Ethio telecom
319K subscribers
7.24K photos
124 videos
129 files
2.47K links
A Leading Digital Solutions Provider
Provide Reliable Communications & Digital Financial Services to Simplify Life and Accelerate Digital Transformation of Ethiopia.

Pioneer – Serving Since 1894 Beyond Connectivity

https://t.iss.one/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
በዲጂታል እና ፋይናንሻል አካታችነት ሴቶችን ማብቃት!

ኩባንያችን የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ለማጥበብ እና የሴቶችን የዲጂታል ተካታችነት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት “Connected Women” ኢኒሼቲቭ- ከ GSMA ጋር በባርሴሎና ስፔን ተፈራረመ::

ስምምነቱ በሀገራችን የሴቶችን የሞባይል ኢንተርኔት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት /ቴሌብር/ ተጠቃሚ ቁጥር እ.ኤ.አ እስከ 2026 በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ኩባንያችን ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና በመተግበር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት አካታች የሞባይል ኢንተርኔት እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ “ሴቶች በሀገራችን ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ኩባንያችን አሁን የሚታየውን የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ክፍተት ለማጥበብ የሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለሴቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ሴቶች በዲጂታል ኢኮኖሚው ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
👍8634🥰5
ኩባንያችን ዜጎች እንዲሁም ተቋማት ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች የሚመለከቱበትና በተግባር የሚሞክሩበት የኤክስፒሪየንስ ማዕከል በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ አስመረቀ፡፡

የኤክስፒሪየንስ ማዕከሉ ዜጎች ምርትና አገልግሎቶችን የሚመለከቱበት፣ አዳዲስ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን የሚሞክሩበት፣ ለፈጠራ የሚነሳሱበት፣ የዘመናችንን ግኝቶችን የሚመረምሩበት እና አዳዲስ አሰራርን የሚፈትሹበት ነው፡፡

ማዕከሉ ለሀገራችን ልማትና ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና ያላቸው በተለያዩ ዘርፍ ያሉ ኢንዱስትሪዎች፣ ቢዝነሶች፣ መንግሥታዊ የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት አሰራራቸውን በቴክኖሎጂ መደገፍ እንዲሁም ምርታማነታቸውን ማሳደግ የሚችሉበትን ዘመናዊ አሰራር እውን በማድረግ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መፋጠን አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡



ለተጨማሪ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ https://bit.ly/4c7KgUU

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #Huawei #ZTE #Ericsson #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica
👍14834👏10🥰5😡1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮ ቴሌኮም ኤክስፒሪየንስ ማዕከል በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም

Ethio telecom Experience center
#AdwaMuseum

Experience the Digital Space! Inspire your Imagination! & Explore the Future!

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #Huawei #ZTE #Ericsson #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
👍11137🎉5😁4🙏4🥰2
የኡጋንዳ የመሬት፣ የቤትና የከተማ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ኩባንያችን በቅርቡ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ ያስመረቀውን የኤክስፒሪየንስ ማዕከል በዛሬው ዕለት ጎበኘ፡፡

የመስክ ጉብኝቱ ዓላማ የአፍሪካን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳደግ በአፍሪካዊያን መካከል ሊኖር የሚገባውን ትብብርና ጠንካራ ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ሲሆን በዚሁ ወቅት ልዑካኑ የአፍሪካን ዲጂታላይዜሽን በፍጥነት ለማሳካት በሀገራት መካከል የላቀ ትብብር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት በተመለከተ የተሞክሮ ልውውጥ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም #ዲጂታል_አፍሪካን እውን ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም ልዑካኑ ሌሎች የአፍሪካ አቻዎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ይህን አስደናቂ ዲጂታል ኤክስፒሪየንስ ማዕከል እንዲመለከቱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ኩባንያችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የ#ዲጂታል_ኢትዮጵያን ጉዞ በማፋጠን እንዲሁም አህጉር አቀፍ አጋርነቶችን በማጎልበት ረገድ እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalEconomy #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR @ministry_lands @GovUganda
👍14131😁6🙏5🥰2🤔2😢1
የኡጋንዳ የመሬት፣ ቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የልዑካን ቡድን አባላት የኩባንያችንን ግዙፍ እና ዘመናዊ Tier 3 የዳታ ማዕከል ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የዳታ ማዕከላችን ዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን ለመስጠት ዝግጅት ያጠናቀቀ መሆኑ የተብራራላቸው ሲሆን ልዑካኑም በሀገራቸው እንደ ክላውድ ሰርቪስ የመሳሰሉ የዳታ ማዕከል አገልግሎቶች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ በመግለጽ፣ ሀገራቸው ግዙፍ የዳታ ማዕከል ለመገንባት ለያዘችው ትልም ከኢትዮ ቴሌኮም ተሞክሮ ለመቅሰም እና በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በማጠቃለያም ልዑካኑ በኩባንያችን ለነበራቸው ቆይታ እና ግሩም አቀባበል በማመስገን ኢትዮ ቴሌኮም በገነባው ግዙፍ መሠረተ-ልማት፣ ቁርጠኛ አመራር እና የሰው ኃይል በፈጠረው አስቻይ ሁኔታ #ከኢትዮጵያ_ባሻገር በአህጉር አቀፍ ደረጃ በመሰማራት እና አህጉራዊ የትብብር ማዕቀፎችን በመዘርጋት የ#ዲጂታል_አፍሪካን ጉዞ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

@ministry_lands @GovUganda #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF #DigitalEthiopia #DigitalEconomy
👍12140🥰7😁3😢3🏆3
የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሀገር አቀፍ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ!

በመርሃ ግብሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ፣ የተገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በተደረገ የመድረክ ላይ ወግ ፣ ዘርፉን ከሚመሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የፖነል ውይይት ተዳሰዋል።

በውይይቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ረገድ ሀገራችን መልካም ጅማሮዎች እና ወሳኝ ምዕራፎች ላይ የምትገኝ መሆኗን አንስተው በመሰረተ ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ የተሰሩት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ አክለውም፣ መንግስት ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ የግሉ ዘርፍ በበኩሉ በዲጂታል ሥነምህዳሩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዘርፉ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት እንደሚገባው አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞ በይበልጥ ለማፋጠን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ሃገራዊ ካውንስል እንዲቋቋም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #MINT
#PMO #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #ITU #SmartAfrica #HOPR #HOF
👍19857😁20🥴8🏆7👏6🫡5🤗2😢1
ኢትዮ ቴሌኮም እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮ ቴሌኮምን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውጥኖች በገንዘብ በመደገፍ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ የበለጠ የሚያሳድግ እና የአፍሪካን ሰፊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያሰፋ ስትራቴጂያዊ ውይይት ጀመሩ።


📡 #DigitalEthiopia #DigitalEconomy #AfDB #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #Innovation #SustainableGrowth @AfDB_Group
👍7824🎉12😢1🤩1