Ethio telecom
319K subscribers
7.24K photos
124 videos
129 files
2.47K links
A Leading Digital Solutions Provider
Provide Reliable Communications & Digital Financial Services to Simplify Life and Accelerate Digital Transformation of Ethiopia.

Pioneer – Serving Since 1894 Beyond Connectivity

https://t.iss.one/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

በአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የቴሌኮም ኦፕሬተር የሆነውና ታላቋን ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ለ130 ዓመታት በኩራት ሲያገለግል የቆየው የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ በዛሬው ዕለት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በይፋ መጀመሩን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው!

በዚህ መሰረት 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለኢትዮጵያውን ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በቴሌብር ሱፐርአፕ ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን የአክሲዮን ሽያጩ ሰፊውን ማህበረሰብ ያካተተ እንዲሆን አነስተኛውን የሼር ዋጋ መጠን 9,900 ብር (33 አክስዮኖች) በማድረግ ከፍተኛውን የአክስዮን መጠን ደግሞ 999,900 ብር ወይም (3,333 አክስዮኖች) ተደርጓል፡፡

በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነገዋ ሀገራችን ልዩ የኢንቨስትመንት እድል ተጠቅመው በአገሪቱ ካሉት ግዙፍ ተቋማት መካከል የአንጋፋው ኩባንያ ባለአክሲዮን እንዲሆኑ እና የኢትዮ ቴሌኮምን ቀጣይ እድገት እንዲደግፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

እባክዎ የደንበኛ ሳቢ መግለጫውን (Prospectus) https://teleshares.ethiotelecom.et/ ያንብቡ፡፡

የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይከናወናል!

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/3zRQnyy

#Ethiotelecom #teleshares #telebirr #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍23260😁20😡11🤣7🤔5🍾5🤪5👏3🥴2
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!

ዋና ስራ አስፈፃሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የ ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሚ የተመረጡ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/3YebzqB

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍23153😡24👏19😁15🎉10🤩5🥰3😢3💔2🤪2
ዓለም አቀፉ የሞባይል ኮሙኒኬሽን ሲስተም ማኅበር (ጂ.ኤስ.ኤም.ኤ) ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማፋጠን ረገድ የባለድርሻ አካላት ሚና” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የሀገራችን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን የጋራ ርብርብ እንደሚፈልግ ገለጹ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን አክለውም መንግስት፣ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የይዘት ፈጣሪዎች፣ ሶፍትዌር አልሚዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ እና ሚዲያዎች በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መፋጠን ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ አብራርተዋል፡፡

አከለውም መንግስት ትራንስፎርሜሽኑን የሚያግዙ የሕግ ማዕቀፎችን፣ ፖሊሲዎችን እና ደንቦችን በማዘጋጀት ቁልፍ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅበት በመግለጽ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች መሠረተ ልማት በመገንባት እና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የዲጂታል አካታችነት እና ተደራሽነትን በማረጋገጥ የበኩላቸውን ቁልፍ ሚና መጫወት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

በመጨረሻም ዋና ስራ አስፈፃሚያችን የሀገራችን ዲጂታል ጉዞ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን በመግለጽ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ ስኬታማ እንዲሆን ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና በጋራ ለመስራት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#GSMA #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍9823
ኩባንያችን የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የሆነው የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎት በሀዋሳ ከተማ በይፋ ማስጀመሩን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል!

የ5ጂ ኔትወርክ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዳታ ፍላጎት ለማርካት ከማስቻሉ ባሻገር የደንበኞች ተሞክሮን የሚያሳድጉ አዳዲስ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ የዜጎችን ህይወት ለማዘመን እና ቢዝነስን ለማቀላጠፍ እንዲሁም የሥራ እድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የ5ጂ አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነት ያለው፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን በእጅጉ በመቀነስ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎችን ከማዘመን በተጨማሪ ለሀገራችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ እንደ ግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት ያሉ ዘርፎችን አሰራር በማቀላጠፍ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፡፡

ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ አገልግሎትን ለማግኘት የሚያስችሉ ቀፎዎች በመጠቀም በፈጣኑ ኔትወርክ አስደሳች ተሞክሮ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡

ቀደም ሲል የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ጂግጂጋ፣ ድሬደዋ፣ ሀረር እና ባህር ዳር ከተሞች ማስጀመራችን ይታወሳል፡፡

አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_እውን_በማድረግ_ላይ

ለተጨማሪ: https://bit.ly/4hukXis

#Hawassa #5G #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍9528🤣6🎉2🥴2💔2
ኢትዮ ቴሌኮም በወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና እና አርባ ምንጭ ከተሞች የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የሆነውን 5ኛ ትውልድ (5ጂ) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በይፋ ያስጀመረ መሆኑን በታላቅ ደስታ ያበስራል፡፡

የ5ጂ ኔትወርክ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የደንበኞች ዳታ ፍላጎት ከማርካት ባሻገር ተሞክሮን የሚያሳድጉ አዳዲስ የዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ የዜጎችን ህይወት ለማዘመን እና ቢዝነስን በማቀላጠፍ እንዲሁም የሥራ እድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

5ጂ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን በእጅጉ የሚቀንስ በመሆኑ የማምረቻ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎችን አሰራር ዲጂታላይዝ በማድረግ ምርታማነትን ለመጨመር ከማስቻሉ ባሻገር ለሀገራችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ እንደ ግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት ያሉ ዘርፎችን በማዘመን አለም አቀፍ ተወዳደሪነትን ያሳድጋል፡፡

ክቡራን ደንበኞቻችን የ5ጂ አገልግሎትን ማግኘት በሚያስችሉ ቀፎዎች እና መሳሪያዎች አማካይነት አለም የደረሰበት ፈጣን ኔትወርክ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን፡፡

አዲስ ፍጥነት፣ አዲስ ምቾት፣ አዲስ አኗኗር!

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

ለተጨማሪ: https://bit.ly/4fspKPN

#5G #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍10626😢8😁5🤣4🥰2
እነሆ #5G በሆሳዕና!

የሆሳዕና ከተማን የ5ጂ ሞባይል አገልግሎት ጅማሮ በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች ለነዋሪዎች አብስረናል!

የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጅማሮ ለማብሰር ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ ኃላፊዎች የተገኙበት እንዲሁም በከተማዋ ህዝብ አብሮነት የደመቀ የመንገድ ላይ ትርኢት እና ተያያዥ መርሐ ግብሮች አከናውነናል፡፡

የሆሳዕና ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እና ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#5G_ለሆሳዕና
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #Hosaena #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍8023🥰2👌2🆒2😁1
እነሆ #5G በወላይታ ሶዶ!

በወላይታ ሶዶ የ5ጂ ሞባይል አገልግሎት ጅማሮ በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች አብስረናል!

የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ (5G) አገልግሎት መጀመር በወላይታ ሶዶ ማብሰራችንን ተከትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የታደሙበት፣ በከተማዋ ህዝብ አብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ ጅማሮ ማብሰሪያ የመንገድ ላይ ትርኢት መርሐ ግብሮችን አከናውነናል፡፡

#ወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እንዲሁም ለነበረን ስኬታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!

#5ጂ_በወላይታ_ሶዶ
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #Wolaita #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍7611👀4👌3
#5G በአርባ ምንጭ!

እነሆ በ #አርባ_ምንጭ ከተማ የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ጅማሮን በተለያዩ ደማቅ መርሐ ግብሮች አብስረናል!

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን እና የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በታደሙበት መርሐ ግብር የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #አርባ_ምንጭ መጀመሩን ማብሰራችንን በማስከተል ከአርባ ምንጭ ከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በአብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ 5G መንገድ ላይ ትርኢት መርሐ ግብር አከናውነናል፡፡

#አርባ_ምንጭ ከተማ ህዝብ እና በየደረጃው ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ላደረጉልን ሞቅ ያለ አቀባበል እንዲሁም ለነበረን ውጤታማ ቆይታ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#5G #አርባ_ምንጭ

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #ArbaMInch #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍8115👌6😁2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ ልኡክ የአርባ ምንጭ ከተማን ስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ለመተግበር እንዲሁም መሰረተ ልማት በቅንጅት ለማከናወን የሚያስችል ውይይት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ፣ ከከተማዋ አስተዳዳር ከንቲባ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር አድርጓል።

#SmartCity #ArbaMinch #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍7518😡5🥰4🤣4
የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን በማስመልከት የተለያዩ ደማቅ የመንገድ ላይ መርሐ ግብሮች አከናውነናል!

የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን ማብሰራችንን በማስከተል ከከተማዋ ነዋሪዎች እና ደንበኞቻችን ጋር በአብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ መንገድ ላይ ትርኢት እና የኮንሰርት መርሐ ግብሮች ተካሄደዋል፡፡

#ቢሾፍቱ ከተማ ሕዝብ፣ የከተማ መስተዳድር እና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች የ5ጂ መርሐ ግብራችን ደማቅ እና ስኬታማ እንዲሆን ስላደረገላችሁልን ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

#5G #ቢሾፍቱ

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #Bishoftu #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍9317🤪5😁3👏2🤣1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዘመናችን የመጨረሻው እና እጅግ ፈጣን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በ #ቢሾፍቱ መጀመሩን ማብሰራችንን በማስከተል ከከተማዋ ህዝብ ጋር በአብሮነት የደመቀ አዝናኝ የ5ጂ መንገድ ላይ ትርኢት እና የኮንሰርት መርሐ ግብሮች አካሄደናል፡፡

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#5G #Bishoftu #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍4816🤣6😡2
በዋና ሥራ አስፈፃሚያችን የተመራ የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በባህር ዳር ከተማ በሚገኝ ኢንደስትሪ የሚመረቱ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ግብአቶችን ጎበኘ።

በዚህም ወቅት ልዑኩ ለቴሌኮም እና ዲጂታል መሰረተ ልማት ማስፋፊያ የሚያገለግሉ የቴሌኮም ማማ (ታወሮች)፣ የስማርት ፖሎች እና ተዛማጅ የኢንደስትሪ ምርቶችን ተመልክቷል፡፡

የኢንደስትሪ ምርቶቹን በተመለከተ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን ኩባንያችን ከውጭ የሚገቡ ግብአቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሪ ለማዳን ለያዘው ስትራቴጂ አጋዥ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያን ትራንስፎርሜሽን ከማፋጠን ጎን ለጎን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ሀገራዊ አቅምን ለማሳደግ ለሚደረገው ጥረት የበኩሉን ሚና መጫወቱን ይቀጥላል፡፡

#RealisingDigitalEthiopia #Bahirdar #DigitalAfrica #HOPR #HoF
👍10916😡8😁3
በኦሬንጅ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ቢዝነስ ግሩፕ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ብሬሎት ባ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በቴሌብር የዲጂታል ፋይናንሻል አገልግሎት ዕድገት እና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ረገድ ያሉትን ተሞክሮዎች ለመቅሰም የሚያስችል ጉብኝት በኢትዮ ቴሌኮም አደረገ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ ከፍተኛ ልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን፣ በተለይም የኩባንያውን ፈጣን የለውጥ ጉዞ፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ዕይታ እንዲሁም ከመደበኛው ኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር ዲጂታል ሶሉሽኖችን በማቅረብ ግለሰቦችን፣ የግል ቢዝነስ ድርጅቶችን እና የመንግስት ተቋማትን አቅም በመገንባት የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማፋጠን ላይ ያለውን ከፍተኛ ሚና ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በኤክስፒሪያንስ ማዕከላችን ጉብኝት ያደረገ ሲሆን፣ በጉብኝቱም ወቅት ከግብርና፣ ከትምህርት፣ ከጤና አጠባበቅ፣ ከማዕድን እና ከስማርት ቱሪዝም ጋር ስለተያያዙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላትም እነዚህ ሶሉሽኖች ጠንካራ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት እየተደረገ ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ ስለመሆኑ ያላቸውን አድናቆት የገለጹ ሲሆን፣ ኩባንያው ቴሌብርን እና ዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለማሳደግ እያደረገ የሚገኘው ጥረት በመላ አፍሪካ የዲጂታል ፈጠራ ፋናወጊ ለመሆን ያለውን አቅም ያሳያል ብለዋል፡፡

#RealizingDigitalEthiopia @orangeafrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍9615💔7🎉6🥰5👏4😁3
በጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ኩባንያችን በማህበራዊ ኃላፊነት ረገድ በድምሩ ከ287.17 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአረንጓዴ ልማትና ማስዋብ እንዲሁም ለሀገራዊ ፕሮጀክቶች የተደረገ ሲሆን፣ በዓይነት 131.3 ሚሊዮን ብር፣ በገንዘብ ደግሞ ከ155.9 ሚሊዮን ብር በላይ ነው።

የኩባንያችን ሰራተኞች፣ አጋር አካላት እና የአካባቢ ማህበረሰብ ክፍሎችን በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች በንቃት በማሳተፍ፣ በበጀት አመቱ አጋማሽ በ105 ቦታዎች ከ446,000 በላይ ችግኞችን ለመትከል ተችሏል፡፡

የኩባንያችን ሰራተኞች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር፣ ደም በመለገስ እና የተለያዩ አይነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት በማህበራዊ ኃላፊነት አርአያ የሚሆን ተግባር አከናውነዋል።

ለተጨማሪ https://bit.ly/40RlnYV ይጫኑ

#CSR #Ethiotelecom #telebirr #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍10821🥰8😢5🤣5
በስማርት ስልክ የሚሰራ የፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ ሶሉሽን ለድርጅት ደንበኞች በይፋ አስጀምረናል!

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት ድርጅቶችና ተቋማት የግንኙነት ስርዓታቸውን በእጅጉ ለማዘመን የሚችሉበት ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ (PTT/PTV) የተሰኘ የቡድን ኮሙኒኬሽን ሶሉሽን ይፋ አድርጓል።

ይህ በክላውድ ላይ የተመሰረተ የኮሙኒኬሽን ሶሉሽን በማንኛውም ስማርት ስልክ እና የሞባይል ኔትወርክ ባለበት ቦታ ሁሉ የሚሰራ መሆኑ እንዲሁም ከድምጽ ባሻገር የጽሑፍ፣ ምስል እና ቪዲዮ መለዋወጥ ማስቻሉ ከቀድሞው የፑሽ-ቱ-ቶክ ሬዲዮ አገልግሎት የላቀ ያደርገዋል፡፡

ሶሉሽኑ እንደ ሎጅስቲክስ፣ ደህንነት፣ በግንባታ፣ ትራንስፖርት፣ መስተንግዶ እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ባሉ ዘርፎች የተሰማሩ ድርጅቶች የቡድን ቅንጅትን እና ደህንነትን ለማሳደግ ቅልጥፍናቸው እና ምላሽ ሰጪነታቸው ፈጣን ያደርጋል።

አገልግሎቱ ድርጅቶች ግንኙነታቸውን እንዲያቀላጥፉ፣ ስራቸውን እንዲያሳልጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከየትኛውም ቦታ ሆነው እንዲገናኙ የሚያስችል የቡድን መገናኛ መፍትሔ ይዞ ቀርቧል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG

#RealizingDigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍56👏3614🥰4😁4
ኩባንያችን የዲጂታል አካታችነትን ለማረጋገጥ 2 ሚሊየን ስማርት ስልኮችን በረጅም ጊዜ ክፍያ ሊያቀርብ ነው!

ኩባንያችን የስማርት ስልክ ስርጸትን በማሳደግና የዲጂታል ክህሎት እድገትን በማገዝ አካታችነትን ለማረጋገጥ፣ በዓመት 2 ሚሊየን ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ በረጅም ጊዜ ክፍያ ለዜጎች ለማቅረብ አቅዷል።

ከዚህም ውስጥ፣ ኩባንያችን ከሲንቄ ባንክ ጋር በአጋርነት በዓመት በ4 ቢሊየን ብር በጀት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና በገጠር ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የስማርት ስልኮችን በረጅም ጊዜ ክፍያ ማቅረብን ያካትታል።

ኩባንያችን በቀጣይም የዲጂታልና የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እና ዜጎች በዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርጉ ተመሳሳይ ጥረቶችን ከሌሎች አጋሮች ጋር መተግበሩን ይቀጥላል፡፡

ኩባንያችን ከሲንቄ ባንክ ጋር በድምሩ 15 ቢሊየን የብር መጠን ያለው የሞባይል ፋይናንሺያል እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎቶችን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

#RealizingDigitalEthiopia #Ethiotelecom #telebirr #Siinqee #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍9022😁4🥴3👏2🤩2
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው 20ኛው መሠረተ ልማት ‘ስለ ኢትዮጵያ’ መድረክ ላይ ገለጻ አቅርበዋል።

መድረኩ በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ጫልቱ ሳኒ የተመራ ሲሆን የመግቢያ ቁልፍ መልዕክት በማቅረብ ተወያዮች የመነሻ ሀሳብ እንዲያቀርቡ በመጋበዝ ውይይቱን አስጀምረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን መሠረተ ልማት የጋራ ብሔራዊ ሀብት እንደመሆኑ ባለድርሻዎች በጋራ ለመወያየት መቻላቸው አስደሳች ስሜት የሚፈጥር መሆኑን በማንሳት በቅንጅት የመሥራት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኩባንያችን የቴሌኮም እና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በማዘመን እና ተደራሽ በማድረግ ያከናወናቸውን ተግባራት እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ የአስቻይነት ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የ4ጂ፣ 5ጂ፣ ፋይበር፣ የዳታ ማዕከል እና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ዜጎችን የዲጂታል ሶሉሽን እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።

በተፈጠረው  የዲጂታል መሠረተ ልማት አቅም ተቋማትን በማዘመን፣ ቅልጥፍናን፣ ምርታማነትንና ጥራትን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለመጨመር መቻሉንም አክለዋል።

በመድረኩ በትራንስፖርት መሠረተ ልማት፣  በኃይል ፍላጎት ዕድገት እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት ተደራሽነት ላይ በሚመለከታቸው ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ ተደርጓል።

ክብርት ሚኒስትር መድረኩን ሲያጠቃልሉ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተመዘገበውን የላቀ ውጤት በማድነቅ በተለይም የቴሌብር ፈጣን እድገት እንደ ሀገር የሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል።

#Ethiotelecom #DigitalEthiopia #GSMA #ITU #HOPR #HoF
45👍14👏5
ኩባንያችን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ሲያከናውን የነበረው የ"ስማርት ኮርት" ፕሮጀክት ለአገልግሎት በመብቃቱ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልጻለን!

ኩባንያችን ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ በስኬት በማጠናቀቁ በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ እውቅና የተበረከተለት ሲሆን ለዚህም ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር የክልሉን ፍርድ ቤቶች በአስተማማኝ ዲጂታል መፍትሔዎች በማስተሳሰር ዜጎች ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ዘመናዊ የፍትሕ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል እንግልት ይቀንሳል።

ክልሉ ለጣለብን እምነት በድጋሚ እያመሰገንን በቀጣይም አገልግሎቱን በቀበሌዎችና ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ ለተያዘው እቅድ ስኬት በጋራ የምንሰራ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለፕሮጀክቱ ስኬት ቁልፍ ሚና ለተጫወቱት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለኩባንያችን ቤተሰቦች ምስጋና እናቀርባለን።

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ተቋማትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የማዘመን ቁልፍ ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ኩባንያችን ይህን ፕሮጀክት ለማከናወን በባህር ዳር ከተማ ጥር/2017 ዓ.ም ስምምነት ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር ፈጽሞ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

#Smartcourt #ANRSSupremeCourt #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
55👍31😢2🤩2🥰1
በ2017 በጀት ዓመት ኩባንያችን ከዘላቂ ልማት አንጻር የህብረተሰቡን ሁሉን አቀፍ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ሊያሻሽሉ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ የማኅበረሰብ ተኮር ተግባራትን አከናውኗል፡፡

በትምህርት፣ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማት፣ ሰብአዊ ተግባራት እና የመንግስት ልማት ፕሮጀክቶች በዓይነት እንዲሁም በገንዘብ በድምሩ 450.23 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በተለይም በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የበኩሉን ሚና በመጫወት፣ በ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በ105 ጣቢያዎች ከ446 ሺ በላይ ችግኞች በመትከል ማህበራዊ ሃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡

የበጎ ፈቃድ ተሳትፎም የኩባንያችን እሴት አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ ሰራተኞቻችን በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብና የዓይነት ልገሳ አድርገዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3VWyKnZ

#SustainableDevelopment #CSR #Ethiotelecom #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
76👍24🥴4😁3😢2