ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምስራቅ የተሰኘ አዲስ ሪጅን በማቋቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን፣ የባሌ ዞን አስተዳደር፣ የባሌ ሮቤ ከተማ መስተዳደር ኃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት አስመረቀ!
የደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት መቀመጫውን ባሌ ሮቤ ከተማ ያደረገ ሲሆን 3 የአስተዳደር ዞኖችን (ባሌ ዞን፣ ምስራቅ ባሌ ዞን እና ምዕራብ አርሲ ዞን በከፊል)፣ 29 ወረዳዎችን፣ 38 ከተሞችን እና 471 የገጠር ቀበሌዎችን ያካትታል፡፡
ቀደም ሲል የደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት መቀመጫነቱን አዳማ በማድረግ ለበርካታ አካባቢዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረ ሲሆን በተለይም በቅርቡ አዳዲስ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ሞባይል ጣቢያዎችን ገንብተን ስራ ማስጀመራችን ለተጨማሪ ሪጅን መቋቋም አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡
ይህም ደንበኞችን በቅርበት ለማገልገል ከማስቻል ባሻገር፣ ከዜጎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ውሳኔዎችን በመስጠት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡ እንዲሁም ከአጋሮች ጋር በቅርበት በመስራት የማህበረሰቡን ህይወት በሚያሻሽሉ የዲጂታል መፍትሄዎች አማካይነት አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡ https://bit.ly/3G2T17e
#5G #BaleRobe #Assela #RealizingDigitalEthiopia #Ethiotelecom #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries

👍52❤11❤🔥2
ኢትዮ ቴሌኮም 114 ተጨማሪ ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ተጠቃሚ አደረገ!
ኢትዮ ቴሌኮም በባሌ ዞን፣ አርሲ ዞን፣ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ምዕራብ አርሲ ዞን እና ምስራቅ ሸዋ ዞን በሚገኙ 114 ከተሞችን የላቀ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን!
ኩባንያችን ሲያከናውን የነበረውን መጠነ ሰፊ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በደቡብ ምስራቅ ሪጂን 58 እንዲሁም በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን 56 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አድርጓል።
ይህን ያበሰረው በትላንትናው ዕለት የባሌ ሮቤና የአርሲ ከተሞች የ5ጂ ኔትወርክ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡ በዚህም ወቅት የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ የላቀ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነትን እውን በማድረግ አዳዲስ ዕድሎችን በመክፈት ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተብራርቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የኢንተርኔት ፍጥነት በመላ ሀገራችን በማስፋፋት አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ የበኩሉን ሚና መጫወቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ!
የከተሞቹን ዝርዝር ይመልከቱ፡ https://bit.ly/4lmShKp
#RealizingDigitalEthiopia #4GLTEAdvanced #BaleRobe #Assela

👍66❤11🎉4🤔3❤🔥2🍾2💯1