Ashewa Technologies
7.72K subscribers
2K photos
160 videos
33 files
1K links
We Revolutionize African commerce/business by providing innovative, e-commerce, software development, o,r rmeirslogistics, e-learning, payment, and entertainment to do business easily, affordably, and reliably at any time, and any place through cutting-ed
Download Telegram
በኦንላይን ትምህርት ላይ ከተለመደው የፊት ለፊት የክፍል ትምህርት አንጻር በተመሳሳይ ጊዜ 5 እጥፍ የሚሆን የትምህርት ማቴሪያል መሸፈን ያስችላል። ይህም ሰልጣኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ የትምህርት ክፍል ሸፍነው በትንሽ ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ አለም እንዲገቡ ያስችላቸዋል። በአጭር ጊዜ ብቻ ኮርሶችን መጨረስ መቻላቸው ጊዜን ብቻ ሳይሆን ገንዘብንም እንደሚቆጥብ ግልጽ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በኦንላይን ትምህርት ላይ ሲሳተፉ ኢንተርኔት ላይ የሚያገኙዋቸው ገደብ የለሽ የትምህርት ማገዣ መጻህፍት፣ ቪዲዮዎች እና ሌሎች ማቴሪያሎች የትምህርት ጊዜዎን ቀላል እና ጥራት ያለው ያደርገዋል።
እኛም ይህንን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የኦንላይን ትምህርት ሳቢ እና ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ፕላትፎርም ወደ እናንተ እያቀረብን ቆይተናል። አሁንም ይህንን ፕላትፎርም የበለጠ የተሻለ ለማድረግ እየሰራን ነው። በቅርቡም ሙሉ ለሙሉ ስራ ይጀምራል። እናንተም እስከዛው እየተዘጋጁ ይጠብቁን።
#ኑ አብረን የነገ ህይወታችንን እንገንባ

#Ashewa_Technology_Solutions
#Ashewa_Elearning
የኦንላይን ግብይት እና ትምህርት በዚህ ዘመን የሰዎች ህይወት ላይ የዕለት ከዕለት ተግባር ሆኗል። ስታቲስታ የተባለው የጥናት ድርጅት እንደሚያሳየው በ2023 የኦንላይን ግብይት ከአጠቃላይ ግብይቶች 22% የሚሆነውን ይሸፍናል። ይህም በ2019 ከነበረው 14.1% የኦንላይን ግብይት መጠን አንጻር ሲተያይ ይህ የኦንላይን ግብይት በሚገርም ፍጥነት እያደገ መሆኑን ያሳያል። እኛም በዚህ በዘመናችን ተወዳዳሪ በሌለው የስራ ዘርፍ ላይ ተሰማርተናል። አክሲዮን በመግዛት አብረውን የዚህ አትራፊ ቢዝነስ አካል እንዲሆኑም ታላቅ እድል አቅርበንሎታል። አሁኑኑ ይግዙ

#ኑ_አብረን_የነገ_ህይወታችንን_እንገንባ
#Ashewa_technology_solutions
#Ashewa_share_sell
አክሲዮን ለምን ይገዛሉ?
አክሲዮን መግዛት እጅግ ትርፋማ ቢዝነስ ነው። አንድ ጊዜ የገዙት አክሲዮን የድርጅቱ የትርፍ ተካፋይ ያደርግዎታል። ይህም በየጊዜው አንዴ ኢንቨስት ባደረጉት ብር ድርጅቱ ከሚያገኘው ትርፍ ላይ ባለዎት የድርሻ መጠን መሰረት ክፍያ ይደርስዎታል ማለት ነው። በዚህም በተወሰነ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ኢንቨስት ያደረጉትን ብር ሸፍኖ ከዛ በኋላም ምንም ሳይሰሩ ካሉበት ሆነው ተጨማሪ ትርፎችን እጅዎ ላይ ያስገባልዎታል።
ሌላኛው አክሲዮን ላይ ኢንቨስት የማድረግ ጥቅም ባለበት የተቀመጠ ገንዘብ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መጨመር () ባለባቸው ሀገራት ላይ በየቀኑ ዋጋው እያነሰ መምጣቱ ነው። ዛሬ ላይ ያስቀመጥነው 1000 ብር ከዛሬ አስር አመት በኋላ አውጥተን ብንጠቀመው ምናልባት አሁን ላይ ያለውን የ 100 ብር ያህል ዋጋ ላይኖረው ይችላል። ይህንንም ለማየት በኛው እድሜ ከአስራ አምስት ወይም ሀያ ዓመት በፊት 300 ወይም 400 ብር የአንድ ተቀጣሪ ሰራተኛ የወር ደመወዝ ነበር። አሁን ላይ ግን ለአንድ ቀን ወጪ ቢበቃ ነው። ይህም ማለት ይህ ሰው የዛን ጊዜ የወር ደመወዙን ሙሉ አስቀምጦ እንኳን ቢያቆይ ዛሬ ላይ ከአንድ ቀን ወጪ በላይ አይሸፍንለትም። ለዚህም ነው ገንዘቡን የጊዜውን እና የኑሮውን ለውጥ ተከትሎ አብሮ የሚጨምር ኢንቨስትመንት ላይ ማድረግ አለበት የሚባለው።
ነገር ግን ይህን የአክሲዮን ግዜ ሲፈጽሙ አብሮ የሚያሳድግዎት ጠንካራ መሰረት እና ብሩህ ተስፋ ያለው ድርጅት ላይ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። የአሸዋን አክሲዮን ለምን ሊተማመኑበት እና ምርጫዎ ሊሆን እንደሚገባ ደግሞ በቀጣይ ጊዜያት እንመለስበታለን።
#አሸዋ_ቴክኖሎጂ_ሶሉሽን
#ኑ_የነገ_ህይወታችንን_እንገንባ
በባለፈው ጊዜ ቃል በገባንላችሁ መሰረት የአሸዋን አክሲዮን ከሌሎች አክሲዮኖች ምን እንደሚለየው እና ተመራጭ እንደሚያደርገው ይዘንላችሁ ቀርበናል። የአክሲዮን ግዢ ምን ያህል አዋጪ እንደሆነ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም። ይህ የሚሆነው ግን አክሲዮኑን የገዙት ካምፓኒ ትርፋማ እና በቢዝነሱ አለም ላይ ከፍተኛ ተወዳዳሪ የሚያደርገው አገልግሎት ይዞ ሲቀርብ ነው። አሸዋ አሁን ላይ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት እያደገ በመጣው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የተሰማራ እና በዚህም ዘርፍ ላይ ኢትዮጲያዊው አሊባባን እና አማዞንን የሚተካ ጠንካራ መሰረት ያለው ድርጅት ነው። የአንዱ አክሲዮን ዋጋ በ 1000% ማሳደግ መቻሉ ይህ ማለት 2500 ብር የተሸጠው ወደ 25000ብር ያህል ከፍ ማለቱ እንዲሁም ከፍተኛ ሪተርን ኦን ኢንቨስትመንት ለሼር ሆልደሮች መክፈሉ ከሌሎች ትራዲሽናል አክሲዮን ሽያጮች ተመራጭ ያደርገዋል። በቢዝነስ ፕላኑ መሰረት ቋሚ አመታዊ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገብ የሚችል መሆኑ እንዲሁም በህዝቡ ዘንድ ያለው ትልቅ የቴክኖሎጂ ፍላጎት እና የዚህን ኢኮኖሚ ያክል በፍጥነት እያደገ ያለ ምንም አለመኖሩ ለአሸዋ አክሲዮን ባለቤቶች መተማመኛ የሆነ ቋሚ ሀብት የሚሆን እሴት ያደርገዋል። ይህንን አክሲዮንም መሸጥ መለወጥ አሲዘን መበደር ወዘተ የምንችልበት መሆኑ ምንግዜም የሚደግፍዎ ታላቅ ኢንቨስትመንት ያደርገዋል።
#አክሲዮን_ይግዙ_ያትርፉ
#ኑ_አብረን_የነገ_ህይወታችንን_እንገንባ
የኦንላይን ግብይት ምን ያህል ትርፋማ ነው?
አሁን ላይ የኦንላይን ግብይት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ እድገት እና ለውጥ ያሳየበት ጊዜ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በያዝነው 2021 የኦንላይን ግብይት ተጠቃሚዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ 2.14 ቢሊየን መድረሱን ያሳያል። አሁን ላይ ካለው 7.87 ቢሊየን ህዝብ ዉስጥ 27.2% የሚሆነው ማለት ነው። በዚሁ በያዝነው የፈረንጆቹ 2021 ይህ የኦንላይን ግብይት ከአጠቃላይ አለም ላይ ከሚደረጉ ግብይቶች 18.1% የሚሆኑት እንደሚሸፍን ይገመታል። ይህም የሚያሳየው የኦንላይን ግብይት የተለመደውን እና በአካል የሚደረገውን ግብይት ቀስ በቀስ እየተካው እየመጣ መሆኑን ነው። ይህም ማለት እኛ አሁን ላይ የምናውቃቸው በየቀኑ በሚሊየን ብሮች ትራንሳክሽን የሚደረግባቸው እንደ መርካቶ ያሉ ገበያዎች ወደፊት በኦንላይን ገበያዎች ላይ ነው የሚሆኑት ማለት ነው። ደንበኞችም በስልካቸው ብቻ ካሉበት ሆነው ያለምንም ወከባ እና ጫና፣ የትራንስፖርት ወጪ ሳያሳስባቸው፣ ያሉትን ሁሉንም ለሽያጭ የቀረቡ ምርቶችን እና እቃዎችን ካሉት በጣም ብዙ አማራጮች አማርጠው መግዛት መቻላቸው እና ለመሸጥ የሚፈልጉትንም ነገር እንደዚያው መሸጥ መቻላቸው ወደዚህ የኦንላይን ግብይት እንደመጀመሪያ አማራጭ ፊታቸውን እንዲያዞሩ አስችሏቸዋል። ለዚህም ነው የተሰማራንበት እጅግ አዋጭ እና ነገ ላይ የንግዱ አለም ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነ ወሳኝ ቢዝነስ ላይ ነው የምንለው። ከእኛ ጋር አብረው የዚህ ድንቅ እድል አካል ለመሆን በራችን ክፍት ነው። አክሲዮናችንን በመግዛት መቀላቀል እና የትርፉ አካል መሆን ይችላሉ።
#ኑ_አብረን_የነገ_ህይወታችንን_እንቀይር
#Ashewa_technology_solutions
አክሲዮናችን አሁን ላይ በተለያዩ ባንኮች እየተሸጠ ይገኛል። ባአቢሲኒያ ባንክ አክሲዮናችንን ስንሸጥ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በተለያዩ ባንኮች ጭምር መሸጥ ጀምረናል። አክሲዮናችንን በአቢሲኒያ ባንክ በንግድ ባንክ፣ብርሃን ባንክ፣ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና በአዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገኙታል።

አክሲዮን ሊገዙ ሲሄዱ ችግሮች ቢያጋጥምዎት እና የለም ቢባሉ ወዲያዉኑ ከታች ባሉት ስልኮች ደውለው ያነጋግሩን፤ ይስተካከላል።

ስልክ 09 44070860 ወይም 0976005100

#ኑ_አብረን_የነገ_ህይወታችንን_እንገንባ
#Ashewa_technology_solutions
ኮቪድ 19 እና ኢኮሜርስ
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት የፈረንጆቹ 2019 መጨረሻ አክባቢ ጀምሮ በዓለማችን እንዲሁም በሀገራችን ላይ ዘርፈ ብዙ ተጽእኖዎች አሳድሯል። የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ብዙዎችንም ለከፋ ጉዳት ዳርጓል። ኮቪድ 19 በጤናችን ላይ ቀጥታ ካስከተለው ተጽእኖ በተጨማሪ በብዙ የህይወታችን ክፍል ላይ ተጨማሪ ተጽእኖዎች ነበሩት። ከነዚህም ውስጥ ወረርሹን ለመከላከል ሲባል የተደረጉ እርምጃዎች እና ክልከላዎች ከዚህ በፊት የነበረንን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የህይወት ምህዳር በሰፊዉ የቀየሩ ናቸው። በዚህም ብዙዎች የኢኮኖሚ ክስረት እጋጥሟቸዋል። በኢኮሜርስ ላይ የተከሰተው ነገር ግን ከአብዛኞቹ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተለየ ነበር። እንዲያውም ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ያልተጠበቀ እድገት ያገኘበት ነበር። ከአሁን በፊት በኦንላይን በብዛት ይሽጡ ከነበሩ እንደ ልብስ እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተጨማሪ የእለት ተእለት ፍላጎት የሆኑ ምግቦች እና መጠጦች ጭምር በብዛት ተፈላጊነት የታየበት ጊዜ ነበር። በተለይ ኮቪድ19 በሰዎች መሰባሰብ መተላለፉ እና በሽታውንም ለመከላከል በቤት ውስጥ መቆየት ወሳኝ መፍትሄ ሆኖ መወሰዱ እና የኦንላይን ግብይት ከቤት ሳይወጡ ግብይትን ለመፈጸም ሁነኛው አማራጭ ሆኖ መገኘቱ ብዙዎች እንዲመርጡት አስችሏቸዋል። መንግስታትም እንደ አንድ የመከላከል እርምጃ የነዚህን የኦንላይን ግብይት ፕላትፎርሞች ሲያበረታቱ እና ሲደግፉ ነበር። የዚህ ወረርሽኝ መከሰትም ኢኮሜርስ ከብዙ አመታት ይደርስበታል ተብሎ የታሰበበትን የእድገት ደረጃ ከታሰበበት ጊዜ ቀድሞ ሊደርስ ችሏል። ኮቪድ19 በብዙ የህይወት ክፍላችን ላይ መጥፎ አሻራ ጥሎ ቢያልፍም ለኢኮሜርስ ግን ያልታሰበ ውለታ ውሎለታል።
#Ashewa_technology_solutions
#ኑ_የነገ_ህይወታችንን_አብረን_እንገንባ
ካሉበት ሆነው የሚገበዩበት፣ የሚማሩበት ትልቅ ፕላትፎርም፤ አብረን የምናድግበት ታላቅ አትራፊ ቢዝነስ። አክሲዮን ገዝተው የትርፍ ተካፋይ እና ህጋዊ የድርጅት ባለቤት የሚሆኑበት፤የአባልነት ገቢ የሚያገኙበት፣ ፕላትፎርማችንን ተጠቅመው የነገ ህይወትዎን የሚቀይሩበት፣የስራ እድል የሚያገኙበት አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ላይ ቤተሰብ ይሁኑ።

#Ashewa_technology_solutions
#ኑ_የነገህይወታችንን_አብረን_እንገንባ
በአሸዋ በአንድነት በጋራ አንድ ሚሊዮን ሚሊዬነሮችን እናፍራ ፕሮጀክት ላይ ይሳተፉ
በእድሉ ይጠቀሙ!!
ሙሉ እንኳን መክፈል ቢያቅተዎ ግማሽ ከፍለው ግማሹን በሚሰጥዎት 5ወር የእፎይታ ጊዜ ውስጥ ያጠናቁ።

#Ashewa_technology_solutions
#ኑ_የነገህይወታችንን_አብረን_እንገንባ
በቀጣይ በአሸዋ ከሚፈጠሩ 1ሚሊየን ሚሊየነሮች አንዱ መሆን እንደሚችሉ ያውቃሉ? ከሚፈጠሩት ቀጣይ አንድ ሚሊየን ሚሊየነሮች እንዴት አንዱ መሆን እችላለሁ የሚለውን ብዙዎች ይጠይቃሉ። ሼር/አክሲዮን ካላችሁ በገዛችሁት አክሲዮን ብዛት መሰረት በትርፍ ክፍፍል ብቻ ገንዘባችሁ ብዙ ገንዘብን ይወልዳል። በተጨማሪም ከፍተኛ ጥናት እና ኢንቨስትመንት ተደርጎበት ግለሰቦችን የቢዝነስ ባለቤት የምናደርግበት ሲስተምን ተጠቅመው ከሚፈጠሩት ሚሊዮኖች ውስጥ አንዱ ሚሊየነር መሆን ይችላሉ። ከአሸዋ ጋር ቀጣዩ ጊዜ የከፍታ ነው።

#Ashewa_technology_solutions
#ኑ_የነገህይወታችንን_አብረን_እንገንባ
ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም ገንዘብ መስራት እና ለስኬት መብቃት እንደሚችሉ ያውቃሉ? ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚያባክኑትን ሰዓት ዉጤታማ ወደሆነ እና ወደ ስኬት የሚወስድዎ የነገ ህይወትዎን የሚቀይሩበት እድል ማድረግ ይችላሉ። አሸዋ ህይወትዎን የሚቀይሩ ዘርፈ ብዙ እድሎችን ይዞልዎት እየመጣ ነው። ቤተሰባችን ሆነው ይከታተሉን። ከአሸዋ ጋር መጪው ጊዜ የከፍታ ነው። አብረን የነገ ህይወታችንን እናሳድግ።

#Ashewa_technology_solutions
#ኑ_የነገህይወታችንን_አብረን_እንገንባ