Ashewa Technologies
7.72K subscribers
2K photos
160 videos
33 files
1K links
We Revolutionize African commerce/business by providing innovative, e-commerce, software development, o,r rmeirslogistics, e-learning, payment, and entertainment to do business easily, affordably, and reliably at any time, and any place through cutting-ed
Download Telegram
የምንኖርበትን ዘመን እናገናዝብ፣ እራስን በትምህርት እና በልምምድ ለማሻሻል የገንዘብ፣ የቦታ፣ የርቀት እና የጊዜ መሰናክል ወደ ኋላ ሊያስቀረን አይገባም። ቴክኖሎጂን ራሳችንን ለማማሻሻል እስከ መጨረሻው ድረስ በመሄድ ለመጠቀም መሞከር ይኖርብናል። 📱📲💻⌨️🖥

ካሉበት ሆነው በመረጡት ጊዜ እና የትምህርት መስክ ስልጠናዎችን ከእኛ ያገኛሉ። ስልጠናውን ሲያጠናቅቁም ሰርተፊኬት ስለሚያገኙ በዚህ ብዙዎች በስራ ማጣት በሚቸገሩበት ወቅት እራስዎ ተፈላጊ ያድርጉ። 🏆🏆🏅🏅🎖

አሁን ላይ ገበያ ላይ በብዛት በሚፈለጉ እንደ ዲጂታል ማርኬቲንግ፣ ግራፊክስ ዲዛይኒንግ እና ዌብሳይት ዴቨሎፕመንትን የመሳሰሉ ዘመኑን የዋጁ ክህሉቶችን በቀላሉ የሚማሩበትን ፕላትፎርም አቅርበንላችኋል።

#Ashewa_technologies
#Ashewa_elearning
#Elearning_platform
ኦንላይን ትምህርት በቅርብ ጊዜ ተጀምሮ አሁን ላይ በስፋት በብዙ ሰዎች ተመራጭ መሆን የቻለ መስክ ነው። በተለይ የጊዜ እና የቦታ ገደብ አለመኖሩ፣ ለትምህርት የሚሆኑ ማቴሪያሎች በብዛት እና በቀላሉ መገኘታቸው እንዲሁም ከወጪም አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ ተመራጭ አድርጎታል። ስታቲስታ በተባለው ኢንተርናሽናል ድርጅት የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን በኦንላይን የተማሩ ተማሪዎችን እስከዛሬ ከተማሩበት እና ከተለመደው የአካል የክፍል ትምህርት ጋር በማወዳደር የትኛው የተሻለ ጥራት እንዳዩበት በመረጡበት ጥናት የኦንላይን ትምህርት ስኬታማ መሆኑን የሚያሳዩ ምላሾች ተገኝተዋል። የተማሪዎቹ ምላሽ በዝርዝር በግራፍ በምስሉ ላይ ተካቷል።

#Ashewa_technology_solutions
#Ashewa_Elearning
#Online_learning
“በስራቸው በጣም ውጤታማ እና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ያለማቋረጥ ይማራሉ፤ የተማሩትንም ይተገብራሉ፤ ምንግዜም ራሳቸዉን ለማሻሻል ይተጋሉ” ጆይል ጋርድነር

የአሸዋ ኢለርኒንግ ፕላትፎርም ለናንተ ለተጠቃሚዎቹ ምቹ እና ቀላል እንዲሆን በማሰብ የተለያዩ ማስተካከያዎች እየተደረጉበት ነው። በቅርቡም በተሻለ እና ባማረ መልኩ ወደ እናንተ ወደ ተጠቃሚዎቹ ይመለሳል። እስከዚያው ራስዎን እያዘጋጁ ይጠብቁን።

#Ashewa_Elearning
#Ashewa_technology_solutions
በኦንላይን መማር በአካል ክፍል ውስጥ ከሚደረግ ትምህርት አንጻር ተመሳሳይ ነገርን ለመማር የሚፈጀውን ሰዓት ከ40 - 60% ይቀንሳል። ይህንን ጥናት ይፋ ያደረገው ብራንደን ሃል የተባለ የጥናት ቡድን ሲሆን የኦንላይን ትምህርት ይህንን ያህል ጊዜ ሊቆጥብ ያስቻለው ግዴታ በተወሰነ ሰዓት እና ቦታ መገኘትን ስለማይጠይቅ እና ተማሪው በተመቸው ሰዓት ትምህርቱን መከታተል መቻሉ ይህም ሰዎች ጎንለጎን ከሚሰሯቸው ስራዎች ጋር ተስማምቶ መሄዱ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ይህ ሲባል ግን ሰዓት መቆጠቡ በትምህርት ጥራቱ ላይ ጉድለት እንደማያመጣ እንዲያውም እጅጉን እንደሚጠቅመው ነው ጥናቱ ያሳየው።
ይህም እንደ እኛ ሀገር ብናየው ከውጪዎቹ በተሻለ መልኩ እንደሚያስፈልገን አያጠራጠርም። ከምንማርበት ሰዓት የሚስተካከል ጊዜ በትራንስፖርት ብቻ ማጥፋታችን ሳያንስ የጊዜ አለመከበር እንዲሁም የትምህርት ጊዜ ጎን ለጎን ከምንሰራቸው ስራዎች ጋር አለመስማማትን ብናስብ የኦንላይን ትምህርትን ብንመርጥ ከላይ ከተቀመጠው በላይ ጊዜ ማትረፍ እንደምንችል የማያጠራጥር ሃቅ ነው።
ለእርስዎ ተስማሚ እንዲሆን ማሻሻያዎች እየተደረጉበት ያለው የአሸዋ የኦንላይን ትምህርት ፕላትፎርም ለመቀላቀል ዝግጁ ሆነው ይጠብቁን።ጊዜዎን ቆጥበው አላማዎትን ያሳካሉ።
#መጪው ጊዜ ከአሸዋ ጋር ብሩህ ነው።

#Ashewa_technology_solutions
#Ashewa_Elearning
በኦንላይን ትምህርት ላይ ከተለመደው የፊት ለፊት የክፍል ትምህርት አንጻር በተመሳሳይ ጊዜ 5 እጥፍ የሚሆን የትምህርት ማቴሪያል መሸፈን ያስችላል። ይህም ሰልጣኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ የትምህርት ክፍል ሸፍነው በትንሽ ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ አለም እንዲገቡ ያስችላቸዋል። በአጭር ጊዜ ብቻ ኮርሶችን መጨረስ መቻላቸው ጊዜን ብቻ ሳይሆን ገንዘብንም እንደሚቆጥብ ግልጽ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በኦንላይን ትምህርት ላይ ሲሳተፉ ኢንተርኔት ላይ የሚያገኙዋቸው ገደብ የለሽ የትምህርት ማገዣ መጻህፍት፣ ቪዲዮዎች እና ሌሎች ማቴሪያሎች የትምህርት ጊዜዎን ቀላል እና ጥራት ያለው ያደርገዋል።
እኛም ይህንን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የኦንላይን ትምህርት ሳቢ እና ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ ፕላትፎርም ወደ እናንተ እያቀረብን ቆይተናል። አሁንም ይህንን ፕላትፎርም የበለጠ የተሻለ ለማድረግ እየሰራን ነው። በቅርቡም ሙሉ ለሙሉ ስራ ይጀምራል። እናንተም እስከዛው እየተዘጋጁ ይጠብቁን።
#ኑ አብረን የነገ ህይወታችንን እንገንባ

#Ashewa_Technology_Solutions
#Ashewa_Elearning
ኢለርኒንግ ከፈረንጆቹ 2000 ዓ.ም. ጀምሮ የ900% እድገት አሳይቷል። በአሁኑ ጊዜም በአለማችን ላይ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ከሚማሩ ተማሪዎች ግማሽ ያህል የሚሆኑት ቢያንስ አንድ ኮርስ በኢለርኒንግ ይወስዳሉ። ብዙዎችም ከሚሰሯቸው ስራዎች ወይም ከሚማሩት ትምህርት በተጨማሪ የመማር ፍላጎት ያደረባቸውን ኮርሶች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው እየተማሩ ይገኛሉ። በሀገራችን ኢትዮጵያም ይህ የኢለርኒንግ ትምህርት የብዙዎችን ህይወት እያቀለለ ይገኛል። ኢለርኒንግ ለእርስዎም ሁነኛ መፍትሄ ነው።
የአሸዋ ኢለርኒንግ ፕላትፎርማችን ለእናንተ ይበልጥ ምቹ ይሆን ዘንድ በእድሳት ላይ ነው። በቅርቡም ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ወደ ስራ ይመለሳል። እርስዎም ዝግጁ ሆነው ይጠብቁን።

#Ashewa_Elearning
#Ashewa_technology_solutions
ኦንላይን ትምህርት ከአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን
ህይወትዎን ሊቀይር የሚችል ታላቅ የትምህርት ቦታ ነው። ዌብሳይታችን በቅርቡ ከእንደገና ወደ አገልግሎት ይመለሳል። ዝግጁ ሆነው ይጠብቁን።
#Ashewa_elearning
#Ashewa_technology_solutions