አቢሲንያ ባንክ 7 #ቨርቹዋል የባንክ ማዕከሎችን በዛሬው እለት በተከናወነ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ሥራ ማስጀመሩን ገልጿል።
አቢሲንያ ባንክ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ቨርቹዋል የባንክ ማዕከል አስመርቆ ሥራ ሲያስጀምር፣ ቴክኖሎጂው ለሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ ለባንክ ኢንዱስትሪው ቀዳሚ ከመሆኑ አኳያ ባንኩን ፋና ወጊ እንዲሆን እንዳስቻለው ገልጿል።
ቨርቹዋል የባንክ አገልግሎት ቴክኖሎጂ ደንበኞች የባንክ ቅርንጫፍ የተገደበ የጊዜ ሰሌዳ ሳያሳስባቸው በቅርንጫፍ የሚያገኙትን አገልግሎት በቀን ለ24 ሰዓት በሳምንት ለ7 ቀናት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ደንበኞች ከሚያገኟቸው አገልግሎቶች መካከል ፦
- ሒሳብ መክፈት ፣
- ገንዘብ ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ ፣
- ቼክ መመንዘርና ተቀማጭ ማድረግ ፣፤
- የሃገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ ሓዋላ አገልግሎት ፣
- ገንዘብ ማስተላለፍ፤
- እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ካርድ ባንኪንግና ሞባይል መኒ ያሉ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት ምዝገባ ማከናወን ይገኙበታል።
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የቨርቹዋል አገልግሎት ያስጀመረ ሲሆን ዛሬ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነላቸው 7 ማዕከላት ውስጥ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ የሚገኙ የክልል ከተሞች ፦
-ደሴ፤
- መቐለ፤
- ሆሳዕና፤
- አርባምንጭ የሚገኙበት ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ማዕከላቱን 15 አድርሷል።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሶስት ማእከላት የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከተመረቁት ማዕከላት መካከል በቃሊቲ፤ በጎፋ እንዲሁም በጀሞ አካባቢ ይገኙበታል።
ባንኩ በቀጣይ ሳምንታት የሚመረቁ አምስት የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ማእከላትን ጨምሮ በመላው ሀገራችን የሚገኙ የቨርቹዋል ባንኪንግ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን 29 በማድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
@tikvahethiopia

#ጥቆማ
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፤ የገና ሥጦታ ሎተሪ በትላንትናው ዕለት መውጣቱን ገልጿል።
10 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የዕጣ ቁጥር 1616519 ሆኖ ወጥቷል።
አጠቃላይ የዕጣ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀርጌሳ " ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል። ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ…
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ
የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ #የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ (MOU) ይዘት ምን ይላል ?
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦
- #ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ስታደርግ እንደነበረው፤ ከሶማሌላንድም ጋር ከዚህ በፊት እንደነበረው አይነት ስምምነቶችን ያነሳና ይሄ ስምምነት ወደተሟላ ደረጃ መድረስ እንዳለበት ያስቀምጣል።
- ኢትዮጵያ አሁን ያለባትን ስጋት እንድትቀርፍ የህዝብ እድገቷን ፣ የኢኮኖሚ እድገቷን የሚመጥን አካባቢው ካለው የሁከት ተጋላጭነት የራሷን ደህንነት እንዲሁም የቀጠናውን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ሚና እንዲኖራት የሚያስችል እራሷ የምታለማውና የምትቆጣጠረው የተወሰነ የባህር በር ያስፈልጋታል የሚል ነው። ይህ ሚሊታሪ ቤዝ እና ማሪታይም / ኮሜርሻል አገልግሎት ነው።
- የሚሊታሪ እና የማሪታይም / ኮሜርሻል ቤዝ ቦታው አማካይ እንዲሆን ተሞክሯል።
- ቦታው በበርበራ እና በዛይላ መካከል የሚገኝ ስፍራ ነው። ለኢትዮጵያ ድንበር አጠር ያለና ለሚሰራውም መንገድ እና ባቡርም የቀለለ፣ ለጥበቃውም የተመቸ እንዲሆን ነው። " ሎጋያ " የተባለ ቦታ አለ ለድንበር ቅርብ እዛ ላይ እንሰጣችኃለን በሚል ተስማምተዋል።
- ርቀቱን በተመለከተ እነሱም እኛም ስንለው የነበረው ነበር አማካይ ላይ ተገናኝነትን በ20 ኪ/ሜ የሚሆን ቦታ ቤዝ ይኖረናል በዓለም አቀፍ ህጉ ውሃውንም ይጨምራል ፣ ከውሃው ወደ መሬት ያለውንም እንዲሁ።
- ከድንበር ወደሚመሰረተው ቤዝ የሚሄድ መንገድ ይሰራል።
- ጊዜው 50 ዓመት እንዲሆና ሲያልቅ የሚራዘምበትን አማራጭ ያስቀምጣል።
ምንድነው ኢትዮጵያ የምትሰጣቸው ?
➡ የመንግሥት ፖሊሲ ግልፅ እንዳደረገው ከቴሌኮም ፣ ከኃይል ማመንጫ ፣ ከአየር መንገድ ... ብቻ አዋጭ ከሆኑ ተቋማት #እራሳችን በምንመራበት መንገድ ለሀገርም በሚጠቅም መልኩ #ድርሻ መስጠት ነው። ይሄ ለሶማሌላንድም የሚሰራ ነው። ምናልባት ከኤርትራ ፣ ከኬንያ ፣ ከጅቡቲ ስምምነት ቢደረግ ይሄ ይሰራል።
➡ ፈጥኖ መግባባት ላይ የደረሰው #ከሶማሌላንድ ጋር ስለሆነ ነው እንጂ ንግግሩ ከሁሉም ሀገራት ጋር ይቀጥላል። የአሁኑ ብቻ በቂ ስላልሆነ ከሌላውም ጋር እንነጋገራለን።
➡ በ50 ዓመቱ መግባቢያ ስምምነት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ይኖራቸዋል ብለናል። ድርሻው ስንትነው ? የሚለው ተዘርዝሮ አልተቀመጠም። እኛ ለእነሱ የምንከፍለው #ሊዝ / #ኪራይ ዋጋው ስንት ነው የሚለውን ገና አልጨረስንም። ስንጀምረው ስምምነት በሚሆን መንገድ ላይ ጀምረን እነዚህ ጉዳዮች ስላላለቁ ነው ወደ መግባቢያ ሰነድ (MOU) የተመለሰው።
➡ ገና ዝርዝር ነገሮች ያስፈልጋሉ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትክክለኛ አቅሙ፣ በገበያ ዋጋ ሲተመን ስንት ነው የሚለው ዝርዝር ተሰርቶ ወደ ንግግር ይገባል። እኛ የምንሰጠው ስንትነው የሚለው በሊዝ ከሚገኘው ዋጋ አለመብለጡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
➡ አሁን #በቀጠናው በሊዝ የተከራዩ በርካታ ሀገራት አሉ ፤ ጅቡቲ እንኳን በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት ቤዝ አላቸው በሊዝ የሚጠቀሙት ስለዚህ ትልቁን የሚከፍሉት ስንት ነው ? ለምን ? ትንሹን የሚከፍሉት ስንትነው ? ለምን ? አማካዩ ስንት ነው ? እኛ ካለን ቅርበትና ከምንሰጠው አገልግሎት ተያይዞ ስንት ነው የምንከፍለው የሚለው ይቀመጣል። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስንት ብንሰጥ ነው ተመጣጣኝ የሚሆነው የሚለው ዝርዝር ስራ ይፈልጋል። በዚህ ምክንያት ወደ MOU ተመልሷል።
➡ በሌሎች ሴክተሮች ላይ የተሟላ ትብብር ማድረግ አለብን ፦
• በጤና ፣
• በትምህርት፣
• በውጭ ጉዳይ፣
• በከተማ ልማት
... በእነዚህ እራሳቸውን የቻሉ #ስምምነቶች መዘጋጀት አለባቸው ይሄም ገና አላለቀም።
በአጠቃላይ የመግባቢያ ሰነዱ ፦
* መሬት ከሶማሌላንድ በኪራን እንደምናገኝ
* መሬቱን እራሳችን እነምናለማው
* መሬቱን 50 ዓመታትን እንደምንገለገልበት ፤ እሱን የሚያስችል ክራዩንም የሚመጥን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ድርሻ #እንደምንሰጥ ይስቀምጣል።
ከዚህ ባለፈ ...
ለ30 ዓመታት #የተሟላ እውቅና ሳያገኙ ሀገር ሆነው ቆይተዋል። እውቅና ለማግኘት ይሞክራሉ ፤ ይሄን በተመለከተ የኢትዮጵያ አቋም ምን ይሆናል ? የሚለው ጉዳይ ይነሳል።
' ወደ ተሟላ ስምምነት ደርሶ፣ መሬቱን ተረክበን ሂደቱ ሲቋጭ እነሱ እውቅና ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት በተመለከተ ኢትዮጵያ #አቋም_ትወስዳለች የሚል አመላካች ነገሮች ነው ያሉት ሰነዱ። '
አሁን ላይ ስምምነት ሆኖ አልተረከብንም ፣ ስምምነት ሆኖ አልሰጠንም። #መስማማት እንዳለብን ግን ተስማምተናል ፤ እሱንም በመግባቢያ ሰነድ ፈርመናል።
#AmbassadorRedwanHussein

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የበዓል መዋያ ስጦታ ተበረከተ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት የበዓል መዋያ ስጦታ አበርክቷል፡፡
ስጦታው የተበረከተላቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ ሰባት የሚገኙ አቅመ ደካማ አረጋውያን እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ባንኩ ላደረገላቸው የበዓል መዋያ ስጦታ ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ለጋራ ስኬታችን” በሚል መሪ ቃል የዛሬውን ጨምሮ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ምንጭ፡ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቴሌግራም ገፅ
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ
ለጋራ ስከታችን!
#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #gena #genaholiday

#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ #የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ (MOU) ይዘት ምን ይላል ? አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦ - #ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ስታደርግ እንደነበረው፤ ከሶማሌላንድም ጋር ከዚህ በፊት እንደነበረው አይነት ስምምነቶችን ያነሳና ይሄ ስምምነት ወደተሟላ ደረጃ መድረስ እንዳለበት ያስቀምጣል። - ኢትዮጵያ አሁን ያለባትን ስጋት እንድትቀርፍ የህዝብ እድገቷን ፣ የኢኮኖሚ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹
ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የመግባቢያ ስምምነት አደጋ ይዞ ይመጣል ?
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ያለ አንዳች ግጭት፣ ውጊያ ከባለቤቶቹ ተደርጓል ያሉት የመግባቢያ ስምምነት አደጋ እንደማያመጣ ገልጸዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦
" ኢትዮጵያ የባህር በር የላትም፤ እድገቷ በጣም ጨምሯል። በዙሪያዋ የሚተናኮሳት ፤ እሷን መተናኮስ ባይፈልግም እርስ በእርስ ሲተናኮስ ፍንጣሪው የሚደርስበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።
እጇን አጣጥፋ ተቀመጠች እንበል ... በቃ ጅቡቲ ብቻ ምንም እንዳትሆን እንፀልይ ፣ የጅቡቲ መንገድም ምንም እንዳይሆን እንፀልይ ብሎ መንግሥት ቢቀመጥ የኢትዮጵያን ዋስትና ያረጋግጥ ነበር ወይ ብሎ መከራከር አለባቸው ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች።
ወይም ኢትዮጵያ በዚህ መንገድ ሳይሆን ከዚህ በተሻለ ሌላ አማራጭ ልታገኝ ይገባ ነበር ብለው ማምጣት አለባቸው።
የአንዳንድ ሰዎችን ንግግር እየታዘብኩት ያለው የዛሬ ስንት ዓመት የሆነ መንግሥትን ወቅሰው የኢትዮጵያን የባህር በር አሳጣ ብለው ፤ የሆነ አካልን ወቅሰው በዚህ ምክንያት ' ግማሽ ትውልድ ቢያልቅም መዋጋት አለብን ' ይሉ የነበሩ ሰዎች አሁን ደግሞ ያለ ውጊያ በንግድ ሂሳብ ያለንን ሰጥተን የሌለንን ለማግኘት የሚደረግ ስምምነትን አደጋ ያመጣል ይላሉ።
' ግማሽ ትውልድ ቢያልቅም ችግር የለም ልዋጋ ' የሚል ሰው እንዴት ብሎ ነው ያለ ውጊያ በጋራ የመግባቢያ ሰነድ ፣ ከባለቤቶቹ ጋር በሚደረግ ትብብር የሚደረግ ፊርማ ኢትዮጵያ ላይ አደጋ የሚያመጣው ?
የህዳሴ ግድብን ስንገነባ አደጋ ያመጣል፣ ያጋጨናል፣ ያዋጋናል፣ ስለዚህ ምናለ ትንንሽ ወንዞችን ብናለማ ያሉ ሰዎች አሁን ከለማ በኃላ አደጋ አልመጣም። እንደውም ተጨማሪ አደጋ መከላከል የምትችልበትን አቅም ነው የፈጠረችው።
የባህር በር ቢኖረን ተጨማሪ ጉዳት ሊደርስብን የማይችልበትን አቅም ነው የሚፈጥረው። ሁለት ሶስት አራት አምስት እራሳችን የምናለማው ወደብ ቢኖረን ቤዝ ቢኖረን እራሳችን የምንቆጣጠረው እራሳችን ኢንቨስት ያደረግንበት ቢኖረን የተሻለ አማራጭ ነው የሚኖረን። የተሻለ የመከላከል ፣ የተሻለ በቀላል ዋጋ ንግዳችንን የማሳለጥ ፣ በቀላሉ አቅማችንን የማጎልበት እድል ነው የሚፈጠረው።
እኛስ ጎረቤቶችን ነን የቀጠናው ባለቤቶች ነን፤ ከበርካታ ሺህ ኪሎሜትሮች መጥቶ ቤዝ ያለው ሀገር ነገር ፍለጋ አይደለም የመጣው ግን ጥቅሙን ለማስከበር ነው የመጣው እኛ ባለቤቶቹ እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥና ሌሎች እስኪወስኑ ድረስ ለእነሱ እንፀልይ የሚል ትውልድና ግለሰብ ስለኢትዮጵያ ጥቅም፣ በአጠቃላይ ስለ ብሄራዊ ጥቅም ተገቢ ግንዛቤ፣ ተገቢ ቁርጠኝነትና ይሁንታ ኖሮት ነው የሚናገረው ማለት ይከብዳል። "

#EOTC
በአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ #ወጣት የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማን በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በዝማሬ እና በፀሎት አክብሮ ውሏል።
" ጃንደረባው ትውልድ " በተሰኘ ማህበር አዘጋጅነት በተዘጋጀ " የአእላፋት ዝማሬ " የሚል ስያሜ በተሰጠው መርሃ ግብር እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን አብዛኛው #ወጣት በቤተክርስቲያን ተገኝቶ የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማን በልዩ #በሃማኖታዊ ስነስርዓት ተቀብሏል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ሌሎች ብፁዓን አባቶች ተገኝተው ነበር።
" የጃንደረባው ትውልድ ማኅበር " በቅርቡ በመንበረ ፓተርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ የእውቅና ምሥክር ወረቀት ማግኘቱ ተነግሯል።
ፎቶ፦ TMC / ከማህበራዊ ሚዲያ