TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ

" በተለያዩ ሚድያዎች ከሚሰማው በሬ ወለደ ወሬ በስተቀር ከኤርትራ በሚዋሰኑ የድንበር አከባቢዎች ከበፊቱ የተለየ ነገር የለም " - ኮማነደር ሙሉብርሃን

የድንበር የፀጥታ ጉዳይ የሚመለከት ሪፓርታጅ ! 

ኢትዮጵያ ከባህር በር ተጠቃሚነት ጋር አያይዛ ያነሳቸው ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ እንደነበር ይታወሳል።

ምንም እንኳን ስም ባትጠቅስም ጎረቤት አገር ኤርትራ በዜና ሚኒስተርዋ በኩል መግለጫ እስከማውጣትም ደርሳ ነበር።

ይህንን ተከትሎ ሁለቱ አገራት በሚያገናኘው ሰፊ የድንበር አከባቢ ፦
- ውጥረት እንዳለ ፣
- የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ኃይል ጋር በጥምር ወደ ደንበር መጠጋታቸው ፣
- ከባባድ የጦር መሳሪያዎች እየተጓጓዙ እንደሚገኙ የሚያትቱ ምንጫቸው #ያልተረጋገረጠ የአገር ውስጥና የውጭ ሚድያ ዘገባዎች እንዲሁም የማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፅ ፅሁፎች ተደምጠዋል ተነበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በአካል ለመመልከት ኢትዮጵያን በትግራይ በኩል ከሚያዋስኑ የምስራቃዊና የማእከላዊ ዞን አከባቢዎች ተጉዞ የሚከተለውን ሪፓርታጅ ልኳል።

የቲክቫህ ሪፖርተር እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ዓዲግራትና ፋፂ ተጓዘ ።

ዓዲግራት የምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ስትሆን ፣ ፋፂ የጉሎመኸዳ ወረዳ ዋና ከተማ ሆና ከኤርትራ ደንበር በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ ዛላኣምበሳ ከተማ ጨምሮ ከ5 በላይ ቀበሌዎችዋ እስከ አሁን በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ሰር የሚገኙባት ናት።

በተመሳሳይ በርካታ ቀበሌዎችዋ በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙባት የኢሮብ ወረዳ የኮሙኒኬሽን ባለሞያ ልኡል አፅብሃ ፣ የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ነጋሲ መንገሻና አርአያ ሃይሉ ፣ የፋፂ ከተማ ነዋሪዎች የዕብዮ አለም ፣ ጠዓመ እና ልዋም የተባሉ የቲክቫህ ሪፓርተር አነጋግሮ የሰጡት መልስ በአከባቢያቸው ከበፊቱ የተለየ ነገር እንደሌለ በመግለፅ አሁንም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙ አከባቢዎች እንዲያስለቅቅ ተማፅነዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፓርተር የምስራቃዊ ዞን ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ሙሉብርሃን አነጋግሮም በተለያዩ ሚድያዎች ከሚሰሙት በሬ ወለደ ወሬ በስተቀር በዞኑ ከኤርትራ በሚዋሰኑ የድንበር አከባቢዎች ከበፊቱ የተለየ ነገር እንደሌለ አረጋግጠውለታል።

የቲክቫህ ሪፓርተር የማእከላይ ዞን ከተሞች ሆነው ለኤርትራ ድንበር የቀረቡት እንትጮ ፣ ድብድቦ ዓድዋና አክሱም ድረስ ተጉዟል።

ያለውን ሁኔታ በአይኑ ከመታዘብ በተጨማሪ የከተማዎቹ ነዋሪዎች አነጋግሮ በአከባቢያቸው ከበፊቱ የተለየ ነገር እንዳለዩ ነግረውታል።

ኣክሱም ድረስ በመጓዝ ያነጋገራቸው የማእከላይ ዞን ፓሊስ አዛዥ በለጠ ገ/የሱስም ከነዋሪዎቹ የተለየ አስተያየት እንደሌላቸው በመግለፅ ፣ ይሁን እንጂ ከኤርትራ ድንበር በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ከሚገኙት የራማና ከተማና አሕሳኣ ወረዳ የኤርትራ ሰራዊት አባላት ሾልከው በመግባት ሰዎች አፍነው የመውሰድ ሁኔታ እንዳለ ፣ የዚሁ ዋናው ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ የትግራይ ድንበር አከባቢ በቂ የሆነ የአገር መከላከያ ሰራዊት ባለመኖሩ መሆኑ ለቲክቫህ ሪፓርተር ገልጸዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-04-2

@tikvahethiopia