TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UNHR

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝና አፈጻጸም የሚከታተለውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም አቀፍ ስምምነቶች አካላት (United Nations Human Rights -Treaty Bodies) በመባል የሚታወቀው የገለልተኛ ባለሙያዎች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አስከባሪ አካላት የሚፈጸሙ ማሰቃየትና እንግልቶች፣ በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩና ተጠርጣሪዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ እንዲያደርግ አሳሰበ፡፡

የሰብዓዊ መብት ም/ቤቱ የፀረ ማሰቃየት ኮሚቴ ይህን ያስታወቀው ኢትዮጵያን ጨምሮ በብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ካዛኪስታን፣ ሉክሰምበርግና ስሎቫኪያ ላይ የሰብዓዊ መብቶች ይዞታ የተናጠል ግምገማ ማጠቃለያ ሪፖርት ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በጄኔቫ ስዊዘርላንድ ይፋ ባደረገበት መግለጫ ነው፡፡

በመግለጫው ምን አለ ?

በኢትዮጵያ በፖሊስ መኮንኖች ፣ በእስር ቤት ጠባቂዎች እና ሌሎች ወታደራዊና የፀጥታ ኃይሎች በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በማቆያ ማዕከላት ፣ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ በወታደራዊ ካምፖችና በግልፅ በማይታወቁ ወይም #በሚስጥራዊ እስር ቤቶች ቅሬታ አቅራቢዎች የሚደርስባቸው ስቃይና እንግልት እጅጉን አሳስቦኛል ብሏል።

አሁንም ቢሆን በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚስተዋሉ ማሰቃየት ወይም እንግልት ቅሬታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ገለልተኛ፣ ምቹና ሚስጥራዊ ዘዴ አለመኖሩንና አሁናዊው የምርመራ አካላት ሁኔታ ተፈላጊው ገለልተኝነት እንደሚጎለው ግንዛቤ መወሰዱን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አስከባሪ አካላት የሚደርሱ ማሰቃየቶችና ተገቢ ያልሆነ አያያዝና እንግልቶችን በተመለከተ የቀረቡ ቅሬታዎች፣ በገለልተኛ አካል እንዲጣሩና ተጠርጣሪ ድርጊት ፈጻሚዎችንና ድርጊቱን እንዲፈጸም ያዘዙና በቸልታ የተመለከቱ የሥራ ኃላፊዎች ለሕግ ቀርበው #እንዲጠየቁ እና #እንዲቀጡ ጠይቋል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia