Ethio telecom
319K subscribers
7.24K photos
124 videos
129 files
2.47K links
A Leading Digital Solutions Provider
Provide Reliable Communications & Digital Financial Services to Simplify Life and Accelerate Digital Transformation of Ethiopia.

Pioneer – Serving Since 1894 Beyond Connectivity

https://t.iss.one/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
ኩባንያችን ከተቋቋመለት የቢዝነስ ዓላማ በተጨማሪ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ማህበራዊ ኃላፊነቱን የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ ልማት ተጠቃሚነት ማጠናከር በሚያስችሉ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ሰብአዊ ድጋፍ፣ አካባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማትና ማስዋብ እንዲሁም ለመንግስት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ከ439.9 ሚሊዮን ብር በላይ አስተዋጽዖ ያደረገ ሲሆን በዓይነትና በአገልግሎት 200.6 ሚሊዮን ብር እና በገንዘብ 239.3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም የኩባንያችን ማህበረሰብ በበጎ ፍቃደኝነት የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች 7.5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ እና የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም ደም በመለገስና የመልካም ፍቃድ አገልግሎት በመስጠት አርአያነት ያለው ተግባር አከናውነዋል፡፡

#CSR #CommunityProgress #SustainableDevelopment
👍13840👎20🤩3😢2😁1
በ2016 በጀት ዓመት ኩባንያችን ማህበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር የህብረተሰቡን ሁሉን አቀፍ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ሊያሻሽሉ የሚችሉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

በትምህርት፣ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማት፣ ሰብአዊ ተግባራት እና የመንግስት ልማት ፕሮጀክቶች በዓይነት እንዲሁም በገንዘብ በድምሩ 694.2 ሚሊዮን ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች 900ሺ የደብተር፣ በመላው ሀገሪቱ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላቋቋምናቸው 66 የዲጂታል መማሪያ ማዕከላት ነፃ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም በ42 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ 6000 ድጋፍ ለሚያሻቸው ተማሪዎች የኪስ ገንዘብ ተለግሷል፡፡

በተጨማሪም ባለፉት አምስት ዓመታት በ700 ጣቢያዎች 3.8 ሚሊዮን ችግኞች በመላ አገሪቱ በመትከል እና በመንከባከብ የጽድቀት መጠንን በአማካኝ 82% ለማድረስ ተችሏል፡፡ እንዲሁም በኩባንያችን ቤተሰቦች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች 7.6 ሚሊዮን ብር የገንዘብ እና የተለያዩ ቁሳቁስ ልገሳ ተደርጓል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3VWyKnZ

#SustainableDevelopment #CSR #Ethiotelecom #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
👍15036👏12😡3🥰1
በ2017 በጀት ዓመት ኩባንያችን ከዘላቂ ልማት አንጻር የህብረተሰቡን ሁሉን አቀፍ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ሊያሻሽሉ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ የማኅበረሰብ ተኮር ተግባራትን አከናውኗል፡፡

በትምህርት፣ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ አረንጓዴ ልማት፣ ሰብአዊ ተግባራት እና የመንግስት ልማት ፕሮጀክቶች በዓይነት እንዲሁም በገንዘብ በድምሩ 450.23 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በተለይም በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የበኩሉን ሚና በመጫወት፣ በ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በ105 ጣቢያዎች ከ446 ሺ በላይ ችግኞች በመትከል ማህበራዊ ሃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡

የበጎ ፈቃድ ተሳትፎም የኩባንያችን እሴት አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ ሰራተኞቻችን በራሳቸው ተነሳሽነት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች 3.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብና የዓይነት ልገሳ አድርገዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3VWyKnZ

#SustainableDevelopment #CSR #Ethiotelecom #GSMA #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #HOPR #HoF
76👍24🥴4😁3😢2