TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቢሲንያ ባንክ 7 #ቨርቹዋል የባንክ ማዕከሎችን በዛሬው እለት በተከናወነ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ሥራ ማስጀመሩን ገልጿል።

አቢሲንያ ባንክ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ቨርቹዋል የባንክ ማዕከል አስመርቆ ሥራ ሲያስጀምር፣ ቴክኖሎጂው ለሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ ለባንክ ኢንዱስትሪው ቀዳሚ ከመሆኑ አኳያ ባንኩን ፋና ወጊ እንዲሆን እንዳስቻለው ገልጿል።

ቨርቹዋል የባንክ አገልግሎት ቴክኖሎጂ ደንበኞች የባንክ ቅርንጫፍ የተገደበ የጊዜ ሰሌዳ ሳያሳስባቸው በቅርንጫፍ የሚያገኙትን አገልግሎት በቀን ለ24 ሰዓት በሳምንት ለ7 ቀናት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ደንበኞች ከሚያገኟቸው አገልግሎቶች መካከል ፦
- ሒሳብ መክፈት ፣
- ገንዘብ ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ ፣
- ቼክ መመንዘርና ተቀማጭ ማድረግ ፣፤
- የሃገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ ሓዋላ አገልግሎት ፣
- ገንዘብ ማስተላለፍ፤
- እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ካርድ ባንኪንግና ሞባይል መኒ ያሉ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት ምዝገባ ማከናወን ይገኙበታል።

ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የቨርቹዋል አገልግሎት ያስጀመረ ሲሆን ዛሬ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነላቸው 7 ማዕከላት ውስጥ ከአዲስ አበባ ከተማ  ውጭ የሚገኙ የክልል ከተሞች ፦
-ደሴ፤
- መቐለ፤
- ሆሳዕና፤
- አርባምንጭ የሚገኙበት ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ማዕከላቱን 15 አድርሷል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሶስት ማእከላት የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከተመረቁት ማዕከላት መካከል በቃሊቲ፤ በጎፋ እንዲሁም በጀሞ አካባቢ ይገኙበታል።

ባንኩ በቀጣይ ሳምንታት የሚመረቁ አምስት የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ማእከላትን  ጨምሮ በመላው ሀገራችን የሚገኙ የቨርቹዋል ባንኪንግ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን  29 በማድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopia