TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጊዜ ያለፈባቸው ከ200 ሺ በላይ የቫት ማሽኖች በአዲስ ቴክኖሎጂ ሊቀየሩ ነው!

በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ200 ሺ በላይ የሚሆኑ የቫት (ካሽ ሬጂስተር) ማሽኖች ጊዜ ያለፈባቸውና ለማጭበርበርም ክፍት በመሆናቸው በአዲስ ቴክኖሎጂ ሊቀይራቸው ጥረት እያደረገ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የገቢዎች ሚኒስቴር ከክልል የዘርፉ ኃላፊዎች ጋር ትናንት ውይይት ባደረጉበት ወቅት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በእያንዳንዱ ነጋዴ እጅ ያለው የቫት ማሽን ለደረሰኝ ማጭበርበር እና ለአሰራር ክፍተት እያጋለጠ ይገኛል።

በመሆኑም ማሽኑን በአዲስ ቴክኖሎጂ መቀየር አስፈላጊ ሆኗል። ያደጉ አገራት የሚጠቀሙባቸውን የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን እና ዘመኑ የሚጠይቃቸው አሰራሮችን የያዘ ቴክኖሎጂ በቀጣይ እንዲተገበር ጥናት እየተደረገ ይገኛል።

የቫት መሳሪያውን ለመቀየር የሚደረገው ጥረት እስኪጠናቀቅ ድረስ በማሽኑ አማካኝነት የሚሰሩ ህገወጥነቶችን መከላከል የሁሉም ክልሎች እና መስተዳድሮች ኃላፊነት መሆኑን ወይዘሮ አዳነች አሳስበዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እናመሰግናለን!

እስካሁን በኡ/ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች በድምሩ ከሁለት መቶ በላይ መፅሐፍት ተሰብስቧል፡፡ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ግባችን ከአ/ አበባና ዙርያዋ ከሚጠጉ ቤተሰቦች 1000 መፅሀፍትን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ከከተማ ወጣ ላሉ ቤተ-መፅሐፍት መለገስ ነው፡፡ የቅንድል ኢትዮጵያ የበጎ ፍቃደኞች ማህበር አባላት እያሳያችሁ ላላችሁ ጥረት ምስጋናችን ወደር የለውም፡፡

📚የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሜክሲኮ በመሚገኘው ቡክ ኮርነር እየሄዳችሁ መፅሃፍ ማስቀመጥም ትችላላችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሐዋሳ ያለው ኮማንድ ፖስት ቢነሳም ችግር እንደማይገጥም ተገለፀ!

በደቡብ ብሔር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ የሆነችው የሀዋሳ ከተማ አሁን አስተማማኝ ሰላም ላይ የምትገኝ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ ቢነሳም ችግር እንደማይከሰት ተገለጸ።

የሀዋሳ ከተማ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ ኮሎኔል ተክለብርሃን ገብረመድህን እንደገለጹት፤ በደቡብ ብሔር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አንዳንድ ከተሞች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ አለመረጋጋት ምክንያት በሀዋሳ ከተማ የተጣለው ኮማንድ ፖስት ቢነሳም ችግር አይፈጠርም። ከተማዋ አሁን ላይ በህብረተሰቡ ከፍተኛ እገዛ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ሙሉ ለሙሉ ተመልሳለች ብለዋል።

እንደ ኮሎኔል ተክለብርሃን ገለጻ፤ ሀዋሳ ከተማ የተረጋጋችው በኮማንድ ፖስቱ ኃይል ሳይሆን በነዋሪው ህብረተሰብ ከፍተኛ ጥረት ነው። ኮማንድ ፖስቱ ከህብረተሰቡ ጎን በመቆም በድጋፍ ሰጪነት እየሰራ ይገኛል።

ህብረተሰቡ ግን ችግር በተመለከቱባቸው አካባቢዎችና ግለሰቦችን በእራሱ እየያዘ ለህግ አካላት በማጋለጥ በየጊዜው ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም ከተማዋ የተረጋጋች በመሆኗ የመዝናኛ ቦታዎች 24 ሰዓት አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።

ከተማ ላይ ሠላም እንዳይመጣ ህገወጥ ተግባር ሲፈጽሙ ተገኝተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 68 ሰዎች በኮማንድ ፖስቱ ሥር መያዛቸውን የገለጹት ኃላፊው፤ ይሁንና ከተያዙት ሰዎች መካከል የመንግስት ኃላፊዎች እንደማይገኙበት ተናግረዋል። በቀጣይም እጃቸው በጉዳዩ ውስጥ ያለባቸውን ሰዎች ለህግ ለማቅረብ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑና ሀዋሳ በአሁኑ ሰዓት ማንኛውም ግለሰብ በነጻነት የሚንቀሳቀስባት ከተማ በመሆኗ ምንም የሚያሰጋ ጉዳይ እንደሌለ ተናግረዋል።

https://telegra.ph/ETH-08-31-3

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሙስጠፌ ዑመር...

"....በግሌ ምርጫ ቢካሄድ ጥሩ ነው የሚል ሃሳብ አለኝ። አሁን ካለው የክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ምርጫ ብናካሂድ አሁን እኔ ያለሁበት ፓርቲ /የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ #ያሸንፋል የሚል እምነት አለኝ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንዳትጭበረበሩ!

በዚህ መሰሉ የዝርፊያ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን የሚመለከተው አካል ትኩረት አድርጎ የእርምት ስራ ሊሰራ ይገባል። በርካቶች በሀሰተኛ የሞባይል መተግበሪያ ገንዘባቸው እየተወሰደባቸው ነው። እናንተም ጥንቃቄ አድርጉ መተግበሪያዎችን/apps/ ከplaystore ላይ ወይም ከAppStore ላይ ብቻ ያውርዱ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል። ለመላው ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!

ፎቶ📸AMANI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ4G ኔትዎርክ ማስፋፊያ ሊደረግ ነው!

ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 የበጀት ዓመት የአገልግሎቱን ጥራት በማሻሻል 5ነጥብ1 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል የሞባይል ኔትወርክ አቅምን እንደሚገነባ አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የሦስት ዓመታት ስትራቴጂክ ዕቅድና የ2012 በጀት ዓመትን ዕቅድ አስመልክተው በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 5 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ የሚችል ተጨማሪ የሞባይል አገልግሎትን ለመተግበር ተዘጋጅቷል፡፡

እንደ ስራ አስፈጻሚዋ ገለጻ፤ በበጀት አመቱ በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የሚከናወንና የዳታ ትራፊክ ዕድገትን መሰረት ያደረገ የ4G ኔትወርክ ማስፋፊያ የሚደረግ ሲሆን ይህም እስከዛሬ ከጥራትና ኔትወርክ ችግር ጋር ተያይዞ ሲስተዋል የቆየውን የደንበኞች ችግር እንደሚያቃልል ይታመናል ብለዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በኢትዮጵያ የሱማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ከሆኑት ሚስተር አብዱልሀኪም አብዱላሂ ጋር በጽህፈት ቤታቸዉ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ትብብር ጉዳይ ዙርያ ዉይይት አድርገዋል፡፡

በዉይይታቸው ሚኒስትር ዴኤታዉ የኢትዮጵያ መንግስት በ2012 የትምህርት ዘመን የሶማልያ ዜጎችን ጨምሮ ለተለያዩ የጎረቤት አገራት ዜጎች በቅድመ ምረቃ እና ድህረምረቃ ፕሮግራሞች ከ1ሺህ በላይ የነፃ ትምህርት ዕድሎችን መስጠቱን ገልፀዋል።

ለሶማልያ ፌደራል ሪፐብሊክ ላለፉት አምስት አመታት በተጠናከረ ሁኔታ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ የነፃ ትምህርት ዕድል መመቻቸቱን እና ይህም የሁለቱን ሀገራትና ህዝቦች የጋራ ትስስር እንደሚያጠናክር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ አምባሳደርም በትምህርት ዘርፍ ለዜጎቻቸዉ ለተደረገው ትልቅ እገዛ በሀገራቸዉ መንግስት ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዉ እገዛዉ ለወደፊትም እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር አራተኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ። ምክር ቤቱ በቆይታው የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት የስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ባለፈም የክልሉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ዋና ኦዲት መስሪያ ቤትን ሪፖርትና እቅድን በማድመጥ ያጸድቃል ተብሏል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀድሞው ዛሚ ሬድዮ እና OMN/ኦ ኤም ኤን/ በጋራ ለመስራት ተስማሙ!

በአክቲቪስት #ጃዋር_መሃመድ የሚመራው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ/OMN/ ከቀድሞው ዛሚ ኤፍ ኤም 90.7 ሬድዮ ጣቢያ እና ከአሁኑ የአዋሽ ኤፍ ኤም ለጊዜው የአየር ሰዓት በመግዛት እንዲሁም በአጭር ግዜ ውስጥ ደግሞ ድርሻ በመግዛት ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ከሬድዮ ጣቢያው ስያሜ ለውጥ ባሻገር የአስተዳደር ለውጥም እንደተደረገ እና በመጪው መስከረም ወር ኦ ኤም ኤን/OMN/ በገዛው የአየር ሰዓት ስርጭት እንደሚጀምርም ለማወቅ ተችሏል። በአብዛኛው የአማርኛ ቋንቋ ስርጭት ይኖራቸዋል ያለው አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ምናልባትም ለአንድ ሠኣት የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ፕሮግራሞች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

OMN ከአንድ አመት በፊት የሬድዮ ጣቢያ ለመክፈት ለብሮድካስት ባለስልጣን ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም እስካሁን መልስ ባለማግኘቱ ከዛሚ FM ጋር ለመስራት እንዲወስን እንዳደረገው አዲስ ማለዳ ጨምሮ ገልጿል። ታቅዶ ለነበረው የሬድዮ ጣቢያም ሙሉ እቃ ከውጪ አገር ገብቶ እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። እነዚህ እቃዎች በመጠቀም በአዳማ ከተማ አዲስ ሬድዮ ጣቢያ በማቋቋም ስርጭቱን በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለማድረግ መታሰቡን አዲስ ማለዳ በዛሬው ዕትሙ አስነብቦናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመጀመሪያ?

በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የውሀ ፓርክ በቢሾፍቱ ተመረቀ!

"በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የውሃ ፓርክ ተመርቆ በኩሪፍቱ ሪዞርት ተከፈተ፡፡ በኩሪፍቱ ሪዞርት በ72 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ በቢሾፍቱ የተገነባው የውሃ ፓርክ ተመርቆ ተከፈተ፡፡ ፓርኩ በውስጡ ከመዝናኛ ስፍራዎች በተጨማሪ ከ100 በላይ ሱቆችና ባህላዊ የምግብ አዳራሾች ይገኛሉ፡፡ በ100 ሚሊዮኖች ወጭ ተደረገበት ፓርኩ በአንድ ጊዜ ከ1900 ሰዎች በላይ የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍርካውያን መዝናኛ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡ በኩሪፍቱ የተገነባው የውሃ ፓርክ ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ግንባታውን ለማጠናወቀቅ 2 አመት ከ6 ወር ፈጅቷል፡፡" #EBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ኢ/ር ታከለ ኡማ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር እድሳት የተደረላቸውን ቤቶች #ለአረጋዊያን እና #አቅመ_ደካሞች በማስረከብ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዛሬው ዕለትም ኢ/ር ታከለ ኡማ እራሳቸው እድሳቱን ያስጀመሩትን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቃኘው ሻለቃ ተብሎ በሚጠራው አደባባይ አከባቢ የሚኖሩ እናት መኖሪያ ቤት ስራው ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ለባለንብረቷ ቤታቸውን አስረክበዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር 1000 ለሚሆኑ አረጋዊያን ቤት ለማደስ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም እስከ አሁን 1,573 ለሚሆኑ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት እድሳት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ 1,111 ቤቶች እድሳት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለባለንብረቶቹ ተላልፈዋል፡፡

Via Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባለሃብቶች በአማራ ክልል ዋግህምራና ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ 12 የዳስት ትምህርት ቤቶችን ወደ ህንፃ ለመቀየር ቃል ገቡ። በክልሉ የሚገኙ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ህብረተሰቡ በተቀናጀ መንገድ ሊደግፍ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጠይቀዋል። የዳስ ትምህርት ቤቶች ደረጃ በሚሻሻልበት ጉዳይ ዙሪያ ከባለሃብቶች ጋር ትናንት በባህር ዳር ከተማ ውይይት ተካሄዷል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ2012 በጀት አመት 40 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው 5ኛ ዙር 4ኛ አመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2012 በጀት አመት 40 ቢሊዮን 56 ሚሊዮን 938 ሺህ ብር በጀት አጸደቀ። የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የምክር ቤቱ ጉባኤው ለመዘግየቱ ይቅርታ ጠይቀዋል። በዋናነት በ3 አጀንዳዎች ላይ እየመከረ የሚገኘው ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችንም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፈ ጉባኤዋ ይቅርታ ጠየቁ!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት #ዋና_አፈ_ጉባኤ የምክር ቤቱ አባላት #ይቅርታ ያድርግልኝ ሲሉ በይፋ ጠየቁ። ዋና አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረውን የክልሉን አምስተኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ላለፉት አስራ አንድ ወራት የምክር ቤቱን መደበኛ ጉባኤዎች ባለመጥራቴ የተከበሩ የምክር ቤት አባላት ይቅርታ ያድርጉልኝ ሲሉ ተማፅነዋል።

የህዝብ ውክልና ያለው ምክር ቤት በየጊዜው ማከናወን የነበረበትን ስብሰባ አለማድረጉ በየትኛውም መመዘኛ #ትክክል አይደለም ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ በቀጣይ ተመሳሳይ #ስህተት እንደማይደገም በምክር ቤቱ ፊት ቃል እገባለሁ ብለዋል። በእርግጥ እንደምክንያት ማቅረብ ባይቻልም ምክር ቤቱ ማድረግ የነበረበትን መደበኛ ጉባኤዎች ሳያካሂድ የቀረው ክልሉ አጋጥሞት ከነበረው ነባራዊ ሁኔታ የተነሳ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በዓመት #አራት መደበኛ ጉባኤዎችን ማድረግ የሚገባው ቢሆንም ባለፈው የጥቅምት ወር የመጀመሪያውን ስብስባ ካደረገ ወዲህ ዳግም ሳይሰበሰብ ነው የበጀት ዓመቱ የተጠናቀቀው። በዚህም ምክንያት የክልሉ ዓመታዊ በጀት እስከአሁን ባለመፅደቁ የአስፈጻሚ ቢሮዎች ከሀምሌ 1 2012 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስራዎቻቸውን በምክር ቤት ባልጸደቀ በጀት ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አቶ_ርስቱ_ይርዳው ቀጣዩ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት ማን ይሆኑ? TIKVAH-ETHIOPIA ከቤተሰቡ አባላት ታማኝ ምንጮች እንደሰማው ከሆነ-አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን በመተካት የደቡብ ክልልን በፕሬዘዳንትነት የሚመሩት አቶ #ርስቱ_ይርዳው ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። •በትላንትናው ዕለት #ሪፖርተር_ጋዜጣ የደቡብ ክልል ቀጣይ ፕሬዘዳንት አቶ መለስ አለሙ ሆነው ሊሾሙ እንደሚችሉ መግለጹ አይዘነጋም። @tsegabwolde…
#update አቶ ርስቱ ይርዳው የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ርስቱ ይርዳው በምክር ቤቱ ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡ ምክር ቤቱ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስን ከኃላፊነታቸው በማንሳት ነው ለአቶ ርስቱ ይርዳው በዛሬው ዕለት ሹመቱን የሰጠው፡፡

Via #ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አቶ_ርስቱ_ይርዳው ቀጣዩ የደቡብ ክልል ፕሬዘዳንት ማን ይሆኑ? TIKVAH-ETHIOPIA ከቤተሰቡ አባላት ታማኝ ምንጮች እንደሰማው ከሆነ-አቶ ሚሊዮን ማቲዮስን በመተካት የደቡብ ክልልን በፕሬዘዳንትነት የሚመሩት አቶ #ርስቱ_ይርዳው ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። •በትላንትናው ዕለት #ሪፖርተር_ጋዜጣ የደቡብ ክልል ቀጣይ ፕሬዘዳንት አቶ መለስ አለሙ ሆነው ሊሾሙ እንደሚችሉ መግለጹ አይዘነጋም። @tsegabwolde…
ፎቶ📸አቶ ርስቱ ይርዳው🤝አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ👆

የደቡብ ክልል ምክር ቤት አቶ ርስቱ ይርዳውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ #ሾሟቸዋል። ትላንት ምሽት የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት የሆኑ ታማኝ ምንጮች የአቶ #ርስቱ_ይርዳውን ሹመት በሚመለከት #አስተማማኝ መረጃ አካፍለውን እንደነበር ይታወሳል።

#TIKVAH_ETHIOPIA_FAMILY

ፎቶ: የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምክር ቤቱ ጉባኤ ተጠናቋል!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤው የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመሾምና ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ተጠናቋል። የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ የርዕሰ መስተዳድር ለውጥ እንዲደረግ በወሰነው መሠረት አቶ ርስቱ ይርዳውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ክልሉን እንዲመሩ ሾሟቸዋል።

በተጨማሪም ለ2012 በጀት ዓመት 40 ቢሊዮን 56 ሚሊዮን 938 ሺህ 826 ብር አጽድቋል። በጀቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ3 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው። የበጀቱ ምንጭ ከፌዴራል መንግሥት ድጎማ፣ ከውጭ እርዳታና ከክልሉ ገቢ እንደሚሰበሰብ የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ገልጸዋል ።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ የተገነባው ኤጂ የቧንቧ መገጣጠሚያ ቴክኖለጂ ኩባንያ በ150 ሚሊየን ብር የግንባታና የማሽን ተከላ ስራው ተጠናቆ ተመርቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
30ኛው የትምህርት ጉባኤ አስተናጋጅ ጋምቤላ መሆኗ ታውቋል!

በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው #29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቋል። ጉባኤው በቆይታው የ2011 አም የእቅድ አፈፃፀም እና የ2012 እቅድ ላይ የመከረ ሲሆን፥ በሶስተኛው ቀን ውሎም አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ላይ መክሯል። በዚሁ ፍኖተ ካርታ ላይም በአመዛኙ አተገባበሩ ላይ ቢስተካከሉ እና እንደገና ቢታዩ ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል ጉባኤተኛቹ።

በዚህም ፍኖተ ካርታውን ለመተግበር የሽግግር ጊዜና ከቀደመው ስርአት መውጫ ስትራቴጅ ያስፈልጋል፣ ለመምህራን የተሰጠው ስልጠና በቂ አይደለም፣ የመፅሀፍ እና ትምህርት ግብአት ዝግጅት በበቂ ሁኔታ አልተሟላም፣ ሁሉም ሳይስማማበት ወደ ትግበራ መግባቱ ችግር ይፈጥራል፣ ያልተወያዩ ክልሎችና የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ፣ የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል።

https://telegra.ph/ETH-08-31-4

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia