TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሀርጌሳ " ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል። ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል። አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ…
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ

የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ #የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ (MOU) ይዘት ምን ይላል ?

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦

- #ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ስታደርግ እንደነበረው፤ ከሶማሌላንድም ጋር ከዚህ በፊት እንደነበረው አይነት ስምምነቶችን ያነሳና ይሄ ስምምነት ወደተሟላ ደረጃ መድረስ እንዳለበት ያስቀምጣል።

- ኢትዮጵያ አሁን ያለባትን ስጋት እንድትቀርፍ የህዝብ እድገቷን ፣ የኢኮኖሚ እድገቷን የሚመጥን አካባቢው ካለው የሁከት ተጋላጭነት የራሷን ደህንነት እንዲሁም የቀጠናውን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ሚና እንዲኖራት የሚያስችል እራሷ የምታለማውና የምትቆጣጠረው የተወሰነ የባህር በር ያስፈልጋታል የሚል ነው። ይህ ሚሊታሪ ቤዝ እና ማሪታይም / ኮሜርሻል አገልግሎት ነው።

- የሚሊታሪ እና የማሪታይም / ኮሜርሻል ቤዝ ቦታው አማካይ እንዲሆን ተሞክሯል።

- ቦታው በበርበራ እና በዛይላ መካከል የሚገኝ ስፍራ ነው። ለኢትዮጵያ ድንበር አጠር ያለና ለሚሰራውም መንገድ እና ባቡርም የቀለለ፣ ለጥበቃውም የተመቸ እንዲሆን ነው። " ሎጋያ " የተባለ ቦታ አለ ለድንበር ቅርብ እዛ ላይ እንሰጣችኃለን በሚል ተስማምተዋል።

- ርቀቱን በተመለከተ እነሱም እኛም ስንለው የነበረው ነበር አማካይ ላይ ተገናኝነትን በ20 ኪ/ሜ የሚሆን ቦታ ቤዝ ይኖረናል በዓለም አቀፍ ህጉ ውሃውንም ይጨምራል ፣ ከውሃው ወደ መሬት ያለውንም እንዲሁ።

- ከድንበር ወደሚመሰረተው ቤዝ የሚሄድ መንገድ ይሰራል።

- ጊዜው 50 ዓመት እንዲሆና ሲያልቅ የሚራዘምበትን አማራጭ ያስቀምጣል።

ምንድነው ኢትዮጵያ የምትሰጣቸው ?

የመንግሥት ፖሊሲ ግልፅ እንዳደረገው ከቴሌኮም ፣ ከኃይል ማመንጫ ፣ ከአየር መንገድ ... ብቻ አዋጭ ከሆኑ ተቋማት #እራሳችን በምንመራበት መንገድ ለሀገርም በሚጠቅም መልኩ #ድርሻ መስጠት ነው። ይሄ ለሶማሌላንድም የሚሰራ ነው። ምናልባት ከኤርትራ ፣ ከኬንያ ፣ ከጅቡቲ ስምምነት ቢደረግ ይሄ ይሰራል።

ፈጥኖ መግባባት ላይ የደረሰው #ከሶማሌላንድ ጋር ስለሆነ ነው እንጂ ንግግሩ ከሁሉም ሀገራት ጋር ይቀጥላል። የአሁኑ ብቻ በቂ ስላልሆነ ከሌላውም ጋር እንነጋገራለን።

በ50 ዓመቱ መግባቢያ ስምምነት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ ይኖራቸዋል ብለናል። ድርሻው ስንትነው ? የሚለው ተዘርዝሮ አልተቀመጠም። እኛ ለእነሱ የምንከፍለው #ሊዝ / #ኪራይ ዋጋው ስንት ነው የሚለውን ገና አልጨረስንም። ስንጀምረው ስምምነት በሚሆን መንገድ ላይ ጀምረን እነዚህ ጉዳዮች ስላላለቁ ነው ወደ መግባቢያ ሰነድ (MOU) የተመለሰው።

ገና ዝርዝር ነገሮች ያስፈልጋሉ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትክክለኛ አቅሙ፣ በገበያ ዋጋ ሲተመን ስንት ነው የሚለው ዝርዝር ተሰርቶ ወደ ንግግር ይገባል። እኛ የምንሰጠው ስንትነው የሚለው በሊዝ ከሚገኘው ዋጋ አለመብለጡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

አሁን #በቀጠናው በሊዝ የተከራዩ በርካታ ሀገራት አሉ ፤ ጅቡቲ እንኳን በደርዘን የሚቆጠሩ ሀገራት ቤዝ አላቸው በሊዝ የሚጠቀሙት ስለዚህ ትልቁን የሚከፍሉት ስንት ነው ? ለምን ? ትንሹን የሚከፍሉት ስንትነው ? ለምን ? አማካዩ ስንት ነው ? እኛ ካለን ቅርበትና ከምንሰጠው አገልግሎት ተያይዞ ስንት ነው የምንከፍለው የሚለው ይቀመጣል። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስንት ብንሰጥ ነው ተመጣጣኝ የሚሆነው የሚለው ዝርዝር ስራ ይፈልጋል። በዚህ ምክንያት ወደ MOU ተመልሷል።

በሌሎች ሴክተሮች ላይ የተሟላ ትብብር ማድረግ አለብን ፦
• በጤና ፣
• በትምህርት፣
• በውጭ ጉዳይ፣
• በከተማ ልማት
... በእነዚህ እራሳቸውን የቻሉ #ስምምነቶች መዘጋጀት አለባቸው ይሄም ገና አላለቀም።

በአጠቃላይ የመግባቢያ ሰነዱ ፦

* መሬት ከሶማሌላንድ በኪራን እንደምናገኝ
* መሬቱን እራሳችን እነምናለማው
* መሬቱን 50 ዓመታትን እንደምንገለገልበት ፤ እሱን የሚያስችል ክራዩንም የሚመጥን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ድርሻ #እንደምንሰጥ ይስቀምጣል።

ከዚህ ባለፈ ...

ለ30 ዓመታት #የተሟላ እውቅና ሳያገኙ ሀገር ሆነው ቆይተዋል። እውቅና ለማግኘት ይሞክራሉ ፤ ይሄን በተመለከተ የኢትዮጵያ አቋም ምን ይሆናል ? የሚለው ጉዳይ ይነሳል።

' ወደ ተሟላ ስምምነት ደርሶ፣ መሬቱን ተረክበን ሂደቱ ሲቋጭ እነሱ እውቅና ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት በተመለከተ ኢትዮጵያ #አቋም_ትወስዳለች የሚል አመላካች ነገሮች ነው ያሉት ሰነዱ።  '

አሁን ላይ ስምምነት ሆኖ አልተረከብንም ፣ ስምምነት ሆኖ አልሰጠንም። #መስማማት እንዳለብን ግን ተስማምተናል ፤ እሱንም በመግባቢያ ሰነድ ፈርመናል።

#AmbassadorRedwanHussein

@tikvahethiopia