THIQAH
13.2K subscribers
2.61K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
“በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል። የሃማስ መሪ ሳይገደል አልቀረም” - እስራኤል

"እስራኤል በሆስፒታል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ለመሸፋፈን ያቀረበችው ውሸት ነው። መሀመድ ሲንዋር በህይወት አለ" - ሀማስ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ረቡዕ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል” ብለዋል።

ሚኒስትሩ የሃማሱ መሪ መሃመድ ሲንዋር በእስራኤል መከላከያ ኃይል ባለፈው ሳምንት ሳይገደል እንዳልቀረም ተናግረዋል ተብሏል።

“በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል” ያሉት ጠ/ሚው፣ መሀመድ ሲነዋርን ጨምሮ ሌሎች የሀማስ አመራሮች መገደላቸውን ተናግረዋል።

የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ኦሳማ ሃምዳን በበኩላቸው ለቴህራን ታይምስ፤ ይህ እስራኤል በሆስፒታል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ለመሸፋፈን ያቀረበችው ውሸት መሆኑን ተናግረዋል።

በጋዛ የሚገኘው ወንድማችን መሀመድ ሲንዋር በህይወት አለ ያሉት ኃላፊው፤ አሁንም ጠላትን በጽኑ ይዋጋል ብለዋል።

እስራኤል "ተገደለ"፣ ሃማስ "በህይወት አለ" የተባባሉበት የሃማስ መሪ በደቡባዊ ጋዛ በእስራኤል መከላከያ የተገደለው የቀድሞ የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ወንድም ነው።

መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የሳዑዲ አረቢያ የዜና ማሰራጫ አሻርክ አል አውሳት የመሀመድ ሲንዋር ሞት ከሁለት ቀናት በፊት ለቤተሰቦቻቸው መርዶ መነገሩን ምንጮችን ጠቅሶ ዘ ጀሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።
#GazettePlus #tehrantimes #jerusalempost

@EyobTikuye  @ThiqahEth
👍20🔥3😱1
"ትራምፕ ኢራን ላይ ምንም መፍጠር ስላልቻሉ፤ የጥቃቱን ክሽፈት በግነት እየሸፋፈኑት ነው"- ኢራን

ትራምፕ ኢራን ላይ ምንም መፍጠር ስላልቻሉ፤ የጥቃቱን ክሽፈት በግነት እየሸፋፈኑት ነው ሲሉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ ገለጹ።

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ ትራምፕ የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ያደረሰውን ውጤት አስመልክቶ በማጋነን እየተናገሩ ነው። ሆኖም ጥቃቱ ምንም አይነት ውጤት አላስገኘም ብለዋል።

መሪው በይፋዊ የኤክስ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባልተለመደ መልኩ በተለይ ኢራን ላይ ያደረሱትን ጥቃት ማጋነናቸውን ገልፀዋል።

ኢራን ላይ ምንም ማድረግ አልቻሉም እና  ነገሮችን በማጋነን እውነቱን ለመደበቅ እየጣሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ወደ ኢራን ዘልቆ በመግባት የኒውክሌር አቅማቸውን አጥፍተናል ማለታቸው ይታወሳል።

የሁለቱ ሀገራት ግጭት በአሜሪካ አመቻችነት በተደረሰ የተኩስ አቁም ስምምነት ተቋጭቷል ተብሏል።
#GazettePlus #Anadolu

@ThiqahEth
22🤔4😡4👏1🙏1
100 የኢትዮጵያ ብር በ57.58 የሩሲያ ሩብል እንዲመነዘር ተመን ወጣለት ተባለ።

የሩሲያ ሩብል ከኢትዮጵያ ብር ጋር ያለውን የምንዛሪ ተመን የሩሲያ ባንክ ይፋ አድርጓል።

በዚህም 100 የኢትዮጵያ ብር በ57.5872 የሩሲያ ሩብል እንዲመነዘር ተመን ወጥቶለታል፡፡

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያ ብር የምንዛሪ ተመን ይፋ ሲያደርግ ለኢትዮጵያ ብር ኮድ 230 የመለያ ቁጥር የተሰጠው ሲሆን፤ የምንዛሪ ተመን በየጊዜው ማሻሻያ እየተደረገበት ይቀጥላል ተብሏል።

የሁለቱ ሀገራት ገንዘቦች የእርስ በእርስ የምንዛሪ ተመን መቀመጡ በመካከላቸው ያላቸውን የንግድና ሌሎችንም ልውውጦች በቀጥታ ለማከናወን እንዲችሉ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡
#GazettePlus

@ThiqahEth
48🕊5👏3