Ashewa Technologies
7.71K subscribers
2.01K photos
160 videos
33 files
1.01K links
We Revolutionize African commerce/business by providing innovative, e-commerce, software development, o,r rmeirslogistics, e-learning, payment, and entertainment to do business easily, affordably, and reliably at any time, and any place through cutting-ed
Download Telegram
አክሲዮን ለምን ይገዛሉ?
አክሲዮን መግዛት እጅግ ትርፋማ ቢዝነስ ነው። አንድ ጊዜ የገዙት አክሲዮን የድርጅቱ የትርፍ ተካፋይ ያደርግዎታል። ይህም በየጊዜው አንዴ ኢንቨስት ባደረጉት ብር ድርጅቱ ከሚያገኘው ትርፍ ላይ ባለዎት የድርሻ መጠን መሰረት ክፍያ ይደርስዎታል ማለት ነው። በዚህም በተወሰነ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ኢንቨስት ያደረጉትን ብር ሸፍኖ ከዛ በኋላም ምንም ሳይሰሩ ካሉበት ሆነው ተጨማሪ ትርፎችን እጅዎ ላይ ያስገባልዎታል።
ሌላኛው አክሲዮን ላይ ኢንቨስት የማድረግ ጥቅም ባለበት የተቀመጠ ገንዘብ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መጨመር () ባለባቸው ሀገራት ላይ በየቀኑ ዋጋው እያነሰ መምጣቱ ነው። ዛሬ ላይ ያስቀመጥነው 1000 ብር ከዛሬ አስር አመት በኋላ አውጥተን ብንጠቀመው ምናልባት አሁን ላይ ያለውን የ 100 ብር ያህል ዋጋ ላይኖረው ይችላል። ይህንንም ለማየት በኛው እድሜ ከአስራ አምስት ወይም ሀያ ዓመት በፊት 300 ወይም 400 ብር የአንድ ተቀጣሪ ሰራተኛ የወር ደመወዝ ነበር። አሁን ላይ ግን ለአንድ ቀን ወጪ ቢበቃ ነው። ይህም ማለት ይህ ሰው የዛን ጊዜ የወር ደመወዙን ሙሉ አስቀምጦ እንኳን ቢያቆይ ዛሬ ላይ ከአንድ ቀን ወጪ በላይ አይሸፍንለትም። ለዚህም ነው ገንዘቡን የጊዜውን እና የኑሮውን ለውጥ ተከትሎ አብሮ የሚጨምር ኢንቨስትመንት ላይ ማድረግ አለበት የሚባለው።
ነገር ግን ይህን የአክሲዮን ግዜ ሲፈጽሙ አብሮ የሚያሳድግዎት ጠንካራ መሰረት እና ብሩህ ተስፋ ያለው ድርጅት ላይ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። የአሸዋን አክሲዮን ለምን ሊተማመኑበት እና ምርጫዎ ሊሆን እንደሚገባ ደግሞ በቀጣይ ጊዜያት እንመለስበታለን።
#አሸዋ_ቴክኖሎጂ_ሶሉሽን
#ኑ_የነገ_ህይወታችንን_እንገንባ