“በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል። የሃማስ መሪ ሳይገደል አልቀረም” - እስራኤል
"እስራኤል በሆስፒታል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ለመሸፋፈን ያቀረበችው ውሸት ነው። መሀመድ ሲንዋር በህይወት አለ" - ሀማስ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ረቡዕ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል” ብለዋል።
ሚኒስትሩ የሃማሱ መሪ መሃመድ ሲንዋር በእስራኤል መከላከያ ኃይል ባለፈው ሳምንት ሳይገደል እንዳልቀረም ተናግረዋል ተብሏል።
“በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል” ያሉት ጠ/ሚው፣ መሀመድ ሲነዋርን ጨምሮ ሌሎች የሀማስ አመራሮች መገደላቸውን ተናግረዋል።
የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ኦሳማ ሃምዳን በበኩላቸው ለቴህራን ታይምስ፤ ይህ እስራኤል በሆስፒታል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ለመሸፋፈን ያቀረበችው ውሸት መሆኑን ተናግረዋል።
በጋዛ የሚገኘው ወንድማችን መሀመድ ሲንዋር በህይወት አለ ያሉት ኃላፊው፤ አሁንም ጠላትን በጽኑ ይዋጋል ብለዋል።
እስራኤል "ተገደለ"፣ ሃማስ "በህይወት አለ" የተባባሉበት የሃማስ መሪ በደቡባዊ ጋዛ በእስራኤል መከላከያ የተገደለው የቀድሞ የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ወንድም ነው።
መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የሳዑዲ አረቢያ የዜና ማሰራጫ አሻርክ አል አውሳት የመሀመድ ሲንዋር ሞት ከሁለት ቀናት በፊት ለቤተሰቦቻቸው መርዶ መነገሩን ምንጮችን ጠቅሶ ዘ ጀሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። #GazettePlus #tehrantimes #jerusalempost
@EyobTikuye @ThiqahEth

👍20🔥3😱1
በኢራን አምስት ሰዎች በሽብር ጥቃት ሲገደሉ ከ20 በላይ ለጉዳት ተዳረጉ።
በባልቹስታን ግዛት በተፈጸመው ጥቃት ከ20 በላይ ነዋሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል መወሰዳቸውን የግዛቲቱ ፖሊስ ቢሮ አስታውቋል።
ጥቃቱን የሱኒ ጃዒሽ ባሉች ታጣቂዎች እንደፈጸሙት ተገልጿል።
በአካባቢው ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው ይህ ቡድን ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ብሏል።
ቡድኑ ንጹሐን ከጦር ቀጠና እንዲርቁ ጥሪ አስተላልፏል። #jerusalempost
@ThiqahEth

😢4❤1🤔1🙏1