#ቢግ_5_ኮንስትራክት_ኢትዮጵያ
መቀመጫውን በዱባይ ሻርጃ ያደረገውና ላለፉት 20 ዓመታት ዘመናዊ እና አስተማማኝ የግንባታ መፍትሔዎችን ለግንባታው ዘርፍ ሲያቀርብ የቆየውን MEMAAR BUILDING SYSTEMS FZC በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ኢግዚቢሽን ላይ ያግኙ! የሜማር ምርቶች የግንባታ ፕሮጀክቶችን ፍጥነት፣ ቅልጥፍና እና ዘላቂነት ለማጎልበት ታስበው የተነደፉ ናቸው።
ስለሥራዎቻቸው እና ምርቶቻቸው የበለጠ ለማወቅ በቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ ላይ ዛሬውኑ በመመዝገብ ይሳተፉ !
ለመመዝገብ ይሄን ይጫኑ ፡ https://bit.ly/3oI8P6L
የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይከተሉ: https://t.iss.one/big5ethiopia

የቤት ፈረሳ ጉዳይ ...
(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - ጆሲ)
" የቲክቫህ ቤተሰቦች እንደምታውቁት ' ሸገር ሲቲ ' በሚል ምክንያት በነበረ የቤት ማፍረስ ዘመቻ ብዙ ሰዎች እንደተፈናቀሉ የሚዘነጋ አይደለም።
ግን ለጥቂት ጊዜ የመቆም አዝማምያ አሳይቶ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ከሚባለው በላይ በአስከፊ ሁኔታ ቀጥሏል።
በጣም #በሚያፀይፍ_ሁኔታ በሚባል መልኩ እንደሚታወቀው ወቅቱ የዝናብ ወቅት ነው ህዝቡ በዚ ወቅት እንኳን መፈናቀል አይደለም እንደፈለገ ወጥቶ መግባት እንኳን የማይችልበት ወቅት ነው ታድያ በዚህ ወቅት ይህ ህዝብ የት ይጠለል ?
ህፃናት ልጆች አሉ ፤ አረጋውያን አሉ ፤ ነፍሰ ጡሮች አሉ ታድያ ይሄንን እንኳን ከግምት ውስጥ ያላስገባ የልማት ዘመቻ በየትኛው ወገን ነው ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው ?
እሱ ይቅር እኔ ባለሁበት አካባቢ እየተደረገ ያለው ነገር እጅግ አፀያፊ ተግባር ከሰው ልጅ ማንነት የማይጠበቅ ፤ ሰብዓዊነት የጎደለው ተግባር ነው።
እባካቹ የሚመለከተው አካል ይህንን ቅሬታችን ይስማን ። "
Via @tikvah_eth_Bot
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia

#PNG
" የህዝቡን ገንዘብ አባክነዋል " የተባሉ ሚኒስትር ስራቸውን አቆሙ።
ከሰሞኑን እንግሊዝ ፣ ሎንዶን ውስጥ ለተካሄደው የንጉሥ ቻርልስ በዓለ ሲመት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ፣ ባለስልጣናት ተጉዘው ነበር።
ከነዚህም ውስጥ የፓፕዋ ኒው ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀስቲን ታካቺንኮ አንዱ ሲሆኑ በንጉሥ ቻርልስ በዓለ ሲመት ወቅት ገንዘብ አባክነዋል የሚል ውዝግብ መነሳቱን ተከትሎ ሥራ ማቆማቸው ተሰምቷል።
አገሪቱ ሚኒስትሩን በይፋ ለበዓለ ሲመቱ በላከችበት ገንዘብ ማባከናቸው ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ25 ዓመት እድሜ ካላት ልጃቸው ሳቫና ጋር ነበር ለበዓለ ሲመቱ የተጓዙት ተብሏል ፤ ልጃቸው የመጀመሪያ ደረጃ የአውሮፕላን በረራቸውንና በሲንጋፖር ያደረጉትን ግብይት በቲክቶክ ገጿ ስታጋራ ነበር።
ልጅቷን የተቹ ሰዎችን ሚኒስትሩ " ኋላ ቀር እንስሳት " ብለዋቸዋል። ንግግራቸውን ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጄምስ ማራፔ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ " ከሥራ ለመልቀቅ " እንደተስማሙ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የሕንዱ ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ ወደ አገሪቱ ጉብኝት ሲያደርጉ ውዝግቡ እክል እንዳይፈጥር ሥራ እንደለቀቁ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ፤ " ስለ ጉዳዩ የተነዛው ሐሰተኛ ወሬ እንደጠራም ለማሳወቅ እወዳለሁ " ብለዋል።
የአገሪቱ ጋዜጣ እንደዘገበው ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጭ ሚኒስትሩ ከ10 ባለሥልጣኖች ጋር በበዓለ ሲመቱ ላይ ተገኝተዋል።
የመንግሥት ቃል አቀባይ ቢል ቶራሶ 10 ባለሥልጣኖች ከ10 እንግዶች ጋር ወደ ለንደን እንደተጓዙ ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ልጅ በለቀቀችውና አሁን ከገጿ በጠፋው ቪድዮ ቅንጡ የፋሽን መደብሮች ስትገባ ይታያል።
ለሕዝብ አገልግሎት መዋል ያለበት ገንዘብ እየባከነ ነው በሚልም ቁጣ ተነስቷል።
አባቷ ግን " በእነዚህ ሰዎች ልጄ ተጎድታለች። ቅናት መጥፎ ነው። እነዚህ ሰዎች ለአገራቸው የሚያገለግሉ ሰዎችን ከማጠልሸት ውጭ ሥራ የላቸውም " ብለዋል።
ይህንን ንግግር ካደረጉ በኋላ መልሰው ለንግግራቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሕዝቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ይቅርታ እንዲቀበል ጠይቀዋል።
Credit : BBC NEWS

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ቢሯቸው ወስጥ በስራ ላይ እያሉ በጥይት ተመተው የተገደሉት የአቶ አለባቸው አሞኜ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።
በአ/አ ከተማ የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኜ ዛሬ ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙን ከክ/ከተማው ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
አቶ አለባቸው ፤ እድሜያቸው 33 የነበረ ሲሆን ባለትዳር እንዲሁም የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ አቶ አለባቸውን የገደላቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑንና በቁጥጥር ስር መዋሉን ማሳወቁ ይታወሳል።
ፎቶ፦ የቂርቆስ ኮሚኒኬሽን

የዘማሪት ሂሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር ሰኞ ግንቦት 7 ይፈፀማል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ባገኘው መረጃ ፤ የዘማሪት ሂሩት በቀለ ስርዓተ ቀብር በጴጥሮስ ወ ጳውሎስ የሚፈፀም ይሆናል።
መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፤ " ዘማሪት ሂሩት በቀለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዘላለም ሞት እንደሚያድን አምነው በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሕይወት አጥቢያ ሲገለገሉና ሲያገለግሉ ቆይተው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ወደ ጌታቸው እቅፍ ተሰብስበዋል " ብላለች።
ስርዓተ ቀብሩን ለማስፈፀም የተቋቋመ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ደግሞ ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ ሻላ መናፈሻ ጀርባ በሚገኘው የዘማሪት ሂሩት በቀለ ቤት ሽኝት እንደሚደረግ እና በወዳጅነት አደባባይም የሽኝት ስነስርዓት እንደሚከናወን ገልጿል።
በወዳጅነት አደባባይ በሚኖረው ስነስርዓት ላይ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አማካኝነት የፀሎት ስነሥርዓት እንደሚደረግ ተነግሯል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፤ ለዘማሪት ሂሩት በቀለ ቤተሰቦች እና ለወደጅ ዘመዶች በጠቅላላ መጽናናት የተመኘች ሲሆን ሁሉም በጸሎት አብሯቸው እንዲሆን አሳስባለች።
ዘማሪት ሂሩት በቀለ ትላንት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ይታወቃል።

#UNHR
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝና አፈጻጸም የሚከታተለውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም አቀፍ ስምምነቶች አካላት (United Nations Human Rights -Treaty Bodies) በመባል የሚታወቀው የገለልተኛ ባለሙያዎች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አስከባሪ አካላት የሚፈጸሙ ማሰቃየትና እንግልቶች፣ በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩና ተጠርጣሪዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ እንዲያደርግ አሳሰበ፡፡
የሰብዓዊ መብት ም/ቤቱ የፀረ ማሰቃየት ኮሚቴ ይህን ያስታወቀው ኢትዮጵያን ጨምሮ በብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ካዛኪስታን፣ ሉክሰምበርግና ስሎቫኪያ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ የተናጠል ግምገማ ማጠቃለያ ሪፖርት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ይፋ ባደረገበት መግለጫ ነው፡፡
በመግለጫው ምን አለ ?
በኢትዮጵያ በፖሊስ መኮንኖች ፣ በእስር ቤት ጠባቂዎች እና ሌሎች ወታደራዊና የፀጥታ ኃይሎች በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በማቆያ ማዕከላት ፣ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ በወታደራዊ ካምፖችና በግልፅ በማይታወቁ ወይም #በሚስጥራዊ እስር ቤቶች ቅሬታ አቅራቢዎች የሚደርስባቸው ስቃይና እንግልት እጅጉን አሳስቦኛል ብሏል።
አሁንም ቢሆን በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚስተዋሉ ማሰቃየት ወይም እንግልት ቅሬታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ገለልተኛ፣ ምቹና ሚስጥራዊ ዘዴ አለመኖሩንና አሁናዊው የምርመራ አካላት ሁኔታ ተፈላጊው ገለልተኝነት እንደሚጎለው ግንዛቤ መወሰዱን ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አስከባሪ አካላት የሚደርሱ ማሰቃየቶችና ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እንግልቶችን በተመለከተ የቀረቡ ቅሬታዎች፣ በገለልተኛ አካል እንዲጣሩና ተጠርጣሪ ድርጊት ፈጻሚዎችንና ድርጊቱን እንዲፈጸም ያዘዙና በቸልታ የተመለከቱ የሥራ ኃላፊዎች ለሕግ ቀርበው #እንዲጠየቁ እና #እንዲቀጡ ጠይቋል፡፡
መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

#Update ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ የተገኘው የአርቲስት ዳዊት ፍሬው አስክሬን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል። ትላንት በሮም ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፍታት እንዲሁም የአስክሬን ሽንት ፕሮግራም ተካሂዷል። የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ግንቦት 6 /2015 ከቀኑ 6 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈፀም ሲሆን…
#Update
የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈጸመ።
የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
አርቲስት ዳዊት ፍሬው በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ትምህርቱን 'ሜጀር ክላርኔት' በማድረግ የተመረቀ ሲሆን የአልቶ ሳክስፎን እና ክራር ተጨዋችም ነበር።
በአስደናቂ ክላርኔት ጨዋታው የሚታወቀው ዳዊት ፍሬው በሙዚቃ ትምህርት ቤት ቆይታው፣ የታላላቅ ሙዚቃ አቀናባሪዎች /ኮምፖዘሮችን/ የክላርኔት ሥራዎች ተጫውቷል።
በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበሩ አልበሞችንም ለአድማጮች ማቅረብ ችሏል።
አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ውስጥ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ መገኘቱ ይታወሳል።
Credit : #ኤፍቢሲ