#Update
ዛሬ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ መሆን ጀመረ።
ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ፤ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡
የነዳጅ ድጎማውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160,000 በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ሰኔ 29 /2014 ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል።
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ ነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት ተለይቷል። ይህም እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለ ብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች ብቻ ዕለታዊ የነዳጅ መጠን ፦
👉 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
👉 መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
👉 ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
👉 መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
👉 የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
👉 የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
👉 ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
@tikvahethiopia

ገና የግንባታው ስራ ባልተጠናቀቀ ማደያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ የተከማቸ 184 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተገኘ።
ህገወጥ ነዳጁ የተገኘው በእንጅባራ ከተማ ነው።
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር አደረኩት ባለው ክትትል ግንባታው ባልተጠናቀቀ ማደያ በአንድ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የቀረበ 184 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተገኝቷል።
ከነዳጁ ውስጥ 46 ሺህ ሊትር የሚሆነው ቤንዚን ሲሆን ቀሪው ናፍጣ መሆኑንም ተገልጿል።
ይኸው ነዳጁ የተገኘበት ያልተጠናቀቀ ማደያ ከከተማ አስተዳደር ከተሰጠው የግንባታ ፈቃድ ውጭ ገና ህጋዊ ዕውቅና ያላገኘና የማጠራቀሚያ ታንከር ብቻ የተቀበረበት መስፈርቱን ያላሟላ ነው ተብሏል።
ነዳጁ ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ ተከማችቶ መገኘቱም ተጠቅሷል።
የድርጊቱ ፈፃሚዎች ተጠናቂ እንደሚደረጉ ከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።
በሌላ በኩል ፤ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ ልዩ ቦታው ጉንጫ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በአራት ቦቴ የተገለበጠ ነዳጅ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ መገኘቱ ተገልጿል።
መረጃ፦ ከአዊ ኮሚኒኬሽንና ከአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ የተገኘ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ 📈 ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህ መሰረት ፦ 👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም 👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም 👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም 👉 ከባድ…
ነዳጅ ምን ያህል ጨመረ ?
ከሚያዚያ 30 / 2014 ዓ/ም አስንቶ ይኸው ያለንበት ሰኔ ወር ማብቂያ ድረስ የነበረው የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋ መሸጫ ይህ ይመስል ነበር (ጭማሪ የተደረገው ሚያዚያ 30 እንደነበር እና በሰኔ ወር ባለበት መቀጠሉ አይዘነጋም) ፦
👉 ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ፣
👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
👉 ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም
ከዛሬ #ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ #ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ፦
👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም
👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር 02 ሳንቲም
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር 10 ሳንቲም
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር 37 ሳንቲም
#ልብ_ይበሉ ፦ ከዛሬ በኃላ ባለው ጭማሪ የቤንዚን ፣ የኬሮሲን እና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 % በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 % እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል።

#ብርሃን_ባንክ
በብርሃን ኢንተርኔት ባንኪንግ ካሉበት ሆነው ክፍያ፤ ገንዘብ ማስተላለፍ እና መሰል ጉዳይዎትን በምቾት ይከውኑ!
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc

ዛሬ በልዩ ስብሰባ በመከረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምን ተባለ ?
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በልዩ ስብሰባ መክሯል።
ምክር ቤቱ በንጹኃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተባበረ ድምፅ እንደሚያወግዝም ገልጿል።
የምክር ቤቱ አባላት በቀጣይ መሰል አደጋዎችን ለመከላከል በጋራ እንደሚቆሙም ፤ የኢትዮጽያ ህዝብም ከጐናቸው በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምክር ቤቱ በወቅታዊ የፀጥታ እንዲሁም በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሐሳብ ያስተላለፈ ሲሆን የዕለቱን መርኃ-ግብር በግፍ ለተጨፈጨፉት ዜጎች የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በማድረግ ነው የጀመረው።
(ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው የውሳኔ ሐሳቦች ከላይ ተያይዟል)
በሌላ በኩል በዛሬው ስብሰባ " ብሔራዊ የሀዘን ቀን " እንዲታወጅ ጥያቄ ቢቀርብም፤ ምክር ቤቱ ለጊዜው ይህን አካሄድ ሳይከተል ቀርቷል።
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ " መጀመሪያ በህገ መንግስቱ መሰረት ሂደቱን ጠብቆ መታወጅ ካለበት ህጉን እንመልከት እና ምንም ችግር የለውም። እዚሁ አምጥተን ጸድቆ ይታወጃል " ማለታቸውን ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አንድ የፓርላማ አባል እንደነገሩት " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ፅፏል።
እኚሁ የፓርለማ አባል ፤ በዛሬው ልዩ ስብሰባ ላይ 17 የሚሆኑ የምክር ቤት አባል አስተያየት መስጠታቸውን ገልፀዋል።
" መንግስት ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም፤ መንግስት ኃላፊነቱን ይወጣ " እና " የመንግስት ሹማምንት እጃቸው አለበት እና መንግስት ራሱን ያጥራ " የሚሉ ሀሳቦች ተደጋግመው መነሳታቸውን የምክር ቤት አባሉ ለድረገፁ አስረድተዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ #ክረምቱ_ጠንከር እያለ በመምጣቱ መላው የከተማው ነዋሪዎች ሁሉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ትላንት በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ያጋጠመው የበረዶ ክምር ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ መንገድ በመዝጋት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጫና አሳርፎ መስተዋሉን ገልጿል።
በዚህም የከተማው ነዋሪዎች በየአካባቢው የክረምት ወቅቱን ተከትሎ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ አደጋዎች ከወዲሁ የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲያደርጉ የከተማው አስተዳደር አሳስቧል።
(Mayor Office of AA)

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ በ3ኛው ዙር የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ 24 ሺህ 491 ቤቶች ነገ ዕጣ ይወጣባቸዋል ተብሏል።
በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአት ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ላይ " በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአቱ 79 ሺህ 794 ተመዝጋቢዎች በዕጣ አወጣጥ ውድድሩ ውስጥ ይካተታሉ " ብለዋል።
#ከ1997 ዓ.ም የ20/80 ተመዝጋቢዎች መካከልም 60 ወራት ሳያቋርጡ የቆጠቡ ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውም ገልፀዋል።
ነገ ጠዋት ሁለት ሰአት ላይ በሚካሄደው የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ላይ ከንቲባ አዳነች አበቤን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችና ታዛቢዎች ይገኛሉ መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#HoPR
ነገ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ህ/ተ/ምክር ቤት ይቀርባሉ።
በዚህም በ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።
በተጨማሪ ፓርላማው በተለያዩ ጉድዮች ላይ ውይይት ያደርጋል።

Photo
" ሰሚ አጥተናል፤ ነገስ ዋስታናችን ምንድነው ? " - የቲክቫህ አባላት ቄለም ወለጋ
ከሰሞኑን ጭፍጨፋ በተፈፀመበት የቄለም ወለጋ ፤ አካባቢ የሚኖሩ እና ቤተሰቦቻቸው በቦታው ያሉ ወገኖች አሁን ላይ ፀጥታ ኃይል በአካባቢው ቢኖርም የነገ ዋስትናቸው እንደሚያሳችባቸው ገልፀዋል።
ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ ጥቃት ተፈፅሞ ሌላ ሀዘን እንዳይከተል ፀጥታው መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል።
" እኛ ሰሚ አጠተናል፣ እጅግ በጣም ተሰቃየን ፣ መፍትሄ እንፈልጋለን ፣ ፍትህን እንፈልጋለን ፣ ተጠናቂነት እንዲሰፍን እንፈልጋለን " ሲሉ በሀዘን ስሜት ውስጥ ሆነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ከጭፍጨፈው የተረፉት ወገኖች " የሀዘን መግለጫ ጋጋታ አንፈልግም ፣ በየጊዜው ንፁሃን ሰው ይጨፈጨፋል መግለጫ እንደጉድ ይወጣል በኃላም ይረሳል ተጎጂዎችን ዞር ብሎ እንኳን የሚያየ የለም " ብለዋል።
" እኛ የሀዘን መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የሚታይ ተግባር ፣ የመኖር ዋስትና መረጋገጥን ብቻ ነው የምንፈልገው ፤ ምንም ስለፖለቲካ የማያውቁ ህፃናት፣ ሴቶች እናቶች ያለሃጢያታቸው ለምን ይጨፈጨፋሉ ? መቼ ነው ይሄ የሚያበቃው " ሲሉ ጠይቀዋል። የንፁሃንን ሞት ለፖለቲካ ንግድ እና በየሚዲያው ለገንዘብ የሚጠቀሙ በሀዘናችን ላይ ሀዘን እየደረቡ ነው ብለዋል።
ለደረሰብን አስከፊ ነገር ሁሉ " አላህ ብቻ ነው ፍርዱን ከሰማይ የሚሰጠው " ሲሉም ገልፀዋል።
ከትላንት ወዲያ ሰኞ ዕለት በተፈፀመው ጭፍጨፋ ህይወታቸው ያለፉትን ሰዎች የመቅበር ስነስርዓት የተከናወነ ሲሆን እዛ አካባቢ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ አባል አንድ የሚያውቀው ሰው ወንድሞቹ ከነቤተሰቦቹ መገደላቸውን ፤ ከዚህ ባለፈ የታገቱ ሰዎች መኖራቸውን አመልክቷል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Family-07-06

የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም !
" ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ብለዋል።
ከንቲባዋ በመግለጫቸው የከተማ አስተዳደሩ በየ3 ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰዋል።
በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩ በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉን አስረድተዋል።
በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ አይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም አይነተ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።
#አከራዮችም ሆኑ #ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመው ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አሳስበዋል።
በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብት እና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።
#ENA

#AddisAbaba በአዲስ አበባ በ3ኛው ዙር የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ 24 ሺህ 491 ቤቶች ነገ ዕጣ ይወጣባቸዋል ተብሏል። በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአት ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይ " በዕጣ አወጣጥ ሥነ ስርአቱ 79 ሺህ 794 ተመዝጋቢዎች በዕጣ አወጣጥ ውድድሩ ውስጥ ይካተታሉ " ብለዋል። #ከ1997…
#AddisAbaba
የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ስነስርዓት ወደ ዓርብ ተሻገረ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ14ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ስነስርዓት ነገ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚካሄድ ገልጾ ነበር።
ነገር ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ምክንያት የእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ወደ ዓርብ ሃምሌ 1 ቀን 2014 የተዛወረ መሆኑን አስተዳደሩ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ ለተፈጠረው የፕሮግራም ለውጥ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ታዛቢዎች፣ ባለዕድለኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሚዲያ አካላት በተለዋጩ ፕሮግራም እንዲገኙ (ማለትም ዓርብ) መልዕክት አስተላልፏል።