TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አርቲስት ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የክላርኔት ሙዚቃ ተጫዋቹ ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ። የአርቲስቱን ህልፈት ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬድዮ ጣቢያ ከቅርብ ወዳጆቹ ማረጋገጡን አሳውቋል። አርቲስት ዳዊት ፍሬው ለሙዚቃ ስራ ወደ ጣሊያን ሀገር ተጉዞ እንደነበር የሬድዮ ጣቢያው ዘገባ ያለመለክታል። ክላርኔት ተጫዋቹ እና ሙዚቀኛው ዳዊት ህይወቱ አልፎ የተገኘው #በተኛበት_ክፍል…
#Update

ለሙዚቃ ስራ ወደ አውሮፓ ሄዶ ጣልያን ፣ ሮም ከተማ ባረፈበት ክፍል ህይወቱ አልፎ የተገኘው የአርቲስት ዳዊት ፍሬው አስክሬን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል።

ትላንት በሮም ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፍታት እንዲሁም የአስክሬን ሽንት ፕሮግራም ተካሂዷል።

የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ግንቦት 6 /2015 ከቀኑ 6 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት  ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የሚፈፀም ሲሆን ከዛ ቀደም ብሎ ረፋዱን በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የሽኝት እና የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ይካሄዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተከፋፈለ ሲኖዶስ የለም " የ2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት የሁለተኛው ቀን ጉባኤ ዛሬ ሲካሄድ ውሏል። ይህ አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባባቢዋ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው በሁለተኛው ቀን በነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሁለት ርዕሰ ጉዳዮች መወያያየቱን ገልጸዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ…
#EOTC

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ   ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ የደቡብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቀደም ሲል ያገለግሉባቸው በነበሩ አህጉረ ስብከቶች አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ወስኗል።

ይህን ውሳኔ የተላለፈው ትላንት በነበረው የምልዓተ ጉባኤው ሶስተኛ ቀን ውሎ ነው።

ከዚህ ባለፈ ጉባኤው በትላንት ውሎው እንዲነጋገርበት ተይዞ የነበረው #የኤጲስ_ቆጶሳት ምርጫ ጉዳይ የጉባኤው የመጨረሻ አጀንዳ እንዲሆን የአጀንዳ ሽግሽግ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።

ጉባኤው ትላንት የዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነምሕረት ማህበረ ደናግል ገዳምን በተመለከተ የያዘው አጀንዳ ላይ መወያየቱ የተገለፀ ሲሆን ለውሳኔ በይደር እንዲቆይ ተደርጓል።

የመረጃው ምንጭ ፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ለኢኦተቤ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሰጡት ማብራሪያ ነው።

@tikvahethiopia
" ... በመንግስት አሰራሮች ላይ በሚያቀርቡት የፖለቲካ ትችት ምክንያት መንግሥት ያሰራቸውን ግለሰቦች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ ጠይቃለሁ " - አቶ ክርስቲያን ታደለ (የህ/ተ/ም/ቤ አባል)

የፓርላማ አባሉ በመንግስት ታስረዋል ያሏቸው የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስታያን ታደለ ፤ መንግስት በፖለቲካ አመለካከታቸውና በመንግስት አሰራሮች ላይ በሚያቀርቡት የፖለቲካ ትችት ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች ያሰራቸው ግለሰቦች መኖራቸውን በመግለፅ እነዚህን እስረኞች በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈታ ጠይቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ በእስር ላይ ይገናኛሉ ካሏቸው ግለሰቦች አንዱ አቶ ዘሪሁን ገሰሰ ናቸው።

" ፓርቲ የመሰረትነው መንግስትን መቼና እንዴት መተቼት እንዳለብን ከራሱ ከመንግስት አቅጣጫ እየተቀመጠልን ለመንቀሳቀስ አይደለም " ያሉት አቶ ክርስቲያን " በተለይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በትንሹ የራሱን አባላት ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን በወጉ እንዲወጣም እጠይቃለሁ። " ብለዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ ከአብን መስራቾች አንዱ እና ፓርቲውን ወክለው በህዝብ ተመርጠው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ከፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነት መልቀቃቸውን ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ይነሣልኝ " ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ህወሓት ያቀረበው ጥያቄ ምንድነው ?

ህወሓት የፓርቲውን ህጋዊ ሰውነት ስረዛ፤ የፓርቲው ሃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉ እና የፓርቲው ንብረት ተጠርቶ ፓርቲው ዕዳ ካለበት ለዕዳ መሸፈኛ እንዲውል፤ ቀሪው ገንዘብና ንብረት ለሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ከዚህ በፊት በምርጫ ቦርድ የተላለፈው ውሳኔ እንዲነሳ ሲል በደብዳቤ ጠይቋል።

ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር አሁን ላይ ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፓርቲው ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/2011 ተደንግጎ አይገኝም ሲል ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በዚህም የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይ በህግ የተደገፈ ሆኖ እንዳላገኘው ቦርዱ አመልክቷል።

ፓርቲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በአዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 66 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ህጉን መሰረት አደርጎ ሲፈቅድ መሆኑን ቦርዱ ወስኗል።

የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው ላይ የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደአዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ አይደሉም ያለው ምርጫ ቦርድ በዚህ በኩልም የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

(ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል። በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል። ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል። " ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ…
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም በ " ፋይበር መቆረጥ " ምክንያት በትግራይ ተቋርጦ የነበረውን የኔትዎርክ አገልግሎት ለማስቀጠል ሲያከናውን የነበረውን የጥገና ስራ ማጠናቀቁንና አገልግሎት መመለሱን አሳውቆናል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ፤ ሰራተኞቹ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ በሁለት ቦታዎች ላይ የነበረውን የፋይበር መቆረጥ በመጠገን ወደነበረበት መመለስ ችለዋል።

የፋይበር መቆረጥ ያጋጠመው በ " አላማጣ " እና በ " ሰመራ " በኩል ሲሆን በምን ምክንያት ሊቆረጥ እንደቻለ የማጣራት ስራ ለመስራት እየተሞከረ ነው ተብለናል።

" የፋይበር መቆረጥ በተለያዩ ቦታዎች አልፎ አልፎ ያጋጥማል " ያለን ኢትዮ ቴሌኮም በሁለቱ ቦታዎች ያጋጠመውን የፋይበር መቆረጥ ምክንያት ለማወቅና " በዚህ ነው ሊቆረጥ የቻለው " የሚለውን ለመለየት እየተሰራ ነው ሲል አስረድቶናል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ባይቶና

ቦርዱ ባይቶና መስራች ጉባኤ እንዲየከናውን ወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ የብሔራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) ፓርቲ አደራጅ ኮሚቴ ዐዋጁን መሠረት በማድረግ የመሥራች ጉባዔውን እንዲያከናውን ውሳኔ አሳልፏል።

ቦርዱ ፤ ዛሬ ለነ ኪዳነ አመነ በላከው ደብዳቤ ፓርቲው ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ያደረገው የመስራች ጉባኤ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተቀመጡትን መስፈርቶች በማሟላት የተከናወነ ባለመሆኑ በጉባኤ የተከናወኑ የአመራር ምርጫም ሆነ የፀደቁ ሰነዶችን እውቅና ያልሰጠ መሆኑን አሳውቋል።

ምርጫ ቦርድ፤ የፓርቲው አደራጅ ኮሚቴ አዋጁን መሰረት በማድረግ የመስራች ጉባኤውን እንዲያከናውን ወስኗል።

(ይህ ውሳኔ የተላለፈበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ የተወሰኑ መንገዶች #ይዘጋሉ

" የሚጠብቁንን ጀግኖች እናክብር " በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ24ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ የሚከበረውን ' የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቀን ' ክብረ በዓልን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ለተወሰነ ሰዓት  መንገድ ዝግ ይደረጋል ተብሏል።

በመስቀል አደባባይ ዙሪያ መንገዶች ዝግ የሚደረጉት ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ መሆኑ ተገልጿል።

የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ፤

- ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ፤

- ከላንቻ ወደ መስቀል አደባባይ አራተኛ ክፍለ ጦር ዝግ የሚደረግ ሲሆን #ለከባድ ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል።

- ከከፍተኛው ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ  መስቀል አደባባይ ለገሐር መብራት ፤

- ከጎማ ቁጠባ በብሔራዊ ቴአትር ወደ  መስቀል አደባባይ ቴሌ መስቀለኛ ወይም ክቡ ባንክ፤

- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መስቀለኛ ፤

- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ ፤ ከማለዳው 12:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ 5:00 ሠዓት ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ሌሎች #አማራጭ_መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

" ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሕንፃዎች በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በመገንባት ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ብርሃን እና ውበት እንጨምራለን " - አቶ ግሩም ፀጋዬ

ብርሃን ባንክ የዋና መ/ቤት ህንጻ አርኪቴክቸራል ዲዛይን ውድድር በማካሄድ አሸናፊ ለሆኑ የሽልማት መርሃግብር አካሂዷል፡፡

መርሃግብሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ጉማቸው ኩሴ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ግሩም ፀጋዬ፣  የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ባለ አክሲዮኖች፣ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በዕለቱም የዚሁ ህንፃ ግንባታ የመጀመሪያው አካል የሆነውን የህንፃውን ዲዛይን የመምረጥ ሂደት በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ ያሸነፈው ድርጅት የተለየ ሲሆን ከ1ኛ-3ኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች ዕውቅና የመስጠት መርሃግብር ተካሂዷል፡፡

የብርሃን ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ግሩም ፀጋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት፤ ባንኩ በአዲስ አበባ የፋይናንስ ተቋማት መገኛ በሆነው ሰንጋተራ አካባቢ 5400 ካ.ሜ ስፋት ያለው መሬት ተረክቦ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ የዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታውን ለማከናውን በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

አክለውም ቀጣይ ሂደቶች ሲጠናቀቁ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሕንፃዎች በቴክኖሎጂ የበለፀገ ዘመናዊ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ በመገንባት ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ብርሃን እና ውበት በመጨመር የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡

https://t.iss.one/berhanbanksc