምህርት፣ ከጤና አጠባበቅ፣ ከማዕድን እና ከስማርት ቱሪዝም ጋር ስለተያያዙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላትም እነዚህ ሶሉሽኖች ጠንካራ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየተደረገ ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ ስለመሆኑ ያላቸውን አድናቆት የገለጹ ሲሆን፣ ኩባንያው ቴሌብርን እና ዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለማሳደግ እያደረገ የሚገኘው ጥረት በመላ አፍሪካ የዲጂታል ፈጠራ ፋናወጊ ለመሆን ያለውን አቅም ያሳያል ብለዋል፡፡

#RealizingDigitalEthiopia @orangeafrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍9615💔7🎉6🥰5👏4😁3
በጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ኩባንያችን በማህበራዊ ኃላፊነት ረገድ በድምሩ ከ287.17 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአረንጓዴ ልማትና ማስዋብ እንዲሁም ለሀገራዊ ፕሮጀክቶች የተደረገ ሲሆን፣ በዓይነት 131.3 ሚሊዮን ብር፣ በገንዘብ ደግሞ ከ155.9 ሚሊዮን ብር በላይ ነው።

የኩባንያችን ሰራተኞች፣ አጋር አካላት እና የአካባቢ ማህበረሰብ ክፍሎችን በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች በንቃት በማሳተፍ፣ በበጀት አመቱ አጋማሽ በ105 ቦታዎች ከ446,000 በላይ ችግኞችን ለመትከል ተችሏል፡፡

የኩባንያችን ሰራተኞች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር፣ ደም በመለገስ እና የተለያዩ አይነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት በማህበራዊ ኃላፊነት አርአያ የሚሆን ተግባር አከናውነዋል።

ለተጨማሪ https://bit.ly/40RlnYV ይጫኑ

#CSR #Ethiotelecom #telebirr #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍10821🥰8😢5🤣5
በስማርት ስልክ የሚሰራ የፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ ሶሉሽን ለድርጅት ደንበኞች በይፋ አስጀምረናል!

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት ድርጅቶችና ተቋማት የግንኙነት ስርዓታቸውን በእጅጉ ለማዘመን የሚችሉበት ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ (PTT/PTV) የተሰኘ የቡድን ኮሙኒኬሽን ሶሉሽን ይፋ አድርጓል።

ይህ በክላውድ ላይ የተመሰረተ የኮሙኒኬሽን ሶሉሽን በማንኛውም ስማርት ስልክ እና የሞባይል ኔትወርክ ባለበት ቦታ ሁሉ የሚሰራ መሆኑ እንዲሁም ከድምጽ ባሻገር የጽሑፍ፣ ምስል እና ቪዲዮ መለዋወጥ ማስቻሉ ከቀድሞው የፑሽ-ቱ-ቶክ ሬዲዮ አገልግሎት የላቀ ያደርገዋል፡፡

ሶሉሽኑ እንደ ሎጅስቲክስ፣ ደህንነት፣ በግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ መስተንግዶ እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ባሉ ዘርፎች የተሰማሩ ድርጅቶች የቡድን ቅንጅትን እና ደህንነትን ለማሳደግ ቅልጥፍናቸው እና ምላሽ ሰጪነታቸው ፈጣን ያደርጋል።

አገልግሎቱ ድርጅቶች ግንኙነታቸውን እንዲያቀላጥፉ፣ ስራቸውን እንዲያሳልጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከየትኛውም ቦታ ሆነው እንዲገናኙ የሚያስችል የቡድን መገናኛ መፍትሔ ይዞ ቀርቧል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍56👏3614🥰4😁4
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምስራቅ የተሰኘ አዲስ ሪጅን በማቋቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን፣ የባሌ ዞን አስተዳደር፣ የባሌ ሮቤ ከተማ መስተዳደር ኃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት አስመረቀ!

የደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት መቀመጫውን ባሌ ሮቤ ከተማ ያደረገ ሲሆን 3 የአስተዳደር ዞኖችን (ባሌ ዞን፣ ምስራቅ ባሌ ዞን እና ምዕራብ አርሲ ዞን በከፊል)፣ 29 ወረዳዎችን፣ 38 ከተሞችን እና 471 የገጠር ቀበሌዎችን ያካትታል፡፡

ቀደም ሲል የደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት መቀመጫነቱን አዳማ በማድረግ ለበርካታ አካባቢዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረ ሲሆን በተለይም በቅርቡ አዳዲስ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ሞባይል ጣቢያዎችን ገንብተን ስራ ማስጀመራችን ለተጨማሪ ሪጅን መቋቋም አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

ይህም ደንበኞችን በቅርበት ለማገልገል ከማስቻል ባሻገር፣ ከዜጎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ውሳኔዎችን በመስጠት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡ እንዲሁም ከአጋሮች ጋር በቅርበት በመስራት የማህበረሰቡን ህይወት በሚያሻሽሉ የዲጂታል መፍትሄዎች አማካይነት አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3G2T17e

#5G #BaleRobe #Assela #RealizingDigitalEthiopia #Ethiotelecom #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries
👍5211❤‍🔥2
በካሜሩን ቴሌኮሙኒኬሽን (ካምቴል) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጁዲት ያህ ሰንደይ የተመራ የልዑካን ቡድን፣ በዲጂታል ፋይናንሻል አገልግሎት እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ረገድ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም የሚያስችል ጉብኝት በኢትዮ ቴሌኮም አደረገ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮምን ፈጣን የለውጥ ጉዞ፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እንዲሁም ከመደበኛ ኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር በዲጂታል ሶሉሽኖችን የዜጎች፣ ቢዝነስ እና ተቋማትን አቅም በመገንባት የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማፋጠን ላይ ያለውን ቁልፍ ሚና ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኤክስፒሪያንስ ማዕከላችንና ዳታ ሴንተር ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ በጉብኝቱም ወቅት ከግብርና፣ ከትምህርት፣ ከጤና አጠባበቅ፣ ከማዕድን እና ከስማርት ቱሪዝም ጋር ስለተያያዙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላትም ሶሉሽኖቹ ጠንካራ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየተከናወነ ስለሚገኘው ቁርጠኛ ሥራ ማሳያ ስለመሆናቸው እንዲሁም በኩባንያችን ደንበኞች ቁጥር እድገት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡

የካምቴል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኩባንያው ቴሌብርን እና ዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለማሳደግ እያደረገ የሚገኘው ጥረት በመላ አፍሪካ የዲጂታል ፈጠራ ፋናወጊ ለመሆን ያለውን አቅም ያሳያል ብለዋል፡፡

#DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #Camatel #GSMA #ITU #Ethiotelecom #telebirr
👍89😡109😁4🥰2
ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማስፋት ያለመ ስትራቴጂያዊ ምክክር አደረጉ!

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና የሲንቄ ባንክ ፕሬዚዳንት ነዋይ መገርሳ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚያቀርቡትን አካታችነትን እና ተደራሽነትን የሚያረጋግጡ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማስፋት ያለመ ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ኢትዮ ቴሌኮም ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በአጋርነት ዜጎች የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ በማድረግ አካታች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ቀጣይነት ላለው ሀገራዊ እድገት የበኩሉን ሚና በመጫወት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ከሲንቄ ባንክ ጋር በአጋርነት በማህበረሰባችን ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያፋጥኑ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል፡፡

የሲንቄ ባንክ ፕሬዚደንት ነዋይ በበኩላቸው ባንካቸው በአጭር ጊዜ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማድረግ ፈጣን ለውጥ በማስመዝገብ ላይ መሆኑን በመግለጽ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር አጋርነት ማጠናከር የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት በፍጥነት ለማረጋገጥ አስቻይ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኢትዮ ቴሌኮም ከቅርብ አመታት ወዲህ በተለይም በዲጂታል ፋይናንስ ስነ-ምህዳሩ ላይ እያደረገ ያለው ፈጣን ለውጥ በማድነቅ ለዚህም አመራሩ ለባንካቸው መልካም አርአያና መበረታቻ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #SmartAfrica #GSMA #ITU #Ethiotelecom #Siinqee #telebirr
👍8215😁10🥴8
ኩባንያችን የዲጂታል አካታችነትን ለማረጋገጥ 2 ሚሊየን ስማርት ስልኮችን በረጅም ጊዜ ክፍያ ሊያቀርብ ነው!

ኩባንያችን የስማርት ስልክ ስርጸትን በማሳደግና የዲጂታል ክህሎት እድገትን በማገዝ አካታችነትን ለማረጋገጥ፣ በዓመት 2 ሚሊየን ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ በረጅም ጊዜ ክፍያ ለዜጎች ለማቅረብ አቅዷል።

ከዚህም ውስጥ፣ ኩባንያችን ከሲንቄ ባንክ ጋር በአጋርነት በዓመት በ4 ቢሊየን ብር በጀት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና በገጠር ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የስማርት ስልኮችን በረጅም ጊዜ ክፍያ ማቅረብን ያካትታል።

ኩባንያችን በቀጣይም የዲጂታልና የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እና ዜጎች በዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርጉ ተመሳሳይ ጥረቶችን ከሌሎች አጋሮች ጋር መተግበሩን ይቀጥላል፡፡

ኩባንያችን ከሲንቄ ባንክ ጋር በድምሩ 15 ቢሊየን የብር መጠን ያለው የሞባይል ፋይናንሺያል እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶችን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

#RealizingDigitalEthiopia #Ethiotelecom #telebirr #Siinqee #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍9022😁4🥴3👏2🤩2
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!!

ኢትዮ ቴሌኮም ዘመን ገበያ የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ገበያ በይፋ አስጀመረ!

ኩባንያችን የሀገራችንን የግብይት ሥርዓት በማዘመን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል፣ አካታች፣ ምርት እና አገልግሎት አቅራቢዎችን ከሸማቾች የሚያገናኝ ዘመን ገበያ የተሰኘ የዲጂታል ገበያ በይፋ ማስጀመሩን ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ይህ የዲጂታል ገበያ ለሀገራችን አዲስ ምዕራፍ የምናበስርበት፣ ፈጠራ እና ሁሉን አቀፍ ዕድገትን ለሁሉም ዜጎች ለማድረስ መሰረት የሚጥል ሲሆን፣ ይህም አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ከሸማቾች ጋር በቀላሉ ለማገናኘት፣ ለማብቃት እና አዳዲስ የገበያ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ነው።

በተለይም ለሀገራችን ለዲጂታልና ፋይናንስ አካታችነት፣ ሰፊ የገበያ ተደራሽነት፣ ምርታማነት፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) እድገትና የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የንግድ ዕድሎችን ለማመቻቸት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት ለማረጋገጥ የላቀ ሚና ይኖረዋል፡፡

ዘመን ገበያ ለነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ ዕደ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እና ለንግድ ድርጅቶች በርካታ እድሎችን የሚፈጥር ሲሆን፣ ለደንበኞች በቴሌብር ሱፐርአፕ ውስጥ በሚገኝ ሚኒአፕ አማካኝነት ቀርቧል፡፡

በቀጣይም ከዘመን ገበያ ጋር በአጋርነት በመስራት የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ወደፊት በማራመድ ጉዞ ውስጥ የበኩላቸውን ለማበርከት ለሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች እና የሎጂስቲክ አገልግሎት ሰጭዎች ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3Z3mTHa

#Ethiotelecom #ZemenGebeya #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU
👍17521👏12🤗6😁5🥰3😡1
እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮ ቴሌኮም በ15ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ምርጥ ብራንዶች ሽልማት መርሃ ግብር "Most Admired Ethiopian Brand in Telecommunications" (በቴሌኮም ዘርፍ እጅግ ተወዳጅ የኢትዮጵያ ብራንድ) የተሰኘ ዕውቅና ማግኘቱን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ለዚህም መላውን ደንበኞቻችን፣ የኩባንያችንን ቤተሰቦች እና አጋሮቻችን ለአብሮነታችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እያቀረብን በቀጣይም ከኮኔክቲቪቲ ባሻገር የዲጂታል መፍትሄዎች ተደራሽ የማድረግ ጥረታችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እንገልጻለን።

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/4juP1KR

#Ethiotelecom #BrandAfrica #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries
39🤣15👍13🤪4
እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን!

ኢትዮ ቴሌኮም በ15ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ምርጥ ብራንዶች ሽልማት መርሃ ግብር "Most Admired Ethiopian Brand Doing Good for Society and the Environment" (ለማህበረሰቡ እና ለአካባቢ ጥበቃ በጎ አስተዋጽኦ በማድረግ እጅግ ተወዳጅ የኢትዮጵያ ብራንድ) የተሰኘ ዕውቅና ማግኘቱን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ለዚህም መላውን ደንበኞቻችን፣ አጋሮቻችንና የኩባንያችንን ቤተሰቦች ለአብሮነታችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እያቀረብን በቀጣይም የኮኔክቲቪቲ እና የዲጂታል መፍትሄዎች ከማቅረብ ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት ለማህበረሰባችን ዘላቂ እድገት እና ለአካባቢ ጥበቃ ያለንን ቁርጠኝነት አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እንገልጻለን።

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/4juP1KR

#Ethiotelecom #BrandAfrica #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries
👍5741🤣29😁7🤪4😡4👏3🥰1
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

ኩባንያችን በላቀ የታዳሽ ኃይል አጠቃቀም፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መሙያ ጣቢያዎችን በማስፋፋት፣ ያገለገሉ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በአግባቡ በማስወገድ እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ከኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን እውቅና በማግኘቱ ታላቅ ደስታ ይሰማናል!

እውቅናው የተሰጠን ባለሥልጣኑ የአለም የአካባቢ ቀንን አስመልክቶ “ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ የብክለት ቅነሳ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው።

የማህበራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት የአካባቢ ብክለትን በመከላከልና ለማህበረሰባችን ንጹህ እና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን በመፍጠር ለዘላቂ እድገት ያለንን ቁርጠኝነት አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እንገልጻለን።

ይህ ስኬት የደንበኞቻችን፣ የአጋሮቻችን እና የሰራተኞቻችን የጋራ ጥረት ውጤት በመሆኑ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለን፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries
103👍22🥰4😁4🏆4🤩2🤝1
ኩባንያችን የፕላቲንየም ስፖንሰር የሆነበት፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀው 18ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በታላቅ ድምቀት ተከናወነ።
            
የኩባንያችን ድጋፍ የሀገራችንን ስም በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያስጠሩ አዳዲስና ተተኪ አትሌቶችን የማፍራት ሀገራዊ ራዕይን እውን ለማድረግ ያለመ ነው።

በቀጣይም ለሀገራችን አትሌቲክስ እድገት የምናደርገውን ትርጉም ያለው ድጋፍ አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እንገልጻለን።

#Ethiopia #Athletics #Marathon
#DigitalEthiopia #GSMA
57👍28👏8
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው 20ኛው መሠረተ ልማት ‘ስለ ኢትዮጵያ’ መድረክ ላይ ገለጻ አቅርበዋል።

መድረኩ በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ጫልቱ ሳኒ የተመራ ሲሆን የመግቢያ ቁልፍ መልዕክት በማቅረብ ተወያዮች የመነሻ ሀሳብ እንዲያቀርቡ በመጋበዝ ውይይቱን አስጀምረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን መሠረተ ልማት የጋራ ብሔራዊ ሀብት እንደመሆኑ ባለድርሻዎች በጋራ ለመወያየት መቻላቸው አስደሳች ስሜት የሚፈጥር መሆኑን በማንሳት በቅንጅት የመሥራት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኩባንያችን የቴሌኮም እና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በማዘመን እና ተደራሽ በማድረግ ያከናወናቸውን ተግባራት እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ የአስቻይነት ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የ4ጂ፣ 5ጂ፣ ፋይበር፣ የዳታ ማዕከል እና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ዜጎችን የዲጂታል ሶሉሽን እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።

በተፈጠረው  የዲጂታል መሠረተ ልማት አቅም ተቋማትን በማዘመን፣ ቅልጥፍናን፣ ምርታማነትንና ጥራትን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለመጨመር መቻሉንም አክለዋል።

በመድረኩ በትራንስፖርት መሠረተ ልማት፣  በኃይል ፍላጎት ዕድገት እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት ተደራሽነት ላይ በሚመለከታቸው ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ ተደርጓል።

ክብርት ሚኒስትር መድረኩን ሲያጠቃልሉ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተመዘገበውን የላቀ ውጤት በማድነቅ በተለይም የቴሌብር ፈጣን እድገት እንደ ሀገር የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል።

#Ethiotelecom #DigitalEthiopia #GSMA #ITU #HOPR #HoF
45👍14👏5
ኩባንያችን ከኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ጋር የተቀናጀ የግብርና እሴት ሰንሰለት ዳታ ሶሉሽን ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት አደረገ!

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት ከኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ጋር የግብርና እሴት ሰንሰለትን የሚያዘምን በቴሌ ክላውድ የዲጂታል መሠረተ ልማት አማካኝነት ግዙፍ ሁለገብ የዳታ ማዕከል ሶሉሽን (Agriculture Value Chain Big Data Platform Solution) ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት አድርጓል፡፡

ሶሉሽኑ፣ ኩባንያችን በመላ ሀገሪቱ በዘረጋው የዲጂታል ኔትወርክ መሠረተ ልማት በመጠቀም ከአይ.ኦ.ቲ (IoT)፣ ሳተላይት፣ ሪሞት ሴንሲንግ፣ ድሮን እና ከባለሙያዎች የሚገኙ መረጃዎችን ወደ ዳታ ማዕከላችን በማስተላለፍ የዘርፉን የእሴት ሰንሰለት ለማስተሳሰር ያስችላል፡፡

ይህ ማዕከል ከግብዓት አቅራቢዎችና ከአርሶ አደሮች ጀምሮ በግብርናው ሂደት ውስጥ ያሉ የተለያዩ ተዋናዮችን በዲጂታል በማገናኘት ለመረጃ ትንተና ያገለግላል፡፡

ስምምነቱ በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን፣ ቅልጥፍናን፣ ጥራትን፣ ትርፋማነትንና የገበያ ትስስርን በማሳደግ የዘርፉን የእሴት ሰንሰለት በዘላቂነት ለማዘመን ጉልህ ሚና ይኖረዋል፤ በመጀመሪያው ምዕራፍም በተመረጡ ዞኖችና ወረዳዎች ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/3HJ6lOT

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU
46👍17🥰1
ኩባንያችን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ሲያከናውን የነበረው የ"ስማርት ኮርት" ፕሮጀክት ለአገልግሎት በመብቃቱ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልጻለን!

ኩባንያችን ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ በስኬት በማጠናቀቁ በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ እውቅና የተበረከተለት ሲሆን ለዚህም ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር የክልሉን ፍርድ ቤቶች በአስተማማኝ ዲጂታል መፍትሔዎች በማስተሳሰር ዜጎች ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ዘመናዊ የፍትሕ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል እንግልት ይቀንሳል።

ክልሉ ለጣለብን እምነት በድጋሚ እያመሰገንን በቀጣይም አገልግሎቱን በቀበሌዎችና ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ ለተያዘው እቅድ ስኬት በጋራ የምንሰራ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለፕሮጀክቱ ስኬት ቁልፍ ሚና ለተጫወቱት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለኩባንያችን ቤተሰቦች ምስጋና እናቀርባለን።

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የማዘመን ቁልፍ ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ኩባንያችን ይህን ፕሮጀክት ለማከናወን በባህር ዳር ከተማ ጥር/2017 ዓ.ም ስምምነት ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር ፈጽሞ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

#Smartcourt #ANRSSupremeCourt #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
52👍31😢2🤩2🥰1
በ2017 በጀት ዓመት ኩባንያችን ከዘላቂ ልማት አንጻር የህብረተሰቡን ሁሉን አቀፍ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ሊያሻሽሉ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ የማኅበረሰብ ተኮር ተግባራትን አከናውኗል፡፡

በትምህርት፣ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማት፣ ሰብአዊ ተግባራት እና የመንግስት ልማት ፕሮጀክቶች በዓይነት እንዲሁም በገንዘብ በድምሩ 450.23 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በተለይም በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የበኩሉን ሚና በመጫወት፣ በ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በ105 ጣቢያዎች ከ446 ሺ በላይ ችግኞች በመትከል ማህበራዊ ሃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡

የበጎ ፈቃድ ተሳትፎም የኩባንያችን እሴት አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ ሰራተኞቻችን በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብና የዓይነት ልገሳ አድርገዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3VWyKnZ

#SustainableDevelopment #CSR #Ethiotelecom #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
73👍23🥴4😁3😢2