“በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል። የሃማስ መሪ ሳይገደል አልቀረም” - እስራኤል
"እስራኤል በሆስፒታል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ለመሸፋፈን ያቀረበችው ውሸት ነው። መሀመድ ሲንዋር በህይወት አለ" - ሀማስ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ረቡዕ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል” ብለዋል።
ሚኒስትሩ የሃማሱ መሪ መሃመድ ሲንዋር በእስራኤል መከላከያ ኃይል ባለፈው ሳምንት ሳይገደል እንዳልቀረም ተናግረዋል ተብሏል።
“በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን አስወግደናል” ያሉት ጠ/ሚው፣ መሀመድ ሲነዋርን ጨምሮ ሌሎች የሀማስ አመራሮች መገደላቸውን ተናግረዋል።
የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ኦሳማ ሃምዳን በበኩላቸው ለቴህራን ታይምስ፤ ይህ እስራኤል በሆስፒታል ላይ የደረሰውን የቦምብ ፍንዳታ ለመሸፋፈን ያቀረበችው ውሸት መሆኑን ተናግረዋል።
በጋዛ የሚገኘው ወንድማችን መሀመድ ሲንዋር በህይወት አለ ያሉት ኃላፊው፤ አሁንም ጠላትን በጽኑ ይዋጋል ብለዋል።
እስራኤል "ተገደለ"፣ ሃማስ "በህይወት አለ" የተባባሉበት የሃማስ መሪ በደቡባዊ ጋዛ በእስራኤል መከላከያ የተገደለው የቀድሞ የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ወንድም ነው።
መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የሳዑዲ አረቢያ የዜና ማሰራጫ አሻርክ አል አውሳት የመሀመድ ሲንዋር ሞት ከሁለት ቀናት በፊት ለቤተሰቦቻቸው መርዶ መነገሩን ምንጮችን ጠቅሶ ዘ ጀሩሳሌም ፖስት ዘግቧል። #GazettePlus #tehrantimes #jerusalempost
@EyobTikuye @ThiqahEth

👍20🔥3😱1
ኢራን ሦስት የF-35 ጄቶችን "መትቼ ጥያለሁ" አለች።
የኢራን ጦር ሁለት የእስራኤል አብራሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ገልጿል።
ጦሩ አብራሪዎቹ በምዕራብ ኢራን መያዛቸውን አስታውቋል።
"በአምስት አቅጣጫ ፈጸምኩት" ባለው የሚሳዔል ጥቃትም ከ150 በላይ የጦርና ኢንተሊጀንስ ስፍራዎችን "አውድሚያለሁ" ብሏል።
በአሁኑ ወቅት በካሚካዜ ድሮን የታገዘ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ የገለጸው ጦሩ፣ በመጪዎቹ ሰዓታት ከባድ የሚሳዔል ጥቃቶች እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።#tehrantimes
@ThiqahEth

❤30😡4🕊3
"ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚፈጥሩ ወይም ጠላትን የሚደግፉ እንቅስቃሴዎች የእርምጃችን አካል ይሆናሉ" - የኢራን ባህር ኃይል
ኢራን ወደ እስራኤል ስታቀና የነበረች የእንግሊዝ የጦር መርከብ በቁጥጥር ስር አዋለች።
መርከቧን የያዛት የኢራን ባህር ኃይል፣ "የፅዮናዊውን መንግስት የሚሳዔል ጥቃት ለመፈጸም የሚያግዝ ድጋፍ ይዛ ነበር" ብሏል።
"ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚፈጥሩ ወይም ጠላትን የሚደግፉ እንቅስቃሴዎች የእርምጃችን አካል ይሆናሉ" ሲል ገልጿል። #tehrantimes

❤42👏13😡7🕊3
ኢራን " 10 የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖችን መትቼ ጣልኩ " አለች።
የካታም አል አንቢያ አየር ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አሊረዛ ሳባህፋርድ፣ "የጦር አውሮፕላኖቹን ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ከጥቅም ውጭ አድርገናቸዋል" ብለዋል።
ጄነራል ሳባህፋርድ " የኢራን አየር መከላከያ የእስራኤልን ድሮን በስኬታማ መንገድ በማክሸፍ ወደ ዋና ከተማዋ የተቃጣውን ኢላማ አስቀርቷል " ብለዋል።
እርምጃው የተወሰደው ለሦስተኛው ዙር በቀጠለው የምሽቱ የእስራኤል ጥቃት እንደሆነ አብራርተዋል።
ኢራን F_35 የእስራኤል የጦር ጄቶችን መትታ መጣሏንና ሁለት አብራሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገልፃ ነበር። #tehrantimes

❤49🕊4👏2🙏2😢1
ኢራን በ4 ቀናት ውስጥ ለ9ኛ ጊዜ በእስራኤል ላይ ጥቃት አደረሰች።
በዚህ ጥቃቷ በባለስቲክ ሚሳዔል በመታገዝ የሀይፋ ከተማን፣ ኔጌቭ በረሃን እና ክርያትጋት ከተማን አጥቅታለች ነው የተባለው።
ቴህራን በዚህ የአጸፋ እርምጃዋ ወታደራዊ ስፍራዎችን እና የኢንዱስትሪ መንደሮችን ኢላማ እንዳደረገች ተገልጿል።
በዚህ የኢራን ጥቃት የተነሳ እነዚህ ሦስት ከተሞች የሀይል መቆራረጥ አጋጥሟቸዋል ተብሏል።
የእስራኤል ቴክኖሎጂ ማዕከል እየተባለ የሚጠራው የሀይፋ ከተማ የኑክሌር ጣቢያ የሚገኝበት እና የሚሳዔል ማከማቻ ስፍራ እንደሆነ ተገልጿል።
ከስፍራው የወጡ ምስሎች እንደሚያሳዩት ሆነ ሰባት ህንፃዎች በሙሉ በሙሉ በመውደማቸው የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች አደጋውን ለመቆጣጠር እየተረባረቡ ይገኛሉ። #tehrantimes
(እስራኤል በቀናት ውስጥ የሰነዘረችው ጥቃትና የጉዳት መጠን በቀጣይ ይቀርባል)

👏30❤19🕊4😭2