TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከምን ደረሰ ? ሳፋሪኮ ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እንዲሁም አሁናዊ የተቋሙን እንቅስቃሴ በተመለከተ በቀጣይ ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል። ተቋሙ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት ሊጀምር ነው " የሚሉ፣ ቀኖች እና ሌሎች ተቋማዊ መረጃዎችን ያካተቱ ዜናዎችና መረጃዎች በማሕበራዊ ድረገጾች መውጣታቸውን…
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም በሃምሌ ወር በድሬዳዋ አገልግሎት ይጀምራል።

በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኤክስተርናል አፌርስ እና ሬጉላተሪ ዋና ኃላፊ ማቲው ሀሪሰን ሀርቪ ፦

" ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኔትወርኩን በማስጀመር አገልግሎቶችን ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው።

ይህንንም በድሬዳዋ በሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም በመጀመር በቀጣይ ወራት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ 24 ከተሞች የሚስፋፋ ይሆናል።

በአሁኑ ወቅት ያለንበት የሙከራ ጊዜ አገልግሎታችንን ሙሉ በሙሉ ስንጀምር ጥራት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚረዳን ነው።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና አካታትችነት እቅድ በመደገፍ የገባነውን ቃል ጠንካራ መሠረት በመገንባት እየተገበር ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ሕይወት ፋይዳ ያለው አበርክቶ ለማድረግም በትጋት እየሠራን እንገኛለን "

(ሙሉ የሳፋሪኮም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR ነገ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ህ/ተ/ምክር ቤት ይቀርባሉ። በዚህም በ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል። በተጨማሪ ፓርላማው በተለያዩ ጉድዮች ላይ ውይይት ያደርጋል። @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ !

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በህ/ተ/ም/ቤት ቀርበው ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።

የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የንፁሃን ዜጎች ግድያን ፣ የህግ ማስከበርን፣ ሰላማዊ ሰልፍ፣ የሰላም ጉዳይን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ያንብቡ 👉https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-07-07

(የጠ/ሚ ፅ/ቤት)

@tikvahethiopia
የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ !

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ሚኒሰቴሩ የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እንዲሁም የትራንስፖርት መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

(አዲስ ይፋ የተደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia ሳፋሪኮም በሃምሌ ወር በድሬዳዋ አገልግሎት ይጀምራል። በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኤክስተርናል አፌርስ እና ሬጉላተሪ ዋና ኃላፊ ማቲው ሀሪሰን ሀርቪ ፦ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኔትወርኩን በማስጀመር አገልግሎቶችን ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው። ይህንንም በድሬዳዋ በሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም በመጀመር በቀጣይ ወራት በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ 24 ከተሞች የሚስፋፋ ይሆናል።…
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን ምን ምን ስራ ሰራ ?

በሰኔ 2013 ዓ.ም የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድ ከተሰጠው ጀምሮ ፦

👉 የኔትወርክ እና የመሰረተ ልማቶች ግንባታዎች ላይ በማተኮር የሞባይል ሬድዮ ታወሮችን፤ ብሔራዊ የማሰራጫ ኔትወርኮን እና ለዓለም አቀፍ ግንኙነት የሚሆኑ ስምምነቶችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ገንብቷል።

👉 የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድን ጨምሮ ለልዩ ልዩ ሥራዎች 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስት አድርጓል።

👉 ከ300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ የሚያወጡ መገልገያዎችን ወደ አገር ውስጥ አስገብቷል።

👉 ኮር ኔትወርዎርኩ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (1) እንዲሁም ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ማበልፀግ ጀምሯል።

👉 የደንበኞች ጥሪ ማስተናገጃን አደራጅቷል።

👉 ሁለት የመረጃ ቋት ማዕከላት (Data Centers) ገንብቷል።

👉 በቅርቡ የመሠረተ ልማት መጋራት እና #ከአንዱ_ወደ_ሌላው_ለመደወል የሚያስችሉ ስምምነቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራርሞ ትግበራው በጥሩ መልኩ እየተካሔደ ነው።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SafaricomEthiopia ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን ምን ምን ስራ ሰራ ? በሰኔ 2013 ዓ.ም የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድ ከተሰጠው ጀምሮ ፦ 👉 የኔትወርክ እና የመሰረተ ልማቶች ግንባታዎች ላይ በማተኮር የሞባይል ሬድዮ ታወሮችን፤ ብሔራዊ የማሰራጫ ኔትወርኮን እና ለዓለም አቀፍ ግንኙነት የሚሆኑ ስምምነቶችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ገንብቷል። 👉 የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪነት ፍቃድን ጨምሮ…
የቀጠለ ...

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመሠረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ ሌሎች የሰራቸው ስራዎች ፦

👉 የተሳካ አገልግሎት ለማቀረብ አንዲሁም የሙያ እና የክህሎት ሽግግርን ለማጠናከር ብቃት ያለው የአመራሮች ሰብስቦ አዋቅሯል።

👉 የሰው ኃብቱን ወደ 500 ያሳደገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 320ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። በቀጣይም ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ ሠራተኞች እንዲኖሩት ለማድረግ እየሰራ ነው።

👉 50 አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን መልምሎ ጊዜውን የዋጁ ኃሳቦችን እና መፍትሔዎችን ሊጠቁም የሚችሉ ዲጂታል የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያዊያንን ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 100 አዲስ ተመራቂዎችን ለመመልመል በልዩ ልዩ ክልሎች ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየሠራ ነው።

👉 በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሊያዳርሱ የሚችሉ 29 አከፋፋዮችን በአቅራቢነት በመያዝ ድርጅቶቹ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እየተሰራ ነው።

👉 አገልግሎት መስጠት ለመጀመር ያዘጋጀነው ዕቅድ የችርቻሮ መደብሮችን እንዲያካትት በማድረግ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችሉ ጨረታዎች አውጥቷል።

👉 ማህበራዊ ኮንትራቱን ማዘጋጀት የቀጠለ ሲሆን 'ዲጂታልን በመጠቀም ሕይወትን የማሻሻል' ርዕዩን በሚያሳካ መንገድ ለዚህ መሠረት ለመጣል የሚያስችሉ እቅዶችን አውጥቷል።

#SafaricomEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ! ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በህ/ተ/ም/ቤት ቀርበው ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል። የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የንፁሃን ዜጎች ግድያን ፣ የህግ ማስከበርን፣ ሰላማዊ ሰልፍ፣ የሰላም ጉዳይን በተመለከተ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል። ያንብቡ 👉https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-07-07 (የጠ/ሚ…
#HoPR

የ2015 ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ/በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ሙሉ ለሙሉ አውቶሜት ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል።

ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በርካታ ታብሌት ኮምፒዩተሮች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በኮቪድ-19 ምክንያት አምራች ድርጅቱ ኮምፒዩተሮቹን በተያዘለት ጊዜ ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል።

ኮምፒዩተሮቹ በተያዘላቸው ጊዜ ከደረሱ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የቀጣይ ዓመት ፈተና ኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

ታብሌቶቹ በሚጠበቀው ጊዜ ካልደረሱ፥ መንግስት የፈተና ስርቆት የሚቀነስበት የተሻለ አሰራር በመከተል ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
𝐀+ 𝐎𝐧𝐥𝐢𝐧𝐞 𝐓𝐮𝐭𝐨𝐫𝐬 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚

ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ በመጠቀም ለልጆችዎ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በኦንላይን አዘጋጅተናል።

*ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች በ2015 ዓ.ም ተግባራዊ በሚሆነው የት/ት ስርአት
*ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ የሆነ የማትሪክ ዝግጅት

ለመመዝገብ ባሉበት ሆነው ይደውሉ
፦+251-960-60-17-18 ፣ +251-960-60-00-00
ለተጨማሪ መረጃ Telegram_Channel https://t.iss.one/APlusOnlineTutorsEthiopia
Facebook_Channel
https://www.facebook.com/APlusOnlineTutorsEthiopia/
#BorisJhonson

• ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን በገዛ ፍቃዳቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን ለቀቁ።


• አዲስ ጠ/ሚ እስኪሰየም ቦሪስ ጆንሰን ቦታው ላይ ይቆያሉ።


ከምክር ቤት እና ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸው ድጋፍ ማግኘት ያልቻሉት የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ከወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው መሪነት እንዲሁም ከጠ/ሚ ስልጣናቸው ለቀቁ።

ለፓርቲው መሪነት የሚደረገው ፉክክር በቅርቡ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ደግሞ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር ይሰየማል ተብሏል።

አስከዚያው ድረስ ግን ቦሪስ ጆንሰን በአገሪቱ የጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ላይ ይቀጥላሉ።

ጆንሰን በአመራራቸው ላይ በርካታ ትችቶች ሲቀርብባቸው ቆይቶ በርካታ ባለሥልጣኖቻቸው በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ነው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት።

ቻንስለር ናዲም ዛሃዊን ጨምሮ ከፍተኛ ካቢኔ አባሎቻቸው “ በክብር የሥልጣን መንበራቸውን እንዲለቁ ” ለጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣን እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስከ ሐሙስ ረፋድ ድረስ ሳይቀበሉት ቆይተው ነበር ፤ ነገር ግን የፓርላማ አባሎቻቸውን ድጋፍ ማግኘት ሳይችሉ በመቅረታቸው በመጨረሻ ወስነዋል።

ሚኒስትሮቻቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን በመልቀቃቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ከፓርላማ አባላት ማግኘት ያልቻሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፓርቲ መሪነትና ከጠ/ሚ የስልጣን መንበራቸው በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።

ከወራት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያስረክባሉ።

#SkyNews #BBC

@tikvahethiopia
#AhaduBank

አሐዱ ባንክ ሐምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል።

ይህ አስመልክቶ ባንኩ ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ ፤ 10 ሺህ በሚደርሱ ባለአክሲዮኖችንና በ564 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል እና በ702 ሚሊዮን በተፈረመ ካፒታል ተዋቅሯል ብለዋል።

ሀላፊው እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም የቅርንጫፎቹን ብዛት 50 እደሚያደርስም ተናግረዋል።

ባንኩ ፦

➡️ ከሚያቀርበው ብድር እስከ 15 በመቶ የሚሆውን ለስራ ፈጣሪዎች እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማቅረቡ ፤

➡️ ከተለመደዉ በሰራተኛ ከታገዘ የቅርንጫፍ አገልግሎት በተጓዳኝ ደንበኞች በራሳቸዉ የዲጂታል አገልግሎት የሚያገኙበት የቅርንጫፍ ዉስጥ አገልግሎት አደረጃጀት ማመቻቸቱ ፤

➡️ የገጠር የባንክ አገልግሎትን ለአርሶና አርብቶ አደሮች፣ የገበሬ ማህበራት ለማዳረስ መዘጋጅቱ ፤

➡️ የውስጥ አሰራሩን ወረቀት አልባ ማድረጉ ፤

➡️ ደንበኞች ካሉበትና ቦታ ሆነዉ ራሳቸዉን የባንኩ ደንበኛ ማድረግ የሚችሉበትን አሰራር ማምጣቱ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።

ባንኩ ከሀምሌ 2 እስከ ሀምሌ 7 /2014 የተለያዩ ማህበራዊ ግዴታዎች እንደሚያከናውን የገለፀ ሲሆን " አንድ ቅርንጫፍ ለአንድ ልጅ " በሚል ባንኩ በሚከፍታቸዉ ቅርንጫፎች ቁጥር ልክ ድጋፍ እና እገዛ ለሚያስፈልጋቸዉ ልጆች ዓመታዊ ወጪያቸዉን እንደሚሸፍን ገልጿል።

ባንኩ በተጨማሪም አዲሱ መለያ ሎጎውንም በይፋ አስተዋውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አልተፈታም " - ቤተሰቦቹ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን እንዲያከበር ጠየቁ። ትናንት ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ መወሰኑ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ቤተሰቦቹ ለዋስትና የተጠየቀውን ብር…
" የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና ታግዷል " - ቤተሰቦቹ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር እንዲፈታ ወይም የማይፈታበትን ምክንያት ካለ ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ ታዞ ነበር።

የታዘዘው ለዛሬ ሀሙስ ሰኔ 30 ሲሆን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ ሽብር ችሎት ቀርቦ፣ የዋስትናው ብይን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የታገደ ስለሆነ ሊፈፅም ያለመቻሉን አስረድቷል።

ችሎቱም ያልተፈታበትን ይሄን የጠቅላይ ፍ/ቤት ምክንያት ተቀብሎ አሰናብቶናል።

በዚህ መሠረት ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዋስትና ሊፈታ አይገባም ክርክር ላይ ይግባኙን ለማድመጥ ለሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ስነስርዓት ወደ ዓርብ ተሻገረ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ14ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ነገ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚካሄድ ገልጾ ነበር። ነገር ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ምክንያት የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ወደ ዓርብ ሃምሌ 1 ቀን 2014 የተዛወረ መሆኑን አስተዳደሩ አሳውቋል። የአዲስ…
#አጭር_ማስታወሻ

ነገ ጥዋት በአዲስ አበባ ፤ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ይወጣል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ አጭር የመረጃ ማስታወሻ ፦

⮕ ነገ የሚካሄደው የ3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነስርኣት ነው።

⮕ አጠቃላይ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች በዕጣ ይተላለፋሉ።

⮕ በ20/80 ፕሮግራም 18 ሺ 648 ፤ በ40/60 መርኃ ግብር 6 ሺህ 843 ቤቶች በድምሩ 25 ሺህ 491 ቤቶች ለነዋሪዎች በእጣ ይተላለፋሉ።

⮕ በዕጣው የሚካተቱት በ1997 እና በ2005 ዓ.ም ተመዝግበው እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በአማካይ ለ60 ወራት የቆጠቡ የ20/80 እና 40 በመቶ እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ የ40/60 ቤት ፈላጊዎች ናቸው።

⮕ 79 ሺ 794 ከሚሆኑ ቤት ፈላጊዎች መካከል 25 ሺህ 491 የሚሆኑት ዕድለኞች በነገው የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት ይለያሉ።

⮕ በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ለባለዕድለኞች የሚተላለፉ ቤቶች የሚገኙት አያት 2፣ ቦሌ በሻሌ፣ ቡልቡላ ሎት ነው።

⮕ በ20/80 ለባለዕድለኞች የሚተላለፉ ቤቶች የሚገኙት በረከት፣ ቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ሳይት 5 እና 6 ወታደር፣ የካ ጣፎ፣ ጀሞ ጋራ፣ ጎሮ ስላሴ ፣ ፉሪ ሀና እና ፋኑኤል ነው።

⮕ የመንግስት ሰራተኛ 20 በመቶ ፣ ሴቶች 30 በመቶ ፣ የአካል ጉዳተኞች 5 በመቶ በእጣው ተጠቃሚ ይሆናሉ።

(ሙሉ መረጃው ትላንት የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከተናገሩት የተወሰደ ነው/ENA)

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጫዋቾች እንዱሁም አሰልጣኝ ሽልማት ትላንት ተካሂዷል።

አሸናፊዎቹ ፦

⚽️ የጅማ አባ ጅፋር ወጣቱ ግብ ጠባቂ አላዛር ማርቆስ የአመቱ ምርጥ ወጣት ተሸላሚ። የ105 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት አግኝቷል።

⚽️ ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው የአመቱ ምርጥ ዳኛ በመባል የተመረጠ ሲሆን 105 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

⚽️ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ ቻርለስ ሉክዋጎ የውድድር ዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመባል 150ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶለታል።

⚽️ የከፍተኛ ግብ አግቢነት በአስራ ስድስት ግቦች ያሸነፈው ይገዙ ቦጋለ የ 200,000ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

⚽️ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል አሸንፏል። የ200 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

⚽️ የቅዱስ ጊዮርጊሱ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም የአመቱ ምርጥ በመባል ተመርጧል። 250ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

Join : @tikvahethsport