TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በታይዋን በደረሰ የባቡር አደጋ 22 ሰዎች ሲሞቱ 171 ዱ ቆስለዋል የባቡሩ አደጋ የደረሰው የቱሪስት መዳረሻ ከሆነችው ዳርቻ ታይፒ ወደ ታይቱንግ ሲጋዝ ነው፡፡ የአደጋ ግዜ ሰራተኞችና የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ደርሰው ተጎጂዎችን መታደጋቸውን ዘገባው ሲጠቅስ በጉዳቱ የቆሰሉ ሰዎች ለህክምና ወደ ቅርብ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ የአደጋመው መንስዔ #እየተጣራ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትንሹ የ70 ሰዎች ህይወት አለፈ🔝

#በባንግላዲሽ ዋና ከተማ #ድሃካ በተከሰተ ቃጠሎ በትንሹ 70 ሰዎች ሞቱ። በዋና ከተማዋ ጥንታዊ የመኖሪያ ሰፈር የተከሰተው ቃጠሎ የተነሳው በአንድ ህንጻ ውስጥ የነበረ ተቀጣጣይ የኬሚካል መጋዘን ውስጥ እንደሆነ ተገልጿል።

የእሳት ቃጠሎው በፍጥነት ወደ መኖሪያ መንደሮች በመስፋፋት ከፍተኛ አደጋ አድረሷል ነው የተባለው።

ከ50 ያላነሱ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን የተወሰኑት አስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው ተብሏል።

በአካባቢው በሰርግ ላይ የታደሙ ሰዎችም የአደጋው ሰለባ ሳይሆኑ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው።

አደጋው የደረሰው ከ300 ዓመታት በላይ እድሜ ባለቤት በሆነው የቻውክባዛር መንደር ነው።

ይህ ጥንታዊ ስፍራ በጣም ጠባብ መንገዶች ያሉት ሲሆን በመኖሪያ ህንጻዎች መካከል ያለው ክፍተትም እጅግ ጠባብ መሆኑ አደጋውን የከፋ እንዳደረገው ተነግሯል።

ቃጠሎውን ለማጥፋት 200 የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ ሲሆን የውሃ እጥረትና የመንገዱ ጠባብ መሆን እንዳስቸገራቸው ተጠቆሟል። እሳቱ የተከሰተበት ምክንያት #እየተጣራ መሆኑም ታውቋል።

ምንጭ፦ቢቢሲ፣ ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍1
ከጦላይ🔝

"ሀይ ፀግሽ! አብደሰላም ነኝ #ከጦላይ---ዛሬ የጦላይ ህዝብ እና የፕሪፓራቶሪ ተማሪዎች #ትላንት በተከሰተው የምግብ #መመረዝ ለተጎዱት የኦነግ ወታደሮች የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ጉዳዩም #እየተጣራ እንደሆነ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UoG

🚨 " አሁንም በርካታ የታመሙ ተማሪዎች ወደ ህክምና ተቋሙ እየሄዱ ነው "- ተማሪዎች

➡️ " በሽታው የተከሰተው ከምግብ ወይም ከውሃ ጋር የተያያዘ መሆኑን ገና
እየተጣራ ነው " - አብርሃም ዘገየ የተማሪዎች ዲን

በጎንደር ዩንቨርስቲ የፋሲል ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፋክሊቲ ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መታመማቸውን ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከባለፈው እሮብ ጀምሮ በግቢው " በውሃና በምግብ ብክለት ነው " ብለው በጠረጠሩት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች መታመማቸውን ህክምና ላይ ያሉ ተማሪዎች አመልክተዋል።

ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁን በግቢው ተማሪ መሆናቸውን እና አሁን በህክምና ላይ መሆናቸውን የገለፁልን ተማሪዎች ግቢው ውስጥ ባለው የህክምና ተቋም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች እየታከሙ መሆኑን ገልፀዋል።

ለተሻለ ህክምናም ወደ ጎንደር ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የተላኩ እንዳሉም ተማሪዎች ተናግረዋል።

በግቢው የአምስተኛ ዓመት ተማሪ እንደሆነ የነገረን ተማሪ ባለፈው እሮብ ምሳ ላይ የተመገቡት ፓስታ እርሱን ጨምሮ በርካቶችን ለህመም እንደዳረጋቸው ይጠረጥራል።

የትኩሳት፣ የተቅማጥ እና እጅና እግር የመቆረጣጠም ምልክት እንዳለው የሚናገሩት ታማሚዎች ወደ ህክምና ተቋም የሄዱ ተማሪዎች በሙሉ " ታይፎድ " ነው እንደተባሉ ተማሪው ተናግሯል።

ሌላው የሶስተኛ አመት የኤሌክትሪካል እንጂነሪንግ ተማሪ መሆኑን የነገረንና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን ተማሪ ደግሞ ምግቡ፤ የሚጠጣው ውኃም ተበርዟል ይላል። ህክምና ተደርጎለት መድሃኒት እየወሰደ እንደሆነ የሚናገረው ይህ ተማሪ የውሃ እጥረት በግቢው ስር የሰደደ ችግር ነው ብሏል።

ከየት እንደሚመጣ የማይታውቅ ውኃ በቦቴ ተጭኖ ይመጣል በጥራቱ ሁሌ እንጠራጠር ነበር። በተለይ ሰሞኑን ከተማሪዎች መታመም ጋር በተያያዘ አብዛኛው ተማሪ የታሸገ ውሃ ገዝቶ እየጠጣ ይገኛል ብሏል።

ተማሪዎቹ ለተማሪዎች ህብረት ተወካይ ችግሩን ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

የኢንጅነሪግ ተማሪዎች ብቻ በሚማሩበት በጎንደር ዩንቨርስቲ የፋሲል ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፋክልቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳት የሆነውን ተማሪ ተመስገን ችግሩ መከሰቱንና እርሱን ጨምሮ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታመማቸውን ገልጾ፥ ችግሩ ከውሃው ነው በመባሉ ትላንት በታንከሩ ያለው ውሃ ተቀይሮ በኬሚካል በታከመ ውሃ መቀየሩን ተናግሯል።

በጎንደር ዩንቨርስቲ የፋሲል ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፋክልቲ የተማሪዎች ዲን አብርሃም ዘገየ በግቢው ከመቶ በላይ ተማሪዎች ወደ ክሊኒክ ታመው መሄዳቸውን ጠቅሰው ከመጡት ውስጥ 84 ተማሪዎች ብቻ " ባክቴሪያ " ተገኝቶባቸው መድሃኒት ተሰጥቶቸው እያገገሙ ነው ብለዋል።

ከዚህ ህመም ጋር በተያያዘ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጎንደር ዩንቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የሄዱት ከ5 እንደማይበልጡና ከእነዚህ ውስጥ ተጏዳኝ የጨጏራና ሌሎች ችግሮች ያለባቸው ናቸው ተብለው ታክመው የተመለሱ ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

ቀለል ያለ ስሜት ላላቸው ተማሪዎችም ኦ አር ኤስ እየተሰጣቸው ነው፤ ከዩንቨርስቲው አመራር ጋር በመሆን የመድሃኒት ችግር እንዳያጋጥምም ወደ ክሊንኩ አስገብተናል ያሉት አብርሃም የውሃና የምግብ ችግር ነው የሚለውን ምክንያት
#እየተጣራ ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirdar

@tikvahethiopia
😭50695💔39🙏33🤔25😡21👏17😢15🕊11😱10🥰1