TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray 657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል። በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል። ይህንን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ሙሴ ኪዳነ የሚባል ሲሆን የ " ቀላሚኖ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመመልከት ችሏል። እንደ ትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ መረጃ አጠቃላይ…
" በጦርነቱ ምክንያት ወደኃላ ባልቀር አሁን የ4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ " - ተማሪ ሙሴ ኪዳነ
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 657 በማምጣት ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው የቀላሚኖ ት/ት ተማሪ ሙሴ ኪዳነ " መድረስ ከነበረብኝ የትምህርት ደረጃ ባለመድረሴ ዓመታት ከእድሜ ላይ ተሰርቋል " ሲል ገልጿል።
የትግራይ #ሃውዜን ነዋሪ የሆነው ተማሪ ሙሴ አሁን ላይ እድሜው 22 ሲሆን ፤ ባስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደስ መሰኘቱን ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግሯል።
አስከፊው ጦርነት በይከሰትና ወደኃላ ባይቅር ኖሮ አሁን ላይ የ4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደነበርም ገልጿል።
ሙሴ ኪዳነ ፥ " አሁን የመጣው የፈተና ውጤት ጥሩ ነው። ደስም ብሎኛል ከውጤቱ ጋር አያይዤ ማለት የምፈልገው ሁሉም ሰው ያሰበውን ደረጃ ለመድረስ የሚያስችለውን ጥረት ካደረገ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው። " ብሏል።
መድረስ ከነበረበት የትምህርት ደረጃ ባለመድረሱ ዓመታት ከእድሜው እንደተሰረቀበት የሚገልፀው ተማሪ ሙሴ አሁን የሚገባውን ሁሉ የሚማርበት እድል ሊመቻች ይገባል ሲል ለትግራይ ቴሌቪዥን ተናግሯል።
በትግራይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ከ9,000 በላይ ተማሪዎች 73.09 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።
(ያለፉ ተማሪዎች ቁጥራዊ መረጃ ምንጭ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጎዑሽ የማህበራዊ ትስስር ገፅ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያሳውቃል)
@tikvahethiopiatigrigna @tikvahethiopia