TIKVAH-ETHIOPIA
#ምደባ ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል። ማብራሪያ ፦ - የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል። - የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ…
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ።
በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
Website: https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot
@tikvahethiopia

የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።
የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ500) የተቆረጠ መሆኑ ተመላክቷል።
ከላይ በተራ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የRemedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡
☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 ከ700 ያመጡ
☑ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 ከ700 ያመጡ
☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 ከ600 ያመጡ
☑ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 ከ600 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ከ700 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 192 ከ600 ያመጡ
☑ ታዳጊ ክልል የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 ከ700 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ
☑ አርብቶ አደር አካባቢ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 180 ከ600 ያመጡ
☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ
☑ ዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 150 ከ500 ያመጡ መሆን አለባቸው ተብሏል።
መረጃውን ትምህርት ሚኒስቴርን ዋቢ በማድረግ ያሰራጨው ኤፍ ቢ ሲ ነው።

#SafricomEthiopia
ዛሬ በ25 ብር ብቻ ለአስደሳች ጊዜ እንዘጋጅ! ጥቅሉን ለመግዛት *777# እንደውል፤
ጨዋታውን ባልተገደበ የኢንተርኔት ፍጥነት እንመልከት።
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

#AddisAbaba
አዲስ አበባ ውስጥ በዘላቂነት መቋቋም የሚሹ የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ከ300,000 በላይ ሰዎች መኖራቸውን የሴቶችና ሕፃናት ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ወይንእሸት ዘሪሁን እንደገለጹት፣ ፦
- ጎዳና ላይ የወደቁ፣
- በጸጥታ ችግር ከተለያዬ ክልሎች ወደ አዲስ አበባ የመጡ፣
- በአጠቃላይ የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ሰዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ታቅዷል።
በዘላቂነት ማቋቋም የሚሹ ምን ያህል ሰዎች እንደሆኑ እንዲገልጹ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " በዘላቂነት መቋቋም የሚሹ የድሃ ድሃ ተብለው የተለዩ ከ300,000 በላይ ሰዎች አሉ " ብለዋል ኃላፊዋ።
ሰዎቹን በዘላቂነት ለማቋቋም ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ሲጠየቁም፣ " ከፍተኛ የሆነ በጀት ይጠይቃል። በጀት ብቻም ሳይሆን ዝግጅትም ይጠይቃል " ነው ያሉት።
እነዚህን ሰዎች ለማቋቋምም የአዲስ አበባ አስተዳደር ሴቶችና ሕፃናት፣ የሴቶችና የፌደራሉ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቢሮዎች ከሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት በቅርቡ ውይይት ተደርጓል።
ጎዳና ላይ የሚገኙን በዘላቂነት መቋቋም የሚሹ አዛኛዎቹ ሰዎች ከየክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሥራ ፍለጋ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በአቻ ግፊት፣ በጸጥታ መደፍረስና በሌሎች መሰል ምክንያቶች ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመጡ መሆቸው ተነግሯል።
በተለያዩ ምክንያቶች ወደ መዲናዋ የመጡ ሰዎችን እጣ ፈንታ በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡም ወ/ሮ ወይንሸት፣ " ከሚመለከታቸው ከጤና ሙያተኞች ጋራ ሆነን ወደዬ አካባቢያቸው ሊመለሱ የሚችሉበትን ሁኔታ ነው የምንፈጥረው። ከዚህ ውጭ ያሉትን ግን የሥራ ዕድል ሊያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታ ከተለያዩ የግል ድርጅቶች፣ መግሥታዊ የሆኑና ያልሆኑ ተቋማት ጋራ በመነጋገር በመግባባት፣ በማሳመንም ጭምር ወደ ሥራ እዲቀላቀሉ ስልጠና እንዲያገኙ ካደረግን በኋላ ወደሥራ የሚገቡበትን ሁኔታ እንፈጥራለን " ብለዋል።
" ሴቶችን በተመለከተ በተመሳሳይ
አሁንም እየሰሩ ያሉ ድርጅቶች አሉ " ያሉት ኃላፊዋ፣ " የአረጋዊ ማቋቋሚያ ተብሎ ከሰንሻይን ጋራ በጋራ የተሰራ አለ። እስከ 750 አረጋውንን በቋሚነት የያዘ ትልቅ ማእከል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ሁልግዜ ተረጂ ሁነው ቀጥታ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ እራሳቸውን ችለው ሰልጥነው ሥራ ይዘው ቤተሰቦቻቸውን የሚመሩበት ደረጃ ላይ ለማድረስም በእንጀራ መጋገር ሥራ (በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ከ3ሺ 280 እስከ 4000 ይይዛል፣ ጉለሌ ላይ ጨምረናል ሌሎችም ሪሀቭቴሽን ሴንተር እያቋቋምን ነው " ብለዋል።
" ወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶችን ለማቋቋም መግሥት በጀት መድቦ ኦረዲ ስራውላይ ናቸው። የእዚህን ጉድለትና ክፍተት ግን ማኅበረሰቡ ሊደግፈን ይገባል " ሲሉ አክለዋል።
ወ/ሮ ወይንሸት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " አብዛኛዎቹ የድሃ ድሃ ተብሎ የተለዩ ናቸው። ግን በምገባ ስርአት ውስጥ የገቡ በቀን አድግዜ መመገብ የሚችሉ ሰዎች ናቸው። በተጨማሪ በሰፍቲነት ቀጥታ ድጋፍ ውስጥ የተካተቱ አሉ የተለያዩ ስራላይ እዲካተቱ ይደረጋል ባለኝ ዳታ 330, 000 ገደማ የተለዩ እዳሉ አውቃለሁ፣ ግን ቁጥር ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል" ሲሉ አብራርተዋል።
መረጃው በአ/አ ቲክቫል ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

Photo
" የሬሜዲያል ተማሪዎች ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትላንት ይፋ በተደረገው የማካካሻ ትምህርት / ሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከተደረገላቸው በኃላ ለ4 ወራት የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ሲሆን ይህንን ተከታትለው በተቋማቸው እና በማዕከል የሚሰጣቸውን ፈተና ማለፍ ሲችሉ በቀጣይ መደበኛ ተማሪ ሆነው ወደ ፌሽማን ይቀላቀላሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የመቁረጫ ነጥብ በሁሉም አማራጮች ማለትም #በግል እና #በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ይህም ማለት 210 ከ700፣ 180 ከ600 እና 150 ከ500 ማስመዝገብ አለባቸው።
በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) በዩኒቨርሲቲ ተመድበው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ በ #ተፈጥሮ_ሳይንስ የመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች መቁረጫው 255 ከ700 ነው። የሴት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫው ደግሞ 234 ከ700 ነው።
በዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚማሩ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡ 218 ከ600 ሲሆን ፤ የሴት ተማሪዎች መቁረጫው 200 ከ600 ነው።
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ዘንድሮ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው ይማራሉ።
#ማስታወሻ ፦ የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
በሌላ በኩል ፤ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ ከትላንት ጀምሮ ይፋ የተደረገ ሲሆን የምደባ መመልከቻው ፦በድረገፅ https://result.ethernet.edu.et/
የቴሌግራም ቦት @moestudentbot መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።
#TikvahEthiopia

አሁን ባሉበት ይችላሉ!!
ባንክ መሄድ ሳይጠበቅብዎ ባሉበት ሆነው ለክፍያ እና ሌሎች አገልግሎት አማራጭዎ በግሎባል ሞባይል ባንኪንግ ቀላል ሆኗል፡፡
መተግበሪያውን ከጎግል ፕሌይ ስቶር በማውረድ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፎቻችን ማስጀመር ይችላሉ፡፡ መተግበሪያውን በቴሌግራም ቻናላችን ያገኙታል፡፡
ቴሌግራም ቻናላችንን ለማግኘት
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
#GBEmobile #Digitalbanking #Finance #Globalbankethiopia

#EHRC
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ለተፈናቃዮች መቅረብ የጀመረው የምግብ ድጋፍ ተፈናቃዮች የሚገኙበትን አሳሳቢ ሁኔታ በሚመጥን ደረጃ ሊጠናከር ይገባል ብሏል ዛሬ በላከልን መግለጫ።
ኮሚሽኑ የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን ፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝቧል።
(ከኢሰመኮ የተላከልን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#ETHIOPIA
- " መንግሥት ኢሰመኮ ስለአማራ ክልል ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ ያወጣው መገለጫ ለሁሉም የሲቪክ ማኅበራት ማስፈራሪያ ነው። ...የሲቪክ ማኅበራት ሪፓርት ማውጣት የሚፈሩበት ጊዜ ላይ ነው ያሉት " - ከኢትዮያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል (አቶ ያሬድ ኃይለማርያም)
- " አሁን ያለንበት ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ ነው፣ የመንግሥት አካላት በአስቸኳይ መፍትሄ መስጠት አለባቸው ካልሆነ የማንወጣበት አሮንቃ ውስጥ ነው የምንገባው። " - ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) (አቶ ዳን ይርጋ)
- " ፍርድ ቤት ዋስትና የፈቀደለትን ሰው ወስዶ የሆነ ቦታ ማቆየት፣ ያለ ፍርድ ማሰር በተግባር የምናየው ቻሌንጅ ነው። ይህ ባለበት ሁኔታ ፓሊስ በተለይ የዜጎችን መብት በማክበርና በማስከበር በኩል ሁነኛ ተቋም ሆኖ እያለ በተግባር ያለው ግን ያ አይደለም " - ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅት ኅብረት (አቶ መሱድ)
- " 62 የፓለቲካ ፓርቲዎች አሉ ፤ እኛ ልንመርጣችሁ ወይስ እናንተ ልትመርጡን ነው ? እኛ የምንፈልገው 2፣ ቢበዛ ደግሞ 4 ነው። ለምን ወደዛ አትመጡም? የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚናፍቀው የባለስልጣናት ምርጫ አይደለም፣ የፓሊሲ ምርጫ ይፈልጋል። ለዚህስ ተዘጋጅታችኋል? " - ከቪዢንና ኮይግረንስ ፎር ዴሞክራሲ (አቶ ታደለ ደረሰ)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ 75ኛውን የሰብዓዊ መብቶች በዓል በማስመልከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሥትታት ጋር በመተባበር ጥቅምት 23 ቀን በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመገኘት ሁነቱን ተከታትሏል ፤ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ኃላፊዎችንም አነጋግሯል።
(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ተኩዬ ተዘጋጅቶ የቀረበ)
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-04-3

Telegraph
Tikvah Ethiopia
#ኢትዮጵያ 75ኛውን የሰብዓዊ መብቶች በዓል በማስመልከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መግስታት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ዓርብ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም አዘጋጅቶት በነበረው መርሀ ግብር የቲክቫህ ኢትዮጵያው ኢዮብ ትኩዬ ታድሞ ነበር። በዚህም ባለድርሻ አካልን ኢንተርቪው በማድረግ፣ በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች…
TIKVAH-ETHIOPIA
" እባክችሁ መፍትሄ ስጡን ፤ ጊዜው ያለ ትምህርት እየሄደብን ነው " - ተማሪዎች በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የሚማሩ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት እንዳልተመለሱ በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቀረቡ። መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች እስካሁን የሚማሩባቸው ግቢዎች እንዳልጠሯቸው በማመልከት ያለ ትምህርት መቀመጣቸውን ገልጸዋል። በእነሱ እድሜና…
#Update
በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዜዳንቶች በቅርቡ ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት እንዳደረጉ ቪኦኤ ዘግቧል።
የክልሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ፀሀፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዜዳንቶች ባደረጉት ውይይት ወቅታዊው የክልሉ የፀጥታ ችግር በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስቀጠል የሚያስችል እንዳልሆነ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።
ዶ/ር አስማረ ደጀን፦
" ተማሪዎችን አስገብተን እንዲህ ያሉ ግጭቶች በሚመጡበት ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊነት አይወስዱም።
የፀጥታ አካሉ፣መንግሥት ነው ኃላፊነት የሚወስደው ምክንያቱም ፀጥታውን የሚያስከብረው መንግሥት ነው።
በተለይ የ12ኛ ክፍል ስናስፈትን የሁለተኛው ዙር ፈተና ሃምሌ አካባቢ ነበርና ተማሪዎች እንደነበሩ ግጭቱ ተጀመረ ተማሪዎችን የሚወስዳቸው ጠፋ ኃላፊነት የሚወስድ መቶ በመቶ ጠፋ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ምንም ማድረግ አልቻሉም፤ የተለያዩ አካላትን ማግኘት አልቻሉም ተማሪዎችም የ200፣ የ120፣ የ100 ኪ/ሜ መንገድ በእግራቸው ተጉዘው ወደቤተሰቦቻቸው የሄዱበት ሁኔታ ነው ያለው፤በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በሚባልበት ደረጃ።
ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ ለ2016 የሚሆን የምግብ አቅርቦት ማዘጋጀት ነበረባቸው ነገር ግን አቅራቢዎቹ ከቦታ ቦታ ምርት ካለበት ቦታ ሄደው ተዘዋውረው መግዛት ስላልቻሉ የምግብ ግብአቶች በጠቅላላው ተማሪን ለመጥራት የሚያስችልበት ሁኔት አይደለም/ተማሪን ሊያስጠራ የሚችል ግብአት የለንም።
ተማሪ ይጠራ ቢባል ተማሪዎቻችን ከተለያዩ ክፍለ ሀገራት፣ ከክልሎች ነው የሚመጡት። "
ፎረሙ መንግስት የሚጠየቀውን ቅድመ ሁኔታ ማመቻቸት ከቻለ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን ለመጥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አሳውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር " ለ2016 ትምህርት በአሁን ሰዓት ተማሪዎችን ጥሩ እያለ ነው " የሚልው ፎረሙ ነገር ግን ለፀጥታው ኃላፊነት የሚወስድ አካል ከሌለ ይህን ማድረግ እንደሚያስቸግር አስገንዝቧል።
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ፤ ዘንድሮ በአካባቢው የቀጠለው አለመረጋጋት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እንደማያስችል ከተስማሙት የፎረሙ አባላት እንደሆኑ አሳውቀዋል።
ዶ/ር ታፈረ " ያለው ሁኔታ ካልተሻሻለ
በስተቀር አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ግቢ ውስጥ ተማሪ ማስገባት በእጅጉ ፈታኝ ነው የሚሆነው ለልጆችም ደህንነት በጣም አስጊ ነው " ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የምግብ አቅርቦት አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል። ምግብ የሚቀርበው ከወረዳ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ጭምር ስለሆነ መንገዶች ደህንነታቸው ካልተጠበቀ በስተቀር አቅርቦቱን ማሟላት ከባድ እንደሆነ አክለዋል።
ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው የሰጡ ወላጆች የአካባቢው የደህንነት እና ሰላም ሁኔታ በአስተማማኝነት እስካልተረጋገጠ እና ለልጆቻቸው ደህንነት ዋስትና እስካላገኙ ድረስ ልጆቻቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይልኩ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ስለሚማሩ ተማሪዎች ተከታታይ መልዕክቶችን መላኩ ይታወቃል።
ተማሪዎች ያለ ትምህርት ረጅም ወራት መቀመጣቸውን በመግለፅ መንግስት ከተቻለ ወደ ተቋማቸው እንዲያስገባቸው ካልሆነም ወደ ሌሎች ተቋማት አስገብቶ እንዲያስተምራቸው ሲጠይቁ ከርመዋል።
በእነሱ ተመሳሳይ እድሜና የትምህርት ደረጃ ያሉና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ገብተው ትምህርት መማር ከጀመሩ ሳምንታት ማለፉን በመግለፅም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ይገኛሉ።

በትግራይ ምን ያህል ተማሪ አለፈ ?
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ሆኗል።
በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በድረ-ገጽ eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተጨማሪም በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች በተመሳሳይ ድረ-ገጽ ላይ እስከ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ፤ ምላሽም በተመሳሳይ መልኩ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።
በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ9ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው ይታወሳል።
ምን ያህል ተማሪ 50 በመቶ እና በላይ አመጣ ?
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰራጩት ፅሁፍ የወጣውን የፈተና መስፈርት አሟልተው ብሔራዊ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ፦
🔹73.09 በመቶ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች
🔸 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች
በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።
ዝርዝር ቁጥራዊ መረጃው በቀጣይ ይገለፃልም ብለዋል።
ዶ/ር ኪሮስ ውጤቱን ላስመዘገቡ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን ይህ ውጤት እንዲመዘገብ የማይተካ ሚና ለተጫወቱት መምህራን፣ የትምህርት አመራሮች፣ ወላጆች ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ ፈተና በማዘጋጀት እና በመፈትን ውጤቱን በአጭር ጊዜ ለማሳወቅ ሌት ተቀን ላደረጉት ርብርብ የቢሮው ኃላፊ ምስጋና አቅርበውላቸዋል።
ተጨማሪ ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiatigrigna