TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጳጉሜ 1/2011 በመላ ሀገሪቱ የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ ይከበራል!

የፊታችን ጳጉሜ 1/2011 የፀሎትና ምህላ ቀን ሆኖ በመላ ሀገሪቱ እንዲከበር የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ወሰነ። ጉባኤው የፀሎትና ምህላ ቀኑን እንዲሁም መጪውን አመት አስመልክቶ በፅ/ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ነው። በመግለጫው ጳጉሜ 1 መላው ኢትዮጵያውያን በአንድ መንፈስ በመነሳት ለሀገርና ለወገን የሚያስቡበት እና ፀሎትና ምህላ የሚያደርጉበት ሆኖ እንዲውል ጉባኤው መወሰኑ በመግለጫው ተጠቅሷል። በሀገሪቱ ያለው ውስብስብ ችግር ተወግዶ አዲሱን አመት በሰላም፣ ፍቅርና አንድነት በአዲስ መንፈስ እንድንቀበል ያለው ጉባኤው በአዲሱ አመት ለሀገር የሚበጀውን እንድንሰራ፣ የቀደመውን ፍቅር የምንመልስበት እንዲሆን ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሶሪያ #PEACE😢ከአመታት በፊት ይህቺ ምድር ማንም እንዲህ ወደ ፍርስራሽነት ትቀየራለች ብሎ አልገመተም፤ግን ሆነ! ሶሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን አጣች፤ በሚሊዮኖች ተወልደው ካደጉበት ሀገር ተሰደዱ!! ጦርነቱ ዛሬም አላባራም ዛሬም ሰው ይሞታል!! #ያሳዝናል! #ልብ_ይሰብራል! ሶሪያውያን ይህ ከመሆኑ በፊት ከስሜታዊነት ወጥተው፤ በሰከነ መንገድ ተረጋግተው ተነጋግረው ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ባልመጣ ነበር። ማስተዋልን የመሰለ #ጥበብ ከየት ይመጣ ይሆን?

መገንባት እንደማፍረስ ቀላል አይደለም!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲሱ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ!

በዛሬው ዕለት ምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ የፈፀሙት አቶ ጥራቱ ሐዋሳ #የቀደመ ስሟን በሚያስጠብቅ ሁኔታ ሁሉም ዜጎች በሰላም የሚኖሩባትና ሀብት የሚያፈሩባት እንዲሁም ምቹ የኢንቬስትመንት መዳረሻ ከተማ እንድትሆን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በታማኝነት እና በትጋት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንታረቅ

እንታረቅ በሚል በተዘጋጀዉ መርኃግብር ላይ በርካታ ሰዎች ባለመግባታቸው ቅሬታቸውን እያቀረቡ ነው፡፡ ያነጋገርናቸው ቅሬታ አቅራቢዎች ፕሮግራሙ ላይ ለመሳተፍ ከክልል ከተማ ከተጠቀሰው ጌዜ ቀድመን ብንመጣም መግባት አልቻልንም በማለት ቅሬታዎችን በጁፒተር ሆቴል በር ላይ ለነበሩ የሆቴሉ ሰራተኛኞችና ለጸጥታ አካላት ያቀረቡ ሲሆን የፕሮግራሙ አስተባባሪ በበኩላቸው "ቦታ ስለሞላ ነው የመረጥነው ሰው የለም ብለዋል በቀጣይ ሳምንት ተመሳሳይ ፕሮግራም እናዘጋጃለን ሰፊ አዳራሽ ባለማዘጋጀታችን ግን ይቅርታ እንጠይቃለን" የሚል ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቃውሞ አሰማች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ነሐሴ 24/2011 ባወጣችው መግለጫ እሁድ ነሐሴ26/2011 በቀሲስ በላይ መኮንን በኦሮሚያ ባህል ማዕከል የተጠራውን እወጃ እና ጋዜጣዊ መግለጫ እውቅና እንደሌለው እና ሕገ ወጥ እንደሆነ አስታውቃለች። ቤተ ክርስቲያኗ አያይዛም መንግስት ይህን ሕገ ወጥ ተግባር እንዲያስቆም አሳስባለች።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ የእውቁ ኬንያዊ ፎቶ ጋዜጠኛ መሐመድ አሚን ልጅ ሳሊም አሚን ገለፁ። ሳሊም አሚን በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ከሚሲዮኑ ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ማስተዋወቅ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከአምባሳደር #መለስ_ዓለም ጋር መክረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
«15 ሚሊዮን ብር #በማጭበርበር ከባንክ የወሰደ ሰው ታስሯል። በፌስቡክ ላይ ያለው ታሪክ ይኸ ሰው የታሰረው መንግሥትን ስለተቃወመ ነው የሚል ነው» የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ዑመር ተቃዋሚዎች ለምን ይታሰራሉ? ተብለው በOMN ሲጠየቁ።

«ለአካል ጉዳተኞች የሚገዙ #ዊልቸሮችን አጭበርብሮ የተሰባበሩ ያመጣና በኦዲት ከተረጋገጠ በኋላ የታሰረ ሰው አለ። እሱም በሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶው እየዞረ ይኸ ሰው የታሰረው በመንግሥት ላይ ቅሬታ ስላቀረበ ነው የሚባል ነገር አለ»

#ኦሮሚያ_ሚዲያ_ኔትዎርክ

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በዛሬው ዕለት ያደረጉት ንግግር...

📹#DW

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ትምህርት_ሚኒስቴር || በየትኛውም መማርያ መጽሀፍት ላይ የኢትዮጵያ ካርታ ስራዎች መስሪያ ቤት ከሚሠጠው ካርታ ውጭ ለማስተማሪያነት እንደማይውል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የሚገኙ ካርታዎች ለተማሪዎች ትክክለኛውንና ማወቅ የሚገባቸውን ካርታ በማሣየት ረገድ ችግሮች መታየታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ተናግረዋል። በመሆኑም በሁሉም የትምህርት ዘርፍ የሚሠሩ አካላት በኢትዮጵያ ካርታ ሥራዎች የሚዘጋጁ #ካርታዎችን ብቻ ለማስተማሪያነት መጠቀም እንዳለባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡ 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ መምጣት ያለበት ምእመናኑ #ተወያይቶበት እንጂ በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት መሆን የለበትም!" ቅዱስ ሲኖዶስ
.
.
የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የጠራውን መግለጫ መንግሥት እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ጠየቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቤተ ክህነት በኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ የተጠራውን መግለጫ እንደማያውቀውና እውቅናም እንዳልሰጠው የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ ርዕሰ ደብር መሀሪ ኃይሉ በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ በላይ መኮንን ምንም እንኳ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ትልቅ ሃላፊነት የነበራቸው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የኦሮሚያ ክልል እንባ ጠባቂ ቢሮ ሃላፊ መሆናቸውን የቤተክህነት የስብከተ ወንጌል እና ሃዋሪያዊ ተልእኮ መምሪያ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሶሎሞን ቶልቻ ገልፀዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ መምጣት ያለበት ምእመናኑ ተወያይቶበት እንጂ በተወሰኑ ሰዎች ፍላጎት መሆን የለበትም ብሏል።

🏷ከቀናት በፊት #ቢቢሲ ያናገራቸው የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ የኦሮሚያ ቤተክህነትን የማቋቋም ጥያቄ ከማንነት እና ከቋንቋ ጋር የሚገናኝ እንደሆነ ገልፀው ነበር። ኮሚቴው ጥያቄውን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ እንደነበርም ገልፀው ነበር።

ምንጭ፦ #BBC/#ቢቢሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እየለማ ያለዉ የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱሰትሪ ፓርክ /Yirgalem Integrated Agro Industrial Park/ በከፊል ስራ መጀመሩን ኮርፖሬሽኑ አሳውቋል፡፡

በተጨማሪም በርካታ የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እየተመዘገቡ የሚገኙ መሆኑንና በአሁን ሰዓትም ለ11 የውጭና የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ማምረቻ ሼዶች በመገንባት ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከሚያስገነባቸው ከእነዚህ ሼዶች መካከል ቀድሞ ተጠናቅቆ ወደ ስራ የገባው የኔዘርላንዱ SUNVADO Organic Avocado Oil Manufacturing PLC አንዱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ምርቶችን ወደ አሜሪካ ፣ጃፓን እና አውሮፓ አገራት ለመላክ ምርት የጀመረ መሆኑንና በቅርቡም ለእነዚህ አለም አቀፍ ገበያዎች ምርታቸውን እንደሚልኩ ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

Via www.snnprsipdc.com

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል የጎብኚ ቁጥር አሽቆልቁሏል!

በደቡብ ክልል #የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው #አለመረጋጋት የጎብኚዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የስራ ሃላፊ እንዳሉት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ክልሉን የጎበኙ የውጭ አገር ጉብኚዎች ቁጥር አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ አየለ እንዳሉት በክልሉ የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው አለመረጋጋት በጎብኚዎች እንቅስቃሴ ላይ የራሱን ተፅህኖ አሳድሯል።

ለአብነትም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ወደ ክልሉ የመጡ የውጭ አገር ጎብኚዎች አምና ከነበረው በአራባ ዘጠኝ ሺህ ያህል ቀንሶ መገኘቱን ነው የቢሮ ሃላፊዋ ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ የጠቀሱት። የቱሪዝም ዘርፈ ጥንቃቄ የሚያሻው በትንሽ ስጋት ሊደናቀፍ የሚችል መሆኑን የጠቆሙት ወይዘሮ ሰብለ ፀጋ በቀጣይ መስህቦችን መልሶ የማስተዋወቅ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።

በደቡብ ክልል የሆቴሎች ህብረት ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ ጌታቸው በከተማው ተፈጥሮ በነበረው ሁከት የጎብኚዎች ቁጥር አስከመቆም በመደረሱ በከተማው በሆቴል ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች ላይ የገበያ መቀዛቀዝ ማጋመጠሙን ተናገረዋል። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ መንግስት ባከናወናቸው የማረጋጋት ስራዎች ዘርፉ አንፃራዊ መሻሻል እያሳየ መምጣቱን ነው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደጀኔ የገለጹ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ገለቱ ገረመው በበኩላቸው የአስተዳደሩ የፀጥታ መዋቅር ከጊዚያዊ ኮማንድ ፖስትና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ከጀመረ ወዲህ ከተማዋ ወደ ነበረ ሰላሟ እየተመለሰች ትገኛለች ብለዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  አገልግሎት የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽህፈት ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ”በገቢና የመንግሥት ንብረት ከብክነት በመከላከል እመርታ” አስመዘገብኩ አለ። ጽህፈት ቤቱ 2011 በጀት ዓመትና አፈጻጸምና የ2012 ዕቅድ ዙሪያ ከሠራተኞቹ ጋር ዛሬ ተወያይቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አካል ጉዳተኞችን በሰፊው ታሳቢ ያደረገ የፋሽን ሾው ፕሮግራም እሁድ ነሐሴ 26 /2011 ዓ.ም በ እዩ ፒክቸርስ የተዘጋጀ ዳህላክ ፋሽን ዊክ በኢትዮጵያን ስካይ ላይት ሆቴል ይቀርባል። ለዚህም ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ድጋፍዎን ያሳዪ።

ትኬት በር ላይ ማግኘት ይቻላል...

ለበለጠ መረጃ 0947317608 ይደዉሉ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ7 የማዕድን ምርመራና ለ3 የማዕድን አምራቾች ፍቃድ ተሰጠ!

የኢፌድሪ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የፈቃድ መስፈርቶችን አሟልተዋል ላላቸው በማዕድን ፍለጋና ምርት ለማምረት ፈቃድ ለጠየቁ ኩባንያዎች ፈቃድ ሰጠ።

በዚህም መሰረት ዛሬ ለ7 በማዕድን ምርመራ ለተሰማሩና ሶስት ደግሞ የማዕድን ምርት ለማምረት ፍቃድ ለጠየቁ 6 ኩባንያዎች ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ፍቃድ ሰጥቷል።

ኩባንያዎቹ ለኢንቨስትመንት ወጪ በአጠቃላይ 258 ሚልዮን 500 ሺህ ብር በላይ የመደቡ ሲሆን፤ ለ281 ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ይሆናሉ ተብሏል።

ኩባንያዎቹ የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገርም የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ ያሉት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴሩ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ኩባንያዎቹ ስራቸውን የፌደራልና የክልሎችን የመዕድን አዋጆች፣ ደንቦችና መመርያዎችን መሰረት አድርገው ያከናውናሉ ብለዋል።

ዶክተር #ሳሙኤል አክለውም ኩባንያዎቹ ተግባራቸውን በጥንቃቄና ቅልጥፍና በተሞላበት ሁኔታ በማከናወን ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት እንዲያደርጉ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤምሬትስ አየር መንገድ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ቆይታ!

ትላንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል የኤምሬትስ አየር መንገድ ከጋዜጠኞች ጋር ባደገው የውይይት መድረክ ላይ አየር መንገዱ በአገልግሎት ዘርፉ በሚያካትታቸውና በቅርብ አገልግሎት መስጠት በጀመረባቸው ስራዎች ላይ በአትዮጲያ የኤምሬትስ ማናጀር በሆኑት አቶ ማኖጅ ናየር በኩል ገለጻ የተሰጠበት ሲሆን ከጋዜጠኞችም ጥያቄዎች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የኢምሬትስ አየር መንገድ በንጽጽር በአጭር ጊዜ ውስጥ አንጋፋ የሆነ አየር መንገድ መሆኑንና የመጀመሪያውን በረራ በኦክቶበር 25 1985 እ.ኤ.አ ወደ ካራቺ ካደረገበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 34 ዓመታት ውስጥ የአገልግሎቱን ስፋት ወደ 158 መዳረሻዎችና ወደ 85 ሀገራት በማሳደግ የበራራና የካርጎ አገልገሎት መስጠት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይ አየር መንገዱ 58.6 ሚሊዮን ያክል ደንበኞችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡ በአፍሪካም በ23 ሀገራት መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን ኢትዮጲያም ከነዚህ መዳረሻዎች አንዷ መሆኗን በውይይቱ ወቅት ተገልጻል፡፡ ከዛም በተጨማሪ ወደ ሰሜን አሜሪካ 13 ወደ ደቡብ አሜሪካ 4 ወደ ኢሮፕ ሀገራት 41 ወደ ኤዢያ 60 ወደ መካከለኛው ምስራቅ 11ና ወደ አውስትራሊያ 7 ያክል በረራዎችን እየሰጠ ያለ አየር መንገድ ነው፡፡  

#TIKVAH_ETHIOPIA

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/የኤምሬትስ-አየር-መንገድ-ከጋዜጠኞች-ጋር-ያደረገው-ቆይታ-08-30
#Emirates

አለማቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፦

“የኢትዮጲያ አየር መንገድ ከአብዛኞቹ አየር መንገዶች ትርፋማና ስኬታማ አየር መንገድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እናንተ ይሄንን እያወቃችሁ በኢትዮጲያ በዚህ ዘርፍ ለመሳተፍ እንዴት መረጣችሁ?”

የኤሜሬትስ አየር መንገድ ማናጀር፦

“እኛ እንደ አንድ በዚህ ቢዝነስ ውስጥ እንደተሳተፈ ድርጅት በዘርፉ የተሻለ ነገርን ማቅረብ አማራጭ አድርገን እየሰራን እንገኛለን፡፡” 

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የግድያ ሙከራ ጨምሮ እስርና እንግልት እየደረሰብን ነው ሲሉ የአረናና ትዴት አመራሮች ገልፀዋል!

በዓረናና ትዴት አመራሮችና አባላት ላይ የግድያ ሙከራ ጨምሮ እስርና እንግልት እየደረሰ መሆኑ ሁለቱ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታወቁ፡፡ የዓረና ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ "ሕገ መንግስት ይከበር» በሚባልበት ወቅት ሕገ መንግስቱ የሚሰጠንን መብት ተነፍገን እንግልት እየደረሰብን ነው" ብለዋል፡፡ በመላ ሀገሪቱ በተለየም በትግራይ 'አፈና እየተፈፀመ' ነው ሲሉም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የትግራይ ዴሞክራስያዊ ትብብር ቃል አቀባይ አቶ ሙሉብርሃን ሃይለ በበኩላቸው ሰሞኑን በመቐለ የተካሄደው 'ሕገ መንግስትና ፌደራል ስርዓትን ማዳን' የተሰኘው መድረክ በትግራይ ያሉ የፖለቲካ ሀይሎች ያገለለ ነበር ሲሉ ተችተዋል፡፡ በመጪው ምርጫ ጉዳይ የተናገሩት የትዴት ቃል አቀባይ አቶ ሙሉብርሃን ሃይለ ምርጫው መካሄድ ያለበት አስቀድሞ የፖለቲካ ምህዳሩን አስፍቶ መሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ወርቁ በዳዳ ከታሰሩ 15 ቀን ሆኗቸዋል!

ነሃሴ 10 ቀን 2011 ዓ/ም ከመኖሪያ ቤታቸው የኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆኑ በተነገረላቸው ሲቪል በለበሱ ሰዎች የተወሰዱት መምህሩ ዶክተር ወርቁ በዳዳ ከታሰሩ 15 ቀን እንደሆናቸው፤ እስካሁን ድረስም ለመታሰራቸው ምክንያት እንዳልቀረበ፤ ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ቤተሰቦቻቸው ለTIKVAH-ETH ተናግረዋል።

ከቤተሰቦቻቸው መካከል ለTIKVAH-ETH በስልክ የተናገሩት፦

"ነሃሴ 10 ቀን 2011 ዓ/ም - 7 ሰዓት ከቤት ሊወጣ ሲል ነው የመጡት፤ ሰቪል ለብሰው ነው የመጡት ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ነው የመጣነው ብለው ቤት ፈተሹ ከዛም ይዘውት ሄዱ። እስካሁን ይሄነው የሚባል ነገር አልተናገሩም፤ ቡራዩ ወረዳ 1 ፖሊስ ጣቢያ ነው ያስቀመጡት። ፍርድ ቤትም ቀርቦ ይሄን አጥፍተሃል የሚሉት ነገር የለም። ላፕቶፑ፣ ስልኩ ፣የሱም የባለቤቱም ሃርድዲስኮች፣ ካሜራ፣ፍላሽ.. የቀረ ነገር የለም ተወስዷል። አንድ ጊዜ ብቻ ለምርመራ ቀርበው አናግረውታል ከዛ በተረፈ የላፕቶፕና የሌሎች ሰነዶች ውጤቶች ስላልመጡን ነው ምክንያታቸው፤ 15 ቀን ሙሉ እንዲህ ነው ተብሎ ፍርድ ቤትም አልቀረበም፤ እንዲህ አጥፍተሃልም አልተባለም።"

እያያዛቸው እንዴት ነው?

"እዛ ያሉት #ፖሊሶች ጥሩ አመለካከት ነው ያላቸው፤ #ድብደባም ምንም ነገር አልተካሄደባትም። ግን ለምን አስረው እንዳስቀመጡት እኛም አልገባንም"

በስልክ ያናገርናቸው እኚሁ የዶ/ር #ወርቁ_በዳዳ ቤተሰብ ለበላይ አመራሮችም ጉዳዩን እንዲያብራሩ ቢጠይቁም ምላሽ እንዳላገኙ ተናግራዋል። የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አቶ_ርስቱ_ይርዳው

ቀጣዩ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት ማን ይሆኑ?

TIKVAH-ETHIOPIA ከቤተሰቡ አባላት ታማኝ ምንጮች እንደሰማው ከሆነ-አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን በመተካት የደቡብ ክልልን በፕሬዘዳንትነት የሚመሩት አቶ #ርስቱ_ይርዳው ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

•በትላንትናው ዕለት #ሪፖርተር_ጋዜጣ የደቡብ ክልል ቀጣይ ፕሬዘዳንት አቶ መለስ አለሙ ሆነው ሊሾሙ እንደሚችሉ መግለጹ አይዘነጋም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia