በትንሹ የ70 ሰዎች ህይወት አለፈ🔝
#በባንግላዲሽ ዋና ከተማ #ድሃካ በተከሰተ ቃጠሎ በትንሹ 70 ሰዎች ሞቱ። በዋና ከተማዋ ጥንታዊ የመኖሪያ ሰፈር የተከሰተው ቃጠሎ የተነሳው በአንድ ህንጻ ውስጥ የነበረ ተቀጣጣይ የኬሚካል መጋዘን ውስጥ እንደሆነ ተገልጿል።
የእሳት ቃጠሎው በፍጥነት ወደ መኖሪያ መንደሮች በመስፋፋት ከፍተኛ አደጋ አድረሷል ነው የተባለው።
ከ50 ያላነሱ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን የተወሰኑት አስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው ተብሏል።
በአካባቢው በሰርግ ላይ የታደሙ ሰዎችም የአደጋው ሰለባ ሳይሆኑ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው።
አደጋው የደረሰው ከ300 ዓመታት በላይ እድሜ ባለቤት በሆነው የቻውክባዛር መንደር ነው።
ይህ ጥንታዊ ስፍራ በጣም ጠባብ መንገዶች ያሉት ሲሆን በመኖሪያ ህንጻዎች መካከል ያለው ክፍተትም እጅግ ጠባብ መሆኑ አደጋውን የከፋ እንዳደረገው ተነግሯል።
ቃጠሎውን ለማጥፋት 200 የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ ሲሆን የውሃ እጥረትና የመንገዱ ጠባብ መሆን እንዳስቸገራቸው ተጠቆሟል። እሳቱ የተከሰተበት ምክንያት #እየተጣራ መሆኑም ታውቋል።
ምንጭ፦ቢቢሲ፣ ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia