#PNG
" የህዝቡን ገንዘብ አባክነዋል " የተባሉ ሚኒስትር ስራቸውን አቆሙ።
ከሰሞኑን እንግሊዝ ፣ ሎንዶን ውስጥ ለተካሄደው የንጉሥ ቻርልስ በዓለ ሲመት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ፣ ባለስልጣናት ተጉዘው ነበር።
ከነዚህም ውስጥ የፓፕዋ ኒው ጊኒ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀስቲን ታካቺንኮ አንዱ ሲሆኑ በንጉሥ ቻርልስ በዓለ ሲመት ወቅት ገንዘብ አባክነዋል የሚል ውዝግብ መነሳቱን ተከትሎ ሥራ ማቆማቸው ተሰምቷል።
አገሪቱ ሚኒስትሩን በይፋ ለበዓለ ሲመቱ በላከችበት ገንዘብ ማባከናቸው ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ25 ዓመት እድሜ ካላት ልጃቸው ሳቫና ጋር ነበር ለበዓለ ሲመቱ የተጓዙት ተብሏል ፤ ልጃቸው የመጀመሪያ ደረጃ የአውሮፕላን በረራቸውንና በሲንጋፖር ያደረጉትን ግብይት በቲክቶክ ገጿ ስታጋራ ነበር።
ልጅቷን የተቹ ሰዎችን ሚኒስትሩ " ኋላ ቀር እንስሳት " ብለዋቸዋል። ንግግራቸውን ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጄምስ ማራፔ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ " ከሥራ ለመልቀቅ " እንደተስማሙ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የሕንዱ ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ ወደ አገሪቱ ጉብኝት ሲያደርጉ ውዝግቡ እክል እንዳይፈጥር ሥራ እንደለቀቁ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ፤ " ስለ ጉዳዩ የተነዛው ሐሰተኛ ወሬ እንደጠራም ለማሳወቅ እወዳለሁ " ብለዋል።
የአገሪቱ ጋዜጣ እንደዘገበው ወደ አንድ ሚሊዮን ዶላር በሚጠጋ ወጭ ሚኒስትሩ ከ10 ባለሥልጣኖች ጋር በበዓለ ሲመቱ ላይ ተገኝተዋል።
የመንግሥት ቃል አቀባይ ቢል ቶራሶ 10 ባለሥልጣኖች ከ10 እንግዶች ጋር ወደ ለንደን እንደተጓዙ ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ልጅ በለቀቀችውና አሁን ከገጿ በጠፋው ቪድዮ ቅንጡ የፋሽን መደብሮች ስትገባ ይታያል።
ለሕዝብ አገልግሎት መዋል ያለበት ገንዘብ እየባከነ ነው በሚልም ቁጣ ተነስቷል።
አባቷ ግን " በእነዚህ ሰዎች ልጄ ተጎድታለች። ቅናት መጥፎ ነው። እነዚህ ሰዎች ለአገራቸው የሚያገለግሉ ሰዎችን ከማጠልሸት ውጭ ሥራ የላቸውም " ብለዋል።
ይህንን ንግግር ካደረጉ በኋላ መልሰው ለንግግራቸው ይቅርታ ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሕዝቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ይቅርታ እንዲቀበል ጠይቀዋል።
Credit : BBC NEWS
@tikvahethiopia