TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ምን ያህል ተማሪ አለፈ ? በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ሆኗል። በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በድረ-ገጽ eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በተጨማሪም…
#Tigray
657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።
በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል።
ይህንን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ሙሴ ኪዳነ የሚባል ሲሆን የ " ቀላሚኖ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመመልከት ችሏል።
እንደ ትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ መረጃ አጠቃላይ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 73.09 በመቶ የሚሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።
በትግራይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኃላም በደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው መቆየታቸው የሚዘነጋ አይደለም።
ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiatigrigna
@tikvahethiopia

ስኬታማ ምዕራፍ፤ ብሩህ ተስፋ!
****
ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም - በሀገራችን የባንክ ሥራ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የተከፈተበት ቀን፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት በመጀመር እንደ ሁልጌዜው ሁሉ ፈር ቀዳጅነቱን አስመሰከረ፡፡
ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶችን በማለፍ የስኬት ታሪክ መፃፍም ተቻለ፡፡
ሲቢኢ ኑር 10 ዓመት ሞላው፡፡
በጉዟችን የገጠሙንን ተግዳሮቶች ያለፍንበትን መንገድ በመማማር፣
ከስኬቶቻችን ልምድ በማካፈል፣
አብረውን ለነበሩ ሁሉ ምስጋናን በማቅረብ፣
ለበለጠ ስኬትም ቃል በመግባት፣
10ኛ ዓመታችንን ከክቡራን ደንበኞቻችን ጋር በጋራ እንዘክራለን፡፡
ስኬታማ ምዕራፍ ነበረን፣ የወደፊቱም በብሩህ ተስፋ የተሞላ ነው፡፡
ትክክለኘውን የቴሌግራም ቻናል https://t.iss.one/combankethofficial

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SUNChips
መምጣቱ ላይቀር የሚያስጠብቀን የእረፍት ቀን ደርሷል! ዘና ፈታ እንበል! #መክሰስTime ደርሷል- ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
Looking forward to snacking on the weekend with SUNChips. #SUNChips 😋 #SunnyMoments. ☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

#NBE #CustomsCommission #LC
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጥያቄ መሠረት አስመጪና ላኪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ወደ አገር ቤት እንዳያስገቡም ሆነ ወደ ውጪ እንዳይልኩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ እንደሚለው ፤ ኮሚሽኑ በወሰነው ውሳኔ አንዳንድ ላኪዎችና አስመጪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያየ ጊዜ ምርቶችን መላክና ማስመጣት የሚፈቅደውን ሕግ፣ የአገርን ጥቅም በሚያሳጣና በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀሙበት በመሆኑ አንድ LC (LETTER OF CREDIT) ለአንድ ምርት ብቻ እንዲሆን ሊያደረግ ነው።
ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚሆነው ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. እነድሆነ ተገልጿል።
አስመጪና ላኪዎች ትዕዛዙ በአሁኑ ሰዓት በክፍልፋይ (Partial Shipment) መሠረት ስምምነት ያደረጉ ድርጅቶችን ያካተተ መሆን የለበትም ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
እኚሁ አስመጪና ላኪዎች አንዳንድ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያሰሩትን ስምምነት መቀየር እንደማይችሉና ትዕዛዙ ተግባራዊ መሆን ያለበት አዲስ ስምምነት ለሚያደርጉ ድርጅቶች መሆን እንደሚገባ ለብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በባንኮች በኩል የሚከፈተው LC (LETTER OF CREDIT) በገዥና በአቅራቢ ድርጅት መካከል የሚደረግ ጠንካራ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል፡፡
የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) ማለት ገዥውና አቅራቢ በስምምነታቸው መሠረት በአንድ ጊዜ ሁሉንም ምርት በተለያየ ምክንያት መላክ ስለማይቻል ከሥር ከሥር እየተመረተ ለመላክ የሚስማሙበት አካሄድ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በኮንቴይነር እጥረት፣ ገዥው በቂ ማከማቻ ቦታ ከሌለው፣ የክፍልፋይ ስምምነት ይደረጋል፡፡ ይህ ስምምነት ጥሬ ዕቃዎቹ በወቅቱ እንዲገቡ ያደርጋል እንጂ አገርን የሚጎዳ አይደለም ሲሉ አስመጪ ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡
የአስመጪዎች ትልቅ ሥጋት የሆነው የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) መሠረት የታዘዙት ዕቃዎች ጂቡቲ የሚደርሱት የጉምሩክ ኮሚሽን ውሳኔ ከሚጀመርበት ቀን በኋላ ነው፡፡
በአዲሱ ትዕዛዝ ቀድሞ ስምምነት የነበራቸውን በማካተቱ ምርቶቹ መጥተው ወደብ ላይ መዘግየት፣ የባንክ ብድር መክፈል አለመቻል፣ የቀረጥ ክፍያ አለመስተናገድና ለተጨማሪ " ዴሜሬጅ " ክፍያ እንደሚያወጡ ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ዕገዳው ቀድሞ ስምምነት የተደረገባቸውን ሳያካትት ከኅዳር 10 ቀን በኋላ ለሚደረግ አዲስ ስምምነት ፈቃድ መከልከል አለበት ብለዋል፡፡
በክፍልፋይ ጊዜ በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያዩ ወቅቶች ምርቶችን ማስገባት መፈቀዱ፣ አስመጪዎቹ ባንክ ከፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ በላይ የሚያወጡ ምርቶችን የማስገባት ዕድሎችን እንደመፍጠሩ፣ በዚህም ባንኩ ከፈቀደላቸው ውጪ ጥቅም ላይ ያዋሉት ገንዘብ ከጥቁር ገበያ የተገኘ ነው የሚለውን ጥርጣሬ ከማሳደጉ ባለፈ፣ አሠራሩም ሕገወጥ ገበያን አበረታቷል በሚል የተላለፈ ትዕዛዝ ነው፡፡
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የዘርፉ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነ የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) አገርን ችግር ውስጥ የሚከት አይደለም ብለዋል፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን ሕገወጥ ተግባርን ለመከላከል የሚፈልግ ከሆነ በቀላሉ ሕገወጦቹን በመለየት በሕግ መጠየቅ እንጂ በትክክለኛ አካሄድ የሚሠሩትንም በአንድ ላይ በማገድ መፍትሔ አይመጣም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

መምህራን ምን አሉ ? • " የመምህራን ደመወዝ ይቆረጣል የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ አሳማኝ አይደለም " • " የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች አይልኩም " • " አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው ይጠብቃሉ፤ ግማሽ ደመወዝ ብቻ የሚከፈልበት ጊዜም አለ " የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው 36ኛው ጉባዔ ላይ፣ በክልሎች የበርካታ…
#የኢትዮጵያ_መምህራን_ማህበር #ቲክቫህኢትዮጵያ
የመማሪያ መፅሀፍት ጉዳይ
" ቅሬታችንን መንግሥት ይወቅልን " ያሉ #ተማሪዎች ፣ የመማሪያ መፅሀፍት ሶፍት ኮፒ እንኳን ማግኘት ቢቻል ማንበቢያ ስልክ ያስፈልጋል ፣ ስማርት ስልክ ደግሞ የቤተሰቦቻችን ገቢ ዝቅተኛ በመሆኑ ሊገዛልን አይችልም ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አክለውም፣ በዚህ ሁኔታ እንዴት መማርና ውጤታማ መሆን እንችላለን ? ነው ወይስ ትምህርት መማር ያለባቸው የባለሃብት ልጆች ብቻ ናቸው ? ሲሉ ጠይቀዋል።
36ኛውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ምክር ቤት ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን በጅግጅጋ በነበረ ውይይት የተማሪዎችን የመጽሐፍ እና የሶፍት ኮፒ አለምግኘት ጨምሮ ሌሎች መምህራን የሚያነሷቸውን ቅሬታዎች በተመለከ ምን የመፍትሄ ሀሳብ እንደተቀመጠ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ጥያቄ አቅርቧል።
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ " አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ሳውላ ጎፋ አካባቢ) ፕሪንተርም፣ ፎቶ ኮፒም የለውም " ብለዋል።
" አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የማባዣ ቁሳቁስ እንኳን የሌላቸው አሉና ሶፍት ኮፒ ብቻ ልኮ ተማሪዎች መፅሐፍ አግኝተዋል ማለት አይቻልም " ያሉት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት፣ " ሶፍት ኮፒ ደግሞ በሞባይል ነው የሚታየው፣ ሁሉም ተማሪ ደግሞ ለዛ የሚመጥን ስማርት ስልክ ላይኖረው ይችላል፣ አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል " ነው ያሉት።
" ተማሪዎች ሀርድ በእጃቸው ይዘው የሚያነቡት ሀርድ ኮፒ ያስፈልጋቸዋል " ያሉት ዮሐንስ (ዶ/ር)፣ ይህንን በተመለከተም በጅግጅጋ በነበረው የማኅበሩ ምክር ቤት ክልሎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መፅሐፍ እጥረት እንዳለ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መፅሐፍ እንዳልደረሰ ተነግሯል ብለዋል።
የተነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) " ወደ 40 ኮንቴነር ጂቡቲ ደርሷል፣ እንደውም ወደ መሀል አገርም እየተጓጓዘ ነው፣ በቅርቡ ወደ ትምህርት ቤቶች ይደርሳል " ማለታቸውን ይሐንስ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
የመምህራን ዝውውር ጉዳይ
ከዝውውር ጋር በተያያዘ መምህራን በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ የሚደመጥ ሲሆን፣ ችግሩን ለመቅረፍ ምን ውይይት እንደተደረገ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የማኅበሩ ፕሬዚዳንት፣ መምህራን የሚዘዋውሩበት የዝውውር ስርዓት እንዳለ ገልጸው ተከታዩን አክለዋል።
" ዝውውር ለመምህራን እንደ #ትልቅ_የመብት_ጉዳይ የሚታይ ነው። " የተለያዩ የአፈፃፀም ጉድለቶች እንዳሉ ምክር ቤቱ በጅግጅጋ በነበረው ስብሰባ ገምግሟል። በየደረጃው ተስተካክሎ በመመሪያው መሠረት እንዲፈጸም ሰፊ ውይይት አድርገንበታል። "
ተፈናቃዮችን ያስጠለሉ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ
" የተፈናቀሉ ዜጎች መጠለያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ አይተናል። በዛ አካባቢ በተለይ ትምህርት ለመስጠት አስቸጋሪ ይሆናል " ሲሉ ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) አስረድተዋል።
ኢሰመኮ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ባድረገው ሪፓርት በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቃዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በሚያገረሽበት አማራ ክልል ውስጥ ትምህርት ቤቶች የተፈናቃይ መጠለያ ካምፖች እንደሆኑ መረዳቱን ማስገንዘቡ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በበኩሉ የተፈናቃይ መጠለያ በሆኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መምህራን ማስተማር እንዳልቻሉ ፣ የትምህርት ተቋማትም ውድመት እንደሚደርስባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የመምህራን ደመወዝ አለመከፈልና መቆረጥ ጉዳይ
መምህራን የሰሩበት ደመወዛቸው #ስለማይከፈላቸው እና የሚከፈላቸውም ስለሚቆረጥባቸው በተለይም ደቡብ ክልል ላይ የሥራ ማቆም አድማ እስከማድረግ የደረሱበትን ሁኔታ በተመለከተ ምን እንደታሰበም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመምህራን ማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጥያቄ አቅርቧል።
ፕሬዝዳንቱ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ ፤ " ቀደም ብሎ እዚያ አካባቢ ባጋጠመው ሁኔታ እኛም ለክልሉ መንግሥት ደብዳቤ ፅፈን ነበር፣ በዚያ መነሻ በወቅቱ ተከፍሎ ነበር። አሁን ኋላ ላይ ደግሞ ተመልሶ እንዳገረሸ ሰምተናል" ብለዋል።
" ምክንያቶቹ የተለያዩ ይሆናሉ። መምህራን የሰሩበትን በጊዜው ማግኘት አለባቸው " ያሉ ሲሆን " ደመወዙ የመምህራኑ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቻቸውም፣ የልጆቻቸውም ጭምር ስለሆነ በየደረጃው ያለው መዋቅር ይህን ተከትሎ መፈጸም እንዳለበት ሁሌም እናሳስባለን " ሲሉ ገልጸዋል።
የደመወዝ አለመከፈልን በተመለከተ ለማኅበሩ ምን ያህል መምህራን ቅሬታ እንዳቀረቡ፣ ለስንቶቹ መፍትሄ እንደተሰጠ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁም፣ በአብዛኛው ቅሬታ ያለው በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል በተወሰነ መልኩ እንዲሁም በአፋርና በሌሎች አካባቢዎች እንድሆነ፣ ቅሬታው ከተለያዩ ወረዳዎች ስለሚመጣ ቁጥሩን ለመግለጽ እንደሚያስቸግር አስረድተዋል።
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ ፤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት ፣ የ36ኛው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ምክር ቤት ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን በጅግጅጋ በነበረው ፕሮግራም ውይይት ተደርጎባቸው የመፍትሄ ሀሳብ የተቀመጠላቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች፡-
- የመምህራን ዝውውር
- የመምህራን ጥቅማጥቅም
- የመምህራን የትምህርት ዕድል
- የመኖሪያ ቤት አቅርቦት
- መልካም አስተዳደር
- የትምህርት ጥራት
- የተማሪዎችን የውጤት ቀውስ
- የጸጥታ ችግር በትምህርት ላይ ያስከተለው ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ በተመለከተ ነው ብለዋል።
መረጃው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

#ትግራይ
" በተለያዩ ሚድያዎች ከሚሰማው በሬ ወለደ ወሬ በስተቀር ከኤርትራ በሚዋሰኑ የድንበር አከባቢዎች ከበፊቱ የተለየ ነገር የለም " - ኮማነደር ሙሉብርሃን
የድንበር የፀጥታ ጉዳይ የሚመለከት ሪፓርታጅ !
ኢትዮጵያ ከባህር በር ተጠቃሚነት ጋር አያይዛ ያነሳቸው ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ እንደነበር ይታወሳል።
ምንም እንኳን ስም ባትጠቅስም ጎረቤት አገር ኤርትራ በዜና ሚኒስተርዋ በኩል መግለጫ እስከማውጣትም ደርሳ ነበር።
ይህንን ተከትሎ ሁለቱ አገራት በሚያገናኘው ሰፊ የድንበር አከባቢ ፦
- ውጥረት እንዳለ ፣
- የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ኃይል ጋር በጥምር ወደ ደንበር መጠጋታቸው ፣
- ከባባድ የጦር መሳሪያዎች እየተጓጓዙ እንደሚገኙ የሚያትቱ ምንጫቸው #ያልተረጋገረጠ የአገር ውስጥና የውጭ ሚድያ ዘገባዎች እንዲሁም የማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፅ ፅሁፎች ተደምጠዋል ተነበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በአካል ለመመልከት ኢትዮጵያን በትግራይ በኩል ከሚያዋስኑ የምስራቃዊና የማእከላዊ ዞን አከባቢዎች ተጉዞ የሚከተለውን ሪፓርታጅ ልኳል።
የቲክቫህ ሪፖርተር እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ዓዲግራትና ፋፂ ተጓዘ ።
ዓዲግራት የምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ስትሆን ፣ ፋፂ የጉሎመኸዳ ወረዳ ዋና ከተማ ሆና ከኤርትራ ደንበር በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ ዛላኣምበሳ ከተማ ጨምሮ ከ5 በላይ ቀበሌዎችዋ እስከ አሁን በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ሰር የሚገኙባት ናት።
በተመሳሳይ በርካታ ቀበሌዎችዋ በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙባት የኢሮብ ወረዳ የኮሙኒኬሽን ባለሞያ ልኡል አፅብሃ ፣ የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ነጋሲ መንገሻና አርአያ ሃይሉ ፣ የፋፂ ከተማ ነዋሪዎች የዕብዮ አለም ፣ ጠዓመ እና ልዋም የተባሉ የቲክቫህ ሪፓርተር አነጋግሮ የሰጡት መልስ በአከባቢያቸው ከበፊቱ የተለየ ነገር እንደሌለ በመግለፅ አሁንም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙ አከባቢዎች እንዲያስለቅቅ ተማፅነዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፓርተር የምስራቃዊ ዞን ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ሙሉብርሃን አነጋግሮም በተለያዩ ሚድያዎች ከሚሰሙት በሬ ወለደ ወሬ በስተቀር በዞኑ ከኤርትራ በሚዋሰኑ የድንበር አከባቢዎች ከበፊቱ የተለየ ነገር እንደሌለ አረጋግጠውለታል።
የቲክቫህ ሪፓርተር የማእከላይ ዞን ከተሞች ሆነው ለኤርትራ ድንበር የቀረቡት እንትጮ ፣ ድብድቦ ዓድዋና አክሱም ድረስ ተጉዟል።
ያለውን ሁኔታ በአይኑ ከመታዘብ በተጨማሪ የከተማዎቹ ነዋሪዎች አነጋግሮ በአከባቢያቸው ከበፊቱ የተለየ ነገር እንዳለዩ ነግረውታል።
ኣክሱም ድረስ በመጓዝ ያነጋገራቸው የማእከላይ ዞን ፓሊስ አዛዥ በለጠ ገ/የሱስም ከነዋሪዎቹ የተለየ አስተያየት እንደሌላቸው በመግለፅ ፣ ይሁን እንጂ ከኤርትራ ድንበር በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ከሚገኙት የራማና ከተማና አሕሳኣ ወረዳ የኤርትራ ሰራዊት አባላት ሾልከው በመግባት ሰዎች አፍነው የመውሰድ ሁኔታ እንዳለ ፣ የዚሁ ዋናው ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ የትግራይ ድንበር አከባቢ በቂ የሆነ የአገር መከላከያ ሰራዊት ባለመኖሩ መሆኑ ለቲክቫህ ሪፓርተር ገልጸዋል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-04-2

ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎች ፤ " ጤና ሚኒስቴር በሕግ የተወሰነልንን ልዩ አበል አልከፈለንም " አሉ።
የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት፤ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ማኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን 1,050 ብር፣ ለየመጀመሪያ ድግሪ ባለሙያዎች 900 ብር ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ተወስኖ ነበር።
በዚህ መሠረት ጤና ሚኒስቴር በኮቪድ - 19 ወቅት የአገልግሎት ሥራ ለሰሩት የተወሰኑ ወራት አበል እንደከፈላቸው ፣ ይሁን እንጂ ከዚያ በኃላ ክፍያውን እንዳቆመ ፣ ይህን ተከትሎም ቀሪው ልዩ አበል እንዲከፈላቸው በቃልና በደብዳቤ ቢጠይቁም ምላሽ እንዳላገኙ ፣ በመጨረሻም ክስ እንደመሰረቱ፣ በክሱ መሠረትም ገንዘቡ እንዲከፈላቸው ቢወሰንም ጤና ሚኒስቴር ግን ከውሳኔው በኋላም ለመክፈል ፈቃደኛ እንዳሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
በአጠቃላይ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በቁጥር 71 ሲሆኑ አንድ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ባለጉዳይ እና የጤና ባለሙያዎቹ ተወካይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦ " ጤና ሚኒስቴር ከተሰጠው ኃላፊነት አንፃር የጤና ሥርዓቱን ማዘመን፣ የጤና ባለሙያውን መብቶች፣ ጥቅሞች ማክበር፣ ለጤና ባለሙያዎች ምቹ ከባቢና የሥራ ዋስትና መፍጠር ነበር። ነገር ግን መንግሥት ነኝ በማለት በማን አለብኝነት በጤና ባለሙያዎች ላይ ከማሾፉም በላይ ጤና ባለሙያዎች ከአቅም በላይ ሲሆንባቸው መብታቸውን በፍትህ አካል ጠይቀው ተወስኖላቸው 'እንደውሳኔው ክፈል' ተብሎ ሲታዘዝ 'ያለውሳኔ ነው' በማለት ነገሮችን ማጣመም ተገቢና ከአንድ ሥሙ ትልቅ ከሆነ ተቋም የማይጠበቅ ነው " ሲሉ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ላይ ወቀሳ አቅርበዋል።
ጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ማስረጃ ጤና ሚኒስቴር ፦
▪️ከ1ኛ - 14ኛ ተራ ቁጥር ላሉት የጤና ባለሙያዎች ከኅዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለእያንዳንዳቸው 400 ሺሕ 050 ብር፣
▪️15ኛ ተራ ቁጥር ላይ ላሉ የጤና ባለሙያ ከሚያዚያ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ 242 ሺሕ 550 ብር፣
▪️ከ16ኛ - 66ኛ ተራ ቁጥር ላሉ የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ከመስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለእያንዳንዳቸው 396, 900 ብር በአጠቃላይ ከ1ኛ እስክ 66ኛ የጤና ባለሙያዎች የተጠቀሰው የኮቪድ - 19 ልዩ አበል እንዲከፈላቸው አቤቱታ ማቅረባቸውን ያትታል።
ይህ የገንዘብ መጠን የጤና ባለሙያዎቹ ክስ ሲመሰርቱ ያካተቱት ሲሆን፣ በውሳኔ ግልባጩ ጤና ሚኒስቴር ለከሳሾች የልዩ አበሉን ከኀዳር 1 ቀን 2013 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲከፈል ተብሎ ቢወሰንም የተጠቀሰ የልዩ አበል መጠን ግን የለም።
ቲክቫህ - ኢትዮጵያ የተመለከተው #የውሳኔ_ግልባጭ ፣ ጤና ሚኒስቴር (መልስ ሰጭ ተቋም) ለይግባኝ ባዮች ያቀረቧቸው ሁሉንም የመቃወሚያ ሀሳቦች ውድቅ አድርጎ ከኅዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ወራት ውስጥ (የሚከፈልባቸው ወራት ከፋፍሎ አስቀምጦ) ፣ ጤና ሚኒስቴር ለ66ቱ የጤና ባለሙያዎች የጠየቁትን የኮቪድ - 19 ልዩ አበል እንዲከፍል ውሳኔ ማሳለፉን ያስረዳል።
የውሳኔ ግልባጩ " 15ኛ ይግባኝ ባይ አቶ ክንዳለም መኳንንት በኮቪድ - 19 ሥራ ላይ ያገለገሉበት ክፍያ አቤቱታቸውን ካቀረቡ በኋላ የተከፈላቸው መሆኑን የይግባኝ ባዮች ተወካይ በችሎት በማስረዳታቸው 15ኛ ይግባኝ ባይ ከክርክሩ ውጭ ሆኗል " ይላል።
ቲክቫህ የጤና ባለሙያዎቹ በሕግ የተወሰነላቸውን ልዩ አበል ያልከፈለበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ጤና ሚኒስቴርን ጠይቋል።
በተቋሙ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የሚያገለግሉት አቶ ዮርዳኖስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት የፅሑፍ ምላሽ ፣ " ክልሎች ናቸው ጤና ባለሙያዎችን የሚቀጥሩት ስለሆነም የቀጠራቸው ክልል ጤና ቢሮ ማናገሩ ጥሩ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስራ የሰሩበት አበል ሊከፍላቸው የሚገባው " የቀጠራቸው ክልል ነው " ስለተባለ የቀጠራቸው ተቋም ማን እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹን ጠይቋል።
ይሁን እንጂ አንድ ቅሬታ አቅራቢ ለቲክቫህ በሰጡት ምላሽ ፣ "ጤና ባለሙያዎች የከሰስነው የቀጠረንን ተቋም ነው። ክልሎች ቀጥረውን እንዴት ጤና ሚኒስቴርን እንከሳለን ? ይህን እኮ እነሱም ያውቃሉ ውልም አለን። አሁን ከእነሱ ተቋም የለቀቅን ብዙዎች ነን እንጂ ከለቀቅን በኋላ ያለውን ደግሞ አልከሰስንም " ብለዋል።
እኚሁ ታማኝ ምንጭ በተጨማሪ ልዩ አበሉ ይከፈለን የሚሉች የጤና ባለሙያዎች የጤና ሚኒስቴር ሠራተኞች እንደነበሩ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ልከዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይበልጥ ይህንን ጉዳይ ለማጣራት የተመለከተው የውሳኔ ግልባጭ ፤ " መልስ ሰጭ መ/ቤት ይግባኝ ባዮች የልዩ አበል ክፍያ መጠየቅ ያለባቸው ተመድበው እየሰሩ ያሉበትን ተቋም ነው እንጂ ጤና ሚኒስቴርን አይደለም በማለት ያቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም " ሲል ውድቅ እንዳደረገው በግልጽ ያሳያል።
በመሆኑም አቶ ዮርዳኖስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ለምን " ክልሎች ናቸው ጤና ባለሙያዎችን የሚቀጥሩት ስለሆነም የቀጠራቸው ክልል ጤና ቢሮ ማናገሩ ጥሩ ነው " የሚል ምላሽ እንደሰጡ በድጋሚ ለመጠየቅ በፅሑፍና መልዕክትና በስልክ ጥሪ ቢሞክርም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
በመጨረሻም ለጉዳዩ ምን አይነት ምላሽ እንዳላቸው ለመጠየቅ ለጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ስልክ ቢደወልም ባለማንሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።
የክሱን ሂደት በተመለከተም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሁነኛ አካላት ባደረገው ማጣራት የጤና ባለሙያዎቹ ልዩ አበሉ እንዲከፈላቸው መወሰኑን፣ አፈጻጸሙ ግን ገና እንዳልተቋጨ ለማወቅ ችሏል።
ይህ መረጃ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#Tigray 657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል። በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል። ይህንን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ሙሴ ኪዳነ የሚባል ሲሆን የ " ቀላሚኖ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመመልከት ችሏል። እንደ ትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ መረጃ አጠቃላይ…
" በጦርነቱ ምክንያት ወደኃላ ባልቀር አሁን የ4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ " - ተማሪ ሙሴ ኪዳነ
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 657 በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው የቀላሚኖ ት/ት ተማሪ ሙሴ ኪዳነ " መድረስ ከነበረብኝ የትምህርት ደረጃ ባለመድረሴ ዓመታት ከእድሜ ላይ ተሰርቋል " ሲል ገልጿል።
የትግራይ #ሃውዜን ነዋሪ የሆነው ተማሪ ሙሴ አሁን ላይ እድሜው 22 ሲሆን ፤ ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደስ መሰኘቱን ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግሯል።
አስከፊው ጦርነት በይከሰትና ወደኃላ ባይቅር ኖሮ አሁን ላይ የ4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደነበርም ገልጿል።
ሙሴ ኪዳነ ፥ " አሁን የመጣው የፈተና ውጤት ጥሩ ነው። ደስም ብሎኛል ከውጤቱ ጋር አያይዤ ማለት የምፈልገው ሁሉም ሰው ያሰበውን ደረጃ ለመድረስ የሚያስችለውን ጥረት ካደረገ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው። " ብሏል።
መድረስ ከነበረበት የትምህርት ደረጃ ባለመድረሱ ዓመታት ከእድሜው እንደተሰረቀበት የሚገልፀው ተማሪ ሙሴ አሁን የሚገባውን ሁሉ የሚማርበት እድል ሊመቻች ይገባል ሲል ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግሯል።
በትግራይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 73.09 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።
(ያለፉ ተማሪዎች ቁጥራዊ መረጃ ምንጭ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጎዑሽ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያሳውቃል)
@tikvahethiopiatigrigna @tikvahethiopia

አንድ ዓመት ስለደፈነው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፣ ህወሓት እና ሀገራት ምን አሉ ? የኢትዮጵያ መንግሥት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የፕሪቶሪያው ግጭት የማስቆም ስምምነት ዋና ዉጤት " የጦር መሣሪያ ላንቃ መዘጋቱ " እንደሆነ አሳውቋል። ሚኒስቴር ከግጭት ማቆሙ ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት…
#Update
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
በዚህም መግለጫ የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲከበር ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቋል።
በአከራካሪ ቦታዎች ተፈናቃዮች እንዲመለሱና በህገመንግቱ መሰረት ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ አቋም ይዞ ተግባር ላይ እንዳለ አመልክቷል።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ፤ መንግሥት በጦርነቱ የመጨረሻ ወቅት ምንም እንኳን ሁሉን ነገር በኃይል ለመፈፀም የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና የነበረው ቢሆንም ጦርነቱ በሰላም ስምምነት ቢቋጭ ሀገርን አትራፊ የሚያደርግ መሆኑ ስለታመነበት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲፈረም መደረጉን አስታውሷል።
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ውሳኔ " ሀገርን ለመገንባትና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ሲባል የተከፈለ መሥዋዕትነት ነው " ብሎታል።
ከሰላም ስምምነቱ በኋላ መንግሥት በሆደ ሰፊነትና ቁስሉ እንዲሽር ካለው ፍላጎት ረጅም ርቀት መጓዙን ገልጿል። ወደ ትግራይ በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ መላኩ ፤ በፍጥነት የቴሌኮሚኒኬሽን፣ የባንክ ፣ የአውሮፕላን አገልግሎት መጀመሩን በማሳያነት አንስቷል።
በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተመሠረተ ጊዜ መሳሳብና መጓተትን ለማስቀረት ሲባል የአመራሩን ድርሻ ክልሉ እንዲወስድ ተደርጎ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፋታ አግኝቶ ፊቱን ወደ ሰላምና ልማት እንዲያዞር ተደርጓል ብሏል።
የኮሚኒኬሽን አገልግሎቱ በዚህ መግለጫው ፤ የፌዴራል መንግሥት አንዳንድ ነገሮችን እያገዘ ፤ አንዳንድ ነገሮችን ችሎ እያለፈ፣ አንዳንድ ነገሮችን እየመከረ አንዳንድ ነገሮችንም ራሱ እየሠራ የሰላም ስምምነቱ በተሟላ መልኩ በሂደት እንዲፈጸም ለማድረግ መሞከሩን አመልክቷል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአንዳንድ ነገሮች ወደኋላ እየቀረና ስምምነቱን በተሟላ ሁኔታ ሳይፈጽም እያነከሰ ለክልሉ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ የፌዴራል መንግሥቱ እንዳላቋረጠ በመግለጫው ተገልጿል።
መግለጫው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በምን በምን ጉዳዮች ወደኃላ እንደቀረ በግልፅና በዝርዝር አልገለጸም።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ፤ አከራካሪ የሚባሉ አካባቢዎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥቱ አቋም ወስዶ እንደሰራ እንደሆነም ይፋ አድርጓል።
" የፌዴራል መንግሥት በዚህ ረገድ ያለው አቋም ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ፣ ሁሉንም ወገን በሚጠቅም መንገድ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ብልጽግና በሚያረጋግጥ መንገድ መፍትሔ መሰጠት አለበት " የሚል እንደሆነ አመላክቷል።
🔹ክረምት ደርሶ የእርሻ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ፤
🔹የአካባቢ ነዋሪዎች #በመረጧቸው አካላት እንዲተዳደሩ፤
🔹በመጨረሻም ደረጃ በደረጃ በሕገ መንግሥቱ መሠረት #ሕዝበ_ውሳኔ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡንና ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።
" ይህ ሁሉ ቢደረግም እንኳን በዚያኛው ወገን እግር የመጎተት አዝማሚያ ይታያል፡፡ " ያለው መግለጫ " ይህ ግን ዘላቂ ሰላምን፣ ብልጽግናንና የሕዝቦችን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አያረጋግጥም ብሏል።
የፌዴራል መንግሥት የፕሪቶርያውን ስምምነት በተመለከተ ከሚጠበቅበት በላይ መጓዙን፤ በዚህም ለሰላም ያለውን ጽኑ አቋም ደጋግሞ ማሳየቱን የኮሚኒኬሽን አገልግሎት አመልክቷል።
የፕሪቶርያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር መንግሥት አሁንም ቁርጠኛ አቋም እንዳለው
ሁሉም አካላት ተመሳሳይ ቁርጠኝት በማሳየት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ቴክኖ ‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ !
ቅንጡ ዲዛይንን ከልዩ ልዩ አገልግሎቶቹ ጋር በማቀናጀት የተመረተው ‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’፣ ሲታጠፍ 88.77 ሚሊ ሜትር፣ ሙሉ ለሙሉ ሲዘረጋ ደግሞ 171.72 ሚሊ ሜትር የሆነ ማንኛውንም ምስል ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ 1080 x 2640 ፒክስል ስክሪን ዲስፕሌ በመያዝ የተመረተ ነው።
እጅግ የላቀ እና የዘመነ የካሜራ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ ጥራት ያላቸውን ፎቶዎችን በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ማንሳት የሚያስችል ብቃት ያለው 64 ሜጋ ፒክስል ከ13 ሜጋ ፒክስል አልትራ ዋይድ (Ultra Wide) የኃላ ካሜራዎች እንዲሁም በባለ 32 ሜጋ ፒክስል የፊት ለፊት ካሜራ የተገጠመለት ነው።
ዘመኑ ያፈራውና በአገልግሎቱ የተመሰከረለት ሚዲያቴክ 8050 Mediatek Dimensity 8050 የተባለ ፕሮሰሰር ከ256 ጂቢ ሜሞሪ ከ(8+8) ጂቢ ራም የያዘው ‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ በፍጥነት እና ያለእንከን እንዲሰራ የሚያስችለው ሲሆን 45ዋት የፍጥነት ቻርጅ የማድረግ አቅም ያለው ባለ4000 ሚሊ አሚፒር ባትሪ የያዘው ይህ ሞዴል አገልግሎትን ያለ ማቋረጥ እየሰጠ ያለ ስጋት መጠቀም ያስችለናል።
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip #TecnoMobile #TecnoEthiopia

ለቀን ወጪያችን M-PESA መጣልን!
በአቅራቢያዎ ባሉ ንግድ ቤቶች ቀልጠፍ ብለው ክፍያ መፈፀም ይችላሉ።
M-PESAን ለመጠቀም የሞባይል አፑን ያውርዱ ወይም *733# ይደውሉ
ጉግል ፕለይ ስቶር/ አፕል ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricomET #FurtherAheadTogether

#NEBE
በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነታቸው በለቀቁት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ምትክ አዲስ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ለመተካት 8 አባላት ያሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ዛሬ ተሰይሟል።
ይኸው ኮሚቴ የተሰየመው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነው።
የኢፌዴሪ ህገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ላይ በሰፈረው መሰረት #ጠቅላይ_ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል።
የተቋቋመው መልማይ ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱ የተነገረ ሲሆን በቅርቡ #ጥቆማ መቀበል እንደሚጀምር ተገልጿል።
የምርጫ ቦርድ ሰብሰቢ መልማይ ኮሚቴው ፦
- ቀሲስ ታጋይ ታደለ (ሰብሳቢ)
- ፕ/ር ተከተል ዮሐንስ (አባል)
- አቶ ባዩህ በዛብህ (አባል)
- ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ (አባል)
- አቶ ካሳሁን ፎሎ (አባል)
- ወይዘሮ ርግበ ገብረሃዋርያ (አባል)
- ወይዘሮ እንግዳዬ እሸቴ (አባል)
- ኢ/ር መላኩ እዘዘው (አባል)
መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተገኘ ነው።

" የጤና ባለሙያዎች የ17 ወራት ደመወዝ፣ የ22 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈላቸውም " - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ
በትግራይ ክልል የነበረው የጤና ኢንሹራንስ ሥርዓት ባለመዘርጋቱ በተለይ አቅመ ደካሞች መታከም እንዳልቻሉ ፣ የጤና ባለሙያዎች አሁንም ደመወዝና አበል እንዳልተከፈላቸው የክልሉ ጤና ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አማኑኤል ኃይለ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ትግራይ ጥሩ የሆነ የጤና ኢንሹራንስ ከነበራቸው ቦታዎች አንዷ ነች። አሁን ያ ስርዓት ሙሉ ለሙሉ የለም " ብለዋል።
" አሁን ደግሞ በእርዳታ ለዘላለም መኖር አይቻልም" ያሉት ኃላፊው፣ " ቢያንስ ጤና ተቋማቱ መድኃኒት ገዝተው ለሕዝቡም አገልግሎት ሰጥተው፣ ከኪስ የሚከፍለው ከኪስ ይከፍላል፣ በጤና ኢንሹራንስ የሚከፍለው አብዛኛው የገጠሪቱ ነዋሪ ደግሞ በጤና ኢንሹራንስ እንዲታቀፍ ነበር አካሄዱ ነገር ግን አሰራሩ የለም አሁን በቦታው፣ ይህም ትልቅ ሥራን ይጠይቃል " ሲሉ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፤ በበጀት እጥረት ምክንያት በክልሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ደመወዝና የትርፍ ጊዜ አበል ስላልተከፈላቸው ችግር መሆናቸውን አማኑኤል (ዶ/ር) አስረድተዋል።
በዚሁ ጉዳይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሲሰጡ ፤ " የጤና ባለሙያዎች የ17 ወራት ደመወዝ፣ የ22 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈላቸውም " ነው ያሉት።
አክለውም፣ " በቅርቡ የትግራይ ክልል ተቋማት በጀት ተለቆላቸዋል፣ ነገር ግን በጀቱ ደመወዝ ከመክፈል የዘለለ ፍላጎታችውን የሚያሟላ አይደለም፣ ወደ ኋላ እንኳ ተመልሰው ደመወዝ መክፈል አልቻሉም " ብለዋል።
" ብዙ ሰው ደግሞ ገና ለገና 'ለወደፊት ነገሮች ሲስተካከሉ ይከፈለኛል' በሚል አስተሳሰብ ብር ከነበራቸው ጋ እየተበደሩ፣ ለቤት አከራዮቻቸውም ቃል እየገቡ ነው የመጡት። የጤና ባለሙያው ትልቅ የሆነ ኪሳራ በሚባል ደረጃ ላይ ነው ያለው ፣ ብቸኛ ገቢያቸው ደመውዛቸው ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ኃላፊው በተጨማሪም የጤና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ የሕክምና እገልግሎት መስጠት እንዳልቻሉ የተመለከቱትን እውነታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።
" የተወሰኑ ለውጦች ቢጀምሩም ገና
ብዙ እርቀትን ይጠይቃል፣ ለምሳሌ ማይጨው ከተማ ትልቅ ከተማ ነው ላብራቶሪ ውስጥ ቀላል የተባለ የደም አይነት እንኳ አይሰራም " ያሉት አማኑኤል (ዶ/ር)፣ " በተመሳሳይ እንደዚሁ ሽረ ነበርኩ ባለፈው ሳምንት x ray ያላቸው አራት ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው። ሌላው ዝም ብሎ መሳሪያ ከቶ በድሮው አይነት አሰራር ሕክምና የሚሰጥበት ሁኔታ አለ " ብለዋል።
በሌላ በኩል በተለይ በመጠለያ ካምፕ ለሚኖሩ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ እጥረት ማጋጠሙ በተደጋጋሚ ይነገራል።
የጤና ቢሮ ኃላፊው በበኩላቸው፣ በሰሜን ምዕራብ መጠለያ ጣቢያ አደረኩት ባሉት ምልከታ አምስት በሦስት በሆነች መጠለያ ከ25 በላይ ሰዎች እንደሚኖሩ ገልጸው፣ " ልጅ ያላቸው አሉ፣ የሚኖሩት እየለመኑ ነው። ለረጅም ጊዜ መቆየት አይችሉም በጣም አስቸኳይ ስራን ይጠይቃል። የሚረዱን አጋሮች አሉ ግን ከእነርሱም አቅም በላይ ነው " ብለዋል።
ከጦርነቱ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የተወሰኑ መሻሻሎች እንዳሉ፣ ይህን እንጂ አሁንም የመድኃኒት እጥረት እንደሚያጋጥም፣ በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችም እንዳሉና ጥናቱ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።