TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ እስካሁን 17 ሰዎች በኮሌራ ሞተዋል፤ በኮሌራ ተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 871 ደርሷል። #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አርከበ ሆስፒታል ናቸው...

"በሚንስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚንስትሩ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር #አርከበ_እቁባይ ታመው ቤልጅዬም በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ።" ይህ መረጃ #PetrosAshenafi እና ethiopiaobserver.com ናቸው ያወጡት።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ኣርከበ #በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ...

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ዶ/ር #ኣርከበ_እቁባይ በጠና ታመው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሎ በፌስቡክ እና መሰል ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ስህተት እንደሆነ የዶክተር ኣርከበ የቅርብ ሰውና የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆኑ ሰው ከደቂቃዎች በፊት በላኩልኝ የፅሁፍ መልዕክት አሳውቀውኛል። ዶክተር ኣርከበ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለህዝቡ ንገርልኝ ብለዋል።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ኒጀር አቅንተዋል፡፡ የጉዟቸው ዐለማ በኒያሚ በሚካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ኅብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመገኘት እንደሆነ ኢዜአ ዘግቧል፡፡ ከጉባዔው በፊት ነገ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ይካሄዳል፡፡ ለመሪዎቹ ጉባዔ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ይገኙ አይገኙ ዘገባው ያለው ነገር የለም፡፡ ጉባዔው ኢትዮጵያ ያጸደቀችውን የአፍሪካ አሕጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና በይፋ ያውጃል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ይቅርታ ጠይቋል!

#ኢትዮ_ቴሌኮም በሃገሪቱ ተዘግቶ የሰነበተው የፊክስድ ብሮድባንድ እና የሞባይል ኢንተርኔት የተቋረጠው ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት ተወስኖ እንደሆነ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል። በተገልጋዮች በኩል ለተፈጠረው መጉላላት እና ለደረሰው የኢኮኖሚ ኪሳራም #ይቅርታ ጠይቋል። የፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎቱ ከሰኔ 18 ጀምሮ መለቀቁን የገለጸው ኩባንያው የስልክ ኢንተርኔት በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ተለቋል ብሏል። ነገር ግን አሁንም የስልክ ኢንተርኔት የማይሠራባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ኩባንያው በበኩሉ እንዲህ ያለው ችግር እንዳይደጋገም ምን ይበጃል የሚለውን በመለየት የመፍትሄ እያፈላለገ መሆኑን ይናገራል።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማስታወቂያዎችን በተመለከተ፦

TIKVAH-ETH ለሚሰራቸውና ለሚያደርጋቸው ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴዎች ከየትኛውም የመንግስት እና የግል አካላት እስካሁን ልዩ ድጋፍ አልተደረገለትም፤ አሁንም አይደረግለትም፤ ይደረግልህ ቢባልም አይቀበልም! ቻናሉ በራሱ የቤተሰቦቹ አቅም የሚንቀሳቀስ ነው። ከገንዘብ በፊት ሀገር እና ህዝብ እንዲሁም ስራን የሚያስቀድም ቻናል ነው።

TIKVAH-ETH ለማስታወቂያ ክፍት የሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ የቤተሰቡ አባላት በየቀኑ በሚከታተሉት ገፅ በሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ምናልባት ተገልጋዮች አገልግሎት አቅራቢዎች የሚጠቅሟቸው በርካታ ጥቅሞች ስላሉ ነው። ነገር ግን የማስታወቂያ ስራው ለሁሉም ክፍት ከመሆኑ አንፃር እጅግ በርካታ ማስታወቂያዎች በTIKVAH-ETH እንዲቀርቡ ይጠየቃል እስከዛሬም ሲቀርቡ ቆይቷል፤ ነገር ግን የማስታወቂያ ብዛት ተከታዩን እያማረረ እንደሆነ ለመረዳት ችለናል። በርካታ አስተያየቶችምንም ተቀብለናል። በዚህም የማስታወቂያ ቁጥር እንዳይበዛ ለማድረግ አዲስ የማስታወቂያ ፓኬጅ አዘጋጅተናል። አዲስ በተዘጋጀው ፓኬጅ መጠቀም የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አነጋግሩን።

ማስታወቂያ አስነጋሪዎች፦

▪️ህጋዊነታችሁ የተረጋገጠ/ፍቃድ ያላችሁ/
▪️ለምታስተዋውቁት ማንኛውም ነገር ተጠያቂ እንዲሁም
▪️ማስታወቂያችሁ ተገልጋዩን የሚጠቅም ሊሆን ይገባል።

በሌላ በኩል...

√ከዚህ ቀደም ውል ያላችሁ በኔትዎርክ መጥፋት ብዙ ስራዎች ባለመሰራታቸው ከነገ ጀምሮ ሁሉም ማስታወቂያዎች ወደ መደበኛ ቦታቸው ይመለሳሉ።

እናመሰግናለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሙስ እና ቅዳሜ በነፃ!!

√አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች እና ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች የTIVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለህዝብ የሚጠቅም #አዲስ የስራ ፈጠራ ውጤት ካላችሁ በተጨማሪም በአዲስ የስራ ዘርፍ የተሰማራችሁ ካላችሁ ሀሙስ እና ቅዳሜ በነፃ አገልግሎታችሁን ስራችሁን ማስተዋወቅ ትችላላችሁ።

TIKVAH-ETH የቤተሰቡ አባላት ነው!
ለህዝብ ሊጠቅሙ ይችላሉ የምንላቸውን ነገሮች በሙሉ ከማድረግ ወደኃላ አንልም!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ክንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በመዲናዋ አምስቱ መግቢያ በሮች የመሠረታዊ ፍጆታ የግብይት መጋዘኖች ሊገነቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የመጋዘኖቹ መገንባት አሁን ላይ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ መልካም ስራችን እንመለስ!

በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት ለእህት እና ወንድሞቻችን እንዲሁም ለልጆቻችን ተገቢውን ነገር ሳናደርግ ቆይተናል፦

#1

√ስም፦ #ሳምራዊት_አረጋ
√እድሜ 22
√የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ
√በደረሰባት ድንገተኛ የኩላሊት ህመም በአልጋ ላይ የወደቀች እህታችን...ልጃችን

#2

√ስም፦ #ምህረቱ_መንግስቴ
√ከ8ተኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጦ ለ11አመታት በየሆስፒታሉ ሲንከራተት የቆየ በሰው እቅፍ ካልሆነ መንቀሳቀስ የማይችል ሲመገብም ሆነ ለተፈጥሮ ግዳጅ መቀመጥ የማይችል
√በከፋተኛ የአጥንት ቁስለት እየተሰቃየ ከግራታፋው 5 የተለያዩ ቁስለቶች ፈሳሽ የሚፈሰው
√ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ውጭ ሀገር እንዲታከም ሪፈር የፃፈለት 1.2ሚሊየን ብር የተጠየቀ ነገር ግን ወላጁን በሞት ያጣና ምንም ገቢ የሌለው አሳዛኝ የ21 አመት ታዳጊ

#3

√ስም፦ #ካሊድ_ኡመር
√የ16 አመት ታዳጊ
√በኩላሊት ህመም የሚሰቃይ ልጃችን..ወንድማችን

በTIKVAH-ETH አተባባሪነት 1የጋራ የባንክ አካውንት እንዲከፍቱ ተደርጓል።

1000278664612 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

💰400,000 ብር (ለማሰባሰብ የታቀደው ገንዘብ)

በትንሹ 40 ሺ አባላት ተሳታፊ እንድትሆኑ እንማፀናለን ፦ 10 ብር * 40,000 የtikvahethiopia አባላት=400,000 ብር

🏷እስካሁን የተገኘው 48,000 ብር

የሞባይል ባንኪንግ ተጠቅችሁ አሁኑኑ ድጋፋችሁን ታደርጉ ዘንድ እንማፀናለን! #TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት የአቢዬ ግዛት የዘመቱ 860 ገደማ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ 30 ወታደራዊ ሰራተኞችና የተባበሩት መንግሥታት ፖሊሶች የግዛቲቱን ሰላም እና ፀጥታ ለመስጠበቅ ለነበራቸው ሚና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሜዳይ ተሸለሙ። በአቢዬ የተባበሩት መንግሥታት ጊዜያዊ የጸጥታ ጥበቃ ኃይል ምክትል አዛዥ ብርጋዴየር ጄኔራል ሙሉ ገብረሕይወት በሽልማቱ ወቅት በአቢዬ የደፈሩ ወታደሮችን አመስግነዋል። የኢትዮጵያ ሴት ወታደሮች የአካባቢው ሴቶች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ለተጫወቱት ሚና ተመስግነዋል።

Via #EshetBekele
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና ተቃዋሚ ሃይሎች ተቋርጦ የነበረውን ውይይት በድጋሚ መጀመራቸው ተገልጿል።

🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጄኔራል ሰዓረ መኮንን የመጨረሻ ሰዓታት
-----------------------------------------------------
(በእንግሊዝኛ የካፒታል ጋዜጣ እንደተፃፈዉ)
-------------------------------------------------------
ከአንድ የጄኔራሉ ቤተሰብ እንደተገኘዉ መረጃ የዚያች ቀን የሆነዉ ይህ ነበር፦

ሰኔ 15 በዕለተ ቅዳሜ ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ ላይ የመከላከያ ሃይል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ቦሌ ደሳለኝ ሆቴል ጀርባ በሚገኝ ቤታቸዉ እየጠበቃቸዉ የነበረዉን ጓደኛቸዉን ለማግኘት እየተቻኮሉ ከቢሯቸዉ ወጥተዉ ወደ ቤታቸዉ አቀኑ፡፡ ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ቤታቸዉ እንደደረሱ ከሳምንት በፊት የተካሄደዉን የልጃቸዉን የመዓሾ ሰዓረን ከዩኒቨርስቲ መመረቅን በማስመልከት እንኳን ደስ ያለህ ለማለት ሲጠብቃቸዉ የነበረዉን ጓደኛቸዉን ቤት ሲያገኙት አቀፉት፤ ቀጥሎም ወደ ቤታቸዉ በረንዳ በማምራት በረንዳዉ ላይ በነበሩት ሁለት ትናንሽ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጡ፡፡

አብዛኛዉን ጊዜ ጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ብርጋዴር ጌጀነራል ገዛኢ አበራ ሲገናኙ ሁለቱም በጋራ ተሳትፈዉባቸዉ የነበሩትን ጦርነቶች በማነሳሳት አስቂኝ ትዉስታዎቻቸዉን በማዉሳት በመሳሳቅ ያሳልፉ ነበር፡፡

ገዛኢ “ስራ በጣም ስለበዛብኝ ነዉ በልጅህ ምርቃት ላይ ያልተገኘሁት በጣም ይቅርታ ጓደኛዬ” ሲለዉ ጄነራል ሰዓረም በምላሹ ፈገግ እያለ “ችግር የለዉም” አለዉ፡፡

ከዚያም የጄኔራል ሰዓረ-ባለቤት የሆኑት ኮለኔል ጥጌ ወይን መጠጥ ካመጣችላቸዉ በኋላ ምግብ ለማምጣት ወደ ኩሺና በምትመለስበት ወቅት የሁለቱ ጄኔራሎች ህይወት በድንገት ጠፋ፡፡ መስፍን ጥጋቡ የሚባል እድሜዉ ከ25-27 የሚገመተዉ ወጣቱ የጄኔራል ሰዓረ ጠባቂ ብቻዉን ወደ መኖርያ ቤቱ በረንዳ በመምጣት መሳርያዉን ደቅኖ ጥይት አዘነበባቸዉ፡፡ ከዚያም ከፍተኛ ጩሀት አካባቢዉን አደበላለቀዉ፡፡ ኮለኔል ፅጌ ከልጃቸዉ ጋር በመሆን ከተደበቁበት ክፍል ሳይወጡ ማልቀስና መጮህ ጀመሩ፡፡ የተኩስ እሩምታ በብዛት ቢሰማም አንድም ሰዉ ዝር አላለም፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከቤቱ ዉጪ የነበሩ ሌሎች ጠባቂዎች ሲመጡ ጄነራሎቹ መሬት ላይ ተዘርግተዉና ከፍተኛ ደም እየፈሰሳቸዉ አገኟቸዉ፡፡ በጄኔራሎቹ መሃከል ጠባቂዉ መሳፍንትም ተዘርግቶ ነበር፡፡ ቤተሰቦቹ ሁለቱንም ጄኔራሎች ይዘዉ ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ወደ ዋሺንግተን ሜዲካል ማዕከል ቢያቀኑም ሆስፒታሉ ሳይደርሱ ሁለቱ ጄኔራሎች አረፉ፡፡

አንድ የቤተሰቡ የቅርብ ሰዉም እንዲህ አለ “ጄኔራሎቹ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ከጄኔራሎቹ መካከል ተዘርግቶ የነበረዉ ጠባቂ ሁሉም ሰዉ የሞተ መስሏቸዉ ነበር ግን ሰዉዬዉ አልሞተም ነበር፡፡ የሞተ ለማስመሰል ተዘርግቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ከዛን ተነስቶ ለመሮጥ ሞከረ፣ ሌሎቹ ጠባቂዎች ሲዩት ተኩሰዉ እግሩን መቱት፤ ከዚየም ወደ ትንሽ የጥበቃ ክፍል ሮጦ ገባ፤ ከዚያ በኋላ ሰዉዬዉ ራሱ ላይ እስኪተኩስ ድረስ ብዙ የተኩስ ልዉዉጦች ነበሩ፤ ከዚያም ጥበቃዎቹ ጎትተዉ አዉጥተዉት ወደ ሆስፒታል ወሰዱት”፡፡

ከዚህ ሁሉ ግድያ በፊት ጄኔራል ሰዓረን መኖርያ ቤት ለ4 ወራት ሲጠብቅ የነበረዉ ወታደር ከጄኔራሉ ቤት እንዲቀየር መዳቢዎችን (ሃላፊዎችን) ጠይቆ ነበር፡፡ ከዚያም ዉጪ የጄኔራሉ ባለቤት የሆኑት ኮለኔል ፅጌ የመሳፍንትን ሁኔታ ስላልወደዱት ባለቤታቸዉን (ጄኔራል ሰዓረ) ጠባቂዉን በሌላ ጠባቂ እንዲቀየር በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ጄነራሉ ሃሳባቸዉንና ጭቅጨቃቸዉን ባለመስማት ጠባቂያቸዉን በማመን ቀጠሉ ይላል ለካፒታል ጋዜጣ የተሰጠዉ ምላሽ፡፡

Via #ኤግል_ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአሜሪካ #የጥላቻ_ንግግርን የሚያሠራጩ ኢትዮጵያዊያን እንዴት በህግ ይጠየቃሉ
.
.
በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ኢትዮጵያዊያንን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የዜጎች ምክር ቤት አስታውቋል።

ያነጋገርናቸው የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት አቶ አምሳሉ ፀጋዬ፤ ወንድም ወንድሙን በማጣላት፤ ብሔር ከብሔር በማጋጨት እንደ ሃገር ለመቀጠል ፈታኝ ሆኗል፤ ይህንን የሚያደርጉ ግለሰቦችን ለማስተማር ብዙ እየተሞከረ ቢሆንም ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለመጣ ምክር ቤቱ ግለሰቦቹን ወደ ህግ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ይናገራሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር በሌላ ማህበረሰብ በማሰራጨት፤ ሞትና መፈናቀልን ማስከተል በሕግ እንደሚያስቀጣ ይገልፃሉ።በዚህ ረገድ የሚጠቅሱት ፈርስት አመንድመንት የተሰኘው የአሜሪካ ህግን ነው።

እሳቸው እንደሚሉት ምንም እንኳን በፈርስት አመንድመንት የመናገር ነፃነት የተጠበቀ ቢሆንም በዚሁ ህግ ላይ በመናገር ነፃነት የማይካተቱ ድርጊቶችም ተዘርዝረው ይገኛሉ።

"ግድያ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ብሔርን ከብሔር (ማኅበረሰብን ከማኅበረሰብ) የሚያጋጭ ከሆነ፤ የጥላቻ ንግግሩ ያስከተለው የጉዳት መጠን ተለይቶ ግለሰቦቹን ተጠያቂ ለማድረግ ይቻላል" ይላሉ አቶ አምሳሉ።

የሕግ ሂደቱን የሚከታተል የጠበቆች ቡድን ያለ ሲሆን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ማስረጃዎችን በማቅረብ የጥላቻ ንግግርን የሚያሰራጩ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ እንደሚያደርጉም ያክላሉ።

"አብዛኞቹ እዚህ የሚኖሩ ለአገር የሚያስቡ ናቸው፤ ነገርግን የመጡበትን ማህበረሰብ በመርሳት ያ - ማህበረሰብ ቢፈርስ ደንታ የሌላቸው ጥቂቶች አሉ " የሚሉት አቶ አምሳሉ በህጉ መሰረት ቅጣቱ ከእስር ወደ አገር ተጠርንፎ እስከመመለስ የሚደርስ እንደሆነ ይናገራሉ።

በሕጉ መሠረት ጥላቻን መንዛት ፤ የግድያ ዛቻና ቅስቀሳ፣ የወሲብ ፊልም፤ ወንጀል ለመፍጠር መደራጀትን መሠረት ያደረገ ቅስቀሳን የሚያደርግ ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ ያስረግጣሉ።

እርሳቸው እንደሚሉት እንቅስቃሴው አሜሪካን አገር ብቻ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ በሌሎች አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እየተነጋገሩ መሆናቸውንም ገልፀውልናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ንግግር አድርገው ከሆነ ጥያቄ ያነሳንላቸው አቶ አምሳሉ" ምንም ምክክርም ሆነ ንግግር አላደረግንም" በማለት የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት ብቻ እንቅስቃሴውን እንደጀመሩ ነግረውናል።

ከምክር ቤቱ ጋር ግንኙነት ባይኖራቸውም በሚኖሩበት ሜኒሶታ ግዛት ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደ ጀመሩ የነገሩን ደግሞ የአንድ ጥብቅና ቢሮ ባልደረባ የሆኑት አቶ ነጋሳ ኦዱዱቤ ናቸው።

እርሳቸውም ከአቶ አምሳሉ ጋር ተመሳሳይ ኃሳብ ነው ያላቸው፤ 'ፈርስት አመንድመትን' ጠቅሰው የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩን ከሕግ ፊት ማቅረብ እንደሚቻል ያረጋግጣሉ።

"በአሜሪካ የመናገርና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ለብዙ ዘመናት የተከበረ ነው፤ ይሁን እንጂ 'ፈርስት አሜንድመንት' ላይ የተወሰኑ ገደቦች አሉበት" ይላሉ።

ከእነዚህም መካከል የሀሰት ንግግር፣ ስም ማጥፋት፣ ለወንጀል የሚያነሳሱ ንግግሮች፣ ወደ ኃይል ተግባር የሚያነሳሱና የሌላውን መብት የሚጥሱ ንግግሮች በሕጉ ተገድበው ይገኛሉ።

ተፅዕኖው ኢትዯጵያ ውስጥ በሚታይ ድርጊት ግለሰቦችን አሜሪካ ላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚያዋጣ ክርክር ነው ወይ? ስንል የጠየቅናቸው አቶ ነጋሳ " የጁሪዝዲክሽን (የፍርድ ቤቶች የማየት ስልጣን) ጉዳይ አከራካሪ ነው። ነገር ግን ከሶ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ መከራከር ይቻላል፤ ውጤቱ ኢትዮጵያ ነው ብሎ መከላከል ይቻላል" ሲሉ ይህ በፍርድ ሂደት እንደሚታይ ይናገራሉ።

ከዚህም ባሻገር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚኖረው ጥገኝነት ጠይቆ በመሆኑ ይህንን ከሚቆጣጠረው 'አሜሪካ ኢምግሬሽን ሰርቪስ' (ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ) በክስ ሂደቱ ሊካተት እንደሚችል ይናገራሉ።

"እንደ ኢትዮጵያዊያን አገሪቷ ወደ ፍቅርና ሰላም እንድታመራ የሞራል ግዴታ አለብን" የሚሉት አቶ ነጋሳ ነገሩን ወደ ህግ ከመውሰድ ይልቅ የሚያዋጣው የኢትዮጵያ ደህንነት ግድ እንደሚለው ዜጋ መመካከር ነው ይላሉ።

Via #BBC
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርንፈው ይመጣሉ...

"ወንድምን ከወንድሙ #በማጣላት፤ ብሔር ከብሔር #በማጋጨት እንደ ሃገር ለመቀጠል ፈታኝ ሆኗል፤ ይህንን የሚያደርጉ ግለሰቦችን ለማስተማር ብዙ እየተሞከረ ቢሆንም ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለመጣ ምክር ቤቱ ግለሰቦቹን ወደ ህግ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።" የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ዜጎች ምክር ቤት/የህዝብ ግንኙነት አቶ #አምሳሉ_ፀጋዬ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ብ/ጄኔራል #አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ ከBBC አማርኛ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ከታች ያንብቡት👇
https://telegra.ph/ብጄኔራል-አሳምነውን-ቀድቻቸዋለሁ-ጋዜጠኛ-ፋሲካ-ታደሰ-07-04
#update የኦሮሚያ ክልል የሰላምና የልማት ኮንፍረንስ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለፀ። የሰላምና የልማት ኮንፍረንስ ከነገ ጀምሮ በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ የከተማ አስተዳድሮች እና ወረዳዎች የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል።

በኮንፍረንሱም በኦሮሚያ ክልል ሰላምን ስለማስፈን እና በክልሉ የህግ የበላይነትን ማስከበር የሚሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚመከር የኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

እንዲሁም የክልሉን ህዝብ ከልማት ተጠቃሚ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመከርም ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል፣ ያጋጠሙ ችግሮችን በመቅረፍ በአንድነት በመሆን የጋራ አቋም መያዝ ላይ ውይይት እንደሚደረግም አስገንዝበዋል።

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል #የተሻለ እና #አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ሕጋዊ ትጥቅን ‹‹የማስፈታት ሥራ እንደተጀመረ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ›› ተብሏል፡፡ ተጨማሪውን ያንብቡ👇

https://telegra.ph/አማራ-ክልል-ETHIOPIA-07-04
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ፦
https://telegra.ph/ከአማራ-ብሔራዊ-ክልላዊ-መንግስት-በወቅታዊ-ጉዳይ-ላይ-የተሰጠ-መግለጫ-07-04
በሩሲያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን የተሾሙት አምባሳደር #አለማየሁ_ተገኑ ሰኔ 26 ቀን 2011 ዓ.ም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል።

Via #EPA
🗞ቀን ሰኔ 27/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia